Pages

Wednesday, August 27, 2014

የወልድያ ከተማ ህዝብ ብሶቱን አሰማ


ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብአዴን ከፍተኛ ሹሞች ከከተማው ህዝብ ተወካዮች፣ ከኢህአዴግ አባላትና ከተለያዩ የመስሪያ
ቤት ሃላፊዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ነዋሪዎች የተለያዩ ችግሮችን አንስተዋል። አንድ አስተያየት ሰጪ የጤና ተቋማት መድሃኒት በማጣታቸው አግልግሎት
እየሰጡ አለመሆኑን ተናግረዋል ሌላ አስተያየት ሰጪ ደግሞ የመብራት ችግር የከተማው ችግር መሆኑን ገልጸዋል
ኮብልስቶን ለይስሙላ ተብሎ የሚሰራ በመሆኑ ለህዝቡ ችግር እየፈጠረ መሆኑን አንድ ሴት አስተያየት ሰጪ ገልጸዋል
ኢህአዴግ በተለያዩ አካባቢዎች የሚያደርጋቸውን ስብሰባዎችን ስንዘግብ መቆየታችን ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment