Pages

Pages

Saturday, April 19, 2014

የስቀለት በአል እየተከበረ ነው

 

ሚያዚያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የክርስቶስ እየሱስን ስቅለት ለመዘከር በየአመቱ የሚከበረው የስቅለት በአል ዘንድሮም በጾምና በጸሎት እየተከበረ ነው።
የኢሳት ዘጋቢ ያነጋገራቸው አንዳንድ ምእመናን በጾም በጸሎትና ስግደታቸው ወቅት እግዚአብሄር ኢትዮጵያን እንዲጎበኝ መለመናቸውን ተናግረዋል።
“በአገራችን ችጋር ጠፍቶ ሁሉም በደስታ እንዲኖር እመኛለሁ” የምትለው አንዲት የ19 ዓመት ወጣት፣ የዘንድሮው የፋሲካ በአል ለሁሉም ደስታን ይዞ እንዲመጣ ተመኝታለች።
ከጾም ጸሎት በተጨማሪ የታመሙትን በመጠየቅ ማሳለፉን የተናገረ ሌላ ወጣት በበኩሉ፣ በአገራችንና በአካባቢያችን የሚታዩትን ችግሮች እግዚአብሄር መፍትሄ እንዲያመጣ ሲጸልይ መዋሉን ገልጿል።

No comments:

Post a Comment