Pages

Monday, July 20, 2015

በሕወሓት $5 ሺህ ዶላር የተደለለው ድምፃዊ ደረጀ ደገፋው በዲሲ ከፍተኛ መገለል እየደረሰበት ነው

July 20, 2015
ቢሆነኝ ከዋሽንግተን ዲሲ የሕወሓት መንግስት በሰሜን አሜሪካ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ለመከፋፈል የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ ላይ አንጃ በመፍጠር በስርዓቱ ደጋፊ በሼህ መሀመድ አላሙዲ ሌላ ፌዴሬሽን አቋቁመው በኢትዮጵያውያን ቦይኮት መደረጋቸው ይታወሳል:: ከአንድ ዓመት በፊት የወያኔ መንግስት በሚኒሶታ ባዘጋጀው የስፖርት ፌስቲቫል ላይ ትናንት ሃገር ወዳድ በመምሰል ስለታማኝ በየነ ጀግንነት እያወደሰ ሲዘፍን የነበረው ድምፃዊ ደረጀ ደገፋው ከአላሙዲ የተከፈለው 5 ሺህ ዶላር በልጦበት ሃገር ወዳዱን ኢትዮጵያዊያን ክዶ ተገኝቶ ነበር::Ethiopian singer Dereje Degefaw
ይህ ድምፃዊ ለገንዘብ ራሱን በማስገዛቱ እጅጉን በ”መጸጸቱ” በዲሲ ባሉ ራድዮኖችና ዲሲን መሠረት ባደረጉ ሚድያዎች እንዳይዘገብበት አርቲስት ታማኝ በየነ እና አበበ በለው እግር ስር መውደቁ ይነገራል:: በወቅቱ የደረጀ ደገፋው ለገንዘብ ሲል ለወያኔ ፌስቲቫል ማድመቂያ መሆኑን እነዚሁ ሚድያዎች ዝም ብለውለት አለፉ::
ሆኖም ግን ሕዝቡ ዝም አላለም:: ይበላበት የነበረበት ሬስቶራንትና የሚውልበት አካባቢ ያሉ ኢትዮጵያውያን ለገንዘብ ሲል ለወያኔ ራሱን የሸጠ እያሉ ማግለል ጀመሩ::
ድምፃዊው ቀጥሎም የአምናው ሳያንስ ዘንድሮም ሕወሓት በአላሙዲ ስፖንሰርነት ዴንቨር ላይ ባደረገውና ቦይኮት በተደረገው ኳስ ጨዋታ ላይ ዘፍኖ ተመልሷል::
ትናንት እነ አቦነሽ አድነውን ቦይኮት አስደርገው ሬስቶራንቷን እንድትዘጋ ያደርጉ የዲሲ ራድዮ ጣቢያዎችና አክቲቭስቶች ደረጀ ደገፋውን ዝም ቢሉትም ሕዝቡ ግን ድምፃዊውን ከማግለል አልተመለሰም:: በዲሲ ብዙ ጊዜ ከሚዝናናበት ካፌ ከሕዝቡ በሚደስበት ተቃውሞ ለመቅረት ተገዷል:: በአሁኑ ወቅት ይህ ድምጻዊ ራሱን ከኢትዮጵያውያን እየደበቀ ለታማኝ ዘፍኖ ያገኘውን ክብር በሕወሓት $5 ሺህ ዶላር ሸጦታል:: ማሳሰቢያ በተለይ ለዲሲ ራድዮኖችና አክቲቭስቶች:- ከወያኔ ጋር ያበረውን ድምፃዊም ሆነ አርቲስት ቦይኮት ማድረጋችሁን እኮራበታለሁ:: ሆኖም ግን ከአንድ አካባቢ ነው የመጣነው በሚል ከወያኔ ጋር ያበረውን አርቲስትም ዝም አትበሉት:: ዘር ቆጠራ ውስጥ ከገባችሁ እናንተም ከወያኔ አትሻሉም::

ጀርመናዊው የገደላት ሰብለ ከአንድ አመት በኋላ በመኖርያ በትዋ ተቀብራ ተገኘች

July 18, 2015
(ክንፉ አሰፋ ቶሮንቶ) ሰብለ (ሚሚ) ዲትሪች ለመጨረሻ ግዜ የታየችው እ.ኤ. አ. ጁላይ 10 2014 (ባለፈው አመት) ነበር። የሶስት ልጆች እናት የነበረች የዚህች ኢትዮጵያዊት በድንገት መሰወር ለብዙዎች እንቆቅልሽ ሆኖ ሰንብቷል። ለአመት የጠፋችው ይህች ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሴት በህይወት እንደማትኖር በርካቶች ቢጠረጥሩም፣ ማንንም ሳታማክር በድብቅ ወደ ሃገርዋ ገብታለች የሚሉ አልጠፉም። አለም አቀፍ ፖሊስ በአለም ዙርያ ፍለጋውን ተያያዘው።Seble "Mimi" Dietrich
በካናዳ ኪችነር ከተማ ቫንኮቨር ድራይቭ የተገኘው አጽም ግን የሁሉንም እንቆቅልሽ ፈታው። ሰብለ ህይወትዋ አልፏል። የሶስት ልጆችዋ አባት የነበረው ጀርመናዊው ስቴፋን ዲትሪች ገድሎ እዚያው መኖርያ ቤታቸው እንደቀበራት ፖሊስ ጠቁሟል። በፖሊስ እና በሰለጠኑ ውሾች ጥቆማ የተገኘው የሰብለ አስከሬን በቶሮንቶ ኮርነርስ ኮምፕለክስ ለጥናት ተልኮ የተገኘው ውጤት ሰብለ በሰው እንደተገደለች ተረጋግጧል። ዋናው ተጠርጣሪም ጀርመናዊው ባለበትዋ ነው።
በመጀመርያ ደረጃ የግድያ ወንጀል የተከሰሰው የሚሚ ባለቤት ስቴፋን ዲትሪች ፍርድ ቤት ቀርቦ በሰጠው ቃል ጉዳዩ በጀርመን ሃገር እንዲታይለት ጠይቋል። በእለቱ ኢትዮጵያውያን ፍርድ ቤቱን አጥለቅልቀውት ነበር።
ሰብለ ዲትሪች ተገድላ ከተሰወረች ከአመት በኋላ የቀብር ስርዓትዋ እለተ አርብ (ጁላይ 18) በካናዳ ቅዱስ ፓውሎስ ቤተ ክርስትያን ተፈጽሟል። በቀብሩ ላይ ወላጅ እናትዋን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል።
ስቴፋን ዲትሪች የአዞ እንባ እያነባ ምስጢሩን ለአመት ከደበቀው በኋላ መኖርያ ቤቱን ለመሸጥ ማስታወቅያ አውጥቶ ነበር። ይህ ድርጊቱ የፖሊስን ጥርጣሬ እንዳጎላው ግልጽ ነው።
ሰብለ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ነበረች። የቤተ ክርስትያኑ ዘማሪም ናት። ባልዋ ዲትሪችም እንደዚሁ። ከጀርመን ሃገር ወደ ካናዳ ከተዘዋወሩ በሁዋላ እጅግ በጣም የተደላደለ ኑሮ እንደነበራቸው ይነገራል። ሰብለ ከኢትዮጵያውያን የቤተ-ክርስትያን ሰዎች በተለይ ከፓስተሮች ጋር የምታደርገው የአገልግሎት ግንኙነት ግን ለስቴፋን ዲትሪች እንዳልተመቸው የሚመሰክሩ አሉ። ይህም ቢሆን ክቡር ነብስን ለማጥፋት ምክንያት ሊሆን አይችልም። …. ስቴፋን ዲትሪች ሰብለን ለምን ገደላት? ገድሎስ ለምን ቤቱ ቀበራት? ይህንን ከፍርድ ቤቱ ሂደት የምናየው ይሆናል።
የሰብለ እናት የካናዳ የመኖርያ ፈቃድ አግኝተው የመጡ ሲሆን ሶስት ልጆቹን እሳቸው እንደሚንከባከቧቸው ከካናዳ መንግስት መረጃ አግኝቻለሁ።
Seble "Mimi" Dietrich funeral

