Pages

Monday, April 6, 2015

Urgent Appeal on Behalf of Ethiopians Stranded in Yemen

April 5, 2015
Global Alliance for the Rights of Ethiopians (GARE)
Global Alliance for the Rights of Ethiopians (GARE)The Global Alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) was established in response to the crisis emanating from the unexpected decision by the Government of Saudi Arabia to expel Ethiopian migrant workers. GARE campaigned vigorously and raised global awareness and gained responses from the Ethiopian and Saudi governments. In 2013, more than 160,000 migrant workers were airlifted back to Ethiopia. Sadly, with few exceptions, those who returned did not find meaningful work in their home country. According to the International Organization for Migration (IOM), the government of Yemen estimates that of the one million refugees in the country, majority are Ethiopians.
IOM, through which the Global Alliance has channeled financial assistance in support of those in dire need in Yemen, has informed GARE that the flow of Ethiopians, including 15 and 16 year old boys and girls is on the rise. Each month, ten thousand Ethiopians enter Yemen via Djibouti in smugglers’ boats, many dying en-route. In the process, many Ethiopian migrants suffer from human rights abuses including torture, detention, starvation, abductions and forcible extortion of money by criminal gangs as well as sexual violence. IOM has been instrumental in providing lifesaving assistance such as water, medical care, sanitation, meals and nutrition to the most vulnerable Ethiopian migrants, especially young girls with children who are housed in crowded camps.
In the past few weeks with Yemen going through a full-scale civil war, the situation has changed dramatically making these refugees/migrant workers more vulnerable than ever before. Almost all human rights organizations including IOM have closed their local offices. Assistance to Ethiopian refugees/migrants is difficult in the best of times. The war puts every Ethiopian refugee/migrant worker at risk for their lives. Many countries such as Sudan have responded quickly and pulled out their citizens from Yemen. Unfortunately, the Ethiopian government has not responded to the plight of hundreds of thousands of Ethiopian citizens scattered throughout Yemen. Reuters reported last week that more than 40 Ethiopians were killed and 60 wounded when Saudi Arabia’s aircraft bombed rebels near the camps where Ethiopian refugees were sheltered by UNHCR.
Global Alliance for the Rights of Ethiopians is extremely concerned that thousands of Ethiopian citizens will be killed or wounded as the war continues to escalate and expand.
We, therefore, urge:
- the Ethiopian government to airlift these stranded Ethiopian citizens back to their country immediately.
- the UNHCR, to urgently transfer the Ethiopian refugees to safer locations.
-the International Red Cross, the International Red Crescent and other humanitarian agencies to respond to the plight of Ethiopian migrant workers/refugees at the earliest opportunity.
- the government of Saudi Arabia to desist from indiscriminate bombing of refugee camps and support emergency assistance efforts to help Ethiopian refugees who have become victims of its air raids in Yemen.
- the United States government and its allies to use their influence to urge restraint on the part of Saudi Arabia and the Arab coalition forces not to target innocent civilians.
The Global Alliance for the Rights of Ethiopians recognizes that the grim socio-economic and political situation in Ethiopia is driving thousands of young girls and boys from their homeland each year. In spite of the grave dangers to their physical safety en-route and upon arrival in Yemen they still continue to flee from Ethiopia. The current humanitarian crisis Ethiopian migrant workers and refugees face in Yemen is beyond their control. We plead with the global community to respond to this dire emergency before more infants, children, girls and boys perish through no fault of their own.
Finally, the Global Alliance for the Rights of Ethiopians calls upon all Ethiopians and members of civilized society to join us in demanding that the Ethiopian government respond immediately to the plight of its citizens in Yemen. GARE will do everything to raise awareness about the unfolding tragedy and the dire circumstances thousands of Ethiopian citizens stranded in Yemen are facing. We urge all Ethiopians around the world to join GARE in its effort to mitigate the pending humanitarian emergency.

ኢ/ር ይልቃል ከአገር አንዳይወጡ የተከለከሉበትን ምክንያት የሚነግራቸው ማጣታቸው ተዘገበ

መጋቢት ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሰማያዊ ፓርቲ ሊ/መንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ወደ አሜሪካ ሊያደርጉት የነበረው ጉዞ በደህንነት ሰዎች እንዲሰረዝ ከተደረገ በሁዋላ፣ እስካሁን ድረስ ምክንያቱን የሚነግራቸው አካል መጥፋቱን ሊ/መንበሩ
ለነገረ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
የኢሜግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ መስሪያ ቤት ‹‹ፓስፖርቱ እኛ ጋር አልደረሰም፡፡ ቆይተው ደውለው ይጠይቁ››  ብለው ስልክ እንደሰጧቸው የገለጹት ኢ/ር ይልቃል፣ ይህም ሆን ተብሎ ጉዞውን ለማጓተት የተደረገ ነው ብለዋል፡፡ ‹‹ይህን ሁሉ የሚያደርጉት አገር የማስተዳደር
ብቃት ስለሌላቸው፣  የፖለቲከኛን እንቅስቃሴ በማጓተትና በማገድ የተፈጠረባቸውን ስጋት የሚቀርፉ ስለሚመስላቸው ነው፡፡  ከአቅመ ቢስነታቸው የመነጨ ነው›› ሲሉ ለጋዜጣው ተናግረዋል፡፡
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ሰማያዊ ፓርቲ በውጭ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ያለው ተቀባይነት ገዢውን ፓርቲ እንዳስፈራውም አክለዋል።

በአማራ ክልል ባለሀብቱ እና ነጋዴው ለአባይ ግድብ ማሰሪያ የሚጠበቅበትን ያህል አስተዋጽኦ አላበረከተም ተባለ፡፡

መጋቢት ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከፍተኛውን ድርሻ የሸፈኑት የመንግስት ሰራተኞች መሆናቸውም ተገልጿል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአባይ ግድብ ህዝባዊ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ፀሀፊና የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ሰሞኑን ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ፣  በአራት አመቱ ውስጥ በክልሉ የተሰበሰበው ገንዘብ ስድስት መቶ ሚሊዮን ብር አካባቢ መሆኑን ገልጸው፤ ከዚህ ውስጥ ከ384 ሚሊዮን ብር በላይ ከመንግስት ሰራተኛው የተሰበሰበ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በክልሉ የሚገኙ አርሶ አደሮች ፣ ከተለያዩ ነጋዴዎችና ባለሃብቶች በተሻለ መልኩ 57 ሚሊዮን ብር ሲያዋጡ ነጋዴዎችና ባለ ሃብቶች ግን 44 ሚሊዮን ብር ብቻ ማዋጣቸውን ኃላፊው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል፡፡
በሃገሪቱ ልዩ ልዩ ቦታዎች የገቢ ማሰባሰቢያ መድረኮች ቢዘጋጁም የተጠበቀውን ያህል ገቢ እንዳልተሰበሰበ የገለጹት ኃላፊው ፤ ከመጋቢት 24/2007 ዓ.ም ጀምሮ ለስምንት ቀናት በክልሉ ባሉ ከተሞች በተዘጋጀው የቦንድ ግዢ እንቅስቃሴ አጥጋቢ ውጤት አለመገኘቱ አሳሳቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
“የግድቡን ስራ በመደገፍ ተገቢውን ማድረግ እንዳለብን ብናውቅም የመንግስት ባለስልጣናት በየደረጃው ስራችንን በአግባቡ እንዳንሰራ  የሚጥሉብን ተገቢነት የሌለው ግብር ስላማረረን በሁሉም እንቅስቃሴ ለመሳተፍ ይቸግረናል፡፡” ሲሉ ነጋዴዎች ለዘጋቢያችን ገልጸውላታል።
በሌላ በኩል በጎንደር፣በባህርዳርና ደብረታቦር ከተማ የሚኖሩ የመንግስት ሰራተኞች “የግድቡ መሰራት ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚጠቅም ቢሆንም  በአራት አመቱ ውስጥ የተሰበሰበው ገንዘብ ሲታይ እዚህ ግባ የማይባል እና አብዛኛው ገንዘብ የተሰበሰበው ከመንግስት ሰራተኛው ጉሮሮ ተነጥቆ መሆኑ ዘላቂነቱን አጠራጣሪ ያደርገዋል፡፡”ብለዋል፡፡
ሰራተኞቹ በአሁኑ ጊዜ በመንግስት ያሰራር ጉድለት ምክንያት በተለይ በመንግስት ሰራተኛውና ዝቅተኛ ነዋሪው እየደረሰ ያለው የኑሮ ውድነት ከጊዜ ወደ ጊዜ ፈታኝ መሆኑ እየታወቀ፤ ገንዘብ አዋጡ በማለት የሁሉም ፈቃድ ሳይኖር በየጊዜው ከደመዎዛቸው መቆረጡ አግባብነት የሌለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
“ባለብን የኑሮ ክብደት ምክንያት ደመዎዛችን እንዲቆረጥ አንፈልግም፡፡” በማለት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን የተናገሩ የመንግስት ሰራተኞች ፣ በየምክንያቱ ከደረጃ ዝቅ እንዲሉና በሰበብ አስባቡ ልዩ ልዩ ቅጣት ሲደርስባቸው መታየቱ፤ሁሉም የመንግስት ሰራተኞች ዝምታን
በመምረጥ በኑሮ ውድነት ለመሰቃየት መዳረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
በግድቡ ስራ ዙሪያ በመጀመሪያ አካባቢ የነበረው የተነሳሽነትና ቁጭት ስሜት ዛሬ እየጠፋ መሆኑን የሚገልጹት አስተያየት ሰጪዎች፣  አሁንም “ግድቡ 42 በመቶ ደርሷል የሚለው መግለጫ ትክክል ለመሆኑ ጥርጣሬ አለን” በማለት የገዢው መንግስት ሁልጊዜም በቁጥር በኩል እውነት አለመናገሩ የተለመደ መሆኑን  ይናገራሉ፡፡

በቦሌ አየር ማረፊያ በሚስጢር የተመዘገቡ በርካታ ድርጅቶች በህገወጥ መንገድ እየነገዱ ነው

መጋቢት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ከታማኝ ምንጮች እንዳረጋገጠው በቦሌ አየር ማረፊያ  በሚስጢር ስም የተመዘገቡና ባለቤታቸው ተለይቶ ያልተመዘገቡ  ድርጅቶች ካለፉት 10 አመታት ጀምሮ የኮንትራት ጊዜያቸውን ሳያድሱ እና
የቤት ኪራይ ክፍያቸውን ለመንግስት ገቢ ሳያደርጉ በመነገድ  ላይ ናቸው።
በእነዚህ ድርጅቶች ጀርባ የከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እጅ እንዳለበትም ምንጮች ጠቁመዋል።
የኤርፖርቶች ድርጅት ፣ተከራዮችንና ሌሎች የሚመለከታቸውን የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በሚል ምክንያት በየካቲት 1999 ዓም ላይ ኤሮኔቲካል ያልሆኑ የገቢ ምንጮችን ለማስተዳደር የሚል መመሪያ ያወጣ ሲሆን፣ በመመሪያው መሰረት
ተከራዮቹ በየአምስት አመቱ በግልጽ ጨረታ እንደገና መወዳደር ይጠበቅባቸው ነበር።
ይሁን እንጅ ከእነዚህ መካከል፣8ት ባለቤታቸው የማይታወቅ በኮድ ስም የተመዘገቡ ድርጅቶችን ጨምሮ 15 የንግድ ድርጅቶች   የኮንትራት ጊዜያቸውን ሳያድሱ ፣ የሚከፍሉት ወርሃዊ ክፍያ የት እንደገባ ሳይታወቅ ገንዘቡ በባለስልጣናት መበላቱን ምንጮች ጠቁመዋል።
ድርጅቶቹ በ1995 ዓም የኮንትራት ውል የፈረሙ ቢሆንም ፣ በ1999 ዓም በወጣው መመሪያ መሰረት እንደገና አለመመዝገባቸውን፣ ድርጅቶቹን ደፍሮ እንዲመዘገቡ የሚያደርግ አካል መጥፋቱን ምንጮች አክለዋል።
በተርሚናል ቁጥር 2   በኮድ ቁጥር AACS 02 የተመዘገበው ድርጅት፣ የህትመት ውጤቶችን ለመሸጥ በካሬ ሜትር 8 ሺ 100 ብር ክፍያ 54 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ክፍል ተከራይቶ የሚገኝ ሲሆን፣ በአመት 437 ሺ 400 ብር  ሂሳብ የአስር አመት
ጠቅላላ ክፍያ 4 ሚሊዮን 374 ሺ ብር ፤ በተርሚናል ቁጥር 2 በኮድ ቁጥር AACS 07 Cultural Cusin በሚል የይዞታ አይነት የተመዘገበው ድርጅት በአመት በካሬሜትር 5 ሺ 220 ብር ሂሳብ 54 ካሬ ሜትር ቦታ ቢወስድም የ10 አመታት የኪራይ
ክፍያ  2 ሚሊዮን 818 ሺ 800 ብር የት እንደገባ አይታወቅም።
በተርሚናል ቁጥር 2 ለሻንጣ ማሸጊያ በሚል በኮድ ቁጥር AACS 22  የተመዘገበ ድርጅት ለ12 ካሬ ሜትር በአመት በካሬ ሜትር 4 ሺ 100 ሂሳብ በአስር አመት 492 ሺ ብር ለመክፈል ቢዋዋልም ክፍያው የት እንደገባ አልታወቀም።
በተርሚናል 2 በኮድ ቁጥር AARS 12  ለካውንተር ሰርቪስ አገልግሎት ተመዝግቦ የሚገኘው ድርጅት 141.31 ካሬ ሜትር ቦታ ወስዶ በካሬሜትር በአመት 4 ፣ 100 ብር በ10 አመታት በአጠቃላይ 5 ሚሊዮን 793 ሺ 710 ብር ክፍያ እንዲሁም በዚሁ
ተርሚናል በኮድ ቁጥር AACS 09 የተመዘገበው  የወርቅና ጌጣጌጦች ሱቅ ለያዘው 31.10 ካሬ ሜትር ቦታ በአመት በካሬ ሜትር 8 ሺ 100  ሂሳብ በአስር አመት 2 ሚሊዮን 519 ሺ 100 ብር ክፍያ የት እንደገባ አልታወቀም
በተርሚናል ቁጥር 2 በኮድ ቁጥር AACS 21 ለአበባ መሸጫነት የተከራየው በ25.9 ካሬ ሜትር የሰፈረው ቦታ በአመት በካሬ ሜትር 4 ሺ 100 ብር የሚከፈልበት ቢሆንም የ10 አመታት አመታዊ ክፍያው 1 ሚሊዮን 61 ሺ 900 ብር  እንዲሁም  በኮድ
ቁጥር AACS 06  የይዞታዉ መጠን 31.10  ካሬ ሜትር ለብር ጌጣጌጥ/Silver  Shop/   የሚውለው መደብር በአመት በካሬሜትር 8 ሺ 100.00 ብር ተከራይቶ በአስር አመታት ውስጥ 2 ሚሊዮን 519 ሺ 100 ብር ክፍያ የት እንደገባ አይታወቅም።
በተርሚናል ቁጥር 2 በኮድ ቁጥር AACS 16 ለሱፐር ማርኬት የተከራየው በ 33.4 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሰፈረው መደብር በአመት 8 ሺ 100 ብር የሚከፈልበት ቢሆንም አመታዊው ክፍያው 2 ሚሊዮን 700 ሺ ብር ከ40 ሳንቲም እንዲሁ የት እንደገባአይታወቅም።
እነዚህን ድርጅቶች በባለቤትነት የሚያስተዳድሩዋቸው ሰዎች በግልጽ ባይታወቁም ምንጮች : ” በህግ የማይጠየቁ የተወሰኑ ከፍተኛ ባለስልጣናት ዘመዶችና ቤተሰቦች ናቸው” ይላሉ።
በስማቸው ተመዝገበው የሚገኙት የንግድ ድርጅቶችም በአዲሱ መመሪያ መሰረት ውል ሳይገቡ በመነገድ ላይ ሲሆኑ  የሚከፍሉት ክፍያ ከወቅቱ ጋር የማይመጣጠንና ተቆጣጣሪ የሌለባቸው መሆናቸውን ምንጮች ገልጸዋል።
በአዲሱ ውል መሰረት ውል ሳይዋዋሉ ለ5 አመታት ያክል በአውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ በመነገድ ላይ ካሉት ድርጅቶች መካከል ለንደን ካፌና ሳተላይት ሬስቶራንት 109.9 ካሬ ቦታ  በአመት ብር 138 ሺ 474 አላፋራጅ ትሬዲንግ ሃላፊነቱ  የተወሰነ የግል ማህበር ፣
የይዞታ መጠን 631 ካሬ ሜትር፣ አመታዊ ክፍያ በካሬ ሜትር 8 ሺ 100 ብር ላሊበላ ወርቅ ቤት፣  31.10 ካሬ ሜትር፣ አመታዊ የክፍያ መጠን በካሬ ሜትር 8 ሺ 100 ብር ሲቲ ቢዝነስ ኮምፒዩተር ፣ 104 ካሬ ሜትር አመታዊ የክፍያ መጠን በካሬ ሜትር 8 ሺ 100
ብር  ድሬ ኢንዱስትሪ ሃ/የተወሰነ የግል ማህበር 54 ካሬ ሜትር አመታዊ የክፍያ መጠን በሄክታር 8 ሺ 100 ህይወት ለማ ትሬዲንግ 31.10 ካሬ ሜትር የክፍያ መጠን በካሬ ሜትር 8 ሺ 100 ብር ሲማት ትሬዲንግ 31.10 ካሬ ሜትር የክፍያ መጠኑ ባከሬ ሜትር
8 ሺ 100 ብር ይገኙበታል።
በአጠቃላይ አዲስ በወጣው መመሪያ መሰረት ህጋዊ ውል ሳይፈርሙ በመስራት ላይ የሚገኙት ደርጅቶች የ10 አመታት የኪራይ ዋጋ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ሲሆን፣ ኤርፖርቶች ድርጅት እስካሁን እርምጃ ለመውሰድ አለመድፈሩን ምንጮች ገልጸዋል።
ጉዳዩ በተደጋጋሚ ለድርጅቱ ቢቀርብም ምላሽ መጥፋቱን ምንጮች አክለው ይገልጻሉ። በጉዳዩ ዙሪያ የኢትዮጵያ ኤርፖርት ኢንተርፕራይዝን አስተያየት ለማካተት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

የምዕራብ አየር ምድብ የሁሉንም ቋንቋ ተናጋሪዎች በእኩልነት ያላማከለ የማዕረግ እድገት መስጠቱ በአየር ምድቡ ውስጥ ቅሬታ ፈጠረ

መጋቢት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በስራ አፈፃፀማቸው ብልጫ አመጥተዋል እንዲሁም የመቆያ ጊዜያቸውን ሸፍነዋል ለተባሉ  የአንድ አካባቢ ተወላጅ ከፍተኛ መኮንኖች፣መሰረታዊ መኮንኖችና ለባለ ሌላ ማዕረግተኞች  የማእረግ እድገት ተሰጥቷል።
መጋቢት 15 ቀን 2007 ዓ.ም በምድቡ ወታደራዊ መዝናኛ ክበብ በተዘጋጀው የማዕረግ አሰጣጥ ስነ-ስርዓት የምድቡ ታማኝ ሰዎች ብቻ የተገኙ ሲሆን ፣ ስነስርዓቱ ለሁሉም የሚዲያ ሰዎች ዝግ እንዲሆን ተደርጓል።
ለተሸላሚዎቹ ማዕረግ የሰጡት የምድቡ አዛዡ ኮሎኔል ይልማ መርዳሳ በእለቱ ለተሰባሰቡት የስርዓቱ ደጋፊዎች  እንደተናገሩት የማዕረግ እድገት የስራ ታታሪነትንና ታማኝነትን እንዲሁም ኃላፊነትን ስለሚጨምር በዕለቱ ማዕረግ ያገኛችሁም ሆነ ወደፊትም የምታገኙ ምድብ
የሰራዊት አባላት አሁን የጀመርነውን ውጤታማ ስራ አጠናክራችሁ መቀጠል አለባችሁ በማለት በእለቱ ማእረግ ያላገኙ  የአየር ኃይል አባላትን የሚያጽናና  መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የእለቱ ማዕረግ አሰጣጥ ፍትሃዊ አልነበረም በማለት ለዘጋቢያችን መረጃውን ያስተላለፉት አባላቱ፣ በተለያዩ ጊዜያት የሚደረጉት ሽልማቶች ወደ አንድ አካባቢ ያነጣጠሩ መሆናቸው አባላቱን ያስከፋ ድርጊት ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአየር ሃይል አባላት መካከል የተፈጠረውን መከፋፈል ለመቆጣጠር ያልቻለው መንግስት፣  በፖለቲካ አመለካከት የተነሳ እየተከፋፈሉ የመጡትን አባላት  ወደ አንድነት ለማምጣት እርምጃ ይወስዳል ተብሎ ሲጠበቅ ልዩነቱን የሚያሳፋ ድርጊት በመፈጸም
ላይ መሆኑን አባላቱ ይገልጻሉ።
የአየር ሃይል አዛዦች ክፍፍሉን የሚጠቀሙበት ታማኝ የሆኑትንና አልሆኑትን ለመለየት ሳይሆን እንደማይቀር አባላቱ አክለው ይገልጻሉ።
የምእራብ እዝ የማእረግ አሰጣጡን ከሚዲያ በማራቅ በዝግ ለማድረግ የተገደደው ትችቶችን በመፍራት መሆኑን ምንጮች አክለው ተናግረዋል።

ባለፉት 4 አመታት ለአባይ ግድብ የታሰበውን ያክል ገንዘብ መሰብሰብ ሳይቻል ቀረ

መጋቢት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ መንግስት ሁሉንም ኃይሎች ያሳተፈ ብሔራዊ መግባባት መፍጠር ባለመቻሉ ለአባይ ግድብ ፕሮጀክት ሕዝቡ በቂ ድጋፍ እንዳያደርግ ተጽኖ አድርጎበታል ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።
የግድቡ የመሰረት ድንጋይ የተጣለበት 4ኛ ዓመት በዓል በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግድቡ ባለበት ጉባ ከተማ በመከበር ላይ ሲሆን ባለፉት 4 ዓመታት  ሕዝብን በማንቀሳቀስ ለግድቡ ግንባታ የተሰባሰበው መዋጮ ወይንም የቦንድ ሽያጭ 6 ቢሊየን ብር ያህልብቻ
መሆኑ የመንግስትን ኪሳራ የሚሳይ መሆኑን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን የተለያዩ ሰዎችን አነጋግሮ ባጠናከረው ዘገባ አመልከቷል፡፡
ከ4 ኣመታት በፊት ለጠቅላላ ግንባታው 80 ቢሊየን ብር ገደማ ወጪ እንደሚስፈልግ የተገመተ ሲሆን ፣ ወጪውን  በሕዝብ ድጋፍ ሙሉ በሙሉ መሸፈን  ያልተቻለው፡ መንግስት ሁሉን ያሳተፈ ብሔራዊ መግባባት ማምጣት ባለመቻሉና የግድቡን ስራ ለፖለቲካ ዓላማ
እያዋለው በመምጣቱ ነው ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል፡
በግድቡ ግንባታ ጉዳይ መንግስት ራሱን ከፍ አድርጎ ተቀናቃኞቹን በማጣጣል የሚከተለው ስትራቴጂ የልዩነት አድማሱን እንዳሰፋው የጠቆሙት አንድ ምሁር፣  በዚህ ምክንያት ብዙዎቹ ተቃዋሚዎች ግልጽ ድጋፍ በመስጠት ሕዝቡ የግድቡን ግንባታ እንዲደግፍ
የበኩላቸውን እገዛ ከማድረግ መታቀባቸው፦ ሕዝብ የተስተካከለ ዕይታ እንዳይኖረው አድርጎአል ብለው እንደሚያምኑ አስረድተዋል፡፡ በየኢኮኖሚ አቅማቸው የተሻሉ ናቸው ተብለው የሚገመቱ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና
ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ከግድቡ በፊት ዳቦ እና የሰብኣዊ መብት ጥበቃ እንዲሁም የዴሞክራሲና የህግ የበላይነት አጀንዳዎችን ደጋግመው በማንሳታቸው በገዥው ቡድን እንደአክራሪ ኃይል መፈረጃቸው፦ ተሳትፎአቸው እንዲገደብ ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉንም
ጠቅሰዋል፡፡
በዚህ ምክንያት በተለያዩ በአሜሪካና በአውሮፓ ሀገራት በከፍተኛ ባለሰልጣናት  የታገዙ ቦንድ ማሰባሰቢያ መድረኮች የፖለቲካ ውዝግቦችን በማስተናገድ መክሸፋቸውን በማስታወስ ይህ ተደጋጋሚ ክስተት መንግስት ቆም ብሎ አካሄዱን እንዲመረምር ከማስገደድ
ይልቅ ደንግጦ ብቻውን እንዲቆም ማድረጉ ሌላው ችግር ነው ሲሉ አክለዋል፡፡
ኢህአዴግ በአጼ ኃይለስላሴ ዘመን ጀምሮ የታቀደውን የአባይ ግድብ እቅድ የራሱ በማድረግ ዕውቅና ከመንፈግ ጀምሮ በሀገር ውስጥ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ለማሳተፍ እንኩዋን ፍላጎት ማጣቱንም አመልክተዋል፣
የተቃውሞ ኃይሎች አፍራሽ ሚና ብቻ እንዳላቸው አድርጎ መሳሉ ሁሉም ወገኖች በልማት ጉዳይ ላይ እንኩዋን እንዳይስማሙ እንቅፋት መፍጠሩንም አስተያየት ሰጪው ተናግረዋል።
ከኢትዮጵያ ሕዝብ ግማሽ ያህሉ በወጣትነት ለስራ የደረሰ ዕድሜ ላይ እንደሚገኝ ያስታወሱት ምሁሩ መንግስት ራሱ ተዋጥቶልኛል ያለውን 6 ቢለየን ብር አምነን ከሕዝብ ቁጥር ጋር ስናሰላው የተገኘው ውጤት እጅግ ደካማ መሆኑን ያሳየናል ብለዋል።
መንግስት የአባይ ግድብን ብሔራዊ አጀንዳ በማድረግ ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች ድጋፍ እንዲያደርጉ በሩን ቢከፍትና ቢያሳትፍ እንዲሁም በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ብሔራዊ መግባባትን ቢፈጥር የተሻለ ስራ መስራት ይቻላል ሲሉ ሃሳባቸውን አጠቃለዋል።
ከውጭ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን 1 ቢሊዮን ዶላር ለመሰብሰብ እቅድ የተያዘ ቢሆንም፣ እስካሁን የተሰበሰበው በ10 ሚሊዮኖች የሚቆጠር ብቻ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።
አንዳንድ ወገኖች  መንግስት በቅርቡ ከግብጽ ጋር ያደረገውን ስምምነት ተከትሎ ግድቡን ለመጨረስ፦ ምናልባትም ከአንዳንድ አበዳሪ ድርጅቶች ገንዘብ ሊበደር ይችላል በማለት አስተያየት ይሰጣሉ።

Saturday, April 4, 2015

በደቡብ ክልል የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸሙት ከፍተኛ ባለስልጣኖች አልተጠየቁም

መጋቢት ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፉት ሶስት አመታት በደቡብ ክልል በቤንች ማጂ ዞን በጉራ ፈርዳ ወረዳ ይኖሩ በነበሩ በአማራ ተወላጆች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲፈጸም ትእዛዝ ያስተላለፉት ከፍተኛ ባለስልጣናት ፍርድ ቤት ባልቀረበቡበት
ሁኔታ፣  በወረዳ እና በቀበሌ ደረጃ ያሉ ሹማምንት ባለስልጣናት ሰኞ መጋቢት 21 ቀን 2007 ዓም ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ተደርጓል።
አቃቢ ህግ ከ55 በላይ የአማራ ተወላጆች እና በፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ ግድያ እንዲፈጸም አድርገዋል ባላቸው የጉራፈርዳ ወረዳ አስተዳዳሪ በነበሩት አቶ ምፍሳፎ ጉይ ፣ የድርጅት ሃላፊው አቶ ተካልኝ ሽፈራው፣ የወረዳው የካቢኔ አባልና የአስተዳዳሪው አማካሪ
አቶ ክፍሌ ሽፈራው እና በሌሎችም 18 የወረዳው ሹማምንትና ነዋሪዎች ላይ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19 ኛ ወንጀል ችሎት ክስ መስርቶባቸዋል።
አቃቢ ህግ በአቀረበው የክስ ቻርጅ፣ ተከሳሾች ለበርካታ አመታት በአካባቢው ሰፍረው ይኖሩ እንደነበር ጠቅሷል። ይሁን እንጅ ተከሳሾች ” ይህ ክልል የእኛ በመሆኑ አማሮች በሙሉ ለቃችሁ ውጡ፣ የማትወጡ ከሆነ ግን ያለንን ሃይል ሁሉ ተጠቅመን እናስወጣችሁዋለን
” በማለት ከፍተኛ ሰብአዊ መብት ጥሰት መፈጸማቸውን ” አቃቢ ህግ ገልጿል።
የወረዳው አስተዳዳሪና ባለስልጣኖች አማሮች እስከ 2007 ክልሉን ለቀው የማይወጡ ከሆነ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው መዛታቸውንና ይህንንም ተከትሎ ባለፉት 3 አመታት በርካታ ቁጥር ያላቸው አማሮች መፈናቀላቸውን፣ መገደላቸውንና ሃብትና ንብረታቸውን
መዘረፋቸውን በክሱ ተመልክቷል።
በአቃቢ ህግ የክስ ቻርች ላይ  55 አማሮች እና ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የፌደራል ፖሊሶች መገደላቸው እንዲሁም 7 ሰዎች ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ እንዳጋጠማቸው ግምታቸው 1 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ የነዋሪዎች ቤቶች መቃጠላቸውን፣ ግምታቸው 10
ሚሊዮን ብር የሚጠጋ የቀንድና የጋማ ከብቶች መዘረፋቸውን ፣ 19 ሺ ኩንታል የሚሆን ምርት መውደሙን ፣ 1 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የእርሻ መሳሪያዎች፣ ከ1 ሺ ሄክታር በላይ ሰብል መውደሙንና ሌሎችም በርካታ ጥፋቶች ተዘርዝረው ቀርበዋል።
በጉራ ፈርዳ የደረሰውን ከፍተኛ መፈናቀል በመቃወም መኢአድ እና ሰመጉ ተደጋጋሚ መግለጫዎችን ቢያወጡም መልስ ሳያገኙ ቆይተዋል። የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አመራር አቶ ግርማ ሰይፉ በጉራፈርዳ የደረሰው መፈናቀል ”  አንድ አገር አለን ብለን እንድናስብ
ያደርገናል ወይ ሲሉ የቀድሞውን ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ጠይቀዋቸው ነበር
አቶ መለስ ዜናዊ አማሮች ተፈናቀሉ  እያሉ የሚናገሩት በኢትዮጵያ አንድነት እንታወቅ  የሚሉ የፖለቲካ ድርጅቶች መሆናቸውን በመግለጽ፣ በአማሮች ላይ ተፈጸመ የሚለውን ክስ አጣጥለውት ነበር ። ድርጊቱ የተፈጸመው በአማራ ክልል እና በደቡብ ክልል መካከል
ስምምነት ከተደረሰ በሁዋላ ነው ያሉት አቶ መለስ ይሄ በአማራ ወይም በምስራቅ ጎጃም ነዋሪዎች ላይ የተቃጣ ወንጀል አይደለም ሲሉ የተፈጸመውን ድርጊት ተከላክለው ነበር
ይሁን እንጅ አቶ መለስ ከሞቱ ከ2 አመታት በሁዋላ አቃቢ ህግ ” አማሮች ሆን ተብሎ መገደላቸውን፣ ጥቃቱንም የፈጸሙት የወረዳው ባለስልጣናት መሆናቸውን ዘርዝሮ አቅርቧል።
ምንም እንኳ አቃቢ ህግ የወረዳውን ባለስልጣናት ተከታትሎ ለፍርድ ማቅረቡ የሚመሰገን ቢሆንም፣ ትእዛዙን የሰጡት የፌደራል፣ የክልልና የዞን ባለስልጣናት ፣ ጥፋቱን ሁሉ በታችኞች ባለስልጣናት ላይ አድርገው ራሳቸውን ከተጠያቂነት ማውጣታቸው ተገቢ
አለመሆኑን አቶ ተስፋሁን አለምነህ የመኢአድ አመራር ተናግረዋል።
አቶ ሽፈራው ሽጉጤ  የክልሉ ፕ/ት በነበሩበት ወቅት ያወጡት ህግ ለግጭቱ መንስኤ መሆኑ በወቅቱ ተዘግቧል። አቶ ሽፈራው ማንኛውንም ትእዛዝ የተቀበሉት ከአቶ መለስ መሆኑን ለቀረበባቸው ወቀሳ መልስ ሰጥተው ነበር። አቶ መለስ በህይወት ባይኖሩም አቶ ሽፈራው
ሽጉጤና ሌሎች የክልሉ ባለስልጣናት በክሱ አለመካተታቸው የክሱን ተአማኒነት ጥያቄ ውስጥ ጥሎታል።
“የዘር ማጥፋትን ክልከላና ቅጣት” በሚለው አለማቀፍ ደንጋጌ ፣ የዘር ማጥፋት ወንጀል የአንድን ብሄር፣ ብሄረሰብ፣ ዘር አባላትን ወይም የሃይማኖት ተከታዮች ሆን ብሎ በከፊል ወይም በሙሉ ማጥፋትን ወይም የማጥፋት ሙከራ ማድረግ፣  የአንድን ቡድን አባላት
መግደል፣ አካላዊ  ጉዳት ማድረስ፣ በህይወታቸው ላይ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል ጥፋት በከፊል ወይም በሙሉ መፈጸም የሚሉትን ወንጀሎች መቀመጣቸውን በመጥቀስ፣ በጉራፈርዳ የተፈጸመው ወንጀልም የዘር ማጥፋት ወንጀል መሆኑን ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ
የህግ ባለሙያ ገልጸዋል።
ከጉራፈርዳ የተፈናቀሉ ሰዎች የት አካባቢ እንደሰፈሩና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ በግልጽ አይታወቅም። የተወሰኑት ወደ መተማ አካባቢ ሄደው እንዲሰፍሩ ቢደረግም በውሃና በመሰረተልማት አቅርቦት ማነስ የተነሳ አብዛኞቹ አካባቢውን ለቀው ሂደዋል።

አንድነት ፓርቲ በምርጫ ቦርድ ላይ ያቀረበው ክስ ውድቅ ሆነ

መጋቢት ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፍርድ ቤቱ በሰጠው ውሳኔ ክሱን ያቀረቡት ወገኖች የአንድነት ፓርቲን በመወከል ክስ ሊያቀርቡ አይችሉም ብሎአል። ምርጫ ቦርድ ቀደም ብሎ ህወሃት ኢህአዴግ የሰጠውን የፖለቲካ ውሳኔ ማስፈጸሙን የገለጹት
የፓርቲው የቀድሞ አመራር አቶ አስራት ጣሴ፣  የዛሬው የፍርድ ቤት ውሳኔም ህግና ደንብን የጣሰ ነው ብለዋል።
የፓርቲው የስራ አስፈጻሚ አባላት አሁንም እንዳሉ የገለጹት አቶ አስራት ፣ ሁሉንም የፍርድ ቤት ሂደቶች ካጠናቀቁ በሁዋላ፣ ተቃውሞአቸውን በሌሎች መንግዶች ሊቀጥሉ እንደሚችሉ ገልጸዋል። አቶ አስራት ጣሴ አዲስ ፓርቲ የመመስረት ሃሳብ እንደሌላቸው ገልጸው፣
ትግሉን የሚወስነው የኢትዮጵያ ህዝብና በደሉ ነው ብለዋል። ህዝባዊ አመጽ አንድ የሰላማዊ ትግል መንገድ መሆኑን የገለጹት አቶ አስራት፣ ከዚህ በሁዋላ የሚመጣውን እስከ ሞት የሚደርስ መስዋትነት ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውን  ተናግረዋል።
አቶ አስራት ሰላማዊ ትግልን የማይቀበሉ ህዝባዊ አመጽን ይጋብዛሉ የሚባለው ትክክለኛ አባባል መሆኑን ገልጸው፣ ህውሃት ኢህአዴጎች ወደ ህሊናቸው ተመልሰው የተካረረውን ጉዳይ ወደ ውይይት እንዲወስዱት መክረዋል።
ገዢው ፓርቲ ፍትሃዊና ነጻ ምርጫ ያካሂዳል ብለው እንደማያምኑም አቶ አስራት አክለዋል

የሳንቲም ማጠራቀም ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው

መጋቢት ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድምጻችን ይሰማ ይጠራው የሳንቲም ማጠራቀም የተቃውሞ ሰልፍ በቀላልና በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ዘጋቢያችን ገልጿል። በአዲስ አበባ የተለያዩ የእስልምና እምነት ተከታዮችን አነጋግሮ እንደዘገበው በርካታ
ሙስሊሞች ሳንቲሞችን በማጠራቀም ተቃውሞአቸውን እየገለጹ ነው። አንድ መርካቶ አካባቢ የንግድ ድርጅት ያለው ግለሰብ  ” ንጹህ የሆኑ የሙስሊሙ መሪዎች ፍትህ አጥተው በእስር በሚማቅቁበት ወቅት፣ እኔ ከማገኘው ገቢ  የተወሰነውን ሳንቲም  ማጣራቀሜ ጥቅም
እንጅ ጉዳት የለውም፤ በሙሉ ደስታም እያደረኩት ነው ” ሲል፣ ሌላ ነጋዴ ደግሞ ” የቤተሰቡ አባላት መልእክቱን ተግባራዊ እያደረጉት ነው” ብሎአል።  ሌላው አስተያየት ሰጪ ደግሞ ሳንቲም የማጠራቀሙ ውጤት በሚቀጥሉት 2 ሳምንታት ሊታይ ይችላል ሲል አስተያየቱን
ሰጥቷል። ድምጻችን ይሰማ ሳንቲሞችን ከማጠራቀም በተጨማሪ ሌሎች ተጨማሪ እርምጃዎችን እንደሚወስድ መግለጹ ይታወቃል።

ማእከላዊ እስር ቤት ተቃዋሚዎችን ሊቀላቀሉ ሲሉ ተያዙ በተባሉ ሰዎች ተጨናንቋል

መጋቢት ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለፉት 8 ወራት ጀምሮ በማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ የታሰሩት እስረኞች አብዛኞቹ አርበኞች ግንቦት7 ትን ሊቀላቀሉ ሲሉ ተይዘዋል የሚል ክስ ሲመሰረትባቸው እስካሁን ድረስ ክስ ያልተመሰረተባቸው
በርካታ እስረኞች እንደሚገኙ ምንጮች ገልጸዋል።
የሰማያዊ ፓርቲ የአመራር አባላት ከሆኑት ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ ፍቅረማርያም አስማማውና እየሩሳሌም ተስፋው እንዲሁም የቀድሞው የአንድነት አመራር አባል የነበረው መሳይ ትኩና ሶስት የድርጅቱ አባላት፣ ከአብርሃ ጅራ፣ መተማ፣ ጎንደር፣ ባህርዳር እና አዲስ አበባ
የመጡ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን በማእከላዊ ታስረዋል።
በአንዳንዶቹ ላይ ለአርበኞች ግንቦት7 ሰዎችን ሲመለምሉና ወደ ኤርትራ ሲልኩ ነበር የሚል ክስ ሲቀርብባቸው፣ አንዳንዶቹ ደግሞ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች የአርበኞች ግንቦት7 ትን መረብ ( ኔትወርክ) ሲዘረጉ ነበር የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። ምንጮች እንደሚሉት
አንዳንድ ወታደራዊ ሃላፊዎችም ታስረው ከሚገኙት መካከል ናቸው። ቀድሞ ብሎ ከጋምቤላ ተይዘው የመጡት እስረኞች በማእከላዊ ከፍተኛውን ቁጥር ይዘው የነበሩ ቢሆንም፣ በአሁኑ ሰአት ከአርበኞች ግንቦት7 ጋር በተያያዘ እየታፈሰ የሚገቡት ሰዎች ማእከላዊን አጣበውታል።
የአየር ሃይል አባላት የሆኑት ዳንኤል ግርማ ፣ ማስረሻ ሰጠኝ፣ ገዛሃኝ ደረሰ እና ብሩክ አጥናባቸው በማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ ተደብድበዋል። ስማቸውን እስካሁን በትክክል ለማወቅ ባይቻልም፣ ከአብርሃ ጅራ አካባቢ የተያዙት አንድ የኢህአዴግ ወታደር
አመራር ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞበት ማእከላዊ ታስሯል። በቅርቡ ከዚሁ አካባቢ አርበኞች ግንቦት7ትን መንገድ መርተው ወደከተማ አስገብተዋል ተብለው የተያዙት ወደ ማእከላዊ ተዛውረዋል። ቀድሞ ብሎ የአብርሃ ጅራ የአንድነት ፓርቲ  አመራር አባላት አንጋው ተገኝ፣
አባይ ዘውዱና ሌሎችም ተመሳሳይ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸዋል።
መንግስት በሰሜን የአገሪቱ ክፍል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት አሰማርቶ እንደሚገኝ መዘገባችን ይታወቃል። አሁን እንደ አዲስ የተጧጧፈው ዘመቻም በአካባቢው የሚታየው ውጥረት የፈጠረው ሊሆን እንደሚችል ምንጮች ያክላሉ።
ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ የቀድሞው የአንድነት  አመራሪዎች አንዱአለም አራጌና ናትናኤል መኮንን፣ የመኢዴፓው ክንፈሚካኤል ደበበ ( አበበ ቀስቶ)፣ የሽዋስ አሰፋ፣ ሃብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሽበሺ እና ሌሎችም ታዋቂ ፖለቲከኞች ከግንቦት7 ጋር ሲሰሩ
ተገኝተዋል የሚል ክስ ተመስርቶባቸው በእስር ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

ፖሊሶች በግድግዳ ላይ የሚጻፉ ጽሁፎችን ተከታትለው እንዲያጠፉ ታዘዙ

መጋቢት ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በግድግዳዎች ላይ ተጽፈው የሚገኙ የተለያዩ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው ጽሁፎች በአስቸኳይ እንዲጠፉ  የደህንነትና ድርጅት ጉዳይ ጽ/ቤት ለአዲስ አበባ ፖሊስ ትእዛዝ ሰጥቷል። ፖሊሶቹ በግድግዳ ላይ የተጻፉ የነፃነትና የፍትህ ጥያቄዎችን  የሚያቀርቡ የግድግዳ ላይ ጽሁፎችን እግር በእግር ተከታትለው ማጥፋት እንዳለባቸው ተነግሯቸዋል፡፡ ትእዛዙን ተከትሎም የአዲስ አበባ ፖሊሶች በየቀጣናው እየተዘዋወሩ ጽሁፎችን በማጥፋትና በመደለዝ ስራ ላይ ተጠምደዋል፡፡ አንዳንድ ጽሁፎች በቀላሉ በማይጠፉ ቀለሞች የተጻፉ በመሆናቸው  ጽሁፎችን ለማጥፋት ፖሊሶች ሲቸገሩ ተስተውሎአል።

በአዲስ አበባ ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው የተቃውሞ ጽሁፎች በየጊዜው በግድግዳዎች ላይ እንደሚጻፉ ይታወቃል።