Pages

Wednesday, October 22, 2014

በሃረሪ የሚታየው የስኳር እጥረት መባባሱን ነዋሪዎች ገለጹ

ጥቅምት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወኪላችን እንደሚለው በከተማው የታየውን የስኳር እጥረት ተከትሎ፣ አንድ ኪሎ ስኳር እስከ 30 ብር በመሸጥ ላይ ነው። በተመሳሳይ መልኩ የሚታየው የዘይት እጥረት  የነዋሪውን ኑሮ አስከፊ እንዳደረገው ገልጿል።
የስኳር እጥረቱ በደቡብ፣ በኦሮምያና በአማራ አካባቢዎችም በስፋት እየታየ ነው። መንግስት የስኳር ፋብሪካዎች ወደ ምርት ሲገቡ ስኳር ወደ ውጭ መላክ እንችላለን በማለት ህዝቡን ለማረጋጋት ቢሞክርም፣ የተባሉት ፋብሪካዎች እስከሚደርሱ መንግስት የህዝቡን ወቅታዊ ችግር ለመቅረፍ የያዘው ሌላ አማራጭ የለም በሚል እየተተቸ ነው።

No comments:

Post a Comment