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቴዲ አፍሮ ምክንያት 200 ሺህ ዶላር ከሰረ

July 18, 2015
  • ቴዲ በድጋሚ ፓስፖርቱን ተቀምቶ ነበር
(ክንፉ አሰፋ፣ ፍራንክፈርት) ባለፈው ሳምንት ወደ ከአዲስ አበባ ናይሮቢ-ኬንያ ይጓዝ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራውን ከጀመረ በኋላ እንዲመለስ መደረጉን የአየር መንገዱ ምንጮች አስታወቁ። በዚህም ምክንያት አየር መንገዱ የሁለት መቶ ሺህ ዶላር ኪሳራ እንደደረሰበት ምንጮቹ ጠቁመዋል። በተሳፋሪዎች ላይም ከፍተኛ መጉላላት ደርስዋል።Ethiopian Artist Teddy Afro
አውሮፕላኑ ካኮበኮበ በኋላ እንዲመለስ የተደረገበት ምክንያት ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ከባለቤቱ ከአለምሰት ሙጬ ጋር በአውሮፕላኑ በመሳፈሩ ምክንያት መሆኑ ተረጋግጧል። ይህ አስደንጋጭ ክስተት የተፈጸመው አመለሰት ሙጬ በደረሰባት ድንገተኛ ህመም ለህክምና ወደ ኬንያ እየተጓዘች ባለችበት አውሮፕላን ነው።
አውሮፕላኑ ዞሮ ከተመለሰ በኋላም ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ በደህንነቶች ተይዞ ከአውሮፕላኑ እንዲወጣ ተደርጓል። የህወሃት የደህንነት አባላት የቴዲ አፍሮን ፓስፖርት ቀምተው አሰናብተውት ነበር።
ቴዲ አፍሮ በሰሜን አሜሪካ በየዓመቱ የሚደረገው የኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ፌስቲቫል ላይ ድምጻዊ ጎሳዬ ተስፋዬ ጋር መጋበዙ የሚታወስ ሲሆን ይህንን በመቃወም ሚሚ ስብሃቱ እና ባለቤትዋ ዘሪሁን ተሾመ ዘመቻ ከፍተው እንደነበር የሚታወስ ነው። የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን 33ኛ ዓመት በዓል ላይ እነዚህ ድምጻውያን አልተገኙም። ድምጻውያኑ በበዓሉ ያልተገኙበት ምክንያት የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ በደረሰው የኮምፒውተር ሽብር ጥቃት – የቪዛ ችግር ያጋጠማቸው መሆኑ ቢገለጽም፤ ቪዛ ቢያገኙ ኖሮ እንኳ በደህንነቶች አፈና ከሃገር ሊወጡ እንደማይችሉ ግልጽ ነበር።
የኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ፌዴሬሽን አሸባሪ ተብሎ በነሚሚ ስብሃቱ መፈረጁን የህወህት መንግስት ተቀብሎ በውስጥ አጽድቆታል። ቴዲ አፍሮ ባለቤቱን ለማሳከም ወደ ኬንያ በመጓዝ ላይ እንዳለ በኬንያ በኩል ወደ አሜሪካ ሊጓዝ ነው ተብሎ በነ ሚሚ ስብሃቱ በደረሰው ጥቆማ ነው አውሮፕላኑ እንዲመለስ የታዘዘው።
በዚህ በተሳሳተ መረጃ ምክንያት በተሳፋሪው ላይም ከፍተኛ መጉላላት የደረሰ ሲሆን አየር መንገዱም ለከፋ ኪሳራ ተዳርጓል ሲሉ የአየር መንገዱ ምንጮች ተናግረዋል። ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ከባለቤቱ ጋር ወደ ኬንያ ይጓዝ የነበረው የሰሜን አሜሪካው የስፖርት እና የባህል ፌስቲቫል ከተጠናቀቀ በኋላ ነበር። የህወሃት ደህንነት አባላት ይህንን እንኳን ማገናዘብ የማይችሉ ደካሞች እንደሆኑ ምንጮቹ ጠቁመዋል።
ከብዙ መጉላላት በኋላ ቴዲ አፍሮ ፓስፖርቱን አስመልሶ ወደ ጀርመን – ፍራንክፈርት የበረረ ሲሆን በቅዳሜ ምሽት የአውሮፓ ስፖርትና ባህል ፌስቲቫል ላይ ዝግጅቱን ያቀርባል። ከዚያም የጄኔቭ ስዊዘርላንድ ማዘጋጃ ባሰናዳው ዝግጅት ላይ ልዩ ተጋባዥ በመሆን በመጭው ሳምንት ስራውን ለህዝብ በነጻ ያሳያል።
የቴዲ አፍሮ ባለቤት አመለሰት ሙጬ በአሁኑ ሰዓት በአሜሪካ-ቨርጂንያ ህክምናዋን እየተከታተለች ትገኛለች።
ድምጻዊ ቴዲ አፍሮን በአካል አግኝቼ ባነጋገርኩበት ግዜ የዚህን ዘገባ ትክክለኝነት አረጋግጫለሁ። ይህንን እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ወደፊት በስፋት እመለስበታለሁ።

ኢሳት ሙሉ የ24 ሰአት ዝግጅቱን ጀመረ

July 16, 2015
ESAT television new satellite
ሐምሌ ፺፻ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በገዢው መንግስት ከፍተኛ አፈና የሚደርስበት የኢሳት የቴሌቪዝን ስርጭት ከሳምንታት ሙከራ በሁዋላ ዛሬ ሙሉ ስርጭቱን በ ኤም 44 ሳተላይት ጀምሯል።
አዲሱ ሳተላይት ጠንካራ ሲግናል ያለው ቢሆንም፣ ገዢው ፓርቲ በሙከራው ወቅት ስርጭቱን ለማፈን ተደጋጋሚ ሙከራ ሲያደርግ መቆየቱን የኩባንያው ኢንጂነሮች ገልጸዋል።
ተመልካቾች አልፎ አልፎ የድምጽ ወይም የምስል መዛባት ቢያጋጥማቸው ስርጭቱን ለማፈን ከሚደረግ ሙከራ የመጣ መሆኑን እንዲያውቁት ኢንጂነሮች መክረዋል።
ኢሳት በዚህ ሳተላይት ለርጅም ጊዜ የሚያቆየውን ስምምነት ፈርሟል። ሌሎች ተጨማሪ ሳተላይቶችን ለመከራየት በድርድር ላይ ሲሆን፣ እንደተሳካለት ለህዝብ ያስታውቃል፡፡
ገዢው ፓርቲ ኢሳትን ለማፈንና የኢሳት ጋዜጠኞችን ኮምፒዩተሮች ለመሰለለል ብዙ ሚሊዮኖችን እያወጣ ሲሆን፣ ለአንድ አመት ብቻ 1 ሚሊዮን ዩሮ ወይም ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ ሀኪንግ ቲም ለተባለ ድርጅት መክፈሉ ሰሞኑን የአለም የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት እንዲያገኝ አድርጎታል። ስለላውን ተከትሎ አንድ አሜሪካ የሚኖር ኢትዮጵያዊ የከፈተው ክስ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን ተከሳሹ ለኢሳት ተናግሯል።
ለደህንነት ሲባል ስሙ እንዳይገለጽ የተፈለገው ከሳሽ ፣ የኢህአዴግ ባለስልጣናት በሰሞኑ ችሎት ላይ አለመገኘታቸውን ይሁን እንጅ በጠበቆቻቸው አማካኝነት መልስ መስጠታቸውን ገልጿል። ከፍተኛ ገንዘብ ከፍለው የቀጠሩዋቸው ጠበቆች ጠንካራና ታዋቂ ቢሆኑም፣ በከሳሽ በኩል የቀረቡት የህግ ባለሙያዎች ለእውነት የቆሙ በመሆናቸው ያሸንፋሉ ብሎ እንደሚገምት ገልጿል። ፍርድ ቤቱ የኢህአዴግን መንግስት ጥፋተኛ ብሎ ከወሰነ ውሳኔው በአለም ላይ ስለላን በተመለከተ አዲስ የህግ አካሄድ እንደሚፈጥር ተገልጿል። ውሳኔው በአሜሪካ የስለላ ድርጅት ላይ ሳይቀር ተፈጻሚ ሊሆን እንደሚችልም ፍንጭ ሰጥቷል።

July 15, 2015 ‹‹እጄን ወደ ላይ አስረው ብልቴ ላይ ሀይላንድ አንጠልጥለውበታል፡፡ ሴቶቹ ሀይላንዱን የሚበቃቸውን ያህል ያወዛውዙታል፡፡ በዚህም ምክንያት ከጥቅም ውጭ ሆኗል፡፡ የዘር ፍሬየን ከጥቅም ውጭ አድርገው ዘሬን እንዳልተካ አድርገውኛል፡፡ ሽንቴንም መቆጣጠር አልችልም፡፡›› Ethiopian prisoner tortured in Kality አበበ ካሴ እኔ አበበ ካሴ እባላለሁ፡፡ የሰሜን ጎንደር ተወላጅ ነኝ፡፡ በማዕከላዊ እስር ቤት ከ5 ወር በላይ ታስሬለሁ፡፡ ከዚህ መካከል 4 ወር ከ25 ቀናት በጨለማ ቤት ተቆልፎብኝ ቆይቻለሁ፡፡ ማዕከላዊ በነበርኩበት ወቅት የሁሉም እግርና እጆቼ ጥፍሮች ተነቅለዋል፡፡ አንዳንድ ቀን እጄ ላይ የሆነ ነገር ስለሚወጉኝ ጥፍሮቼ ሲነቀሉ አላውቅም፡፡ ስነቃ ነው መነቀላቸውን የማውቀው፡፡ ከዛም ቁስሉን እየነካኩ ያሰቃዩኛል፡፡ ማደንዛዣ ለምን እንደሚወጉኝ አላውቅም፡፡ ጥፍሮቼን ሲነቅሉኝ ብቻ ሳይሆን ሌላ ጊዜም ራሴን እንድስት ያደርጉኛል፡፡ እጅና እግሬን አስረው እንደ ፍሪጅ ያለ እቃ ውስጥ ያለ በረዶ ውስጥ ያስቆሙኛል፡፡ ለብዙ ሰዓት በጣም ቀዝቃዛ የሆነ ቦታ ላይ እስክደነዝዝ ቆሜ እውላለሁ፡፡ እስኪበቃቸው ከደበደቡ በኋላ እጅና እግሬን አስረው ከምርመራ ክፍሉ በታች በሚገኝ ምድር ቤት ክፍል ውስጥ ያለ ጉድጓድ ላይ ጥለውኝ ይሄዳሉ፡፡ ጉድጓዱ ጉንዳንን ጨምሮ ተባዮች ያሉት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እግሬንና እጄን አስረው ዘቅዝቀውኝ ይሄዳሉ፡፡ የመጣው ሁሉ ዝዋዥዌ እንደሚጫወት ህፃን ወዲያና ወዲህ ያደርገኛል፡፡ ገልብጠው አስረው ሲዘቀዝቁኝ በአብዛኛው ራሴን እስታለሁ፡፡ እግርና እጄን ከወንበር ጋር ያስሩኛል፡፡ ከወንዶች በተጨማሪ ሴቶችም ይመረምሩኛል፡፡ ሴቶቹ የሚመረምሩኝ ራቁቴን አርገው ነው፡፡ እነሱም ራቁታቸውን ሆነው ነው የሚመረምሩኝ፡፡ አሁን ለመናገር የማልደፈርው አፀያፊ ነገርም ፈፅመውብኛል፡፡ ይህን አፀያፊ ነገር የሚፈፅሙት አደንዛዥ እፅ እየተጠቀሙ ነው፡፡ ይህን ሲያደርጉ በአይኔ አይቻቸዋለሁ፡፡ መርማሪዎቹ ሰውነቴን በኤሌክትሪክ አቃጥለውኛል፡፡ ኤሌክትሪኩን የሚሰኩት ደረቴና የውስጥ እግሬ ላይ ነው፡፡ በዚህም የውስጥ እግሬ ተገልብጦ ሌላ ሰውነት አምጥቶ ነበር፡፡ እጄን ወደ ላይ አስረው ብልቴ ላይ ሀይላንድ አንጠልጥለውበታል፡፡ ሴቶቹ ሀይላንዱን የሚበቃቸውን ያህል ያወዛውዙታል፡፡ በዚህም ምክንያት ከጥቅም ውጭ ሆኗል፡፡ የዘር ፍሬየን ከጥቅም ውጭ አድርገው ዘሬን እንዳልተካ አድርገውኛል፡፡ ሽንቴንም መቆጣጠር አልችልም፡፡ ይህን ያህል አሰቃይተው ከጥቅም ውጭ ስሆን ቂሊንጦ አምጥተው ጣሉኝ፡፡ 11 ወር ያህል አልጋ ላይ ነበርኩ፡፡ በኤሌክትሪክ ግርፊያው ምክንያት ግራ ሰውነቴ ሽብ ሆኖ ነበር፡፡ ግራ እግሬ መንቀሳቀስ አይችልም ነበር፡፡ በምርኩዝ ነበር የምሄደው፡፡ አሁን እያነከስኩ ነው የምሄደው፡፡ በተለይ ማዕከላዊ ውስጥ ይህን ያህል የሚሰቃዩኝ አንደኛ የሚያግዛችሁ አገር ማን ነው በሚል ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ አማራ ክልል ውስጥ እንድትንቀሳቀሱ የሚተባበሯችሁን የብአዴን ባለስልጣናት ስም ተናገር እያሉ ነው፡፡ በሶስተኛ ደረጃ የሚያሰቃዩኝ የት የት ቦታ ነው የሰለጠንከው እያሉ ነው፡፡ እዚህ ቂሊንጦ ከመጣሁ በኋላም ያሰቃዩኛል፡፡ ወጣቶች እንዳይቀርቡኝ ያስፈራሩዋቸዋል፡፡ ማንም ጠርቶ እንዳይጠይቀኝ እየተደረገ ነው፡፡ ጨለማ ክፍል ወስደውም አስረውኝ ያውቃሉ፡፡ እነሱ ደብድበው ከጥቅም ውጭ ካደረጉኝ በኋላ የምደገፍበትን ምርኩዝም ቀምተውኛል፡፡ ‹‹ይህኮ የጦር መሳሪያ አይደለም፡፡ እንጨት ነው፡፡ ለምን ትቀሙኛላችሁ? ደግሞም እናንተ ናችሁ እንዲህ ያደረጋችሁኝ፡፡›› ብያቸው ነበር፡፡ የሚሰሙ ሰዎች አይደሉም፡፡ የታሰርኩበት ክፍል ውስጥ እንድተኛበት የተሰጠኝ ቦታ ሽንት ቤቱ አጠገብ ነው፡፡ ሽንት እየሸተተኝ ነው የምተኝው፡፡ ‹‹ወደ ሌላ ቦታ ቀይሩኝ!›› ስላቸው ‹‹ደግሞ ለአንተ ይህ አንሶህ ነው?›› ይሉኛል፡፡ ያ ሁሉ ድብደባ ደርሶብኝ አልጋ ላይ በነበርኩበት ወቅት ወጣቶቹ ህክምና እንዳገኝ ወደ ሀኪም ቤቱ ወሰዱኝ፡፡ እነሱ ግን ‹‹ለአንተ ህክምና ሳይሆን ጥይት ነበር የሚገባህ›› ብለው መለሱኝ፡፡ እንዲህ እያሉ ለምን እንደማይገድሉኝ ይገርመኛል፡፡ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ልጆችዋ ለእልቂት፣ ለስደት፣ ለግድያ እየተዳረጉ ነው፡፡ በአካልም ሆነ በስነ ልቦና ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው ነው፡፡ ዓለም ለሰው ልጅ ምቹ በሆነችት ከዓለም ውጭ ሆነናል፡፡ የመገናር፣ የመሰብሰብ፣ የመደራጀት በአጠቃላይ ሰው የሚያደርጉንን መብቶች ተነጥቀናል፡፡ ከሰው የማንቆጠርበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡ ገዥዎቻችን ህዝብን እየገደሉና ከሰው በታች አድርገው እየገዙም ቢሆን ግን ዓለምን እያታለሉ ነው፡፡ በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ይህ ሁሉ የሚደረገው የአንድን ቡድን የበላይነት ለማስፈን መሆኑ ነው፡፡ እንዲጠፋ ሆን ተብሎ ጥቃት የሚደርስበት ህዝብም እንዳለ እያየን ነው፡፡ ግን ኢትዮጵያ የ95 ሚሊዮን ህዝን ሀገር ናት፡፡ አሁን ያለው ስርዓት የአንድ ቡድን ስርዓት ነው፡፡ ለእሱ መኖር ደግሞ ሌሎቹን ገድሎ፣ አሰቃይቶ፣ አሳድዶ መኖር ይፈልጋል፡፡ ለስሙ የብሄር ብሄረሰብ መብት እናከብራለን ቢባልም እውነቱ ግን ኢትዮጵያውያን የመናገር፣ የመፃፍ፣ የመደራጀትና ሌሎች መብቶችን ተነፍጎ ከሰውነት ወጥተው ይገኛሉ፡፡ በዓለም ደረጃ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ቋንቋና ዘርን አይለይም፡፡ ይህ የሚደረገው በህወሓት ስርዓት ብቻ ነው፡፡ እኔ በርካታ ሰቆቃ የደረሰብኝ ሰው ስለሆንኩ ስርዓቱ የሚፈፅመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ለመመስከር እችላለሁ፡፡ እኔን ሰቆቃ ያደረሱብኝ ሰዎች ማንነታቸው መታወቅ ስላለባቸው እንደሚከተለው ስማቸውን እዘረዝራለሁ 1. አቶ አሸነፍ ተስፋሁን ላቀው 2. አቶ አብርሃም አይሸሽም 3. ሙሉጌታ ወርቁ 4. አቶ ደረሱ አያናው 5. የአማራ ክልል ደህንነት ኃላፊ የሆነው አቶ ተሾመ 6. የሰ/ጎ/መ/የታክቲክ ኃላፊ አቶ ሙላ እንየው 7. የማዕከላዊ ምርመራ ኃላፊ ኮማንደር ተክላይ 8. የማዕከላዊ ምርመራ ኃላፊ ኮማንደር ጌትነት 9. አቶ አሰፋ አትንኩት (ምርመራበ ኃላፊ) 10. መቶ አለቃ ተስፋዬ (መርማሪ) 11. ሳጅን ፍሬ ህይወት (መርማሪ) 12. ሳጅን ፅጌ (መርማሪ) ከላይ የጠቀስኳቸውን በስምና በአካል የማውቃቸው ሲሆኑ ከእነዚህ በተጨማሪ ከደህንነት መስሪያ ቤቱ እየመጡ የሚያሰቃዩን ስማቸውን የማላስታውሳቸውና በመልክም የማውቃቸው የህወሓት ደህንነቶች አሉ፡፡ እዚህ እኛን እንደዚህ ሲያሰቃዩ ሀገሪቱን ገንዘብ መዝብረው የታሰሩ ሰዎች ምንም አይሆኑም፡፡ ተመችቷቸው ነው የሚኖሩት፡፡ ቂሊንጦ ውስጥ ሰው እንዳይቀርበኝም ቢፈልጉም ሰው ግን በጣም ይወደኛል፡፡ አሁን ጥፍሮቼ በቅለዋል፣ መራመድ ችያለሁ፡፡ አንድ ሽህ አመት አይኖርም፡፡ በጣም ብዙ ወገኖቻችን ሞተዋል፡፡ እኔ አለሁ፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ባለስልጣናት እኔ ላይ የደረሰውን ጨምሮ በበርካታ ኢትዮጵያውያን ላይ በፈፀሙት ወንጀል መጠየቃቸው የማይቀር ነው፡፡ ይህ ሁሉ በደል ደረሰብኝ ስል ዝም ብዬ አይደለም፡፡ ማንኛውም ሰው መጥቶ የተሸማቀቀውን እግሬን፣ ቅጥ ባጣ ድብደባ የተጎዳው ሰውነቴን ማየት ይቻላል፡፡ ጥፍሮቼንም ለመስክርነት ይዤያቸዋለሁ፡፡ እነሱ ነቅለው ጥለው ሲሄዱ እኔ ስነቃ ሰብስቤ አስቀምጣቸዋለሁ፡፡ የተወሰኑትን ለመረጃነት አስቀምጫቸዋለሁ፡፡ ይህን ስል ግን እኔ ላይ የደረሰው ስቃይም የማይጠበቅ ሆኖ አይደለም፡፡ እነዚህ ሰዎች እንኳንስ ግለሰብ ሀገርም ገንጥለዋል፡፡ ከ40 አመት በፊት የነበረው የኢትዮጵያ ካርታ ተሸርፏል፡፡ እንኳን ሰው ሀገርም ለማጥፋት እየሰሩ ነው፡፡ ታሪካቸው፣ አመጣጣቸውም የሚያሳየው ይህን ነው፡፡ ይህን ሁሉ የምለውም መታወቅ ስላለበት ነው፡፡

July 16, 2015
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በእነ ዘመነ ካሴ መዝገብ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ድረስ ለተጠቀሱት ተከሳሾች የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ ወሰነ፡፡ የፌደራል አቃቤ ህግ ‹‹ከአንዳርጋቸው ጋር በአካል ተገናኝታችኋል›› የሚል ክስ የመሰረተባቸው ተከሳሾቹ ‹‹ከአንዳርጋቸው ጋር ተገናኝታችኋል ከተባለ አቶ አንዳርጋቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ታስረው የሚገኙ በመሆናቸው መከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ ፍርድ ቤቱ ይታዘዝልን›› የሚል ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡Ato Andargachew Tsige, Ginbot 7
የፌደራል አቃቤ ህግ በበኩሉ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በእነ ጀኔራል ተፈራ ማሞ መዝገብ እና በእነ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ መዝገብ ላይ ክስ ቀርቦባቸው በእድሜ ልክና በሞት እንዲቀጡ ተወስኖባቸው የህዝባዊ መብታቸው የተሻረ በመሆኑ በምስክርነት ሊቀርቡ አይችሉም ብሎ ተቃውሟል፡፡ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ህዝባዊ መብት በመሻሩ ለፍርድ ስራ ልዩ አዋቂ ወይንም ነባሪ ሆነው መስራት አይችሉም ያለው የፌደራል አቃቤ ህግ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በተጨማሪ ምስክርነት ቀርበው መመስከር አይገባቸውም ሲል የተከሳሾቹ ጥያቄ ውድቅ እንዲሆን ለፍርድ ቤቱ አመልክቶ ነበር፡፡
ሆኖም ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ አቶ አንዳርጋቸው እንዲቀርቡላቸው የጠየቁት ለዋስት አሊያም ልዩ አዋቂ ምስክር ሆነው ሳይሆን ነበሩበት የተባለውን ጉዳይ ለመናገር ለምስክርነት በመሆኑ፣ ምስክርነትም ግዴታ እንጅ መብት በመሆኑ ሰኞ ሰኔ 13/2007 ዓ.ም በእነ ዘመነ ካሴ መዝገብ ለተከሰሱት ተከሳሾች ልደታ ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲመሰክሩ ወስኗል፡፡ ተከሳሾቹ አቶ አንዳርጋቸው የት እንደሚገኙና ማዘዢያው የት ተብሎ ሊፃፍላቸው እንደሚገባ ተጠይቀው ለቃሊቲ ማረሚያ ወይንም ለፀረ ሽብር ግብረ ኃይል ሊጻፍላቸው እንደሚገባ፣ ካልቀረቡላቸውም ክሳቸው ከአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጋር የተገናኘ በመሆኑ አቶ አንዳርጋቸው በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድረስ አቤቱታ እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል፡፡
ተከሳሾቹ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡላቸው በጠየቁበት ወቅት በዳኞችና በአቃቤ ህጎች ላይ ከፍተኛ ድንጋጤ መፈጠሩንና ከአቶ አንዳርጋቸው ይልቅ ሌሎች መከላከያ ምስክሮችን ማቅረብ እንደሚችሉ፣ አቶ አንዳርጋቸውን በመከላከያ ምስክርነት ለማቅረብ መሞከር እንደሌለባቸው እንደገለፁላቸው ታውቋል፡፡ ዳኛው በድንጋጤ ‹‹እኛ እዚህ ጉዳይ ላይ የለንበትም›› ማለታቸውን ተከሳሾቹ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ውስጥ ላነጋገራቸው የነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር ገልጸውለታል፡፡

