Pages

Pages

Monday, January 5, 2015

የእስቴ መምህራን ተቃውሞ አሰሙ

ታኀሳስ ፳፪(ሃያ ሁለትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :- በደቡብ ጎንደር እስቴ ወረዳ የሚገኙ  መምህራን ለ3 ቀናት የሚቆይ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ስብሰባ እንዲካፈሉ ቢጠሩም፣ መምህራኑ በስብሰባው ላይ ከተገኙ በሁዋላ፣ በአንድ ድምጽ ስብሰባ ኣንሳተፍም በማለት ጥለው ወጥተዋል። መምህራኑ መንገድ የመሳሰሉ የመሰረተ-ልማቶች አልተሟሉም፣ ለመምህራን በቂ የሆነ ክፍያ አይሰጥም በማለት ተደጋጋሚ ቅሬታ ሲያቀርቡ ቆይተዋል።
በዚህ ሁኔታ ውስጥ የተጠራው ስብሰባ በተቃውሞ ታጅቦ መበተኑንና የመምህራኑ  ያለተጠበቀ እርምጃ የአካባቢውን ባለስልጣናት ማስደንገጡን መምህራን ለኢሳት ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment