Pages

Saturday, June 7, 2014

የቡድን 7 አገራት ከድሃ አገራት በህገ ወጥ መንገድ የሚወጣውን ገንዘብ ለመቆጣጠር በድጋሜ ቃል ገቡ


ግንቦት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ ለኢሳት በላከው መግለጫ በእንዱስትሪ ሃብታቸው የበለጸጉት 7ቱ አገራት ከድሃ አገሮች እየተዘረፈ በምእራባዊያን ባንኮች የሚቀመጠውን ገንዘብ ለመቆጣጠር በድጋሜ ቃል ገብተዋል።
የቡድን 7ቱንአገራትአቋምያደነቀውግሎባልፋይናንሻልኢንተግሪቲ፣ቃሉበተግባርመለወጥእንዳለበትአሳስቧል።
ግሎባል ፋይናንሻል ኢንትግሪቲ ከኢትዮጵያ በ9 አመታት ውስጥ ከ11 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ በህገወጥ መንገድ ወደ ውጭ መውጣቱን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል።
ወደ ውጭ የወጣው ገንዘብ ኢትዮጵያ በዚህ አመት ከመደበችው 8 ቢሊዮን ዶላር መንግስታዊ በጀት ይበልጣል።

No comments:

Post a Comment