ሰቆቃ በማዕከላዊ – አበበ ካሴ (ነገረ ኢትዮጵያ)

July 15, 2015
‹‹እጄን ወደ ላይ አስረው ብልቴ ላይ ሀይላንድ አንጠልጥለውበታል፡፡ ሴቶቹ ሀይላንዱን የሚበቃቸውን ያህል ያወዛውዙታል፡፡ በዚህም ምክንያት ከጥቅም ውጭ ሆኗል፡፡ የዘር ፍሬየን ከጥቅም ውጭ አድርገው ዘሬን እንዳልተካ አድርገውኛል፡፡ ሽንቴንም መቆጣጠር አልችልም፡፡››
Ethiopian prisoner tortured in Kality
አበበ ካሴ
እኔ አበበ ካሴ እባላለሁ፡፡ የሰሜን ጎንደር ተወላጅ ነኝ፡፡ በማዕከላዊ እስር ቤት ከ5 ወር በላይ ታስሬለሁ፡፡ ከዚህ መካከል 4 ወር ከ25 ቀናት በጨለማ ቤት ተቆልፎብኝ ቆይቻለሁ፡፡
ማዕከላዊ በነበርኩበት ወቅት የሁሉም እግርና እጆቼ ጥፍሮች ተነቅለዋል፡፡ አንዳንድ ቀን እጄ ላይ የሆነ ነገር ስለሚወጉኝ ጥፍሮቼ ሲነቀሉ አላውቅም፡፡ ስነቃ ነው መነቀላቸውን የማውቀው፡፡ ከዛም ቁስሉን እየነካኩ ያሰቃዩኛል፡፡ ማደንዛዣ ለምን እንደሚወጉኝ አላውቅም፡፡ ጥፍሮቼን ሲነቅሉኝ ብቻ ሳይሆን ሌላ ጊዜም ራሴን እንድስት ያደርጉኛል፡፡ እጅና እግሬን አስረው እንደ ፍሪጅ ያለ እቃ ውስጥ ያለ በረዶ ውስጥ ያስቆሙኛል፡፡ ለብዙ ሰዓት በጣም ቀዝቃዛ የሆነ ቦታ ላይ እስክደነዝዝ ቆሜ እውላለሁ፡፡ እስኪበቃቸው ከደበደቡ በኋላ እጅና እግሬን አስረው ከምርመራ ክፍሉ በታች በሚገኝ ምድር ቤት ክፍል ውስጥ ያለ ጉድጓድ ላይ ጥለውኝ ይሄዳሉ፡፡ ጉድጓዱ ጉንዳንን ጨምሮ ተባዮች ያሉት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እግሬንና እጄን አስረው ዘቅዝቀውኝ ይሄዳሉ፡፡ የመጣው ሁሉ ዝዋዥዌ እንደሚጫወት ህፃን ወዲያና ወዲህ ያደርገኛል፡፡ ገልብጠው አስረው ሲዘቀዝቁኝ በአብዛኛው ራሴን እስታለሁ፡፡ እግርና እጄን ከወንበር ጋር ያስሩኛል፡፡
ከወንዶች በተጨማሪ ሴቶችም ይመረምሩኛል፡፡ ሴቶቹ የሚመረምሩኝ ራቁቴን አርገው ነው፡፡ እነሱም ራቁታቸውን ሆነው ነው የሚመረምሩኝ፡፡ አሁን ለመናገር የማልደፈርው አፀያፊ ነገርም ፈፅመውብኛል፡፡ ይህን አፀያፊ ነገር የሚፈፅሙት አደንዛዥ እፅ እየተጠቀሙ ነው፡፡ ይህን ሲያደርጉ በአይኔ አይቻቸዋለሁ፡፡ መርማሪዎቹ ሰውነቴን በኤሌክትሪክ አቃጥለውኛል፡፡
ኤሌክትሪኩን የሚሰኩት ደረቴና የውስጥ እግሬ ላይ ነው፡፡ በዚህም የውስጥ እግሬ ተገልብጦ ሌላ ሰውነት አምጥቶ ነበር፡፡ እጄን ወደ ላይ አስረው ብልቴ ላይ ሀይላንድ አንጠልጥለውበታል፡፡ ሴቶቹ ሀይላንዱን የሚበቃቸውን ያህል ያወዛውዙታል፡፡ በዚህም ምክንያት ከጥቅም ውጭ ሆኗል፡፡ የዘር ፍሬየን ከጥቅም ውጭ አድርገው ዘሬን እንዳልተካ አድርገውኛል፡፡ ሽንቴንም መቆጣጠር አልችልም፡፡ ይህን ያህል አሰቃይተው ከጥቅም ውጭ ስሆን ቂሊንጦ አምጥተው ጣሉኝ፡፡ 11 ወር ያህል አልጋ ላይ ነበርኩ፡፡ በኤሌክትሪክ ግርፊያው ምክንያት ግራ ሰውነቴ ሽብ ሆኖ ነበር፡፡ ግራ እግሬ መንቀሳቀስ አይችልም ነበር፡፡ በምርኩዝ ነበር የምሄደው፡፡ አሁን እያነከስኩ ነው የምሄደው፡፡
በተለይ ማዕከላዊ ውስጥ ይህን ያህል የሚሰቃዩኝ አንደኛ የሚያግዛችሁ አገር ማን ነው በሚል ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ አማራ ክልል ውስጥ እንድትንቀሳቀሱ የሚተባበሯችሁን የብአዴን ባለስልጣናት ስም ተናገር እያሉ ነው፡፡ በሶስተኛ ደረጃ የሚያሰቃዩኝ የት የት ቦታ ነው የሰለጠንከው እያሉ ነው፡፡
እዚህ ቂሊንጦ ከመጣሁ በኋላም ያሰቃዩኛል፡፡ ወጣቶች እንዳይቀርቡኝ ያስፈራሩዋቸዋል፡፡ ማንም ጠርቶ እንዳይጠይቀኝ እየተደረገ ነው፡፡ ጨለማ ክፍል ወስደውም አስረውኝ ያውቃሉ፡፡ እነሱ ደብድበው ከጥቅም ውጭ ካደረጉኝ በኋላ የምደገፍበትን ምርኩዝም ቀምተውኛል፡፡ ‹‹ይህኮ የጦር መሳሪያ አይደለም፡፡ እንጨት ነው፡፡ ለምን ትቀሙኛላችሁ? ደግሞም እናንተ ናችሁ እንዲህ ያደረጋችሁኝ፡፡›› ብያቸው ነበር፡፡ የሚሰሙ ሰዎች አይደሉም፡፡ የታሰርኩበት ክፍል ውስጥ እንድተኛበት የተሰጠኝ ቦታ ሽንት ቤቱ አጠገብ ነው፡፡ ሽንት እየሸተተኝ ነው የምተኝው፡፡ ‹‹ወደ ሌላ ቦታ ቀይሩኝ!›› ስላቸው ‹‹ደግሞ ለአንተ ይህ አንሶህ ነው?›› ይሉኛል፡፡ ያ ሁሉ ድብደባ ደርሶብኝ አልጋ ላይ በነበርኩበት ወቅት ወጣቶቹ ህክምና እንዳገኝ ወደ ሀኪም ቤቱ ወሰዱኝ፡፡ እነሱ ግን ‹‹ለአንተ ህክምና ሳይሆን ጥይት ነበር የሚገባህ›› ብለው መለሱኝ፡፡ እንዲህ እያሉ ለምን እንደማይገድሉኝ ይገርመኛል፡፡
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ልጆችዋ ለእልቂት፣ ለስደት፣ ለግድያ እየተዳረጉ ነው፡፡ በአካልም ሆነ በስነ ልቦና ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው ነው፡፡ ዓለም ለሰው ልጅ ምቹ በሆነችት ከዓለም ውጭ ሆነናል፡፡ የመገናር፣ የመሰብሰብ፣ የመደራጀት በአጠቃላይ ሰው የሚያደርጉንን መብቶች ተነጥቀናል፡፡ ከሰው የማንቆጠርበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡ ገዥዎቻችን ህዝብን እየገደሉና ከሰው በታች አድርገው እየገዙም ቢሆን ግን ዓለምን እያታለሉ ነው፡፡ በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ይህ ሁሉ የሚደረገው የአንድን ቡድን የበላይነት ለማስፈን መሆኑ ነው፡፡ እንዲጠፋ ሆን ተብሎ ጥቃት የሚደርስበት ህዝብም እንዳለ እያየን ነው፡፡ ግን ኢትዮጵያ የ95 ሚሊዮን ህዝን ሀገር ናት፡፡
አሁን ያለው ስርዓት የአንድ ቡድን ስርዓት ነው፡፡ ለእሱ መኖር ደግሞ ሌሎቹን ገድሎ፣ አሰቃይቶ፣ አሳድዶ መኖር ይፈልጋል፡፡ ለስሙ የብሄር ብሄረሰብ መብት እናከብራለን ቢባልም እውነቱ ግን ኢትዮጵያውያን የመናገር፣ የመፃፍ፣ የመደራጀትና ሌሎች መብቶችን ተነፍጎ ከሰውነት ወጥተው ይገኛሉ፡፡ በዓለም ደረጃ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ቋንቋና ዘርን አይለይም፡፡ ይህ የሚደረገው በህወሓት ስርዓት ብቻ ነው፡፡ እኔ በርካታ ሰቆቃ የደረሰብኝ ሰው ስለሆንኩ ስርዓቱ የሚፈፅመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ለመመስከር እችላለሁ፡፡ እኔን ሰቆቃ ያደረሱብኝ ሰዎች ማንነታቸው መታወቅ ስላለባቸው እንደሚከተለው ስማቸውን እዘረዝራለሁ
1. አቶ አሸነፍ ተስፋሁን ላቀው
2. አቶ አብርሃም አይሸሽም
3. ሙሉጌታ ወርቁ
4. አቶ ደረሱ አያናው
5. የአማራ ክልል ደህንነት ኃላፊ የሆነው አቶ ተሾመ
6. የሰ/ጎ/መ/የታክቲክ ኃላፊ አቶ ሙላ እንየው
7. የማዕከላዊ ምርመራ ኃላፊ ኮማንደር ተክላይ
8. የማዕከላዊ ምርመራ ኃላፊ ኮማንደር ጌትነት
9. አቶ አሰፋ አትንኩት (ምርመራበ ኃላፊ)
10. መቶ አለቃ ተስፋዬ (መርማሪ)
11. ሳጅን ፍሬ ህይወት (መርማሪ)
12. ሳጅን ፅጌ (መርማሪ)
ከላይ የጠቀስኳቸውን በስምና በአካል የማውቃቸው ሲሆኑ ከእነዚህ በተጨማሪ ከደህንነት መስሪያ ቤቱ እየመጡ የሚያሰቃዩን ስማቸውን የማላስታውሳቸውና በመልክም የማውቃቸው የህወሓት ደህንነቶች አሉ፡፡
እዚህ እኛን እንደዚህ ሲያሰቃዩ ሀገሪቱን ገንዘብ መዝብረው የታሰሩ ሰዎች ምንም አይሆኑም፡፡ ተመችቷቸው ነው የሚኖሩት፡፡ ቂሊንጦ ውስጥ ሰው እንዳይቀርበኝም ቢፈልጉም ሰው ግን በጣም ይወደኛል፡፡ አሁን ጥፍሮቼ በቅለዋል፣ መራመድ ችያለሁ፡፡ አንድ ሽህ አመት አይኖርም፡፡ በጣም ብዙ ወገኖቻችን ሞተዋል፡፡ እኔ አለሁ፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ባለስልጣናት እኔ ላይ የደረሰውን ጨምሮ በበርካታ ኢትዮጵያውያን ላይ በፈፀሙት ወንጀል መጠየቃቸው የማይቀር ነው፡፡
ይህ ሁሉ በደል ደረሰብኝ ስል ዝም ብዬ አይደለም፡፡ ማንኛውም ሰው መጥቶ የተሸማቀቀውን እግሬን፣ ቅጥ ባጣ ድብደባ የተጎዳው ሰውነቴን ማየት ይቻላል፡፡ ጥፍሮቼንም ለመስክርነት ይዤያቸዋለሁ፡፡ እነሱ ነቅለው ጥለው ሲሄዱ እኔ ስነቃ ሰብስቤ አስቀምጣቸዋለሁ፡፡ የተወሰኑትን ለመረጃነት አስቀምጫቸዋለሁ፡፡ ይህን ስል ግን እኔ ላይ የደረሰው ስቃይም የማይጠበቅ ሆኖ አይደለም፡፡ እነዚህ ሰዎች እንኳንስ ግለሰብ ሀገርም ገንጥለዋል፡፡ ከ40 አመት በፊት የነበረው የኢትዮጵያ ካርታ ተሸርፏል፡፡ እንኳን ሰው ሀገርም ለማጥፋት እየሰሩ ነው፡፡
ታሪካቸው፣ አመጣጣቸውም የሚያሳየው ይህን ነው፡፡ ይህን ሁሉ የምለውም መታወቅ ስላለበት ነው፡፡

