Pages

Tuesday, May 27, 2014

ግብጻውያን መሪያቸውን እየመረጡ ነው


ግንቦት ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዲሞክራሲያዊ መንገድ ተመርጠው፣ አንድን ወገን ጥቅም ብቻ ያራምዳሉ በሚል በህዝቡ ተቃውሞና በወታደሩ ድጋፍ ከስልጣን እንዲነሱና ወደ እስር እንዲጋዙ በተደረጉት ሙሀመድ ሙርሲ ምትክ፣ ግብጻውያን አዲሱን መሪወያቸውን ለመመርጥ ዛሬ ድምጽ ሲሰጡ ውለዋል።
በቀድሞው የጦር አዛዥ በ ፊልድ ማርሻል አብዱል ፋታህ አልሲሲና በሶሻሊስት ተቀናቃኛቸው ሃምዲን ሳባሂ መካከል በሚደረገው ፉክክር ፣ አል ሲሲ በቀላሉ ያሸንፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
አል ሲሲ ሙሀመድ ሙርሲን በማስወገዱ በኩል ከፍተኛውን ሚና የተጫወቱ ሲሆን፣ በአብዛኛው ግብጻውያን ዘንድ ይወደዳሉ። የሙስሊም ብራዘርስ ሁድ ደጋፊዎች ደግሞእንደ አምባገነንና ጨፍጫፊ ይመለከቱዋቸዋል።
አል ሲሲ በምርጫ ለመወዳደር ወታደራዊ ስልጣናቸውን ከወራት በፊት አስረክበዋል።

No comments:

Post a Comment