Pages

Tuesday, March 3, 2015

ፋብሪካዎች በውጭ ምንዛሬ እጥረት ስራቸውን ለመስራት ተችግረዋል

የካቲት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የሚታየው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ፋብሪካዎች ስራቸውን በተገቢው መንገድ እንዳያከናውኑ እንቅፋት ፈጥሮባቸዋል።
ከዚህ ቀደም ከደንበኞቻቸው ጋር የተለያዩ የስራ ውሎችን ተዋውለው በጊዜው ማድረስ ያልቻሉ ፋብሪካዎች፣ ለደንበኞቻቸው ” በአገራችን በሚታየው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት በሰአቱ ማድረስ አልቻልንም” በማለት የይቅርታ ደብዳቤዎችን በመጻፍ ላይ ናቸው።
በማኑካንቸሪንግና በኮንስትራክሽን ዘርፍ እንዲሁም በአስመጪነት የተሰማሩ ባለሃብቶች ለከፍተኛ ችግር የተዳረጉ ሲሆን፣ መንግስት በአብዛኛው ራሱ ለሚያስገነባቸው ፕሮጀክቶች የውጭ ምንዛሬ ቅድሚያ እንዲሰጣቸው በማድረጉ፣ የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ በከፍተኛ ሁኔታ እየተጎዳ ነው።
መንግስት የውጭ ምንዛሬ ችግር የለም በማለት በተደጋጋሚ ቢናገርም፣ ችግሩ ግን በገሃድ የሚታየው መሆኑን ነጋዴዎች ይገልጻሉ።

No comments:

Post a Comment