Pages

Tuesday, January 27, 2015

የአንዳርጋቸው ጽጌ ልደት በዋሽንግተን ዲሲ ሊከበር ነው * (አዳዲስ የአንዳርጋቸው ፎቶዎች ይዘናል)

mesay 1
andargachew
andualem 2
በሕወሓት የማሰቃያ እስር ቤት ውስጥ የሚገኙት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ 60ኛ ዓመት የልደት በዓል በዋሽግተን ዲሲ እና በተለያዩ ሃገራት እንደሚከበር ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱ የጥሪ ወረቀቶች አመለከቱ::
ከ3 ቀን በፊት ዘ-ሐበሻ በኖርዌይ የአንዳርጋቸው ጽጌ የልደት በዓል እንደሚከበር የዘገበች ሲሆን; ዛሬ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው ማስታወቂያ ደግሞ በዋሽንግተን ዲሲም እንደሚከበር ይጠቁማል::
“ለአገራችን ኢትዮጵያ ክቡር ሕይወቱን መስዋእት በማድረግ እየታገለና በአሁኑ ሰዓት በህወሓት/ወያኔ የማሰቃያ እስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰበት የሚገእው የነፃነት ተመሳሌት የአርበኛውና ጀግናው አንዳርጋቸው ጽጌ የልደት በዓለ በዓለም አቀፍ ደረጃ በደማቅ ሁኔታ ይከበራል” በሚል የሚጀመረው የዋሽንግተን ዲሲው የጥሪ ወረቀት ቀጥሎም “እኛም በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ይሄን የልደት በዓል ተሰባስበን በደማቅ ሁኔታ እንድናከብር የአክብሮት ጥሪያችንን ለሁሉም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እናቀርባለን” ይላል::
ሰኞ ፌብሩዋሪ 9 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 9:00 ሰዓት በብሪታኒያ ኢንባሲ ደጃፍ የአንዳርጋቸው ጽጌ ልደት የሚከበር መሆኑን ያስታወቀው የዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የጋራ ግብረ ኃይል ለበለጠ መረጃም 571-40302474 እንዲደውሉ ጥሪውን አቅርቧል::
የብሪታኒያ ኢምባሲ አድራሻ British Embassy
3100 Massachusetts Avenue NW Washington DC 20008 ነው::
በሌላ በኩል ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን የአንዳርጋቸው ጽጌን በረሃ የወረደባቸውን አዳዲስ ፎቶ ግራፎች በፌስቡክ ገጹ ለቋቸዋል:: ጋዜጠኛ መሳይ አስመራ በነበረበት ወቅት 5 አዳዲስ የአንዳርጋቸው ፎቶ ግራፎችን የለቀቀ ሲሆን ዛሬም 3 አዳዲስ ፎቶዎች አሳይቶናል – ለዘ-ሐበሻ አንባቢዎችም እነዚህን አዳዲስ ፎቶዎች ቅክቅፍለናል::

ማን ይናገር የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ! – አቶ ነሲቡ ስብሃት(አሉላ)

መጽሐፍ ፍጹም ነው እምነቴ”  ቀይ ሽብርና፤ የከፍተኛ 15 እውነተኛ ታሪክ
ደራሲ፡ አቶ ነሲቡ ስብሃት(አሉላ) መስከረም 2007
አስተያየት
በአቶ ክንፈ ኪሩቤል ተስፋሚካኤል(አዲስ አበባ) ጥር 2007 ዓ.ም

Yat weldይህ የአቶ ነሲቡ ስብሃት መጽሐፍ በትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሰረተ የስራ ውጤት ነው፡፡ በ1970 ዓ.ም “በቀይ ሽብር” ስም ያለ ፍትሕ ስርዓት ስቃይና መከራ ለተቀበሉት፤ ለአካል ጉዳተኛነት ለተዳረጉት፤ ለስነ ልቦና ጉዳት ሰለባ ለሆኑት፤ ለተሰደዱት፤ ውድ ልጆቻቸውንና ወላጆቻቸውን እስከ ፍጻሜው በሞት ላጡት ኢትዮዽያውያን ታላቅ መታሰቢያ ነው፡፡
መጽሐፉን ልዪ የሚያደርገው ስለ “ቀይ ሽብር” የተጻፈ እውነተኛ ታሪክ መሆኑ ብቻ አይደለም፡፡ በ1969-70ዎቹ የነበረውን የፖለቲካ የማህበራዊና አኮኖሚያዊ ሁኔታዎችን፤ የፀሐፊውን የግል ሕይወት፤በካዛኢንችስ በወቅቱ የነበረውን የወጣት ሁኔታ ይዳስሳል፡፡ ታሪክነቱ በአንድ የአዲስ አባበ ከተማ በከፍተኛ 15 ውስጥ የተካሄደ ቢሆንም፤ድርጊቱን በመላው የኢትዮዽያ ከተሞችና ገጠሮች “በቀይ ሽብር ይፋፋም” መፈክር ስር ወታደራዊ ደርግና በዙሪያው የተሰባሰቡ ስልጣን ፈላጊ ምሁራን በቅንብር ያካሄዱትን ዘግናኝ የግድያ ድርጊት ትዕይንታዊ በሆነ መልኩ ያሳያል፡፡
አንባቢው ሊገነዘበው የሚገባው ይህ ዕልቂት በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮዽያ  በተመሳሳይ ሁኔታ እንደተደረገና በዚህም ከ1940-1960ዎቹ የተወለደ አንድ የኢትዮዽያ ወጣት ትውልድ በጅምላ ዕልቂት ማለፉንም ጭምር ነው፡፡
መጽሐፉ በተጨማሪ የሚዳስሰው የታመቀው የኢትዮዽያ ሕዝብ ብሶት በድንገት 1966 ዓ.ም በመቀጣጠሉ የተነሳ በወቅቱ የሕዝቡን የለውጥ ፍላጎትና ብሶት በተደራጀ የፖለቲካ አመራር ሊመራ የሚችል የፖለቲካ ፓርቲ ባለመኖሩ ወታደራዊ ደርግ መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም ስልጣን በሃይል መንጠቁንና የሕዝብን ዲሞክራሲ መብቶች መግፈፉና የግፍ አገዛዙ  የኢጣሊያን ፋሽስቶች ኢትዮዽያን በወረሩበት ዘመን ከፈጸሙት ያላነሰ  መሆኑን ያነፃፅራል፡፡
ሌላው መጽሐፉ አንባቢውን የሚያስገነዝበን የማርክሲስት  ርዕዮተ ዓለም እናራምዳለን የሚሉ ምሁራኖች በተከተሉት የፖለቲካ መስመር ልዩነቶች የተነሳ መቻቻልና መደማመጥ በመጥፋቱ በሃገሪቱና በሕዝቦቿ ላይ የደረሰውን ጥፋት ነው፡፡ በተለይ የመላው ኢትዮዽያ ሶሻሊስት ንቅናቄ(መኢሶን) የተባለ ቡድን ደርግን ወግኖ ስለመቆሙ፤ የኢትዮዽያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ(ኢሕአፓ) ደግሞ ደርግን ኮንኖ የራሱን አቋምና መስመር ስለመከተሉ፤ ኢሕአፓ ለኢትዮዽያ ሕዝቦች ነጻነትና እኩልነት በጽኑ ስለመቆሙና ስለመታገሉ ያስረዳል፡፡ በዚህም የተነሳ በለጋ ወጣትነት ዕድሜያቸው የኢሕአፓን መስመር በፍጹም እምታቸው የተከተሉት ወጣቶች በኢሕአወሊ ድርጅታቸው ስር ያካሄዱትን የመረረ ትግልና የተቀበሉትን መስዋዕትነት በግልጽ ያሳያል፡፡
አቶ ነሲቡ፤ የኢሕአፓን የሕዝብ ፓርቲነትን አበክረው ገልጸዋል፤ ሆኖም ትግሉ እየመረረ በሄደበት ወቅት መኢሶን፤ ወዝ ሊግ፤ ማሊሬድ፤ ኢጭአት በተባሉ የድርጅት ካድሬዎችን በመጠቀም ወታደራዊው ደርግ በቀይ ሽብር ስም ድርጅቱን የመምታቱ ሃይል በተፋፋመበት ወቅት በኢሕአፓ ድርጅት ውስጥ መከፋፈል ስለመከሰቱ፤ መዋቅሩ ስለመዘበራረቁና መፈራረሱ፤ መክዳትና ከደርግ ጋር መሰለፍን ስለማስከተሉ፤ በከተማው ትጥቅ ትግል የተነሳ ስህተቶች ሰለመፈጸማቸው በግልጽ አስቀምጠውታል፡፡ ይህም ሚዛናዊነታቸውንና እውነተኛነታቸውን ያሳያል፡፡ የሕቡዕ ድርጅታዊ አሰራር በውስጡ አለመተማመንና መከፋፈል ከተፈጠረ ጉዳቱ ቀላል እንደማይሆን ያስተምራል፡፡
ካድሬ ከፈለኝ ዓለሙ እንደ ምሳሌ ቀረቡ እንጂ፤ በአጠቃላ የደርግ ካድሬዎችን ጨካኝነት የአውሬነት ባሕሪይ በግልጽ ያሳያል፡፡ የኢትዮዽያ ሕዝቦች የሚታወቁበት ሃይማኖታዊነት፤ ሰብዓዊነት፤ ታጋሽነት፤ ሩህሩህነት ወዘተ የመሳሰሉትን ታላላቅ ባሕሪያት ፈጽሞ የተቃረነ መሆኑን ይገልጻል፡፡ “ሁሉም ያልፋል” የሚለውን ብሂል ፈጽሞ የዘነጉ፤ ጊዜያዊ የበላይነታቸውን እንደ ዘለዓለማዊነት አድርገው የቆጠሩ፤ በግፍ ያፈሰሱት ደም ጊዜው ይዘግይ እንጂ እንደሚፋረዳቸውና ተገቢውን ፍርድም እንደሚሰጣቸው መጽሐፉ ዋቤ ሰጥቶአል፡፡ ይኸውም ማንነቱን ቀይሮ አሜሪካ የገባው ፈለኝ ዓለሙ በዴኒቭር ኮሎራዶ ተይዞ  ከ36 ዓመታት በኋላ የተሰጠውን የ22 ዓመታት ፍርድ ስንመለከት ለሌሎችም ማስጠንቀቂያ ነው፡፡ አይሁዶችን የጨፈጨፉ የናዚ ሂትለር መንግሥት ሰዎችም እንዲሁ አላመለጡም፡
ከ1980 ዓ.ም በኋላ እና በኢሕአዴግ ዘመን የተወለደው ወጣት ትውልድ ከሞላ ጎደል የኢትዮዽያ ሕዝቦች ከድህነት፤ ከበሽታ፤ ከረሃብ ከብሔር ጭቆና ተላቀው ሕዝባዊና ዲሞክራሲያዊ መንግሥት ለመመስረት ስላደረጉት ትግል ባይተዋር ይመስላል፤ አለያም ስለ ተካሄደው ትግል እምብዛም አያውቅም ማለት ይቻላል፡፡ በመሆኑም አሁን ያለው ይህ ወጣት ትውልድ የቀደመው ያ ትውልድ ስለከፈለው መስዋዕትነት ከአቶ ነሲቡ ስብሀት መጽሐፍ ግንዛቤ እንዲወስድ ያስችለዋል፡፡ የዚህ ዘመን ወጣት ጉዳዩን መገንዘብ ብቻ ሳይሆን ይህንን የመሰለ ድርጊት በድጋሚ አንዳይከሰት የቀደመ ታሪኩን ማወቅ፤ መዘጋጀትና መጠንቀቅ ይገባዋል፡፡
ባለፉት 23 ዓመታት የተወለደው የአሁኑ ትውልድ ማንነቱንና ምንነቱን ወደፊትስ አቅጣጫው ምን መሆን እንዳለበት ከወዲሁ መገንዘብ የሚኖርበት ዘመን ላይ ተደርሷል፡፡ ታላቅ የነበረ ሕዝብ ወደ ጥንቱ የታላቅነቱ መሰረት እያመራ መሆኑን ማጤን ጊዜው አሁን ነው፡፡
በ1966 ዓ.ም አብዮት የዲሞክራሲ መብቶቹን ሊቀዳጀ የነበረ ሕዝብ  በወታደራዊው ደርግ መብቶቹን በመነጠቁ የተነሳ መብቱን ለማስመለስ የኢትዮዽያ ብሔር ብሔረሰብ ወጣቶች በቀጣይነት በየድርጅታቸው ረጅም ከገጠር የትጥቅ ትግልን ለማካሄድ ወስነው በከፈሉትን መስዋዕትነት ደርግን በ1983 ዓ.ም ከስልጣን ለማስወገድ በቅተዋል፡፡
በዚህ አጋጣሚ ለዚህ አስተያየት አንባቢዎች ለማሳወቅ የምፈልገው “ ኢሕአፓ እና ስፖርት ” እውነተኛ ታሪክ በሚል ርዕስ በገነነ መኩሪያ(ሊብሮ) 2005 ዓ.ም የተጻፈው መጽሐፍ አቶ ነሲቡ ያቀረቡትን መረጃ የሚያጠናክር ሆኖ አግንቼዋለሁ፡፡ ፈልገው ያንብቡት፡፡
ክንፈ ኪሩቤል ተስፋሚካኤል(አዲስ አበባ) ጥር 2007 ዓ.ም

