ጉዳዩ ከሚያንገበግባቸው የአትላንታ ሰአሊተ ምህረት ቅድስተ ማርያም ካቴድራል ኣባላት
ቀን፡ 6/2/2009 አ/ም (10/16216 እ.ኤ.አ.)
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ: አሃዱ አምላክ: አሜን!!
- የወያኔ ምልምል አባላት እና ድብቅ ደጋፊወችች ሴራም ግልፅ ሆነ
- የቦርዱ ሰብሳቢ እና ግብረ አበሮቻቸው ብብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የሚመራውን ህጋዊውን ቅዱስ ሲኖዶስ እንደማይከተሉ በግልፅ በመናገር የወያኔ ተልዕኮ አስፈፃሚዎች እንደሆኑ አረጋግጠዋል፡፡
የተወሰኑ የአትላንታ ሰአሊተ ምህረት ቅድስተ ማርያም ካቴድራል ቤተክርስትያን ቦርድ አባላት በእምባገነኖቹ አቶ አባተ ዘውዴ አና አቶ አየለ ገብሩ በመመራት የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የሆኑትን ብፁዕ አባታችን አቡነ ያዕቆብን ከክርስትያናዊ እና አባታዊ አገልግሎታቸው ለማሰናበት እጅግ አሳዛኝ እና እንዲሁም ፈጣሪን እና ቤተ ክርስትያንን ከሚያገለግሉ ምዕመናን የማይጠበቅ የስንብት ወረቀት መፃፋቸውን ተከትሎ ከሁለት ሶስተኛ በላይ የሚሆኑት የካቴድራሉ አባላት ቅሬታቸውን ሲያሰሙ ዉለዋል፡፡ በዕለቱ፡ እጅጉን ያዘኑ ምዕመናን በከፍተኛ ለቅሶ እና ሃዘን ተዉጠው ብፁዕ አባታችን አቡነ ያዕቆብን ከብበው ፀሃይ እና ዝናብ እየተፈራረቀባቸው ሲዘምሩ እና ሲፀልዩ ዉለዋል፡፡
No comments:
Post a Comment