የተስፈኞች የሰሞኑ ጫጫታና እንደምታው (ዶ/ር አሸናፊ ጐሳዬ)

July 15, 2015
ዶ/ር አሸናፊ ጐሳዬ
የአገራችንን ፖለቲካ በቅርብ የምትከታተሉ ሰሞኑን ለነጻነት የሚደረገውን ጉዞ ለማዳከም የተከፈተውን ዘመቻ እና የዘንድሮውን አገር አቀፍ የምርጫ ውጤት ተከትሎ ብዙ አዳዲስ የሚመስሉ ነገር ግን የጠበቅናቸው ክስተቶች እንዳስተዋላችሁ እገምታለሁ። ከእነዚህ ውስጥ ቀጥሎ የተዘረዘሩት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፦
1. ወያኔ/ኢሕአዴግ 100% አሸንፌአለሁ በማለት ከእንግዲህ በምርጫ የሚመጣ የፖለቲካ ለውጥም ሆነ ለይስሙላ የነበረው የመድብለ ፓርቲ ስርአት እንዳበቃለት አሁንም በድጋሚ ማረጋገጡ፤
2. በሰላማዊ ትግል ወያኔ/ኢሕአዴግን አሸንፈን የስርአት ለውጥ እናመጣለን ብለው በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች የምርጫውን ኢፍትሀዊነት በየመግለጫቸው ከማውገዝ ያለፈ የተሰረቀባቸውን የህዝብ ድምፅ ለማስመለስም ሆነ እጩዎችቸውንና አባሎቻቸውን በጠራራ ፀሀይ የገደሉ በህግ እንዲጠየቁ ለማድረግ ህዝብ ቀስቅሰው አደባባይ ውጥተው ድምጻቸውን እንኳን ማሰማት ሳይችሉ መቅረታቸው፤
3. ወያኔ/ኢሕአዴግን በሰላማዊ መንገድ ብቻ ማስወገድ እንደማይቻል ካወቅን ቆይተናል የሚሉ ኃይሎች ደግሞ ወያኔን በሚገባው ቋንቋ ለማነጋገርና ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ዝግጅታችንን ጨርሰን የነጻነት ጉዞ ፊሽካ ነፍተን ጀምረናልና ነጻነት ናፋቂዎች ሁሉ ተቀላቀሉን ሲሉ ማውጃቸው እና
4. አላማው ከላይ በቁጥር ሁለትና ሶስት ከተጠቀሱት ኃይሎች የተለየ ወገን ደግሞ በቅርቡ የትጥቅ ትግሉን አስመልክቶ የከፈተው የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ የመገናኛ ብዙሀንን ትኩረት የሳበና ህዝብን እያነጋገረ መሆኑ ናቸው። በዚህ አጭር ጽሁፍ እነዚህን ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች በጥልቀት ለመዳሰስ ስለማይቻልና ምናልባትም ብዙዎች በተራ ቁጥር አራት የጠቀስኩትን ኃይል ማንነትና ድብቅ አላማ እንዲሁም በቅርቡ የትጥቅ ትግሉን አስመልክቶ የከፈተውን የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ በተመለከተ ጥያቄዎች ሊኖራቸው ስለሚችል የታዘብኩትን ባካፍልና በዚህ ጉዳይ ላይ በግልጽ መወያየት ብንጀምር ለነጻነት የሚደረገውን ትግል ያግዛል ብዬ ስላመንኩ ነው።
ባለፉት አምስት ዓመታት የአገራችን የፖለቲካ ኃይሎች ለምን በሚግባቡባቸው ጉዳዮች ተባብረው በመስራት ውጤታማ ለመሆን አልቻሉም ለሚለው ጥያቄ መልስ ለማግኘት ብዙ ጊዜዬን አጥፍቻለሁ። ችግሩ የርዕዮተ-ዓለም ልዩነት፣ በዘር በቋንቋ መከፋፈላችን፣ ታሪካችን ጥሎብን ያለፈው ጠባሳ ወይስ የወያኔ ጥንካሬ ይሆን ለሚለው ጥያቄዬ መልስ ለማግኘት ብዙ ሞክሬአለሁ።
የማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባል ሳልሆን እዚህ ሲያትል ውስጥ ከሚገኙ አክቲቪስቶች ጋር ሆነን በፈጠርነው ሕዝባዊ ፎረም አማካይነት በብዙ ሕዝባዊ ስብሰባዎች ተካፍያልሁ መርቻለሁ፣ ከአብዛኛዎቹ የተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎች፣ የሲቪክ ማህበራት ሀላፊዎችና ታዋቂ ግለሰቦች ጋር ለመወያየትም እድሉን አግኝቻለሁ። የተቻለኝን ያህል ስለ አገሬ ፖለቲካ እከታተላለሁ አነባለሁ። በዚህ ጽሁፌ የማቀርበው ትዝብት ከዚህ ሁሉ የመነጨ ነው።
ትዝብት አንድ
ከላይ በተራ ቁጥር አራት የጠቀስኩት ኃይል በአንድ ድርጅት ጥላ ስር የተሰባሰበ ሳይሆን በሁሉም የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ ያለ ነው። ሆኖም ይህ ኃይል ድብቅ ዓላማ አለው። ብዙ ጊዜ የዚህ ዓላማ አራማጆች የተቀላቀሉት ድርጅት የቆሙለትን አላማ የማያሳካ መስሎ በታያቸው ቁጥር እና አመራሩን እነሱ ካልተቆጣጠሩት የሚወስዱት እርምጃ ሁሌም አፍራሽና አደገኛ ነው። አንድም ድረጅቱን አዳክመው ያፈርሱታል አልያም መሰሎቻቸውን ይዘው በመውጣት አላማቸውን ለማሳካት ይሞክራሉ። ቅንጅትን ጨምሮ ብዙ ተስፋ የተጣለባቸው ድርጅቶች ለውድቀታቸው ምክንያቶች ከወ ያኔ ይልቅ እነዚህ ኃይሎች መሆናቸው ቢታወቅም ይህን በይፋ ስላልተነጋገርንበትና መፍትሄ በጊዜ ስላልሰጠነው ደግመን ደጋግመን እዛው ወጥመድ ውስጥ ስንወድቅ እንገኛለን። መቼ ይሆን “ዓላማችሁ ገብቶናል በቃችሁ” የምንላቸው?
ትዝብት ሁለት
የዚህ ዓላማ አራማጆች ከማንም በላይ የወያኔ ጠላት ናቸው። ብዙ ጊዜ የነዚህን አፍራሽ ኃይሎች ድርጊት ያስተዋሉ ወገኖች፣ ወያኔ ወደ ተቃዋሚ ድርጅቶች አስርጎ ያስገባቸው ናቸው ብለው iske meterater yigersalu ይጠራጠራሉ። ጥርጣሬአቸው እውነት ቢመስልም ሀቁ ግን ሌላ ነው። እንዲያውም ወያኔንና የትግራይን ህዝብ መለየት እስከሚያቅታቸው ድረስ የወያኔን አምባገነንነት፣ ዘረኝነትና አድሎአዊ አገዛዝ ለማጋለጥ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። ወያኔን ለመቃወም በተጠሩ ዝግጅቶች ሁሉ ግንባር ቀደም ተሳታፊ ሲሆኑ ገንዘባቸውንና ጊዜአቸውን ለመሰዋትም ወደኋላ አይሉም።
ትዝብት ሶስት
እነዚህ ኃይሎች ለኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነትና ሉአላዊነት መቆማቸው ምንም ጥርጥር የለውም። ችግሩ ሌሎችም ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ከነሱ ባላነሰ እንደሚወዱ መረዳት አለመቻላቸውና በተለይ የብሄር ጥያቄ የሚያነሱና በዚያ መሰረት የተደራጁ ወገኖች ጋር ተቀራርቦ መስራት እንዳይቻል ዋነኛ እንቅፋት ሆነው መቆየታቸው ነው። በነሱ እምነት በአገራችን የመደብ እንጂ የብሄር ጭቆና መቼም ኖሮ አያውቅም። የኢትዮጵያን አንድነት ለማምጣት በተደረጉ ጦርነቶች ወገኖቻችን አልቀዋል፣ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፣ በባርነት እንዲያገለግሉ ሆነዋል፣ ንብረታቸው ወድሟል ወይም ተወርሷል፣ ስለሆነም ወደድንም ጠላንም እንደምንኮራባቸው ታሪኮች ሁሉ ይህም ያገራችን ታሪክ ነውና ተመዝግቦ ለትውልድ ይተላለፍ የሚሉትን ወገኖች በኢትዮጵያ ጠላትነት ለመፈረጅ ለአፍታም አያቅማሙም።
ትዝብት አራት
የዚህ ዓላማ አራማጆች የትግል ስልት ምርጫ የላቸውም። ወያኔ የሚወድቀው በምርጫ፣ በህዝብ አመጽ ወይም በትጥቅ ትግል ቢሆን ግድ የላቸውም። ወያኔን የሚጥለው ኃይል ከኬንያ፣ ከሱዳን፣ ከሱማሌ ወይም ከኤርትራ ቢነሳ ጉዳያቸው አይደለም። ዋንው ቁም ነገር ወያኔ ወድቆ ያ በሚስጥር የያዙት ዓላማቸው መሳካቱ ብቻ ነው። ታዲያ ሰሞኑን ከኤርትራ ተነስተን ተከዜን አቋርጠን አገራችንና ህዝባችንን ከወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ ነጻ የማውጣት ጉዞአችንን ጀምረናል በሚሉት ኃይሎችና በህዝብ ተሳትፎ የቆመውንና አማራጭ የመረጃ ምንጭ የሆነው ሚዲያ ላይ ኃይለኛ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ የከፈቱት ለምንድነው? ከተወሰነው የአገራችን ክፍል ወጣቶች መጥተው እነዚህን የነጻነት ታጋዮች እንድይቀላቀሉ የሚማጸኑትስ ለምን ይሆን?
ትዝብት አምስት
እኔን ጨምሮ ብዙዎች ተመልሰን ወደ ጦርነት መግባታችንና ወንድማማቾች ሊገዳደሉ መሆኑን ስናስብ እናዝናለን። ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት ስለማንችል ስጋታችንም በዛው ልክ ከፍተኛ ነው። ነገር ግን የሰላሙ ሁሉ በር ተዘግቶ ወደዚህ አማራጭ ተገደን እየገባን እንደሆነም እንረዳለን፣ ህይወታቸውን ለአገራችን ነጻነት ለመስጠት የቆረጡትን
ጀግኖቻችንን እናከብራለን መልካሙን ሁሉ እንዲገጥማቸውም እንመኛለን። በተቃራኒው እኔ እንደምገምተው አፍራሽ ኃይሎቹ ይኸ ሁሉ ጫጫታ የሚያበዙትና አቧራ የሚያስነሱት ይህ የነጻነት ኃይል ከተሳካለት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የቆሙለትን አላማ ገድሎ እንደሚቀብረው ስለሚያውቁ ነው። የነጻነቱ ኃይል በኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ አንዳርጋቸው ጽጌ ራዕይ የታነጸ፣ ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጡ ወጣቶች የተሰባሰቡበት እና ሰብአዊ መብቶች የሚከበሩባት፣ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት፣ በእኩልነት ላይ የተመሰረተች ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መመስረት እንደሚፈልግም ጠንቅቀው ይረዳሉ።
ውድ አንባቢያን
እኔ እስከሚገባኝ ድረስ እነዚህ ኃይሎች ሁለት ገጽታ አላቸው። የመጀመሪያዎቹ ብዙ ተከታይ ያላቸው ሲሆኑ ዋና ዓላማቸው ያለውን የአንድ ብሄር የበላይነትን አስወግዶ በሌላ መተካት ነው። ይህን አላማቸውን ይፋ አውጥተው በዚያ ዙሪያ ተደራጅተው መታገል እንደማያዋጣቸው በሚገባ ስለሚረዱ የተለያዩ ጭንብሎችን አጥልቀው አፍራሽ ተልኮአቸውን ሲፈጽሙ ይስተዋላሉ። ሁለተኞቹ ደግሞ ዓለም የምትሽከረከረው በእነሱ ዙሪያ ብቻ የሚመስላቸው ግለሰቦች ሲሆኑ እነሱ ያልመሩት ድርጅት ወይም ትግል ውጤታማ ሲሆን ማየት ሞታቸው ስለሆነ ያንን ለማጨናገፍ የማይገቡበት የለም።
እነዚህ ኃይሎች ናቸው እንግዲህ ግንባር ፈጥረው የነጻነት ጉዞውን ለማደናቀፍ ሌት ከቀን የሚሰሩት። ለዚህም ነው እንግዲህ በቅርቡ በነጻነት ታጋዮች እቅስቃሴ ላይ ተልካሻ ምክንያቶቻቸውን በመደርደርና የአዞ እንባቸውን በመርጨት ነጻነት ናፋቂው ህዝብ በጥርጣሬ እንዲመለከተው ለማድረግ የሚሞክሩትና በሁላችንም ጥረት በየጊዜው እየጠነከረ የመጣውን የመረጃ ምንጫችንን ጥላሸት በመቀባት ለማጥፋት ከወያኔ ባልተናነሰ ጦርነት የከፈቱበት።
በግልጽ ተነጋግረን እነዚህ አፍራሽ ኃይሎች ያጠለቋቸውን ጭንብሎች እስወልቀን ካላጋለጥናቸው አንድም አፍራሽ ተልእኮአቸውን እንዲቀጥሉ ፈቅደን የወያኔን ዘላለማዊነት እናረጋግጣለን አለያም ለአገር ከፋፋዮችና ገንጣዮች መንገዱን ከፍተን ቁራሽ ቁራሻችንን ይዘን እንበታተናለን።

ጆን ዶ የተሰኘው ኢትዮጵያዊ አማሪካዊና እና የኢትዮጵያ መንግስት በዲሲ ፍርድ ቤት

July 15, 2015
ቢላል አበጋዝ  (ከዋሽንግተን ዲሲ) – ጁላይ 13፡2015
ዛሬ በዲትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ በዋለው ችሎት ጆን ዶ የተሰኘው ኢትዮጵያዊ አማሪካዊና እና የኢትዮጵያ መንግስት ጠበቆች ቀርበው ሁለቱም ወገኖች ዳኛው ፊት ቃላቸውን ሰጥተዋል።ጆን ዶ የተሰኘው ኢትዮጵያዊ አማሪካዊ የተሰጠው ስም (ጆን ዶ) ይህ ስያሜ ስማቸው በግልጽ መገለጥ ለሌለባቸው ሰዎች በጅምላ የሚሰጥ ነው።ጆን ዶ ተብሎ መቅረቡ የክሱ መስራች የኢትዮጵያ መንግስት ወይም ወኪሎቹ ይህን ዜጋ ለይተው እንዳያጠቁት በሚል ወይም ስሜ ቢጠቀስ ጉዳት ያገኘኛል ከሚለው ስጋት ነው።Court trial in Washington DC
የኢትዮጵያ መንግስት ያቆማቸው ጠበቃ ግሪንበርግ ቱሪግ (Greenberg Traurig LLP)ለተባለ እዚህ ዋሽግቶን ዲሲ ለሚገኝ የጥብቅና ተቋም ሰራተኛ ናቸው።ኢትዮጵያዊ አማሪካዊውን ግለሰብ የወከሉት ኤሌክትሮኒ ፍሮንቲር ፋውዴሽ ከተሰኘ ድርጅት የቀረቡ ጠበቆች ነበሩ (Electronic Frontier Foundation) ዋና ድሬክተርዋ ሲንዲ ኮህን የተባሉ ሲሆኑ “ነጻነትና የሰው መብት ሲደፈር ፈጥነው የሚክላከሉ” በማለት ብሄራዊ የአማሪካ ጠበቆች መጻሄት( National Law Journal)ያደነቃቸው ናቸው።በእለቱ የኢትዮጵያዊ አማሪካዊውን ጉዳይ ያቀረበው ናታን ካርዶዞ የተባለው የዚሁ ድርጅት ጠበቃ ነበር።
ክሱ የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮጵያዊ አማሪካዊው ላይ ያደረገው ህገወጥ ድርጊት የኮምፑተር ቫይረስ በመላክ ሰርስሮ በድብቅ ተኮምፑተር ገብቶ ቫይረሱ በኮምፑተሩ ይቀበርና ስለላን ለማካሄድ የሚያስችል የተንል መሳሪያ በተግባር ላይ ማዋል ነው።ይህን ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግስት የተለያዩ ኩባንያዎችን ተጠቅሟል። ወያኔ ዳቪድ ቪንቼንዜቲ በተባለ ጣሊያናዊ የሚመራ ሰርሳሪ ቡድን (The Hacking Team) የተባለ ኩባንያንም ተጠቅሟል።ኩባንያው ሚላኖ ኢጣሊያ የሚገኝ ነው።አገልግሎቱን ለሱዳን ሞሮኮ ግብጽ ከኢትዮጵያ ሌላ የሰጠ ሲሆን ስለ ኢትዮጵያ ሲጠየቅ ክዷል። ጋርዲያ የተባለው ጋዜጣ እንደዘገበው።
በአማሪካን አገር ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ የግለሰቡ መብት በመንግስት አካላት አይደፈርም። ያገሩ መንግስት ያልደፈረውን ህወሃት መሩ መንግስት ተዳፍሯል በማለት የከሳሽ ጠበቃ ሲናገር የተከሳሽ ጠበቃ ድርጊቱ እዚህ አማሪካ አልተፈጸመም የሚል ክርክር ዳጋግሞ አቅርቧል። ቀድሞ ባአማሪካ ዜጎች ላይ ተደርገው ነበር የሚላቸውን ክሶች አጣቅሷል። የከሳሽ ጠበቃ ህገ መንግስታዊ መርሆዎችን፡ስለላ የማካሄድን(መንግስት ከፍርድ ቤት አስፈቅዶ) ስለላው እዲደረግ ገፊ ምክንያቶችን ሁሉ የሚነካ ጉዳይ መሆኑን አስዘግቧል። ፍርድ ቤቱ የሚደርስበት ውሳኔ የህወሃት መሩ መንግስትን ተረቺ ካደረገ ይላል ጠበቃው የአሜሪካንን የስለላ ተቋማትን ሳያሳስብ አይቀርም። ለአጃዚራ እንደሰጠው ቃል።
እንደሚታወሰው ህወሃት መሩ መንግስት ይህኑ የስለላ ተግባር በሚሊዮኖች የሚቆጠር ንዋይ አፍስሶ እነ እስክንድር ነጋ ላይ “መረጃ” አቀረብሁ ማለቱ ይታወሳል።መእራባውያን መንግስታት አይቶ እንዳላየ የሚሆኑት ዛሬ ህወሃት መሩ መንግስት በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ምእራቡን የሚያሳስበውን ሽብርተኝነት ለመዋጋት እንዳአጋር በመወሰዱ ነው።
ህወሃት መሩ መንግስት ልማት ሊያራምድ የሚችሉትን የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በተግባር ለማዋል ቀርቶ ለስለላው መሽቀዳደሙ የመንግስቱ እኩይ ባህሪ ግፊት መሆኑን ከፍርድ ቤቱ መጥተው የታዘቡ ተናግረዋል።
በፍርድ ቤቱ የዲሲ ሜትሮ ነዋሪዎች፡ የኢሳትና የቪኦኤ ጋዜጠኛች፡ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ተገኝተው ነበር።