በኖርዌይ ኦስሎ እንግሊዝ ኢንባሲ ፊት ለፊት በደማቅ ሁኔታ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

norway 1
norway ethiopian
norway ethiopian
norway ethiopian 3
                             ቀን፡ 01/26/2015
በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ በወጣቶች ክፍል አስተባባሪነት በዛሬው እለት ሰኞ( January 26,2015) በኖርዌ ኦስሎ በእንግሊዝ ኢንባሲ ፊት ለፊት በኖርዌይ የሚኖሩ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በህብረት ሁነው ከ14፡00 _15፡00 ስዓት ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፉ በደማቅ ሁኔታ አካሄዱ።
የሰልፉ ዋና አላማ የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ የነበሩትንና የሰባዊ መብት ተቆርቋሪ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በአረመኔው፣ ሰው በላ፣ ጨቋኙና በአንምባ ገነኑ የወያኔ ፋሺስታዊ ቡድን የአለም አቀፍ የሰባዊ መብትን ህግ በጣሰ መንገድ በሰኔ 2014 ታፍነው እስኳሁንም ድረስ ፍትህ ተነፍገው በእስር ቤት መታሰራቸውን ለመቃወም እንዲሁም የእንግሊዝ መንግስት አርበኛው የነጻነት ታጋዩ አንዳርጋቸው እየተፈጸመበት ያለውን ተፈጥሮአዊና ዲሞክራሲያዊ የመብት ጥሰት ተመልክቶ ከእስር ሊወጣበት የሚችልበትን አፋጣኝ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ ለማሳሰብ ነው።
በተጨማሪም አንዳርጋቸው ከተያዘበት ቀን ጀምሮ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በወያኔ የተፈጸመውን የውንብድና ድርጊት በመቃዎም ለእንግሊዝ መንግሥት በተለያየ መልኩ የአገሩን ዜጋ ህይወት ይታደግ ዘንድ በተደጋጋሚ ለማሳሰብ ቢሞከርም አፋጣኝ እርምጃ አለመወሰዱ ብዙዎችን አስቆጥቷል።
አንዳርጋቸው አገር ወዳድ፣ ሰላም ፈላጊ፣ ነጻነትና ፍትህ ናፋቂ፣ ለህዝብና ለአገር ክብር ተቆርቋሪ፣ ከእራሱ እና ከሚወዳቸው ቤተሰቦቹ ይልቅ ለእናት አገሩ ኢትዮጵያ ጊዜውን፣ እውቀቱንና ህይወቱን የሰዋ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ጀግና መሆኑን በኩራት መስክረዋል። የውጭ ዜጎችም ሳይቀሩ ኢትዮጵያዊ ማንዴላ ብለው ሰይመውታል። ለዲሞክራሲ መከበር ለሚታገል አርበኛ እስርና እንግልት ኮቶ እንደማይገባ በተለይ የእንግሊዝ መንግሥት በትኩረት ሊመክርበት የሚገባ አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን እና በወያኔ ላይ ግፊትና ጫና መፍጠር እንዳለበት ሁሉም ተሰላፊዎች ድምጻቸውን ከፍ አድርገው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
እንዲሁም ሰልፈኞቹ የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ በታላቅ ድምጽና ስሜት የኖርዌይ ቅዝቃዜና በረዶ ሳይበግራቸው ለኢንባሲው አሰምተዋል። ከአሰሟቸው መፈክሮች መካከል ለአብነት ፣ “Andargachew is a freedom fithter, UK, were is your citizen, Free Andrgachew Tsige, Andargachew is our icon of democracy, where is your action , stop discrimination among citizens, Yes, we are all Andrgachew Tsige, Yes, Andargachew is an Ethiopian Mandela, Brtain don’t support terrirost regim in Ethiopia, ” የሚሉት ይገኙበታል::
እንደተለመደው በድርጅቱ የተዘጋጀውን ደብዳቤ በድርጅቱ ተወካዮች በአቶ ይበልጣል ጋሹ እና በአቶ ዮናስ ዮሴፍ አማካኝነት ለእንግሊዝ ኢምባሲ ተወካይ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳዩ ትኩረት የሚሻና ጊዜ የማይሰጠው መሆኑን በመግለጽ ህይወቱም በእጅጉ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንዳለ በጥብቅ በማሳሰብ ደብዳቤውን በኢምባሲው ተወካይ አማካኝነት እንዲደርሳቸው ተደርጓል።
በመጨረሻም ግፈኛው የወያኔ ቡድን በለመደው ተራ የሀሰት ወሬ በሚያወራበት ቴሌቪዥኑ ላይ ለትርጉም በሚያስቸግር መልኩ ቆራርጦና በጣጥሶ አንዳርጋቸውን ለማስወራት መሞከሩ የወያኔን ከንቱነት እና እውቀት ዓልባነቱ እንዲሁም ለህዝብና ለአገር የሚሰጠው ንቀት ይበልጥ ለዓለም መጋለጡ ለእኛ ለአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ህብርትና አንድነት ፈጥረን በእልህ፣ በቁጭትና በቁርጠኝነት ከበፊቱ በበለጠ ትግላችንን አጠናክረን እንድንቀጥል ትልቅ በር ከፍቶልናል፤ ለትግልና ለተቃውሞም ይበልጥ አነሳስቶናል። እንደ አርበኞችና ግንቦት ሰባት የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችም ውህደት ፈጥረው በሁለገብ ትግል ዘረኛው ወያኔን  ለማስወገድ ቆርጠው እንዲነሱ የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ዮሐንስ ዓለሙ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። በተመሳሳይም የወጣቶች ክፍል ተወካይ አቶ ይበልጣል ጋሹ ወጣቶች ለፍትህ፣ ለነጻነትና ዲሞክራሲ ለሚደረገው ትግል አስትዋጾ ማድረግ እንዳለባቸው በአጽንኦት አሳስበዋል።
ወጣት ሁሉን ነገር የመለወጥ ኃይልና አቅም አለው!አምባገነን መንግሥትን ማስወገድ እንችላለን! ወያኔን ከኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ማስወገድ እንችላለን!
ዛሬም ነገም ሁላችንም አንዳርጋቸው ፅጌ ነን!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
የወጣቶች ክፍል

Monday, January 26, 2015

የስርዓቱን አረመኔያዊ እርምጃ እናወግዛለን! ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሰጠ መግለጫ

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር አብሮ ስለመስራትና ሌሎቹም ትብብሩን እንዲቀላቀሉ በየጊዜው የሚወተውተው አገራችን በዚህ ዘመን በማይመጥን አምባገነንና የጭካኔ ስርዓት ውስጥ የምትገኝ መሆኑን በመረዳቱ ነው፡፡ ይህ የህወሓት/ኢህአዴግ አምባገነንና ጨካኝ ስርዓት ህዳሩ 27/28 2007 ዓ.ም የአዳር ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በወጡት አመራሮቻችን፣ አባላቶቻችን፣ ደጋፊዎቻችንና በየጎዳናው የተገኙት ንፁሃን ላይ ከፍተኛ ድብደባና የጅምላ እስር በመፈፀም ስርዓቱን ለመታገል የተነሳነበትን አላማ ትክክለኝነት አረጋግጦልናል፡፡
በዛሬው ዕለትም ገዥው ፓርቲ በፓርቲያቸው የውስጥ ጉዳይ ገብቶ የሚፈፅመውን ደባ፣ ምርጫ ቦርድንና የህዝብ ሚዲያን ተጠቅሞ ፓርቲውን ለመከፋፈልና አሳንሶ ለማሳየት የሚያደርገውን እኩይ ተግባር በመቃወም ሰልፍ የወጡ የአንድነት አመራሮች፣ አባላት፣ ደጋፊዎችና የፓርቲው ጽ/ቤት ፊት ለፊት የሚገኘው ቤተ ክርስትያን አካባቢ የነበሩ አዛውንት ምዕመናንን ሳይቀር በመደብደብ ጭካኔውን ዳግመኛ አሳይቶናል፡፡ ፖሊስ በትዕዛዝ በአንድነት አባላት ላይ ከፍተኛ የጭካኔ እርምጃ ወስዷል፡፡ አብዛኛዎቹንም በጅምላ አስሯል፡፡
ስርዓቱ በእነዚህ ሰላማዊ ዜጎች ላይ አሁንም የጭካኔ እርምጃውን መድገሙ ስልጣኑን የማጣት ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንዳለ እና ከይስሙላ ያለፈ ለሰላማዊ ትግሉ ዝግጁ አለመሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ ትብብራችን የስርዓቱን ጨካኝነት እያወቁም ቢሆን በሰላማዊ መንገድ ጥያቄያቸውን ለማቅረብ በስርዓቱ የማይከበረውን ህገ መንግስታዊ መርህ ተከትለው ሰልፍ ለወጡ ቆራጥ የአንድነት አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች አድናቆቱን መግለጽ ይወዳል፡፡ መስዋዕትነታችሁ ለነገ ድላችን ስንቅ በመሆኑ ይበልጡን ተጠናክራችሁ በጋራ ትግላችን እንደምናጠናክርም እምነታችን ነው፡፡
በተቃራኒው ገዥው ፓርቲ ህግ የማክበርና የማስከበር ሚናውን ረስቶ ፖሊስ፣ ደህንነትንና ሌሎች ተቋማትን ለራሱ ስልጣን ማስጠበቂያ በማዋል በአንድነት አመራሮች፣ አባላት፣ ደጋፊዎች ላይ የፈፀመውን ለዘመኑ የማይመጥንና በሰላማዊ መንገድ መብታቸውን ለጠየቁት ኢትዮጵያውያንም የማይገባ የጭካኔ እርምጃ በጥብቅ እናወግዛለን፡፡
ኢትዮጵያውያንን የማስተዳደር አቅምና ሞራል ያጣው ገዥው ፓርቲ የዜጎችን ጥያቄ በኃይል ማዳፈን የማይቻል መሆኑንና አገራችን ወደባሰ ችግር እንደሚከታት ተረድቶ ከዚህ የጭካኔ እርምጃው እንዲቆጠብ፣ እርምጃውን የወሰዱትን አካላት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑና የታሰሩትን በአስቸኳይ እንዲፈታ እናሳስባለን፡፡ ፖሊስ፣ ደህንነት፣ መከላከያና ሌሎች ተቋማት ገዥው ፓርቲ አላፊ መሆኑን በመገንዘብና ከገዥው ፓርቲ ታዛዥነት በመውጣት ወገኖቻቸሁ ላይ እንዲህ አይነት የጭካኔና አሳፋሪ እርምጃ ከመውሰድ ተቆጥባችሁ ከህዝብ ጎን እንድትቆሙ ጥሪያችን እናቀርባለን፡፡
ያለ መስዋዕትነት ድል የለም!
ጥር 17/2007 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የኢትዮጲያ ፖለቲካ መልኩን የሚቀይርበት 11ኛው ሰዓት ላይ ደርሷል!

መግቢያ መውጫ አሳጥቶ፤ የወንድ በር እንኳን ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን በማን አለብኝነትና በትምክህት ስነልቦና ተወጥሮ በአፈና ጅራፉ ሲገርፈን ፀጥ ብለን የምናይበት የፈሪ ልብ፤ መጠን ያለፈውን የጭቆና ቀንበር የምንሸከምበት ጫንቃ የለንም፡፡
ጋዜጠኛ ስለሺ የተደበደበው ሰውነቱ በፋሻ ተጠቅልሎ ይታያል
ጋዜጠኛ ስለሺ የተደበደበው ሰውነቱ በፋሻ ተጠቅልሎ ይታያል
አዎን ኢህአዴግ የደም መስዋዕትነት የከፈልኩበትን ስልጣን በቀላሉ አለቅም በሚል የሞት የሽረት ትግል እንደሚያደርግ ሁሉ እኛም ጓዶቻችን የታሰሩበትን ትግል እና ፓርቲ ወደጎን ትተን የትም አንሄድም፡፡ አንዱአለም አራጌ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ አብርሀ ደስታ፣ አግባው ሰጠኝ እና ሌሎቹም የታገሉለትን አላማ ከግብ ሳናደርስ ወደኋላ ማለት የለም፡፡
ትግሉ ሰላማዊ እና ሰላማዊ ብቻ እንዲሆን ከአንድ ወገን ብቻ (ከተቃዋሚዎች በኩል) እየተደረገ ያለውን ጥረት ኢህአዴግ እንደፈሪነት እየቆጠረው በትዕቢት ተወጥሮ ያስራል ይገላል፡፡ ነገም ኢህአዴግ ከዚህ የተለየ ነገር አያደርግም፡፡
ፓርቲያችን አንድነትን ለጀሌዎችህ ስትሰጣቸው እጃችንን አጣጥፈን ዝም ብለን አናይህም በሚል ነገ የአንድነት አባላቶች እና ደጋፊዎች ሰልፍ ሲወጡ ወያኔ እንደለመደው ያስራል፡፡
ዛሬ በልሳኑ ኢቲቪ/ኢቢሲ ደግሞ ሰማያዊ ምርጫው ሰላማዊ እንዳይሆን እሰራለሁ አመፅንም እጠራለሁ ብሏል ሲል በሬ ጥጃ ወለደ ዲስኩሩን ደስኩሯል፡፡
አንድነትን ለእነ ትዕግስቱ አወሉ ሰጥቼ እውነተኛ አመራሮቹንም አስሬ አፈርሰዋለሁ፤ ሰማያዊን ደግሞ አመፅ ሊጠራ ነው በሚል ፓርቲውን አግዳለሁ አመራሮቹንም አስራለሁ በሚል ስሌት እየሰራ እንደሆነ ከመቼውም ጊዜ በላይ ግልፅ ሆኗል፡፡
እንግዲያው ፓርቲዎችን ከዘጋ፣ ህጋዊ አመራሮችንም ካሰረ እና ሰላማዊውን መንገድ ከዘጋው የኢትዮጲያ ፖለቲካ መልኩን ይቀይራል፡፡
ጓዶቹ የታሰሩለትን ፓርቲ፣ አላማ እንዲሁም ትግል ወደጎን ትቶ የሚሄድ የለምና አሁን ትግሉ ሞትን ፊት ለፊት የመጋፈጥ እና ነፃነትን የመሻት ነው፡፡ ‹‹የሰላም በሮች ሲዘጉ የአብዮት በሮች ይከፈታሉ›› እንዲል ጋዜጠኛው ነቢዩ፡፡

Hiber Radio: የጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ከአስመራ መልስ ቃለምልልስ…የእንግሊዝ ባለስልጣናት በአንዳርጋቸው ጉዳይ መወዛገባቸው… በአ. አ. ደም መፍሰሱና ቃለምልልስ.. የቱርኩ ፕ/ት በኢትዮጵያ ሃይማኖታዊ ት/ቤቶች እንዲዘጉ መጠየቃቸው… በደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያውያን መደብሮች መመዝበራቸው… እና ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ ጥር 17 ቀን 2007 ፕሮግራም
<<..ድብደባውን የጀመሩት ከኔ ነው ።ራሴን እስክስት ድረስ በርካታ ሰዎች ሲደበደቡ አይቻለሁ... ግራ እጄ ተሰብሯል አሁን ህመም የማይሰማኝ ቦታ የለም…>>
ጋዜጠኛ ስለሺ ሀጎስ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ጋዜጣ አዘጋጅ በአንድነት ሰልፍ ላይ በአገዛዙ ፖሊሶችና ደህንነቶች ከፍተኛ ድብደባ ከደረሰባቸው አንዱ (ሙሉውን ያዳምጡ )
<<...ስድስት ፖሊሶች ከፍተኛ ድብደባ አድርሰውብኛል በሰልፉ ላይ ያልተደበደበ አልነበረም...በዚህ አገር ሰላማዊ ትግል...>> ወይዘሪት መስከረም ያደርጋል የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ጋዜጣ አምደኛ እና የፓርቲው አባል (ሙሉውን ያዳምጡ )
ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ከኤርትራ መልስ ስለ ቆይታው ከሰጠን አጠር ያለ ቃለ ምልልስ (ሙሉውን ያዳምጡ )
<<...የነፃነት ጥያቄ በጉልበት በመሳሪያና በድብደባ ሊፈታ አይችልም...>> አቶ በላይ ፈቃዱ የአንድነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት (ሙሉውን ያዳምጡ )
ሌሎችም
ዜናዎቻችን
አንድነት ያነሳሁት የፍትሕ ጥያቄ በአገዛዙ ደም የማፍሰስ እርምጃ አይቀለበስም ትግሉ ይቀጥላል አለ
የዘጠኙ ፓርቲዎች ትብብር በአንድነት ዛሬ በአንድነት ፓርቲ ላይ የተፈፀመውን አረመኔያዊ እርምጃ አወገዘ
በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ በርካታ የኢትዮጵያዊያን መደብሮች በወረበላዎች ተመዘበሩ
አንድ ኢትዮጵያዊ ባለሀብት በዘራፊዎች ተገደለ
ፖሊስ ከዘራፊዎች ጎን መቆሙ ቁጣን ቀስቅሷል
የቱርኩ ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ የሚገኙ ሀይማኖታዊ ት/ቤቶች እንዲዘጉ በመጠየቃቸው ተቃዋሚዎች ቁጣቸውን አሰሙ
የእንግሊዝ ባለስልጣናት በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጉዳይ ተወዛገቡ
ሌሎችም ዜናዎች አሉ

ቢያጥቡት የማይጸዳ ዘረኛ ቡድንን ለማስወገድ ከአንድነት ጋር አንድ እንሁን !!

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከምስረታው እስካሁን ለወያኔ ህወሃት ቡድን ትልቅ የራስ ምታት ሆኖ ቆይቷል።በመሆኑም ድርጅቱን ለማፍረስ በተለያዩ ጊዜያት የድርጅቱን አመራሮች በማሰር፣ በመደብድብ፣ ከሀገር በማስደድ፣ በማስፈራራት እና በድርጅቱ ውስጥ ሰርጎ ገቦችን በማስረግ ያላደረገው ሙከራ አልነበረም። ሆኖም ግን አንድነት በቆራጥ አመራሮቹ ፣ አባላቶችና ደጋፊዎች ታጋድሎና መስዋእትነት እስካሁን ህልውናውን ጠብቆ ቆይቷል።
በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያችን የተከሰተው አገር አቀፍ ቀውስ ህዝቡ ብሶቱን ያለምንም ፍርሃት እንዲገልጽ እያስገደደው መሆኑን የተረዳው የህወሀት ቡድን ትግሉን መርተው ከስልጣን ማማ ያወርዱኛል ብሎ የሚፈራቸውን የፖሌቲካ ድርጅቶችንና ግለሰቦችን ለማጥፋት ቆርጦ ተነስቷል። —

[ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—

 http://www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2015/01/Intriem-Task-Force-of-Andenet-Support-Chapters-in-Europe.pdf

Sunday, January 25, 2015

UK diplomats clash over Briton on death row in Ethiopia - See more at: http://www.zehabesha.com/uk-diplomats-clash-over-briton-on-death-row-in-ethiopia/#sthash.ZZkqrKAS.dpuf

Filed under: News,News Feature | 
andargachew Tisge

UK diplomats clash over Briton on death row in Ethiopia: Officials’ fury after Foreign Secretary claims he couldn’t ‘find time’ to help father-of-three facing execution

    • Andargachew Tsege was snatched by officials at Yemen airport last June
    • The 59-year-old was transferred to Ethiopia where he is thought to remain
    • Father-of-three moved to London in 1979 from native African country
    • He was dubbed ‘Ethiopian Mandela’ after exposing government corruption
    • Leaked emails revealed British officials’ frustration at political inaction
    • Philip Hammond said he could not ‘find time’ for phone call on issue 
    By Ian Birrell for The Mail on Sunday
    An explosive row has erupted between diplomats and Ministers over their reluctance to help a British man on death row in Ethiopia.
    A series of extraordinary emails, obtained by The Mail on Sunday, reveal officials’ increasing frustration at political inaction over Andargachew Tsege.
    Tsege, 59, a father-of-three from London, was snatched at an airport in Yemen last June and illegally rendered to Ethiopia. There are concerns he may have been tortured.
    Yet Foreign Secretary Philip Hammond said he could not ‘find time’ for a phone call to raise the issue and did not want to send a ‘negative’ letter.
    In one email, an exasperated official asks: ‘Don’t we need to do more than give them a stern talking to?’
    MCILG-Ethiopia-Tsege-001.jpgTsege, who has lived in the UK since 1979, has been called Ethiopia’s Nelson Mandela. Tsege fell out with his university friend ex-Prime Minister Meles Zenawi, after he exposed government corruption and helped establish a pro-democracy party.
    In 2009, he was sentenced to death in his absence for allegedly plotting a coup and planning to kill Ethiopian officials – claims he denies.
    He was abducted on June 23 while en route to Eritrea, emerging two weeks later in Ethiopia, where he has since been paraded on TV. It is not known where he is being held.
    The diplomatic exchanges disclose how officials were dismayed when British Ministers rejected requests to raise the case with Ethiopia.
    ‘I feel so shocked and let down,’ said Tsege’s wife Yemi Hailemariam. ‘I thought Britain was a nation driven by fairness but it seems my husband’s life is simply not valued.’
    The series of emails begins on July 1, with Foreign Office officials confirming his capture: ‘His detention in Yemen is significant news, and could get complicated for the UK.’
    Diplomats noted that neither Yemen nor Ethiopia informed Britain about the rendition of its citizen. ‘It feels a bit like I’m throwing the kitchen sink at the Yemenis but I want them to think twice before they do this again,’ wrote one senior figure at the British Embassy in Addis Ababa.
    He also noted that a prominent Ethiopian minister had given assurances over Tsege’s treatment –‘but I wouldn’t take them with complete confidence’.
    Ethiopia has claimed Tsege tried to recruit other Britons to become involved in terrorism. But the regime has used anti-terror laws to jail journalists and silence political rivals, and UK officials had not seen credible evidence.
    Foreign Secretary Philip Hammond said he could not ‘find time’ for a phone call to raise the issue and did not want to send a ‘negative’ letter.
    Foreign Secretary Philip Hammond said he could not ‘find time’ for a phone call to raise the issue and did not want to send a ‘negative’ letter.
        One diplomatic cable says: ‘All we have seen are a few pictures of him standing in an Eritrean village – hardly proof that he was engaged in terrorist training.’
      Three weeks after Tsege’s kidnap, the Foreign Office’s Africa director wrote that Ministers ‘have so far shied away from talking about consequences… their tone has been relatively comfortable’.
      On July 21, Hammond’s office was still reluctant to talk to his Ethiopian counterpart on the phone.
      ‘I don’t think we are going to be able to find time for that at the moment,’ wrote his private secretary. He also turned down sending a ‘negative’ letter, asking for it to be rewritten ‘setting out areas of co-operation. It can end with a paragraph on the Tsege case.’
      Despite concerns over Ethiopia’s human rights record, the nation receives £376 million a year in UK aid. One farmer there is suing Britain, claiming the money was used to usurp him from his land.
      Hammond is believed to have finally called his counterpart at the end of July, one month after the kidnap. It is understood he focused on requesting consular access rather than condemning the capture.
      Reprieve, which campaigns against the death penalty said: ‘These shocking emails show the Foreign Secretary appears to have blocked any meaningful action that could potentially bring this British father home to his family, unharmed.’
      The Foreign Office said they were ‘deeply concerned’ by Tsege’s detention and were lobbying for further consular access as well as seeking confirmation the death penalty would not be carried out.
      - See more at: http://www.zehabesha.com/uk-diplomats-clash-over-briton-on-death-row-in-ethiopia/#sthash.ZZkqrKAS.dpuf

      ለመጪው ምርጫ በአድማ ብተና ስም እየተሰጠ ያለውን ስልጠና የተቃወሙ 97 የፌዴራል ፖሊስ አባላት እርምጃ ሲወሰድባቸው፤ 119 ፖሊሶች በግዳጅ እረፍት እንዲወጡ ተደረገ።

      ጥር ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር የተባረሩት አብዮታዊ ዲሞክራሲን መቀበል ያልቻሉ ናቸው ብለዋል።
      በአሁኑ ወቅት በመላ ሀገሪቱ ፖሊሶችና ሚሊሻዎች ከምርጫው ጋር በተያያዘ ሊነሱ ይችላሉ የተባሉ ህዝባዊ አመጾችን ለማክሸፍ ያስችላል የተባለ የተኩስ ልምምድ እያደረጉ እንደሚገኙ ከየክልሎቹ የመጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።
      ከፍተኛ በጀት ተመድቦለት በፌድራል ፖሊስ  አድማ ብተና አደረጃጀት  በየክልሉ የሚካሄደውን  ይህን  ስልጠና፦ << የፖሊስን ተልእኮና ዓላማ የሳተ ነው>> በማለት በርካታ የፌዴራል ፖሊስ አባላት እንደተቃወሙት  በፌዴራል ፖሊስ ውስጥ ያሉ የኢሳት ምንጮች ጠቁመዋል። ተቃውሞ ካነሱት መካከል  206 የፌዴራል ፖሊስ አባላት ተገምግምው ከስልጠናው እንዲወገዱ መደረጋቸውን ምንጮቻችን ገልጸዋል።  ከነዚህ መካከል  በ97ቱ ላይ እርምጃ ሲወሰድ፤119ኙ እስከ ምርጫው መጠናቀቅ ድረስ የግዳጅ እረፍት እንዲወጡ ተደርጓል።
      የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር ጄነራል አቶ አሰፋ በዩ እርምጃ የተወሰደባቸውንና የግዳጅ እረፍት እንዲወጡ የተደረጉትን የፌዴራል ፖሊስ አባላት  አስመልክተው ለኢህአዴግ የምርጫ ጊዚያዊ ኮሚቴ በላኩት ደብዳቤ ፦<<አብዮታዊ ዲሞክራሲን መቀበል ያልቻሉ ናቸው>> ማለታቸውም ተመልክቷል። በመሆኑም  በምርጫው ዸህንነት ጥበቃ ላይ እንዳይሳተፉ መታገዳቸውን ዳይሬክተሩ በደብዳቤያቸው ገልጸዋል።
      ምንጮቻችን እንደሚሉት ግን <<አብዮታዊ ዲሞክራሲን መቀበል ያልቻሉ>> በሚል ምክንያት ከስራቸው እንዲታገዱም ሆነ በግዳጅ እረፍት እንዲወጡ የተደረጉት  በብሄራቸው እየተመረጡ <<ለስርዓቱ ታማኝ አይደሉም፣ ግርግር ከተነሳ ሊከዱን ይችላሉ>>ተብለው የተጠረጠሩ ፖሊሶች ናቸው። ይህ በእንዲ እንዳለ በአማራ ክልል በከፍተኛ የስራ እርከን ላይ የሚገኙ የስራ ሂደት ሃላፊዎችና ካድሬዎች ትናንት ሀሙስ እና እና ዛሬ በምርጫው ዙሪያ ስብሰባ ማድረጋቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና ያመለክታል።

      የመኢአድ ምክትል ፕሬዝደንት አዘዞ ጦር ካምፕ መወሰዳቸው ተነገረ።

      ጥር ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከቀናት በፊት በፖሊሶች ከፍተኛ ድብደ ተፈጽሞባቸው ወዳልታወቀ ስፍራ ስለመወሰዳቸው የተዘገበው የመላው ኢትዮጰያ አንድነት ድርጅት ምክትል ፕሬዚዳንት  አቶ ዘመነምህረት አዘዞ በሚገኘው መከላከያ ካምፕ መታየታቸውን ፓርቲያቸው ገለጸ።
      መኢአድ ዛሬ በሰጠው መግለጫ የድርጅቱ  ምክትል ፕሬዝደንት እና የሰሜን ቀጠና ኃላፊ የሆኑት አቶ ዘመነ ምህረት የድርጅታቸውን ጠቅላላ ጉባኤ አድርገው ወደ መኖሪያቸው ጎንደር ከተማ ከተመለሱ በኋላ ከፍተኛ የደህንነት ክትትልና ጫና ይደረግባቸው እንደነበር ለፓርቲያቸው አሳውቀው እንደነበር አስታውሷል።
      አቶ ዘመነ በ10/05/2007 ዓ.ም ጎንደር ከሚገኘው መኖሪያው ቤታቸው ከባቤታቸውና ከህጻን ልጃቸው ፊት የፖሊስ ልብስ በለበሱ አካላት ከፍተኛ ደብደባ ተፈጽሞባቸው ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን ያወሳው መኢአድ ፤በአሁኑ ወቅት የፓርቲው አባላት ባደረጉት ክትትል  አዘዞ የሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ውስጥ እንደሚኙ  መረጋገጡን  ገልጿል።
      <<በአቶ ዘመነ ላይ  የደረሰባቸው ስቃይና እንግልት በሰው ልጅ ላይ ይፈጸማል ተብሎ ፈጽሞ የማይገመት ነው >>ብሏል-መኢአድ። ከአቶ ዘመነ በተጨማሪ ጠቅላላ ጉባኤውን ተሳትፈው የተመለሱት የፓርቲው የማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊ አቶ እያሱ ሁሴን 3 አመት ተፈርዶባቸው እስር ቤት እንደሚገኙ እንዲሁም የፓርቲው አመራር አካላት የሆኑት  አቶ ተስፋዬ ታሪኩ፣ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንንና አቶ ጥላሁን አድማሴ   ታስረው እየተሰቃዩ እንደሚገኙ ገልጿል።
      በሌላ በኩል  ምርጫ ቦርድ- መኢአድ በምርጫ 2007 እንዳይሳተፍ የኢህአዴግ ቀኝ እጅ ሆኖ በመስራት ላይ እንዳለ ያወሳው መግለጫው፤ ፓርቲው በምርጫው እንዳይሳተፍ ከተደረገ ሰላማዊ ትግሉን አጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል፡፡
      ምርጫ ቦርድና ኢህአዴግ በፓርቲው ላይ የሚፈጽሙትን በደል ለማስቆም በሚደርገው ትግልም ህዝቡ ከጎኑ እንዲቆም ጥሪ መኢአድ አቅርቧል።

      የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴር- የመንግስት ሚዲያዎችን ተቸ

      ጥር ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቲቪ(ኢቢሲ) ፣ራዲዮ ፋና እና ሌሎች የመንግስት ሚዲያዎች በምርጫው ዙሪያ ጠንካራ ስራ አልሰሩም ሲል የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴር ተቸ።
      የመንግስትና የድርጅት ሚዲያዎች  ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ  ለተፎካሪ ፓርቲዎች በተሰጣቸው አጀንዳ ዙሪያ ብልጫ ያለው ስራ  አልሰሩም ሲል የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴር -የኢትዩጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬትን ወቀሰ።
      ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ -ለኢቢሲ  ባስተላለፈው የደብዳቤ ትእዛዝ በቀጣይ በሁሉም ክልሎች የሚገኙ  ብዙሀን መገናኛዎች ምርጫው እስኪጠናቀቅ ድረስ በምርጫ  ለኢህአዴግ ድጋፍ የሚያስገኙ ፕሮግራሞችንና ዶክመንተሪዎችን ያለማሳለስ እንዲሰሩ ከማስጠንቀቂያ ጋር እንዲነገራቸው አሳስቧል።
      ሚዲያዎቹ በተለይ የደጋፊዎችን ድምጽ በማሰባሰብና የድርጅቱን ፖሊሲና ስትራቴጂ በመከተል  በጽሁፎችና በፕሮግራሞች ብቃት ያላቸውን ስራዎች  በተከታታይ እንዲሰሩ  እንዲደረግ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴር አስጠንቅቋል።
      እስካሁን ፋና ኮርፖሬትንና ኢቢሲን  ጨምሮ በክልል ያሉት ብዙሀን መገናኛዎች አማራጭ ፖሊሲዎች ላይ የአመለካከት ልዩነት እንዳለ ለማሳየት  አንዳንድ ስራዎችን ቢሰሩም፤ የተሰሩት ስራዎች ጠንካራ አደሉም ተብለው ተተችተዋል፡፡

      በመላ ሀገሪቱ ዜጎች የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ እየተገደዱ ነው።

      ጥር ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የባህርዳር፣የአዲስ አበባ፣ የአምቦ፣ የጅማ፣የድብረማርቆስ እና የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ለኢሳት ወኪሎች እንደተናገሩት  በየቤቱ እየዞሩ  የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ በሚቀሰቅሱ ካድሬዎች ከመረበሻቸውም በላይ  የምርጫ ካርድ ካላወጡ ስለሚጠብቃቸው ቅጣት  ዛቻና ማስፈራሪያ እየተፈጸመባቸው ይገኛል።
      ሲጀመር ምርጫ መኖሩ በየቀኑ በራዲዮና በቴሌቪዥን እየተለፈፈ ባለበት ሁኔታ  በር እያንኳኩ ምርጫ ካርድ ውሰዱ ብሎ መቀስቀሱ አስፈላጊ አልነበረም ያሉት የባህርዳር ነዋሪዎች፤ ቅስቀሳው ግዴታ አስፈላሰጊ ነው ከተባለም<<ካርድ አልወስድም!አልመርጥም!>> ያለን ዜጋ ማሰፈራራቱን ምን አመጣው?”ሲሉ ጠይቀዋል። መምረጥም፣ አለመምረጥም  የራሳችን መብት እስከሆነ ድረስ በካድሬዎች ልንረበሽና ልንገደድ አይገባም የሚሉት የየከተሞቹ ነዋሪዎች፤ << እንድንመርጥ አፈ-ሚዝ ከተደቀነብን የምንመርጠውን እናውቃለን>> ሲሉ ተናግረዋል።

      በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደር በተቃዎሟቸው ኢትዮጰያውያን ላይ የመሰረቱትን ክስ የስዊድን ፖሊስ ውድቅ አደረገው።

      ጥር ፲፬(አስራ አራት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቀደም ሲል የኢህአዴግ መንግስት ፤ በስዊድን-ስቶኮሆልም  አዘጋጅቶት የነበረው የቦንድ ሽያጭ ዝግጅት ላይ ኢትዮጰያውያን ከፍተኛ ተቃውሞ ማሰማታቸው ይታወቃል።
      <<ከአባይ በፊት ዘረኝነት ይገደብ>> በሚል መርህ ተቃውሞውን ያደረጉት ኢትዮጰያውያን፤  ዜጎች ያለፍርድ እየታሰሩና እየተገደሉ ባለበት ሁኔታ  ገንዘብ ለመሰብሰብ መሯሯጥ፤ በሀገርና በህዝብ ላይ መቀለድ እንደሆነ በመናገር  ነበር- ተቃውሟቸውን  ጫማና እንቁላል በመወርወር የገለጹት።
      ኢትዮጰያውያኑ -አምባሳደሯን መኪና ላይ የ እንቁላል መዓት በመወርወር ተቃውሟቸውን ሲገልጹ፤አምባሳደር ወይንሽት ከመኪናቸው መውጣት ተስኗቸው ተስተውለዋል። በኦትዮጰያውያኑ ጫማና እንቁላል የተወረወረባቸው በስዊድን የኢትዮጰያ አምባሳደር ወይንሸት ታደሰ፤ <<ስራዬን መስራት እስከማልችል ድረስ በደል ደርሶብኛል>> በማለት  ለስዊድን ፖሊስ ክስ ይመሰርታሉ።
      የአምባሰደሯን ክስ ተከትሎ የስዊድን ፖሊስ  ባቀረበላቸው ጥሪ መሰረት ቃል ለመስጠት የሄዱት የኢትዮ-ስዊድን ግብረ-ሀይል አስተባባሪ አክቲቪስት መቅደስ ወርቁ እና የኢትዮጰያ ዲሞክራቲክ መድረክ ምክትል ሊቀ-መንበር አቶ ሞላ፤ ኢትዮጰያ ውስጥ ስላለው የመብት ረገጣና በስፋት ለስዊድን ፖሊስ በማብራራት፤ ተቃውሞው የተደረገው የሰብዓዊ መብት ጥሰትን፣ዘረኝነትን እና ሙስናን ለመቃወም እንደሆነ አስረድተዋል።
      ጉዳዩን የተመለከተው የስዊድን ፖሊስም በስዊድን ህግ መሰረት የዚህ ዓይነት ተቃውሞ ማድረግ መብት እንጂ ወንጀል እንዳልሆነ በመጥቀስ እና ክሱ ውደ ፍርድ ቤት የሚያመራበት አንዳችም የህግ ምክንያት እንደሌለ በማብራራት የአምባሰደሯን ክስ ውድቅ እንዳደረገው አክቲቪስት መቅደስ ተናግረዋል። የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን ከወራት በፊት በዋሽንግተን ዲሲ የልብስ መደብር ውስጥተቃውሞ ባቀረቡባቸው አክቲቪስቶች ላይ የመሰረቱት ክስ ሰሞኑን በአሜሪካ ፍርድ ቤት ውድቅ መደረጉ ይታወቃል።

      ሰሞኑን የሐመር አርብቶ አደሮች ራሳቸውን ከፖሊስ ጥቃት ለመከላከል በወሰዱት የመልሶ ማጥቃት እርምጃ፤ ከደርዘን በላይ የሚሆኑ የፖሊስ ሀይሎችን ሙትና ቁስለኛ ማረጋቸው ተመለከተ።

      ጥር ፲፬(አስራ አራት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፖሊሶች ልብሳቸውን በመቀየር በእግራቸው ወደ ጅንካ ከተማ እየሸሹ ነው።
      የፖሊስ ግጭት ወቅታዊ መረጃን በመጥቀስ የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ባወጣው መግለጫ እንደተመለከተው፤ ሐመሮች በወሰዱት የመልሶ ማጥቃት እርምጃ የዞኑን የፖሊስ አዛዥ ሻምበል ለማ አሸናፊን ጨምሮ ሰባት ፖሊሶች ሲገደሉ፤ ስድስት  ፖሊሶች ደግሞ ቁስለኛ ሆነዋል።
      ከፖሊሶቹ በተጨማሪ ሁለት ሲቪሎችም መገደላቸውና ሶስት ሰዎች መቁሰላቸው የፖሊስ ሪፖርት ያመለክታል። ፖሊሶችና የዞን መስተዳድር ሰራተኞች ከሐመር አርብቶ አደሮች ይህን ያህል ጥቃት የደረሰባቸው ፤በማጎ ፓርክ  ውስጥ <<የዱር አራዊት ገድላችሁዋል>> ባሏቸው ወጣቶች ላይ  የሀይል እርምጃ በመውሰዳቸው ነው። እንደ ፖሊስ  ወቅታዊ የግጭት ሪፖርት ፣ ጥር 7/2007 ሐሙስ ዕለት በሐመር ወረዳ በ‹‹ላላ›› ቀበሌ በሐመር ብሔረሰብ አርብቶ አደሮችና ፖሊስ መካከል በተፈጠረ ግጭት  የተገደሉት፤- የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ሻምበል ለማ አሸናፊ፣ወታደር ሙሴ ማቱሳላ፣ወታደር ደፋሩ ጦና፣ወታደር ካሬ፣ወታደር በኃይሉ፣ስሙ ለግዜዉ ያልታወቀ የልዩ ኃይል ባልደረባ፣ስሟ ለጊዜዉ ያልታወቀ ሴት ባለሙያ እናነመምህር መሳይነሽ መርነህ ናቸው።
      ከሟቾቹ በተጨማሪ  የደቡብ ኦሞ ዞን ፍትህ ጸጥታና ደንብ ማስከበር ምክትል ሀላፊአቶ ቹሜሬ የረር፣ ምክትል ሣጅን ጌታሁን ቶላ፣ወታደር ተሰማ መሰረት፣ ወታደር ጌታቸዉ ጻንቃ፣ወታደር ቱላ ኪያ፣ ባሻ ወንድማገኝ ጨነቀ፣ ወታደር ሚልኪያስ ግራኝ፣ወታደር ዘለቀ እና የዞኑ ሴቶችና ሕጻናት መምርያ ሾፌር አቶ ደምሳሽ ሞላ ቆስለው ህክምና እየተከታተሉ ይገኛሉ። በአርብቶአደሩ በኩል ስለደረሰው ጉዳት  እስካሁን መረጃ ለማግኘት አልተቻለም፡፡ አስቀድመው ፖሊሶች እርምጃ እንዲወስዱ ዲመካ ሁነዉ   ትእዛዝ ያሰተላለፉትና ኦፕሬሽኑን ሲመሩ የነበሩት – የሐመር ወረዳ ፍትህ ጸጥታና ደንብ ማስከበር ሃላፊ ኮማንደር ቡራ ካሎ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
      ከዞኑ መስተዳድር የወጣ መረጃ እንደሚያመለክተው፤ በነገው ዕለት የዞኑ ሲቪል ሠራተኞች ከስከሬን አንሺ የቀን ሠራተኞችን  ወደ ቦታው  ይዘው በመሄድ አሰከሬኖችን ለማምጣት  የሚንቀሳቀሱ ሲሆን፤ በዚህ ጉዞ ወታደራዊ ኃይል እንዳይኖር ወይም  እንዳያጅባቸው ተወስኗል።
      በአሁኑ ሰዓት በሃመር ወረዳ ዋና ከተማ ዲመካ ምንም የፖሊስ ኃይል የሌለ ሲሆን፤ አንዳንድ የወረዳውና ከዞኑ የተንቀሳቀሱ ፖሊሶች የፖሊስ ልብሳቸውን በመቀየር በእግር ጫካ ለጫካ በመጓዝ ወደ ዞኑ ከተማ  ወደ ጂንካ እያቀኑ ሲሆን፤በሽሽት ነፍሳቸውን ያተረፉት ፖሊሶችም የጂንካ ከተማ ነዋሪ፦ ‹‹እንኳን ለቤታችሁ አበቃችሁ›› እያለ እየተቀበላቸው ነው።
      ፖሊሶቹም፦ ‹‹ በማናውቀው ነገር አስገብተውን ሊያስጨርሱን ነበር፣ የተፈጠረው ሁኔታ እና በወንድሞቻችን ላይ የደረሰው በእጅጉ አሳዛኝ ነው›› በማለት ቁጭታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ ፡፡
      የግጭቱን ምክንያቶች በዝርዝር ያስቀመጠው  የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት፤መንግስት በግጭቱ ስለደረሰው  አጠቃላይ ጉዳት በቂ መረጃ እንዲሠጥና በድርጊቱ አዛዦችና ፈጻሚዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ፤ በግጭቱ ለተጎዱ ወገኖችና ለደረሰው የንብረት ውድመት ካሳ እንዲከፍል፤ ግጭቱ ከመጪው ምርጫ ጋር በቀጥታ የሚገናኝ ስለሆነ አፋጣኝና አሳታፊ መፍትሄው እንዲፈልግለት፤የፖሊስ ተግባራትና ማኅበራዊ አገልግሎቶች ወደቦታቸው እንዲመለሱ እንዲያደርግ ጠይቋል።
      እንዲሁም  ችግሩን ከስሩ ለማስወገድ ሕብረተሰቡን ያሳተፈና በማኅበረሰቡ ተቀባይነት ያለው አካባቢያዊ ዘላቂ መፍትሄ እንዲያበጅና ችግሩ እንዳይባባስና እንዳይስፋፋ አስቸኳይ የማረጋጋት እርምጃ እንዲወስድ የጠየቀው ድርጅቱ፤ የማንአለብኝነት የኃይል እርምጃ መቼውንም መፍትሄ አይሆንምና ፤ለቀጣይም መንግሥት ከዚህ ዓይነቱ አካሄድ እንዲታቀብ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን”ብሏል

