Pages

Tuesday, December 9, 2014

ጋዜጠኛ ተመስገን በእስር ላይ ለሚገኙት ለሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ መሪዎች የመከላከያ ምስክርነት ሰጠ

ኀዳር ፳፭(ሃያ አምስትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ  ህዳር 25/2007 ዓም የመከላከያ ምስክርነቱን የሰጠ ሲሆን  ጥር 11/2004 በታላቁ አወሊያ መስጂድ ቅጥር ጊቢ ተገኝቶ  የሙስሊም መሪዎች በነጻ ምርጫ መመረጣቸውን ተናግሯል።
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሃምሌ 9/2004 የህግ አዋቂውን ኡስታዝ ካሚል ሸምሱን፣ ኡስታዝ አቡበክር አህመድን፣ ኡስታዝ አህመድ ሙስጠፋን፣  ኡስታዝ አህመዲን ጀበልን ማናገሩን ገልጿል።  የመንግስት ባለስልጣን የሆኑት አ/ቶ ሪድዋን ሁሴን በሰንደቅ ጋዜጣላይ በመቅረብ “ኮሚቴው አላማው ኢስላማዊ መንግስት ማቋቋም ነው” ብለው መግለጫ ሲሰጡ ማየቱንና ኡስታዝ አቡበክርን ስለሁኔታው ጠይቆት በጭራሽ አላማቸው እንዳልሆነ መግለፁን አስረድቷል።  ተመስገን መንግስት ለ23 ዓመታት ሙስሊሙን ማህበረሰብ በቀበሌ ምርጫ እያካሄደ መጨፍለቁን፥ እየጨፈለቀ መሆኑን፣ ከጨፍላቂዎቹ አንዱ ደግሞ አ/ቶ ሪደዋን ሁሴን መሆናቸውን ተናግሯል።
ኡስታዝ ያሲን ኑሩ በሰጡት ምስክርነት ደግሞ ሙራድ ሽኩር ኮሚቴው ኢስላማዊ መንግስት ሊያቋቁም አቅዷል፣ የበጎ አድራጎት ድርጅቶቹ ከአልቃዒዳ ጋር ግንኙነት አላቸው እያሉ እየተደበደቡና መስክር እየተባሉ እንደነበር ገልጸዋል።
ኡስታዝ ያሲን ሙራድ ሽኩር በከፍተኛ ሁኔታ መደብደባቸውንም ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment