Pages

Wednesday, April 9, 2014

በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ንብረቶቻቸው ተዘረፉ

መጋቢት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኖርዝ ዌስት ውስጥ ቡልም ኦፍ በምትባል ከተማ ውስጥ የሚገኙ ከ100 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ሱቆች ተዘርፈው ተቃጥለዋል።

የከተማው ነዋሪዎች ከመሰረታዊ ልማት ጋር በተያያዘ ያስነሱትን ተቃውሞ ተከትሎ ረብሻ መፈጠሩንና ኢትዮጵያውያን፣ ሶማሊያውያንና ፓኪስታናውያን ኢላማ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያውያኑ አካባቢውን ለቀው ወደ ተለያዩ ቦታዎች ተሰደዋል። በከተማዋ የሚታየው ግጭት ተባብሶ መቀጠሉንም ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment