Pages

Thursday, October 27, 2016

የዐማራ የጎበዝ አለቆች ሕብረት ተጋድሎ ወደ ሕዝባዊ ንቅናቄ ሊያድግ ነው፤

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች | 
 317  3 

በሙሉቀን ተሰፋው
በተለያዩ አካባቢዎች ያነጋገርናቸው የጎበዝ አለቆች የወያኔ መንግሥት በዐማራው ሕዝብ ላይ የሚያደርሰው ጥቃት ተጠናክሮ በመቀጠሉ በተበታተነ መልኩ በየአካባቢው ሲደረግ የነበረው ሕዝባዊ ተጋድሎ ድርጅታዊ መዋቅር የያዘ ሕዝባዊ ንቅናቄ ሊሆን ነው ብለዋል፡፡ የጎበዝ አለቆቹ ሕብረት የመሠረቱት የሕዝባዊ ንቅናቄ ትግል በቅርብ ይፋ እንደሚደረግም አክለው ገልጸዋል፡፡

amhara
‹‹ወሳኙ›› በመባል የሚታወቀው የጎበዝ አለቃ ‹‹ሕይወታቸውን ለመስጠት ዝግጁ ከሆኑ ወጣቶች ጋር በአንድ ላይ መክረንበታል፡፡ በማንነታችን ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመመከት የእኛን መስዋእትነት ይጠይቃል፤ በተለያዩ አካባቢዎች ካሉ የጎበዝ አለቆች ጥምረት ጋር መክረንበታል›› ሲል ዛሬ ጥቅምት 17 ቀን 2009 ዓ.ም. አረጋግጦልናል፡፡ ወሳኙ ያለበትን ቦታ ዕቅድም በድፍረት የተናገረ ቢሆንም ለጥንቃቄ ሲባል ቦታዎቹን ይፋ አለማድረግ መርጠናል፡፡ ‹‹ፈላሻው›› በመባል የሚታወቀው ሌላው የጎበዝ አለቃ ደግሞ ‹‹ወያኔ በዐማራው ላይ እያደረሰው ያለው ጥፋት ምንም ዓይነት መሻሻል አላሳየም፤ የማንነት ጥያቄ ያቀረቡ የወልቃይት ጠገዴ ዐማራ ኮሚቴዎችን ጥያቄያቸውን ከመፍታት ይልቅ እያሳደደ ማሳር ሥራየ ብሎ ይዞታል፡፡ የዐማራ ወጣት ለበለጠው ተጋድሎ መዘጋጀት አለበት፡፡ ሁሉም የዐማራ ወጣት እንደ አንድ መነሳት አለበት፡፡ ወጣቱ ዛሬ ወይም ነገ ለሚደረግ ጥሪ ዝግጁ ሆኖ መጠበቅ አለበት፡፡ ከሕዝባችን ላይ የተጣለውን ጭቆና ለመገርሰስ የእኛ መስዋትነት የግድ ብሏል›› ሲል አብራርቷል፡፡
የጎበዝ አለቆቹ በሰሜን ጎንደር የኮማድ ፖስት የሚባለው የወያኔ አገዛዝ የገበሬውን ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ መፍጠሩንና በርካታ ወጣቶችን ማሰሩን አውስተዋል፡፡ በምስራቅ ጎጃም በጎንቻ ሲሦእነሴ ጉንደወይን ከተማ የሁለት ወያኔዎች ንብረት የሆነ ዓለም ሆቴል የተባለን ለማቃጠል አስባችኋል በሚል ሳጅን ምናሉ የተባለ ቅጥረኛ የዐማራ ወጣችን ዛሬ ማሰሩን የጎበዝ አለቆቹ ጨምረው ተናግረዋል፡፡ ሳጅን ምናሉ እና ተመሳሳይ ወንጅል እየፈጸሙ ያሉ ቅጥረኞች ከዐማራ ሕዝብ ጎን እንዲቆሙም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ የአበባ እርሻ ባለንብረቶች ዐማራ የሆኑ የድርጅቱን ሠራቶች የሁለት ወር ደመወዝ ካለመክፈላቸውም በተጨማሪ ሠራተኞችን ያለ አግባብ ማንገላታታቸው በኋላ የእጃቸውን እንደሚያገኙም አሰጠንቅቀዋል፡፡ የአበባ እርሻ ጥበቃ ሠራተኞች በገበሬዎች ላይ ምንም ዓይነት እርምጃ እንዳይወስዱ አሳስበዋል፡፡

Monday, October 17, 2016

እጅግ አሳዛኝ ዕለተ-ሰንበት በአትላንታ ሰአሊተ ምህረት ቅድስተ ማርያም ካቴድራል

ጉዳዩ ከሚያንገበግባቸው የአትላንታ ሰአሊተ ምህረት ቅድስተ ማርያም ካቴድራል ኣባላት
ቀን፡ 6/2/2009 አ/ም (10/16216 እ.ኤ.አ.)
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ: አሃዱ አምላክ: አሜን!!
  • የወያኔ ምልምል አባላት እና ድብቅ ደጋፊወችች ሴራም ግልፅ ሆነ
  • የቦርዱ ሰብሳቢ እና ግብረ አበሮቻቸው ብብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የሚመራውን ህጋዊውን ቅዱስ ሲኖዶስ እንደማይከተሉ በግልፅ በመናገር የወያኔ ተልዕኮ አስፈፃሚዎች እንደሆኑ አረጋግጠዋል፡፡
የተወሰኑ የአትላንታ ሰአሊተ ምህረት ቅድስተ ማርያም ካቴድራል ቤተክርስትያን ቦርድ አባላት በእምባገነኖቹ አቶ አባተ ዘውዴ አና አቶ አየለ ገብሩ በመመራት የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የሆኑትን ብፁዕ አባታችን አቡነ ያዕቆብን ከክርስትያናዊ እና አባታዊ አገልግሎታቸው ለማሰናበት እጅግ አሳዛኝ እና እንዲሁም ፈጣሪን እና ቤተ ክርስትያንን ከሚያገለግሉ ምዕመናን የማይጠበቅ የስንብት ወረቀት መፃፋቸውን ተከትሎ ከሁለት ሶስተኛ በላይ የሚሆኑት የካቴድራሉ አባላት ቅሬታቸውን ሲያሰሙ ዉለዋል፡፡ በዕለቱ፡ እጅጉን ያዘኑ ምዕመናን በከፍተኛ ለቅሶ እና ሃዘን ተዉጠው  ብፁዕ አባታችን አቡነ ያዕቆብን ከብበው ፀሃይ እና ዝናብ እየተፈራረቀባቸው ሲዘምሩ እና ሲፀልዩ ዉለዋል፡፡

Friday, October 14, 2016

ከኢትዮጵያ ሴቶች የመብት ማዕከል (CREW) የተሰጠ መግለጫ October 13, 2016 | Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች | Posted by: Zehabesha 44 1

1 


የኢትዮጵያ ሴቶች የመብት ማዕከል (CREW) ለሰብዓዊ መብቶች መከበር፣ ለሴቶች የእኩልነት መብት መረጋገጥ፣ ለዲሞክራሲ ሥርዓት እውን መሆን፣ ለሰላምና ለሕግ የበላይነት ተግባራዊ መሆን የሚታገል ሕዝባዊ ድርጅት ነው።
እኛ በኢትዮጵያ ሴቶች የመብት ማዕከል የተሰባሰብን ሴቶች በሀገራችን እየተካሄደ ያለውን ሕዝባዊ እንቅስቃሴና የመንግሥትንም በሕዝቡ ለተነሱት ጥያቄዎች የሚሰጠውን የጥይት ምላሽ እየተከታተልን ነው። ለመብታቸው ሲታገሉ መስዋዕት የሆኑትን ወገኖቻችን ነፍሳቸው በሰላም እረፍት እንድታገኝ፤ የተሰዉላት ሀገራቸውም ስቃይና መከራዋ በአጭር ሆኖ ትንሣኤዋን ለማየት እንዲያበቃን እየተመኘን ለቤተሰቦቻቸውና ለኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በሙሉ መጽናናትን ያድልልን እንላለን።
በሀገራችን በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ በጣም አስከፊ ደረጃ ላይ ደረሷል። የኢትዮጵያ ሕዝብ የመናገር፣ የመጻፍ፣ የመሰብሰብ የመደራጀት፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መሠረታዊ መብቱ ተረግጦ በገዛ ሀገሩ የበይ ተመልካች ሆኖ፣ ወጣቶች የተሻለ ኑሮና ሕይወት ፍለጋ ወደ ማያውቋቸው ሀገሮች በበረሃ፣ በባህር፣ በዱር በገደሉ እየተጓዙ የአውሬና የአሣ ነባሪ ቀለብ ሆነዋል። ላለፉት 25 ዓመታት ያለማቋረጥ ሀገራቸው የምድር ሲኦል ሆናባቸው በድህነት፣ በሥራ አጥነት፣በማንነት ጥያቄ፣ መተንፈሻ በማጣታቸው ትዕግሥታቸው ገንፍሎ በቃን ተበደልን፣ በደል አንገፈገፈን ብለው በሰላማዊ መንገድ ለመብታቸው ባደረጉት ትግል ከመንግሥታቸው ጥይት እየዘነበባቸው ከፍተኛ የሆነ ቁጥር በመላው ሃገሪቷ ሕዝብ እየረገፈ ነው። ላለፈው አንድ ዓመት በፊት ጀምሮ በኦሮሞ ወገኖቻችን የተነሳው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ዛሬም እንዳለ ነው፤ የወልቃይት የማንነት ጥያቄን መሠረት አድርጎ በጎንደር በጎጃም የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የሀገሪቷን ጎልማሳ ሽማግሌ፣ ሴት ወንድ፣ ህፃንና ወጣት ሳይለይ በሞት እየቀጠፈ ነው። በኮንሶ፣ በቤንሻንጉል፣ በደቡብ፣ በሰሜን፣ በምስራቅና በምዕራብ መላው ሀገሪቷ በሕዝብ ደም ማዕበል እየተጥለቀለቀችና በመንግሥት ታጣቂዎች ጥይት እየታመሰች ትገኛለች።
ይህ ሁኔታ በአግባቡ ከአልተያዘና በአስቸኳይ ካልቆመ ሀገሪቷንና የአካባቢውን ሀገራት ጨምሮ ወደ አልተገመተ አስከፊ የፖለቲካ የማህበራዊና የምጣኔ ሀብት ቀውስ ውስጥ ሊያስገባ ይችላል። ምንም እንኳን መንግሥት በጎሳና በሃይማኖት እየከፋፈለ ላለፉት 25 ዓመታት በእጥፍ እያደገነው የሚለው የምጣኔ ሀብት እድገት ለጥቂቶች መከበሪያ ከመሆነ አልፎ የሕዝቡን የኑሮ ሁኔታ ሊቀይረው አለመቻሉ ግራ የሚያጋባ ስሌት ቢሆንም የሀገሪቱ የኤኮኖሚ ግሽበት ከ90% በላይ የሚሆነው ሕዝብ ከድህነት በታች እንዲኖር አድርጎታል። በ2009 መንግሥት አትራፊ ያልሆኑ ሕዝባዊ ድርጅቶችን የሚገድብ ህግ ደንግጓል። ይህ ህግ ሕዝባዊ ድርጅቶችን፣ ሰብዓዊ መብቶችን ለማስጠበቅ የቆሙትንና ተቆርቋሪ ድርጅቶችን ለሕዝቡ እንዳይደርሱ አምክኗቸዋል።
በዚሁ ሥርዓት ተወልደው የጎለመሱት የነገዋ ኢትዮጵያ ተረካቢ ትውልድ ቀደም ሲል በመካከለኛ ምሥራቅ በስደት ፍዳቸውን ያዩና ያለቁት ቁጥር ስፍር የላቸውም። አሁን ደግሞ ተስፋ በማጣት መረረኝ ብለው በሀገራቸው በስላማዊ ትግል ብሶታቸውን በማሰማታቸው መንግሥት ምላሹ ጥይት ሆኖ በየቀኑ እንደ ጉድ እየረገፉ ነው። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ይባስ ብሎ መንግሥት በሀገሪቱ ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማውጅ በገዛ ሕዝቡ ላይ አመጹን የሚያባብስ እርማጃ ወስዷል።
ይህ አዋጅ የሀገሪቷን መጻኢ ዕድል ከፍተኛ አደጋ ላይ የሚጥል፣ ሕዝቡን ለከፋ ቀውስ የሚዳርግ በመሆኑ አጥብቀን እንቃወማለን።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ እየደረሰበህ ያለው አስከፊ የመብት እረገጣ፣ ግድያና እሥራቱን ለመቋቋም አንድነት ኃይል ነው፣ የሕዝብን የአንድነት ትግል የሚያሸንፈው ኃይል የለምና ትግላችሁን ከዋናውና ከጋራ ጠላታችሁ ጋር ብቻ በማድረግ ይችን ክፉ ዘመን በጋራ በአንድነት በመቆም እንድትወጡት ወገናዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
የተቃዋሚ ኃይሎች ልዩነታችሁን አጥብባችሁ በየቀኑ በሚያለቀው፣ እንታገልልሃለን በምትሉትና ልትሰዉለት በተዘጋጃችሁት ሕዝብ ስም ከምንግዜውም በላይ ዛሬ በሚያግባቧችሁ መሠረታዊ ጥያቄ ላይ በማተኮር በጋራ ቆማችሁ ኢትዮጵያን ለማዳን ለሕዝባችሁ እንድትደርሱለት በአንክሮ እንጠይቃለን።
የተለያያችሁ ሕዝባዊ ማህበራት፣ የእምነት የሃይማኖት ተቋማት፣ የዕድር የእቁብ፣ አትራፊ ያልሆናችሁ ወገናችሁን በመርዳት ላይ ያላችሁ ተቋማት ሁላችሁም የወገናችን ዕልቂት በአስቸኳይ እንዲቆምና ሕዝባዊ መሠረት ያለው ሁሉም ኢትዮጵያውያንና የህብረተሰቡ አካሎች የተሳተፉበት ሕዝብ የመረጠው ሕዝባዊ መንግሥት እንዲመሰረት የበኩላችሁን ተሳትፎ እንድታደርጉ እንጠይቃለን።
የዓለም አቀፍ ህብረተሰብ በተለይ የአሜሪካንና ኃያላን አገሮች፣ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ያላቸውን ፖሊሲ እንድትመረምሩና የገዛ ሕዝቡን በጥይት ከሚጨርስ ከወያኔ ኢህአድግ መንግሥት ጋር ሳይሆን ከኢትዮጵያና ሕዝቧ ጎን እንድትቆሙ አጥብቀን እንጠይቃለን።
ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነት ለዘላለም ትኑር።
የኢትዮጵያ ሴቶች የመብት ማዕከል (CREW)

Thursday, October 13, 2016

በባህር ዳር ከተማ በመካሄድ ላይ ያለው የስራ ማቆም አድማ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

በባህር ዳር ከተማ በመካሄድ ላይ ያለው የስራ ማቆም አድማ  ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በባህር ዳር ከተማ በተደጋጋሚ በተጠሩት የስራ ማቆም አድማዎች አንድነቱን ያሳየው የባህር ዳር ከተማ ማህበረሰብ ለስርዓቱ አንገዛም የሚለውን መፈክር አሁንም በማሳየት የስራ ማቆሙን አድማ ለሁለተኛ ቀን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በትላንትናው እለት በተካሄደው የስራ ማቆም አድማ እንዳይሳተፉ ጫና ተደርጎባቸው ከሰዓት በኋላ የተከፈቱ የአዴት ተራ ሱቆች ዛሬ በእምቢተኝነታቸው በመጽናት ከሌላው  ማህበረሰብ ጋር የአድማው ተሳታፊ በመሆን ሱቆቻቸውን ... Read More »

ዲላ ከተማና አካባቢው አሁንም አለመረጋጋቱን ነዋሪዎች ገለጹ

ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዲላ የአካባቢው ሹሞች ቀስቅሰው እንዳስነሱት በሚታመነው ግጭት በከተማዋ ከሚገኙ የተለያዩ ብሄረሰቦች ብቻ 23 ሰዎች ሲሞቱ፣ ከገጠሩ ህዝብ ወይም ከጌዲዮ ማህበረሰብ በርካታ ሰዎች ተገድለዋል። በዲላ፣ ይርጋጨፌ፣ ወናጎና ሌሎችም አካባቢዎች ግጭቱ መስፋፋቱን ተከትሎ ወደ ከተማዋ የገቡት የአጋዚ ወታደሮች በቀጥታ እርምጃ በመውሰድ በርካቶችን ገድለዋል። በርካታ ሱቆች፣ የቡና መፈልፈያዎች፣ ሆቴሎች፣ መኪኖችና ሌሎችም የንግድ ድርጅቶች ተቃጥለዋል። በርካታ ዜጎችም ... Read More »

ፖሊሶች ዲሽ ሲያስወርዱ መዋላቸውን ከተለያ  አካባቢዎች የሚደርሱን መረጃዎች አመለከቱ

ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአሽኳይ ጊዜ አዋጅ በታወጀ ማግስት ፖሊሶች በተለይ በኦሮምያና በአማራ አንዳንድ ከተሞች ጣራ ላይ እየወጡ ዲሽ ሲያወርዱ ታይቷል። ኢሳትንና ሌሎችን የውጭ ሚዲያ ይከታተላሉ የተባሉ ሰዎች ዲሾቻቸው ከተነቃቀሉ በሁዋላ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። የሞባል ኢንተርኔት የስልክ አገልግሎትን ሙሉ በሙሉ የዘጋው ገዢው ፓርቲ፣ በዲሽ ከውጭ አገር የሚተላለፉ ስርጭቶችን በማፈን ህዝባዊ ተቃውሞውን ለማፈን ሙከራ እያደረገ ነው። የጀርመን መሪ አንጌላ ... Read More »

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ እየከፋ መምጣቱን የአውሮፓ ኅብረት አወገዘ

ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ  የሰብአዊ መብት እና የልማት ኮሚቴ ዛሬ ባከሄደው መደበኛ ስብሰባ በኢትዮጵያ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ላይ አትኩሮት ሰጥቶ ተወያይቷል ፡፡ በኢትዮጵያ በተካሄደው ህዝባዊ አመፅ ስለተገደሉት ንፁሀን የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች እንዲሁም ባለፈው እሁድ በመላው ኢትዮጵያ ለተከታታይ ስድስት ወራት የሚቆየውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስመልክቶ ውይይት ተካሂዷል። በዚህ ስብሰባ ላይ የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ኤክስፐርቶች፣ ... Read More »

በምዕራብ አርሲ ዞን ባልና ሚስትን ጨምሮ በትንሹ ሶስት ሰዎች በጸጥታ ሃይሎች ተገደሉ

ኢሳት (ጥቅምት 1 ፥ 2008) በምዕራብ አርሲ ዞን ስር በምትገኘው የቡልቻና ከተማ በመካሄደ ላይ ያለን ተቃውሞ ለመቆጣጠር የጸጥታ ሃይሎች በወሰዱት ዕርምጃ ባልና ሚስትን ጨምሮ በትንሹ ሶስት ሰዎች መገደላቸውን ዕማኞች ለኢሳት አስታወቁ። በቅርቡ በቢሾፍቱ ከተማ የደረሰውን ዕልቂት ተከትሎ በምስራቅና ምዕራብ አርሲ ዞኖች ስር በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች ህዝባዊ ተቃውሞ በአዲስ መልክ መቀስቀሱ ይታወቃል። ይኸው ተቃውሞ በቡልቻና ከተማ ከቀናት በፊት መካሄድ መጀመሩን ለዜና ... Read More »

አንጌላ መርከል መንግስት በሰላማዊ መንገድ ጥያቄን በሚያቅርቡ ሰዎች ላይ የሚወሰደውን ዕርምጃ እንዲያቆም አሳሰቡ

ኢሳት (ጥቅምት 1 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የጀርመኗ ቻንስለር አንጌላ መርከል መንግስት በሰላማዊ መንገድ ጥያቄን በሚያቅርቡ አካላት ላይ የሚወሰደውን ዕርምጃ እንዲያቆም ማከሰኞ አሳሰቡ። ከጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ጋ በመሆን የጋራ መግለጫን የሰጡት መርከል “ችግር/ጥያቄ ካላቸው ሰዎች ጋር መወያየት ይኖርባችኋል” ሲሉ ለአቶ ሃይለማሪያም በመግለጫው ስነስርዓት ወቅት መናገራቸው ሮይተርስ ዘግቧል። የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የሚወስዱትን ድርጊት የኮነኑት ... Read More »