      ኢህአዴግ ለምርጫው ዝግጅት እንዲሆን በማለት በብሄር ለተደራጁ ፓርቲዎች 200 ሚሊዩን 349 ሺ 231 ብር ፈሰስ አደረገ፡፡

      ጥር ፲፬(አስራ አራት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የድርጅቱ ምንጮች ለኢሳት እንደጠቆሙት፤ በመጀመሪያው ዙር ፈሰስ የተደረገው ይህ ገንዘብ ለቲሸርት ፤ ለኮፍያ ፤ እና ለበራሪ ወረቀቶች ህትመት  የሚውል ነው ተብሏል፡፡
      ለፕሮሞሺን ስራ አገልግሎት የሚውል ተብሎ በብሄር ለተደራጁ ድርጅቶች ፈሰስ  ከተደረገው ከዚህ ገንዘብ ባሻገር ለአራቱ የኢህአዴግ ድርጅቶች ማለትም ለህወሀት፣ ለብአዴን፣ለኦህዴድ እና ለደኢህዴግ  5 ሚሊዮን  87 ሺህ 307 ብር ከ75 ሳንቲም  በየአካውንታቸው ገቢ መደረጉን ምንጮቹ አመልክተዋል።
      ኢህአዴግ ላባል ድርጅቶቹ ያከፋፈለውን ይህን ገንዘብ <<ከአባላት ክፍያ ያሰባሰብኩት ነው>> ማለቱም ተሰምቷል። ኢህአዴግ ከዚህም በላይ ከግንቦቱ ምርጫ ጋር በተያያዘ  ከበለሃብቱ  ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ለማሰባሰብ እቅድ ማውጣቱና ይህንንም እቅዱን  በዚሁ በጥር ወር አጋማሺ ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ታውቋል።
      የሚሰበሰበው ገንዘብ በኢህአዴግ  ግምገማ<< የምርጫው የስጋት ቀጠናዎች >> ተብለው  በተለዩት በአማራ ፤ ኦሮምያ፤ ትግራይ እና ደቡብ ክልሎች   ድጋፍን ለማጠናከር ይውላል መባሉንም የምንጮቻችን መረጃ ያመለክታል።

      በአዲስ አበባ ሳሪስ አካባቢ ቻይናዎች የባቡር ሀዲድ ለማንጠፍ ቁፋሮ ሲያካሂዱ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተደርምሶ በመናዱ በርካታ ህጻናት ተማሪዎች መጎዳታቸው ተሰማ።

      ጥር ፲፬(አስራ አራት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አደጋው የደረሰው ሳሪስ አቦ ማዞሪያ ትንሽ ከፍ ብሎ በሚገኘውና የሀዲድ ንጣፍ ስራ እየተካሄደበት ባለ ቦታ ላይ ነው።
      በአደጋው የደረሰውን ጉዳት ለጊዜው ማወቅ   ባይቻልም፤አምቡላንሶች የተጎዱ ተማሪዎችን  ወደ ሆስፒታል ሲያመላልሱ  መዋላቸውን ሪፖርተራችን ከስፍራው ዘግቧል።

      ኢህአዴግ በምርጫ ቦርድ አማካይነት አንድነት ፓርቲን ለማፍረስ የጠነሰሰው ሴራ ተጋለጠ።

      ጥር ፲፬(አስራ አራት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግና ምርጫ ቦርድ አንድነት ፓርቲ ለሁለት እንደተሰነጠቀ በማስመሰል ያቀነባበሩት ሴራ መጋለጡን እና መክሸፉን ከፓርቲው ጽሕፈት ቤት  የደረሰን ዜና ያመለክታል።
      ምርጫ ቦርድ “የአንድነትን ጠቅላላ ጉባኤ ጠርተዋል” ሲላቸው  የነበሩት አቶ አየለ ስሜነህ፤ በዛሬው እለት “አንድነት አንድ ነው፤ እናት ፓርቲዬን ለማዳን ተመልሻለሁ” በማለት በአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
      በአንድነት ስም ተጠራ የተባለውን የዲ-አፍሪኩን ስብሰባም እነሱ እንዳልጠሩትና ህገ-ወጥ ነው ብለው እንደሚያምኑ አቶ አየለ ተናግረዋል፡፡
      የአንድነት ፓርቲ የሚዲያ ክፍል፤ ህወሃት/ኢህአዴግ፣ ምርጫ ቦርድ፣ ራዲዮ ፋና እና  በቅርቡ ኢቢሲ የተባለው የቀድሞው ኢቲቪ ተቀናጅተው ሲሰሩ የሰነበሩትን ፕሮፖጋንዳ የሚያጋልጥ ዘጋቢ ፊልም  ይፋ እንደሚያደርግም አስታውቋል፡፡ዘግይቶ በደረሰን መረጃ መሰረት  <<ወደ ቤቴ ተመልሻለሁ>> ወደ እናት ፓርቲያቸው የተመለሱት እና የ ኢህአዴግን እና የምርጫ ቦርድን ሴራ ያከሸፉት አቶ አየለ ስሜነህ ከደህንነቶች ማስፈራሪያና ዛቻ እየተሰነዘረባቸው ነው።
      << አንድነት ኖረም አልኖረም፣ ይሄ ትግል ጥርጥር በሌለው ሁኔታ ይቀጥላል>> ሲሉ አቶ በላይ ፈቃዱ ገልጹ። የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ሊቀመንበር አቶ በላይ ፈቃዱ ከድርጅታቸው ልሳን  ከፍኖተ-ነጻነት ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ፤   ፓርቲያቸው  ወደነጻነት ትግል የሚያመራ ከመሆኑ አንጻር ምርጫ ቦርድ ተገቢ ባልሆነ መንገድ ፓርቲውን ለመዝጋት መነሳቱ፤ ትግሉን አንድ እርከን ከፍ እንደሚያደርገው ተናግረዋል።
      <<ትግሉ ከርዕዮተ-ዓለም የዘለለ የነፃነት ትግል ነው፤ይህ ማለት ትግሉ የግድ ስልጣን መጨበጫ ብቻ ሳይሆን፤ ነፃ እና ገለልተኛ የዴሞክራሲ ተቋማት መፍጠሪያ ይሆናል ማለት ነው፡፡>> ያሉት ሊቀመንበሩ፤<< ስለዚህ አንድነት ኖረም አልኖረም፣ ይሄ ትግል ጥርጥር በሌለው ሁኔታ ይቀጥላል፡፡>>ብለዋል። አቶ በላይ አክለውም፦ << አሁን ሌላ አቋም ላይ ደርሰናል፤ እንዲህ አይነት “ምርጫ ቦርድ” ባለበት ሀገር የፓርቲ ፖለቲካ እንደማያዋጣ አቋም ይዘናል፡፡>> ብለዋል።
      ፓርቲ፣ ለስልጣን የሚታገል ኃይል ነው ቢባልም መሠረታዊ የዴሞክራሲ ተቋማት በሌሉበት በፓርቲ ደረጃ ያንን ማሰብ እንደማይቻል ያስረዱት ሊቀመንበሩ፤ <<እዚህ ሀገር መደራጀት አትችልም፤ በራሪ ወረቀት መበተን አይቻልም፤ የደህንነት ክትትሉ ልብህን ያወልቃል፡፡ ይህ ከሆነ በፓርቲ ፖለቲካ ስልጣን መያዝ ይቻላል የሚለውን እምነት መልሰን መላልሰን መጠየቅ አለብን፡፡>> ብለዋል።
      << ጥያቄው የነፃነት ትግሉ እንዴት ይፋፋም? የሚል ነው ያሉት አቶ በላይ፤ << በመላ ሀገሪቱ ወደ 40 የሚጠጉ ቢሮዎች አሉን፤ ለነፃነት ትግሉ ድጋፍ መስጠት የሚፈልግ የትኛውም አካል ቢሮውን መጋራት ይችላል፡፡ ይህን አቋም የያዝነው ነውጥ-አልባ ትግል፤ ብቸኛው የነፃነት መንገድ ነው የሚለውን በሰፊ ጥሞና ስለደረስንበት ነው፡፡>>ብለዋል።
      << ከምርጫ ቦርድ ጋር የገባንበትን ጭቅጭቅ እንደ ትልቅ ዕድልም፣ ድልም አድርገን የምናየው የድሉ መንገድ ይህ ስለሆነ ነው>> ብለዋል የአንድነት ሊቀመንበር።
      ከምርጫ ቦርድ ጋር በመግባባት ለመስራት በርካታ ጥረቶች ቢደረጉም ቦርዱ ፖለቲካዊ አቋም በመያዙ ሊሳካ አለመቻሉን ያወሱት ሊቀመንበሩ፤  <<ስርዓቱ፣ ለአፈና በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር ፈሰስ እያደረገ  ባለበት ሁኔታ ያለው አማራጭ ህዝባዊ ንቅናቄ ማድረግ እንደሆነና ይህንንም  ለማሳካት ከሌሎች የዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ጋር መተባበር የግድ እንደሆነ አስምረውበታል።

