Pages

Wednesday, May 6, 2015

በኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክር መድረክ ተዘጋጀ

ሚያዝያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ከምሁራንና ከዲሞክራሲ አቀንቃኞች ጋር በጋራ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ፣ ተጋባዥ እንግዶች በኢትዮጵያ ወቅታዊ ፖለቲካ ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ወረቀቶችን ያቀርባሉ።
ምሁራኑ ኢትዮጵያ የገጠሙዋትን ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች በማንሳት ተጨባጭ የመፍትሄ ሃሳቦችንም ያመላክታሉ ተብሎ ይጠበቃል። በውይይቱ ላይ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ምሁራን፣ የዲሞክራሲ አቀንቃኞችና የውጭ አገር ዜጎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በፈረንጆች አቆጣጠር ሜይ 9 እና 10 በዋሽንግተን ዲሲ በሸራተን ናሽናል ሆቴል በሚደረገው ዝግጅት ላይ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራዊያን አርቲስቶች ዝግጅት ያቀርባሉ።

No comments:

Post a Comment