በጎንደር ትጥቅ ለማስፈታት ከሚሰራው የህወሃት ኮማንድ ፖስት ጋር በቅንጅት የሚሰሩ የብዓዴን ሰዎች ተለይተው ታወቁ

ኢሳት (ጥቅምት 1 ፥ 2008) በሳምንቱ መጨረሻ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ በአማራ ክልል ትጥቅ የማስፈታት ዘመቻ ለማካሄድ መወሰኑ ተመለከተ። የጎንደር ህዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪ ኮሚቴ ለኢሳት ባደረሰው መረጃ መሰረት አዲስ ከተዋቀረውና በህወሃት ሰዎች በሚመራው ኮማንድ ፖስት ጋር በቅንጅት የሚሰሩ የብዓዴን ሰዎች ታውቀዋል። ከመከላከያ ከፌዴራል ፖሊስ እንዲሁም ከደህንነት የተውጣጣውና በህወሃት ሰዎች በመሪነት በብዛት የሚሳተፉበት ኮማንድ ፖስት በአማራ ክልል ትጥቅ ለማስፈራት እንቅስቃሴ ... Read More »

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሰብዓዊ መብት ጥሰቱን ሊያባብሰው ይችላል ተባለ

ኢሳት (ጥቅምት 1 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት ተግባራዊ ያደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሃገሪቱ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሊያባብስ እንደሚችለው ሂውማን ራይትስ ዎች ማከሰኞ አስታወቀ። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተለያዩ ቦታዎች ይሰፍራል ተብሎ የሚጠበቀው የመከላከያ ሰራዊት ከዚህ በፊት ይወስድ የነበረውን የሃይል ዕርምጃ በማጠናከር ተጨማሪ አፈናን አግባራዊ እንደሚያደርግ የስብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ገልጸዋል። በሃገሪቱ ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መንግስት ከዜጎቹ የተነሱ ... Read More »

በባህርዳር የተካሄደው የመጀመሪያ ቀን የስራ ማቆም አድማ ውጤታማ መሆኑን አስተባባሪዎች ገለጹ

ጥቅምት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከጥቅምት 1 እስከ 5 በተጠራው የአማራ ክልል የስራ ማቆም አድማ  በከተማዋ የሚገኙ  ሱቆች ሙሉ በሙሉ የተዘጉ ሲሆን በሶስቱም የባህር ዳር ታላላቅ ገበያዎች ማለትም በአባይ ማዶ በቅዳሜ ገበያና በኪዳነ ምህረት ገበያዎች ምንም አይነት እንቅስቃሴ ሳያሳዩ የመጀመሪያው ቀን ተጠኗቋል፡፡ በዋናው የቅዳሜ ገበያ ውስጥ የሚገኙ የአዳራሽ ሱቆችና ልዩ ልዩ የሸቀጥ ሱቆች ሙሉ በሙሉ በመዘጋት ... Read More »

በታች አርማጭሆ አንድ የፌደራል ፖሊስ ሲገደል በጠገዴም ሌላ ጥቃት ተፈጸመ

ጥቅምት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአርማጭሆ ወረዳ በቅርቡ ከአገዛዙ ታጣቂዎች የሚደርስባቸውን ጥቃት በመሸሽ ራሳቸውን ያደራጁ የክልሉ ነዋሪዎች ትናንት ሁለት የፌደራል ፖሊሶችን ጭኖ በሚሄድ አንድ መኪና ላይ በፈጸሙት ጥቃት አንደኛው ሲገደል ሌላው ፖሊስ ቆስሏል። በጠገዴ ደግሞ የመንገድ ስራ ለማስጀመር ወደ አካባቢው በተንቀሳቀሱ ባለስልጣናት ላይ ለመውሰድ የታሰበው እቅድ ባለስልጣናቱ   መንገድ ቀይረው በመጓዛቸው ሳይሳካለቸው መቅረቱን የገለጹት እነዙህ ሃይሎች፣ ይሁን ... Read More »