      Sunday, January 18, 2015

      የአማራ ክልል ፖሊሶች ከመቼውም በበለጠ እርምጃ ለመውሰድ በተጠንቀቅ እንዲሆኑ ተነገራቸው

      ጥር ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፖሊሶቹ በበኩላቸው – <<እኛን ህዝብ ጋር አታጣሉን>> ሲሉ ለአዛዦቻቸው ትእዛዝ ምላሽ ሰጥተዋል።
      የክልሎ ፖሊሶች  ከመቼውም በላይ ለእርምጃ እረንዲዘጋጁ  የተነገራቸው፤የማረሚያ ቤቶችንና የትራፊክ ፖሊሶችን ጨምሮ ላለፉት ስድስት ቀናት በአማራ ክልል ለሚገኙ ፖሊሶች በሚሉ ሲሰጥ በነበረው ስልጠና  ላይ ነው።
      እስከ ትናንት ሐሙስ  ድረስ በቆየው በዚሁ ስልጠና ላይ ከምርጫው  እና ከጥምቀት በዓል ጋር በተያያዘ ሁኔታ ሊፈጠሩ የሚችሉ አለመረጋጋቶችን ለማክሸፍ ዝግጁ እንዲሆኑ የታዘዙ  ሲሆን፤ ተልእኳቸውን በብቃት እንዲወጡ  የሚያስችላቸውን ተጨማሪ ትጥቅ ሰሞኑን እንደሚያገኙ ተነግሯቸዋል።
      በባርዳር አባይ ማዶ ባለው የምክር ቤት አዳራሽ የተካሄደውን ስብሰባ የመሩት  የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ኮማንደር ሙሉጌታ ወርቁ እና ምክትላቸው- ፖሊሶቹን ፦<<አግዙን፤ እኛም እናግዛችሀሁዋለን>> በማለት ሲማጸኑ ሰንብተዋል።
      መንግስት ከደመወዝ ጋር በተያያዘ ፖሊሶች የሚያነሱትን ጥያቄ ለመመለስ ጥረት እያደረገ እንደሆነ በመግለጽም ሰልጣኞቹን ለመደለል ሞክረዋል።
      እያንዳንዱ የፖሊስ አባል መሳሪያ እንዲይዝና 240 ጥይት እንዲታጠቅ መመሪያ መተላለፉን የገለጹት ኮሚሽነሩ፤ ጥይትና መሳሪያ ያልተሟላላቸው በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት እንደሚሰጣቸው አስታውቀዋል።
      እንዲሁም ከመጪው ጥር 30 እስከ የካቲት 7  ባሉት ጊዜያት የተለያዩ የመከላከያ ሀይሎች ፤ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች-ወደ ጎንደርና ባህርዳር እንደሚገቡ የገለጹት  ኮሚሽነሮቹ፤  እርምጃ ለመውሰድ ከወትሮው በተለየ መልኩ  በተጠንቀቅ እንዲቆሙ አሳስበዋል።
      ሰልጣኝ ፖሊሶቹ ባነሱት ጥያቄ፤ በአስተዳደር ችግር ህዝብ ጥያቄ ባነሳ ቁጥር ከህዝብ ጋር መጋጨት እንደማይፈልጉ በመጥቀስ፤ <<እኛ ህዝብ ጋር አንጋጪም፣ የህዝብን ቅሬታ እናንተ ፍቱ>>ብለዋል።
      ለስድስት ቀናት በቆየው የባህርዳሩ ስልጠና ከደብረ ማርቆስና ከተለያዩ የክልሉ ከተሞች የመጡ ፖሊሶች የተሳተፉ ሲሆን፤ ለባህር ዳሮቹም ሆነ ከሩቅ ለመጡት አልጋንና ምግብን ጨምሮ 300 ብር ነው የተሰጣቸው።
      በአበሉ ቅር ያላቸው አንድ ፖሊስ ለ ኢሳት በሰጡት አስተያየት፦<<አዛዦችና ሀላፊዎች ለተለያዩ ስብሰባዎች ሲንቀሳቀሱ ከሆቴልና ከምግብ ውጪ ለ አንድ ቀን ብቻ 250 እና 300 ብር አበል በሚያገኙበት ሀገር፤ ከሌላ ከተማ ለስልጠና መጥተው ስድስት ቀን ለቆዩ ፖሊሶች  ምግባቸውንና መኝታቸውን ጨምሮ ለስድስቱም ቀን 300 ብር ብቻ መስጠት ፖሊሱን መናቅ ጭምር ነው>>ብለዋል።
      በሌላ በኩል ከመጪው ማክስኞ ጀምሮ እስከ አርብ ድረስ መምህራን ስልጣና እንዲገቡ በመታዘዛቸው  በባህር ዳር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ትምህርት እንደሌለ ተነግሯል።

      የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወንድም በወታደሮች ተደበደበ

      ጥር ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዝዋይ ወህኒ ቤት የሚገኘውን ወንድሙን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ለመጠየቅ ትናንት ማለዳ ወህኒ ቤቱ በራፍ ላይ የደረሰው ታሪኩ ደሳለኝ በወህኒ ቤቱ ሀላፊና ስምንት በሚደርሱ ወታደሮች ድብደባ እንደደረሰበት በፌስ ቡክ ገጹ ታሪኩ አስታውቋል፡፡ለተመስገን ይዞ የመጣውን ምግብ ወታደሮቹ መሬት ላይ ከመድፋታቸውም በላይ በኪሱ የያዘውን ገንዘብ ወስደውበታል፡፡ታሪኩ ከደረሰበት ድብደባ በላይ ወንድሙን ሳይጠይቅና የሚገኝበትን ሁኔታ ሳያጣራ መመለሱ ህመም እንደፈጠረበት አስታውቋል

      ገዥው ፓርቲ መጪውን ምርጫ ተከትሎ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ብቻ ሳይሆን በህዝቡ ላይ ጭምር ከፍተኛ ጫና እየፈጸመ እንደሆነ በተለያዩ ክልል ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጹ።

      ጥር ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ፣የደሴ፣ የሀዋሳ፣የአርባምንጪ፣ የሀረር፣ የሚዛን ተፈሪ፣የሰበታ፣ የባህርዳር፣ የወልቂጤና የሌሎችም ከተሞች ነዋሪዎች  ለኢሳት እንደገለጹት፣በካድሬዎች አማካይነት ህዝቡ የምርጫ ካርድ በግዳጅ እንዲወስድ እና ድምጹን ለኢህአዴግ እንዲሰጥ እየተደረገበት ያለው ግፊት ከመቼውም ጊዜ በላይ እየከፋ መጥቷል።
      ከካድሬዎቹ ማስፈራሪያዎች መካከል፦<<የምርጫ ካርድ ካልወሰዳችሁ የቀበሌ መታወቂያና ሌሎችንም አስተዳደራዊ አገልግሎቶች አታገኙም፣ በምርጫው ኢህአዴግን ካልመረጣችሁ ሁዋላ ላይ ተጣርቶ እርምጃ ይወሰድባችሁዋል፤የትም የማይደርሱ ተቃዋሚዎችን እንመርጣለን ብላችሁ በራሳችሁ ላይ ችግር እንዳትፈጥሩ ተጠንቀቁ>>የሚሉት ይገኙበታል። << ካድሬዎች በር እያንኳኩ ነዋሪዎችን እንቅልፍ በመንሳት የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ እያስገደዱ ከመሆናቸውም በላይ፤ አንድ ሰው እስከ 12 ሰው ካላስመዘገበ በቀበሌ አገልግሎት እንደማያገኝ እያስጠነቀቁ ነው>>ተብሏልም።።
      በግድ የኢህአዴግ አባል እንዲሆኑና ኢህአዴግን እንዲመርጡ እየተገደዱ መሆናቸውንም የገለጹ በርካቶች ናቸው። ከዚህም በላይ አንዳንድ ውስጥ አዋቂዎች ኢህአዴግ አንዳንድ ሰዎችን ያለፍላጎታቸው በተለያዩ የንግድ እንቅስቃሴዎቻቸው ጫና በመፍጠር ለሱ እንዲሰሩለት በማስጠንቀቅ በየምርጫ ጣቢያው  በገለልተኛ ስም ማስቀመጡ የተጋለጠ ሲሆን፤ ሰዎቹ-ከተቃዋሚዎች ጥያቄ ቢቀርብላቸው <<ገለልተኛ ነን >>የሚል ምላሽ ይሰጡ ዘንድ መመሪያ እንደተነገራቸው ተሰምቷል።
      በተመሳሳይ ምርጫውን ተከትሎ በተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ላይ እየተፈጸመ ያለው እስርና ድብደባ ተባብሶ ቀጥሏል። ታህሳስ 27/2007 ዓ,ም  በባህርዳር ከተማ የኢትዮጰያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መድረክ አባላት – በስርዓቱ አገልጋዮች  ታፍነው ወዳልታወቀ ስፍራ መወሰዳቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና ያመለክታል።
      ታፍነው ከተወሰዱት የመድረክ አባላት መካከል፤ አቶ ቴዎድሮስ መለስ፤ ወ/ሮ ሪዒማ ከድር፤ በባህር ዳር ዩንቨርስቲ መምህር የነበረው አቶ ተፈራ ማሙና ሌሎችም የሚገኙበት ሲሆን፤ የታፈኑበት ምክንያትም ሆነ ፤ያሉበት ስፍራ እስካሁን ድረስ አልታወቀም።
      እንዲሁም ” ኢቲቪ ውሸታም ነው ፣ ኢህአዴግ ሌበ ነው”ብለሀል ተብሎ   ክስ የተመሰረተበትና  የሶስት ዓመት እስራት የተፈረደበት የመላው ኢትዮጰያ አንድነት ድርጅት  አባል የሆነው አዲሱ ሁሴን፤ በእስር ቤት ከፍተኛ ድብደባና ግርፋት እየተፈጸመበት እንደሆነ ድርጅቱ ገልጿል። የደቡብ ወሎ የመኢአድ አባል የሆነው አዲሱ ሁሴን   ፍርደኛ እስረኛ ሆኖ ከድብደባና ግርፋት ማረፍ አለመቻሉ፤  በኢትዮጰያ እስር ቤቶች ለሚፈጸሙ የከፉ ሰብ ዓዊ መብት ጥሰቶች አንድ ማሳያ ነው ብለዋል-መረጃውን ያደረሱን የመኢአድ አባል።
      ከሰሞኑ ብቻ ብቻ ሁለት የአንድነት ፓርቲ አባላት የፐጻርቲውን ጠቅላላ ጉባኤ ተሳትፈው ወደቤታቸው ሲያቀኑ መደብደባቸው እና በወላይታ የሰማያዊ ፓርቲ አስተረባባሪዎች መታሰራቸው ይታወቃል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የመላው ኢትዮጰያ አንድነት ፓርቲና የኢትዮጰያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ በጋራ ባወጡት መግለጫ  ገዥው ፓርቲና  ምርጫ ቦርድ በተቃዋሚዎች ላይ በተለይም  በሰማያዊ፣ በአንድነትና በ መ ኢአድ ፓርቲዎች ላይ የሚፈጽሙትን ዛቻና በደል እንዲያቆሙ መጠየቃቸውን ነገረ-ኢትዮጵያ ዘግቧል
      ፓርቲዎቹ ህዳር 7/2007 ዓ.ም ‹‹በምርጫ ዋዜማ በፓርቲዎች ላይ የሚደርሰው ደባና ዛቻ በአስቸኳይ ይቁም›› በሚል በጋራ ባወጡት መግለጫ ፤ ሰማያዊ ፓርቲ አገራዊ ግዴታውን እየተወጣ በመሆኑ፣ እንዲሁም መኢአድና አንድነት ብቃት ያላቸው ልሂቃንን ማፍራት በመቻላቸው ስጋት የተፈጠረበት  ገዥው ፓርቲ – ፓርቲዎቹን ለማጥፋት እየጣረ መሆኑን በመጥቀስ፤<< ምርጫ ቦርድም የኢህአዴግ አምስተኛ አባል ፓርቲ እስኪመስል ድርስ የገዥው ፓርቲ መጠቀሚያ ሆኗል>> ሲሉ ወቅሰዋል፡፡
      ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው-ገዥው ፓርቲ -በፓርቲዎቹ ላይ እየፈጸመ ካለው ድርጊት እንዲቆጠብ፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድመረ ከገዥው ፓርቲ መሳሪያነት ወጥቶ የተጣለበትን ኃላፊነት እንዲወጣ፤ አሣስበዋል፡፡

      ደቡብ ኦሞ ውስጥ በአርብቶ አደሮችና በፖሊስ መካከል ግችት ተቀስቅሶ የነዋሪዎችና የፖሊሶች ህይወት ጠፋ፤ ግጭቱና ውጥረቱ ሊቆም አልቻለም።

      ጥር ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ኦሞ ዞን አመር ወረዳ- ላላ ቀበሌ ነዋሪ በሆኑ አርብቶ አደሮችና- በፖሊስ መካከል ግጭት ተቀስቅሶ የሰው ነፍስ መጥፋቱን ነገረ ኢትዮጰያ ዘገበ፡፡
      ጋዜጣው ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ትናንት ጥር 7/2007 ዓ.ም  <<አርብቶ አደሮች ማጎ ፓርክ ገብተው አውሬ ገድለዋል>> በማለት  ፖሊስ- አርብቶ አደሮቹ ገዳዩን አሳልፈው እንዲሰጡት በጠየቀበት ወቅት ነው ግጭቱ የተነሳው።
      በአርብቶ አደሮችና በፖሊስ መካከል በተፈጠረ ግጭት ከሁለቱም ወገን የሰው ህይዎት መጥፋቱንና የቆሰሉም እንደሚገኝበት የኦሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ህብረት ሊቀመንበር አቶ ግርማ በቀለ ገልጸዋል፡፡
      ከዞኑ ፖሊስ ሻለቃ ለማ አሸናፊ የተባሉ የፖሊስ ባልደረባ በአርብቶ አደሮች ሲገደሉ፤ የዞኑ የፀጥታና የፍትሕ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ጩመሬ የረር፣ እና የዞኑ የፖሊስ አባል የሆነው ወታደር ተሰማ መሰረት ቆስለው ደቡብ ኦሞ ዞን ሆስፒታል  እየታከሙ ይገኛሉ፡፡
      እንዲሁም በግጭቱ ምክንያትም ከዲመካ ከተማ ቀይ አፈር ወደ ተባለው ከተማ የሚወስደው እንዲሁም ከቱሚ ወደ ዲመካ ከተማ የሚወስደው መንገድ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ተዘግቷል።  በአሁኑ ወቅት  የዞኑ ዋና ከተማ በሆነው የጅንካ ከተማ እና ዲመካ፣ ቱኒ፣ ቀይ አፈር እና ኦሞራቴ ከተሞች ውጥረት መንገሱን አቶ ግርማ በቀለ ገልጸዋል፡፡
      ቀደም ሲልም በአካባቢው ተመሳሳይ ችግሮች እንደሚፈጠሩ ያወሱት ሊቀመንበሩ፤ በማህበረሰቡ ዘንድ ግጭቶች ሲፈጠሩ በባህላዊ መንገድ የሚፈቱ  ሆነው ሳለ ፤ መንግስት  ባህላቸውን ግምት ውስጥ ሳያስገባና የአገር ሽማግሌዎችን ሳያናግር በአርብቶ አደሮቹ ላይ  እርምጃ በመውሰዱ፤ ታጣቂዎች  የሆኑት የአካባቢው አርብቶአደሮች  ምላሻቸውን በኃይል እንደገለጹ አስረድተዋል፡፡
      ‹‹በአብዛኛው ግጭት የሚከሰተው የአካባቢውን የግጭት አፈታት ወደጎን በመተው ችግሩን በኃይል ለመፍታት በሚጥረው መንግስት ነው›› ያሉት አቶ ግርማ የአሁኑ ግጭትም የተነሳው በመንግስት ችግር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ አቶ ግርማ በቀለ አክለውም ‹‹ችግሩን በኃይል ለመፍታት የሚጥረው መንግስት ተጨማሪ የሰው ነፍስ እንዳይጠፋና ወደ እርስ በእርስ ግጭት እንዳያመራ አሁንም ከኃይል እርምጃው ተቆጥቦ ችግሩ በአካባቢው የግጭት አፈታት እንዲፈታ ማድረግ አለበት›› ሲሉ አሳስበዋል፡፡
      ትናንት ጠዋት ላይ የተጀመረው የአርብቶ አደሮችና- የፖሊስ ግጭት ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ አልቆመም።

      አርበኞች- ግንቦት 7 ለ አንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ ለ ኢትዮጰያ ህዝብ፣ ለመከላከያ ሰራዊቱና ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥሪ አቀረበ።

      ጥር ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ንቅናቄው  በግንቦት 7 እና በ አርበኞች ግንባር መካከል የተደረገውን ውህደት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ << እኛ መዋሃድ መወሰናችንን  ስንገልጽ፤ በተናጠል ከሚደረጉት – በጋራ የሚደረጉ የትግል ጥረቶች ውጤታማ ይሆናሉ በሚል ብቻ ሳይሆን፣፡”የተቃዋሚ ድርጅቶች፣ በምንም ዓይነት ሁኔታ በሀገርና በሕዝብ ደረጃ ትርጉም ያለው ሥራ በጋራ መስራት አይቻሉም’ የሚለውን፣ አስከፊ ተመክሮና አመለካካት ለመስበርም ጭምር ነው።” ብሏል።
      <<ከትናናሽ ድርጅቶች ዙሪያ ከሚሽከረከሩ ሀሳቦችና ስሜቶች ለመውጣትና ሀገራዊና ሕዝባዊ የሆነውን ጉዳይ ለማስቀደም የወሰነ ማንኛውም ድርጅት፣ አርበኞችና ግንቦት7፣ እንደደረሱበት የውህደት ውሳኔ ፤ወይም በሌሎች በጋራ ሊያሰሩ በሚችሉ ስምምነቶች አብሮ ለመስራት መወሰን የማይችልበት ምንም ምክንያት አይታየንም።>>ብሏል ንቅናቄው።
      <<በወያኔ አድሎ ስርዓት የተንገፈገፈና ትግሉን ለመቀላቀል የቆረጠ ማንኛውም ዜጋ፣ የተገኘውን አጋጣሚ በመጠቀም ትግሉን መቀላቀል ይችላል>>ያለው አርበኞች-ግንቦት 7፤ <<የኢትዮያ ሕዝብ በአንድነት የተነሳ ቀን ደግሞ፣ የወያኔ ግብዓተ መሬት ይፈጸማል ብለን ከልብ እናምናለን።>> ሲል የመተባበርን አንድነት በ አጽንኦት ገልጿል።
      ንቅናቄው ለተቃዋሚ ድርጅቶች ባስተላለፈው መልእክት <<ዛሬ በአርበኞችና በግንቦት 7፣ የተጀመረው ጉዞ ውጤታማ በመሆን ሀገራዊና ታሪካዊ ትርጉም እንዲኖረው፣ ሌሎችም በተግባር የምትንቀሳቀሱ ተቃዋሚ   ድርጅቶች፣ ወያኔን የማስወገድንና ብሎም ሀገር የማረጋጋቱን ሀላፊነት በጋራ እንድንወጣ የሚያስችል መቀራረብ እንድናደርግ ፣ በውህደት በመሰረትነው- በአርበኞች ግንቦት 7፣ ለአንድነትና ዴሞክራሲ፣ ንቅናቄ፣ ሥም፣ ጥሪያችንን እናቀርባለን።>> ብሏል።
      ንቅናቄው ለወታደራዊና የፖሊስ ሠራዊት አባላት ባስተላለፈው መልእክት ደግሞ፤<<የወያኔን ዘረኛና አምባገነን ቡድንን ዕድሜ  ለማሳጠርና ሁላችንንም በእኩልነት የምታስተናግድ ሀገር እንድትኖር፣ የሰሞኑን ቆራጥ የዓየር ሃይል መኮንንኖች ያሳዩትን ዓርያነት በመከተልና በተገኘው አጋጣሚና ሁኔታ በመጠቀም በየቦታው የሚደረገውን ትግል እንድትቀላቀሉ በውህዱ ድርጅታችን  ሥም፣ ጥሪያችንን እናቀርባለን።>>ብሏል።
      ንቅናቄው በመጨረሻም፦<<የተከበርከው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ፣በረጅም ታሪክህ አይተሄው ለማታውቀው ውርደት፣ ክፋት፣ የመከፋፈልና የመጋጨት አደጋ የዳረገህን እና  ሀገርና ሕዝብን የማራከስና የመሸጥ ዕኩይ ተግባር የተጠናወተውን  አገዛዝ ከነግብር አበሮቹ ጠራርጎ ለማስወገድ በተጀመረው የጋራ ትግል ውስጥ በቀጥታ እንድትሳተፍ አለያም  በምትችለው ቀዳዳ ሁሉ ድጋፍ እንድታደርግ፣ በአርበኞች ግንቦት 7፣ ለአንድነትና ዴሞክራሲ፣ ንቅናቄ ሥም፣ ጥሪያችንን እናቀርባለን።>> ሲል መግለጫውን ቋጭቷል።

      የጥምቀት በዓል መድረሱን ተከትሎ ውጥረት አለ፤ሰማያዊ ቲሸርት የለበሱ ወጣቶች ከሥላሴ በዓል ላይ ተባረሩ

      ጥር ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዛሬ ጥር 7/2007 ዓ.ም የዓመቱን የሥላሴ በዓል ለማክበር አራት ኪሎ የሚገኘው ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን የተገኙ ወጣቶች ሰማያዊ ቲሸርት በመልበሳቸው በፖሊስ መባረራቸውን ነገረ- ኢትዮጰያ ዘግቧል፡፡
      ፖሊስ፤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅስ የተጻፈበት  ሰማያዊ ቲሸርት የለበሱትን ወጣቶች ቲሸርቱን እንዲያወልቁ ሲጠይቅ ወጣቶቹ አናወልቅም በማለታቸው ከበዓሉ እንዳባረራቸው የዐይን እማኞች ገልጸዋል፡፡  ከተባረሩት ወጣቶች መካከል አብዛኛዎቹ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚገቡትንና የሚወጡትን ምእመናን በማስተባበር ላይ እንደነበሩ የተገለጸ ሲሆን ፤ ወጣቶቹ -ይታሰሩ፤ አይታሰሩ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም፡፡
      ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የመጡ ከፍተኛ ኃላፊዎች ለጥምቀት በዓል ሰማያዊ ቲሸርት ያዘጋጁትን የጃንሜዳ እና  አካባቢው የጥምቀት በዓል አስተባባሪዎችን በመሰብሰብ፣ ወጣቶች ያዘጋጇቸውን ሰማያዊ ቲሸርቶች በዓሉ ላይ እንዳይለበሱ በተደጋጋሚ እያስጠነቀቁ ይገኛሉ።
      በፖሊሶችና በደህንነቶች ተደጋጋሚ ጫና የጃንሜዳ አካባቢ ወጣቶች ያዘጋጁትን ሰማያዊ ቲሸርትና  በቲሸርቱ ላይ ያጻፉትን ጥቅስ  መቀየራቸውን ሲናገሩ፤ በአንጻሩ የፈረንሳይና ቤላ አካባቢ ወጣቶች፤ << ሰማያዊ ቲሸርታችንን አንቀይርም!>> በሚል አቋማቸው መጽናታቸው ታውቋል፡፡
      ትናንት ጥር 6 ቀን የአዲስ አበባ መስሪያ ቤቶችና ወረዳዎች ኮሙኒኬሽን ኃላፊዎች፤  በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ባደረጉት ስብሰባ፤ የየካ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ፈረንሳይ ሌጋሲዮን አካባቢ ‹የፈራ ይመለስ› የሚል ሰማያዊ ቲሸርት አስለብሶ ሲበጠብጠኝ ሰንብቷል፡፡›› ሲሉ ሪፖርት ማቅረባቸውን የስብሰባው ተሳታፊዎች ለጋዜጣው ገልጸዋል፡፡
      ስለ ጉዳዩ  የተጠየቁት የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ፦ ‹‹ደህንነት፣ ፖሊሶችና ካድሬዎች እያንዳንዱን የህዝብ እንቅስቃሴ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር በማገናኘት ወቀሳ የሚያቀርቡት፤ ህዝብ ውስጥ ብሶት እንዳለ እና ሰማያዊም የህዝብን ብሶት እንደሚያሳማ ስለሚያውቁ፣ ከምንም በላይ ገዥው ፓርቲ የራሱን ጥላ የማያምንበት ደረጃ ላይ ስለደረሰ ነው›› ብለዋል፡፡
      የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ባነሱባቸው ጊዜያት ሁሉ ገዥው ፓርቲ ሰማያዊ ፓርቲን ‹‹የሙስሊም ፓርቲ ነው›› የሚል ሀሰተኛ ወሬ ሲያሰራጭ እንደነበር ያስታወሱት ኃላፊው፤ <<አሁንም ፓርቲውን ከእያንዳንዱ የህዝብ እንቅስቃሴ ጋር እያገናኘ ቢበረግግ አያስገርምም>> ብለዋል፡፡