Pages

Friday, May 9, 2014

የግብጹ እጩ ፕሬዚዳንት ስልጣን ከያዙ የሙስሊም ብራዘርስ ሁድ ፓርቲን እንደሚያጠፉ ተናገሩ


ሚያዚያ ፳፰ (ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አብዱል አል ፋታህ ሲሲ ከግብጽ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ስልጣን ከያዙ ሙስሊም ብራዘር ሁድስ ፓርቲን ሙሉ በሙሉ እንደሚያጠፉት ተናግረዋል።
እጩ ፕሬዚዳንቱ ሁለት ጊዜ የመግደል ሙከራ ተደርጎባቸው እንደነበር ገልጸዋል።
መከላከያ ሰራዊቱ የግብጽን አብዮት ቀልብሰዋል ተብሎ የሚወራው ትክክል አለመሆኑም ተናግረዋል። ፕሬዚዳንት ለመሆን የሚወዳደሩት ሲሲ፣ የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ሙሀመድ ሙርሲን ከስልጣን ሲያስወግዱ ስልጣን እይዛለሁ ብለው እንዳላሰቡ ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment