Pages

Wednesday, September 3, 2014

የሱዳኑ መሪ ካይሮን ሊጎበኙ ነው

ነሃሴ ፳፮(ሃያስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሱዳኑፕሬዘዳንት ጄኔራል አልበሸር  ከግብጹፕሬዘዳንት አብደልፋታህ አልሲሲ በተደረገላቸው ግብዣ
መሰረት በጥቂት ቀናት ውስጥ ግብጽን እንደሚጎበኙ ታውቋል :: በካይሮ የሚገኙት የሱዳን አምባሳደር አብደልሃሊም አብደልሞሃመድ እንዳስታወቁት
የጉብኝቱ ቀዳሚ አጀንዳ ኢትዮጵያ ስለምትሰራው  የግድብ ስራ ሲሆን ሱዳንም የግብጽን ችግር ለመረዳት ያስችላታልብለዋል:: ግብጽ በተደጋጋሚ
እንዳስታወቀችው ኢትዮጵያ የምትሰራውግድብወደአገርዋየሚገባውንየውሃመጠንይቀንሳልበማለትክስእያሰማችትገኛለች:: አምባሳደር አብዱል
በበኩላቸውእንደተናገሩት  ግድቡላይየሚነሳውአቤቱታየሚፈታው  በሶስትዮሽስምምነትብቻ ነውብለዋል::
ሶስቱ አገሮች ግድቡን በውጭ አገር ባለሙያዎች ለማስጠናት በቅርቡ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment