Pages

Monday, February 23, 2015

12 ፓርቲዎችን በዕጣ አልፋችኋል ለማለት ለ80 ፓርቲ ፈቃድ መስጠት ለምን አስፈለገ?›› ወይንሸት ሞላ


• ‹‹ከምርጫ ቦርድ የመጣ ትዕዛዝ ነው፡፡ መዝግቡ የተባልነውን መዝግበናል›› የምርጫ አስፈጻሚዎች
በአዲስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ሰማያዊ ፓርቲን ወክላ ለተወካዮች ምክር ቤት በዕጩነት ቀርባ የነበረችው ወይንሸት ሞላን ጨምሮ ሌሎችም አዲስ አበባ ውስጥ ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው ለተወካዮች ምክር ቤት በዕጩነት የቀረቡ ዕጩዎች ‹‹ዕጣው ስላልደረሳችሁ አትወዳደሩም›› መባላቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ከወይንሸት ሞላ በተጨማሪ ብሌን መስፍንና አማኑኤል አዱኛ የተባሉ የሰማያዊ ዕጩዎች ‹‹ዕጣው አልደረሳችሁም›› ተብለው ከዕጩነት ውጭ ሆነዋል፡፡
ወይንሸት ሞላ
ወይንሸት ሞላ ‹‹ዕጣው አልደረሰሽም›› በተባለችበት የምርጫ ጣቢያ የክልል ፓርቲዎችን የወከሉ ዕጩዎች አልፈዋል የተባሉ ሲሆን ወይንሸት ‹‹የክልል ፓርቲዎች ድምጽ ያሰባሰቡት በየክልሉ እንጅ አዲስ አበባ አይደለም፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ደግሞ ሐገራዊ ፓርቲ ነው፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ መራጭ የሌላቸው ፓርቲው በዕጣ አለፉ ተብሎ ሐገራዊ ፓርቲ የሆነው ሰማያዊ ወድቋል መባሉ ያለንበትን ስርዓት በድንብ የሚያጋልጥ ነው፡፡›› ስትል ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጻለች፡፡
በወረዳ 7 17 ፓርቲዎችን የወከሉ ዕጩዎች የቀረቡ ሲሆን 12 ያለፉ ሲሆን ሰማያዊን ጨምሮ ሌሎች አምስት ፓርቲዎች ‹‹ዕጣው አልደረሳችሁም›› ተብለዋል፡፡ በወቅቱ ወይንሸት ሞላ ለምርጫ አስፈጻሚዎች ‹‹12 ፓርቲዎችን በዕጣ አልፋችኋል ለማለት ለ80 ፓርቲ ፈቃድ መስጠት ለምን አስፈለገ?›› የሚል ጥያቄ ያቀረበች ሲሆን የምርጫ አስፈጻሚዎችም ‹‹ይህ ከምርጫ ቦርድ የመጣ ትዕዛዝ ነው፡፡ መዝግቡ የተባልነውን ነው የመዘገብነው›› የሚል መልስ እንደተሰጣት ገልጻለች፡፡
ወይንሸት ሞላን ጨምሮ ሌሎች የሰማያዊ ዕጩዎች አትወዳደሩም ተባሉ
• ‹‹12 ፓርቲዎችን በዕጣ አልፋችኋል ለማለት ለ80 ፓርቲ ፈቃድ መስጠት ለምን አስፈለገ?›› ወይንሸት ሞላ
• ‹‹ከምርጫ ቦርድ የመጣ ትዕዛዝ ነው፡፡ መዝግቡ የተባልነውን መዝግበናል›› የምርጫ አስፈጻሚዎች
በአዲስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ሰማያዊ ፓርቲን ወክላ ለተወካዮች ምክር ቤት በዕጩነት ቀርባ የነበረችው ወይንሸት ሞላን ጨምሮ ሌሎችም አዲስ አበባ ውስጥ ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው ለተወካዮች ምክር ቤት በዕጩነት የቀረቡ ዕጩዎች ‹‹ዕጣው ስላልደረሳችሁ አትወዳደሩም›› መባላቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ከወይንሸት ሞላ በተጨማሪ ብሌን መስፍንና አማኑኤል አዱኛ የተባሉ የሰማያዊ ዕጩዎች ‹‹ዕጣው አልደረሳችሁም›› ተብለው ከዕጩነት ውጭ ሆነዋል፡፡
ወይንሸት ሞላ ‹‹ዕጣው አልደረሰሽም›› በተባለችበት የምርጫ ጣቢያ የክልል ፓርቲዎችን የወከሉ ዕጩዎች አልፈዋል የተባሉ ሲሆን ወይንሸት ‹‹የክልል ፓርቲዎች ድምጽ ያሰባሰቡት በየክልሉ እንጅ አዲስ አበባ አይደለም፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ደግሞ ሐገራዊ ፓርቲ ነው፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ መራጭ የሌላቸው ፓርቲው በዕጣ አለፉ ተብሎ ሐገራዊ ፓርቲ የሆነው ሰማያዊ ወድቋል መባሉ ያለንበትን ስርዓት በድንብ የሚያጋልጥ ነው፡፡›› ስትል ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጻለች፡፡
በወረዳ 7 17 ፓርቲዎችን የወከሉ ዕጩዎች የቀረቡ ሲሆን 12 ያለፉ ሲሆን ሰማያዊን ጨምሮ ሌሎች አምስት ፓርቲዎች ‹‹ዕጣው አልደረሳችሁም›› ተብለዋል፡፡ በወቅቱ ወይንሸት ሞላ ለምርጫ አስፈጻሚዎች ‹‹12 ፓርቲዎችን በዕጣ አልፋችኋል ለማለት ለ80 ፓርቲ ፈቃድ መስጠት ለምን አስፈለገ?›› የሚል ጥያቄ ያቀረበች ሲሆን የምርጫ አስፈጻሚዎችም ‹‹ይህ ከምርጫ ቦርድ የመጣ ትዕዛዝ ነው፡፡ መዝግቡ የተባልነውን ነው የመዘገብነው›› የሚል መልስ እንደተሰጣት ገልጻለች፡

Zone 9 bloggers ridicule 'terror' charge, plead not guilty

Defendants in the Zone 9 case blasted the prosecution's terror charge for lack of clarity as they enter a plea of not guilty on Wednesday.

As the case crawls to trial, each of the nine defendants were asked by the three panel judges of the 19th criminal bench of the Federal High Court to enter a plea of guilty.
The bloggers and journalists, who remain in custody since April 2014, took turns to contest the prosecution's charge which accuses them of causing "serious risk to the safety or health of the public or section of the public" and "serious damage to property" under the anti-terrorism proclamation.
"From the reading of the charge it appears I am being accused of terrorism. But an act of terror has been committed against me and not the other way round," Befeqadu Hailu, second defendant, told the court.
"If this was a country where rule of law prevails, it would have been my accusers who should have been in my place," followed Natnael Feleke.
The judges then intervened to reprimand the defendants to observe the legal procedure and avoid making such statements and simply enter a plea of guilty or not guilty.
But the defendants continued to criticize the charge which they said lacked clarity.
"I could not understand what I am specifically being accused of and so it is impossible for me to enter a plea. I ask the court to help me understand the charge," Zelalem Kibret, who was a law instructor at Ambo University prior his arrest, said.
The defendants include three journalists - Tesfalem Waldyes, Asmamaw Hailegiorgis and Edom Kassaye, - who all protested their innocence.
"I am a journalist and journalism is not a crime," said freelance journalist Tesfalem who had worked for the English weekly Fortune newspaper and English monthly magazine Addis Standard.
Judges said the defendant's statements are taken as a plea of not guilty and adjourned the case for March 30. The court will reconvene to hear prosecution witnesses, numbering around 30, for three consecutive days.
Two weeks ago, defendants appealed for the presiding judge Sheleme Bekele to be removed stating that they do not believe he would be fair. Although their motion was rejected by the other two judges, Judge Sheleme said he had withdrawn on his own accord. However, the judge returned on Wednesday.
Before moving on to the plea, one of the judges explained that the request of the presiding judge to be withdrawn is matter which will be addressed by the administrative wing of the court.
The hearing also saw another complaint lodged against the Addis Ababa Prison Administration by the two female defendants - Edom and Mahlet Fantahun - regarding visitation rights. A third female defendant, Solyana Shimeles is tried in absentia.

The female defendants, who are detained at Kality, accused the prison administration of restricting visitation hours and number of visitors who may visit them. They court had ordered the prison administration to respond to the accusations in writing before February 25.

Ethiopians deserve a free press

February 20, 2015
(The Washington Post) The Feb. 9 editorial “Ethiopia’s stifled press” raised fundamental issues of human rights, democracy and governance. The journalists and bloggers languishing in prison committed no crime except to criticize the ruling party.Ethiopians deserve a free press
If the government of Ethiopia is concerned for its citizens, as a spokesman asserted in a Feb. 13 letter [“The Ethio­pian government’s duty is to protect all of its citizens”], it should respect the rights and views of journalists and civilians who oppose its policies. It is repressive to block popular Web sites and broadcasts, such as Voice of America, that provide an alternative to government-controlled media.
Ethiopians should have the right to voice their concerns about their country’s affairs. Private, independent media outlets facilitate the venue for an open discourse. The government’s persistent attack on press freedom, therefore, will only exacerbate the people’s anguish. No government is perfect. Those who use pens to expose the imperfections should not be subjected to abuse and persecution.
All jailed journalists and bloggers — and many others who are incarcerated for speaking against repression and injustice in Ethi­o­pia — should be freed. It will be one small step on a long democratic journey.
Tewodros Abebe, Accokeek

በጨለለቅቱ ከተማ በተነሳ ግጭት አንድ ሰው ሲሞት በርካቶች ቆሰሉ

የካቲት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በጌዲዮ ዞን በኮቾሬ ወረዳ ጨለለቅቱ ከተማ ሃሙስ የካቲት 12 ቀን 2007 ኣም ከቀኑ 11 ሰአት ላይ በተነሳው ግጭት አንድ ሰው ሲሞት ከ10 በላይ የሆኑ ደግሞ ቆስለው ዲላ ሆስፒታል በመታከም ላይ ናቸው። በከተማዋ ያሉ በርካታ ሱቆች ተዘርፈዋል፣ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎም ተነስቷል። የፌደራልና የዞኑ ፖሊስ ወደ ከተማዋ በማምራት ግጭቱን ማብረዳቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ፖሊሶቹ አሁንም በከተማዋ በብዛት እንደሚገኙና ውጥረት እንዳለ ነዋሪዎች ይገልጻሉ።
ግጭቱ በሁለት ሰዎች መካከል እንደተነሳ የሚገልጹት ነዋሪዎች፣ ግጭቱ መልኩን ቀይሮ ” መጤዎች” የተባሉትን ነዋሪዎች ወደ መዝረፍና መደብደብ ማምራቱን ይናገራሉ። በ1998 ኣም ተከስቶ እንደነበረው የወረዳው አስተዳዳሪዎች ሆን ብለው አስነስተውታል የሚሉት ነዋሪዎች፣ ለዚህም በምክንያትነት የሚያቀርቡት ከምርጫው ጋር ተያይዞ በአካባቢው ያሉ ተቃዋሚዎች በስፋት መንቀሳቀሳቸው ነው። ተቃዋሚዎችን ግጭት በማስነሳት ለመክሰስና በህዝቡ ውስጥ ሽብር በመፍጠር አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት የቀዩሰት ዘዴ ነው በማለት የባለስልጣኖችን ድርጊት ኮንነዋል።
በአካባቢው ባሉ ወረዳዎችም ተመሳሳይ ግጭት ሊነሳ ይችላል በማለት ነዋሪዎች ስጋታቸውን ገልጸዋል። በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስት ባለስልጣናትን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

በግንባታ ዘርፍ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እየተዘረፈ ነው

የካቲት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪ ልማት ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ሃይሌ ከስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሺን አጣሪ ቡድን ጋር ባደረጉት ውይይት ከመንገድ ስራ ፣ ከባቡር መስመር ዝርጋታና፣ ከቤቶች ልማት ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዘ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እየተዘረፈ መሆኑን አምነዋል።
የፀረ ሙስና ኮሚሽን ባካሄደው ጥናት በባቡር መስመር ግንባታ 2.3 ኪሜ የባቡር ሃዲድ መስመር በሙስና ምክንያት ከደረጃ ውጭ እንዲሆን በመደረጉ የ124 ሚልዮን በር ኪሳራ ደርሷል።  የአደጋ መከላከያ ብረቶች የተሰሩት  ከወጣላቸው የጥራት ደረጃ በሶስት እጅ ያነሱ ሆነው በመገኘታቸው ጉዳዩ  ለቦርድ ሰብሳቢው ዶ/ር አርከበ እቁባይ ቢቀርብም ምላሺ ሰይሰጠው በመቅረቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ  የት እንደገባ ማወቅ አለመቻሉን ገልጿል።
የስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሺን ያቀረበውን ሪፖርት ተከትሎ ምላሺ የሰጡት ሚኒስትር መኩሪያ ሃይሌ ፣ ችግሩ የተፈጠረው ለምርጫው ሲባል የባቡሩ ግንባታ እንደ ትልቅ የምርጫ ማሰመኛ በመያዙ ነው ።
የግንባታ ኢንዱስትሪው ከሚያወጣው ወጪ  ከ30 እስከ 60 በመቶ የሚሆነው  በሙስና ይባክናል ሲሉም ሚኒስትሩ አክለዋል።
በተመሳሳይ ዜናም በአማራ ክልል በመንግሥት በጀት እየተከናወኑ ያሉ ግንባታዎች የጥራትና በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ ያለመጠናቀቅ ችግር አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች በምሬት ተናግረዋል።
ሰሞኑን በባህርዳር ከተማ የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ከህንፃ ተቋራጮችና ሙያተኞች ጋር ባደረገው ውይይት የግንባታ የጥራት ችግር ምክንያቱ ተቋራጮች በቤተ ሙከራ ባልተፈተሸና እውቅና ባልተሰጣቸው ቁሳቁስ ግንባታ በመፈፀማቸው እና የመንግስት አካላትም የራሳቸውን ድርሻ በማንሳቱ ረገድ ከፍተኛ ሩጫ በማድረጋቸው እንደሆነ ተወስቷል::
የህንፃ ተቋራጭ የሆኑት አቶ አረጋይ  ወልደ ፋኑኤል  ግንባታዎች ተሰርተው መጠናቀቃቸውን ያበሰረው ዜና በደንብ ተደምጦ ሳይጠናቀቅ መርዷቸው ይደርሳል:፣ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ በአሰሪ መስሪያ ቤቶችና በተቋራጮች መካከል የሚፈጠረው “የእከከኝ ልከክልህ” የአሰራር ሰንሰለት አለመበጠስ ነው ብለዋል።
አቶ አረጋይ “የአገር ሀብት ተቆጣጣሪና ‘ሀይ ባይ’ በማጣቱ ለዘራፊዎች እየተዳረገ ነው:: የህዝብ ሀብት የሆኑት ግንባታዎች እየፈረሱ ነው:: የህዝብ ፍላጐትን የሚያሟላለት እየጠፋ ነው:: ዋናው ስጋት ደግሞ የሚገነቡት ህንፃዎች ጥራት መጉደል ጋር ተያይዞ ቀጣይ የሰው ህይወት የማያጠፉበት ምክንያት አይኖርም” በማለት ተናግረዋል፡፡
አቶ አረጋይ “ዛሬ ባለ ገንዘብ እናንተ ናችሁ ሆኖም ገንዘብ ቢኖራችሁም የስልጣን መንበሩን የያዛችሁት ህዝቡን እንድታገለግሉ ተሾማችሁ እንጅ እንደፈለጋችሁ በማድረግ ህዝቡን ገደል ግባ ማለት የለባችሁም፡፡”በማለት የተናገሩ ሲሆን በራሳቸው በኩል ያለውን አቋም ሲገልጹ “አኔ ኢምንት ታህል ገንዘብ አልሰጥም ፡፡ሰርቄ መስራት አልፈልግም፡፡አሁንም ሰርቄ ልጫረት አልችልም ፡፡ካሻሻላችሁ ተሻሽየ እቀርባለሁ ፡፡ካላሻሻላችሁ ግን ወደ ጨረታው አልቀርብም ፡፡ከአሁኑ ሰዓት ጀምራችሁ ወስዳችሁ እሰሩኝ ፡፡” በማለት በድፍረት ተናግረዋል፡፡
አቶ አረጋይ “ከረሜላና ሳሙና ሲሸጡ የነበሩ ኮንትራክተር በመባል የሚጠሩበት ጊዜ ምናለ ቢበቃ” በማለት የተማጽኖ ጥያቄ አቅርበዋል።
በህንፃና የመንገድ ግንባታዎች ውስጥ በተቆጣጣሪ መሀንዲስነት ላለፉት 10 አመታት ያገለገሉት አቶ አህመድ ሲራጅ :በተለይ በመንገድ ግንባታ በቆዩባቸው አምስት አመታት ያስተዋሉትን ስርቆትና ብልሹ አሰራን ለማጋለጥ ሲሞክሩ  ከስራ ገበታቸው እስከመነሳት ደረጃ መድረሳቸውን ተናግረዋል።
ሁኔታውንም ለከፍተኛ ባለስልጣናት ቢያሳውቁም “መጀመሪያውንም ተግባብተህ አትሰራም ነበር፤ ነገር ማመላለስ ደመወዝህ ነው” እንደተባሉ ተናግረዋል።
እንደ ክልሉ ኦዲት ባለስልጣን ሪፖርት በአማራ ክልል የሚታየው የግንባታ መጓተትና የጥራት ችግር አሳሳቢ በሚባል ደረጃ በመድረሱ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር የአገር ሀብት ለምዝበራ እየተጋለጠ ነው:: በአሁኑ ወቅት 354 ፕሮጀክቶች በግል የስራ ተቋራጮች በግንባታ ላይ ሲሆኑ፣  ከ43  በላይ ፕሮጀክቶች ግንባታቸው ተቋርጧል:: ከ129 በላይ የሚሆኑት ደግሞ በከፍተኛ መጓተት ላይ ይገኛሉ:: በዚህ ሁሉ ችግር የገዢው መንግስት ባለስልጣናት የወሰዱት እርምጃ አለመኖር ምዝበራው ቀጣይነት ያለው መሆኑን እንደሚያመላክት የክልሉ ዘጋቢያችን ገልጻለች።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ማደሪያ እንደ አልቤርጎ እየተከራየ ነው

የካቲት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከ2 ሺ 700 በላይ የተማሪዎች ማደሪያ አልጋዎች ለተመላላሽ ተማሪዎችና ለማይታወቁ ሰዎች እየተከራዩ መሆኑ ታውቓል።
በቅርቡ በአክሱም ከተማ በተካሄደው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማዊ ለውጥ ምክርቤት ጉባዔ ላይ ጉዳዩ በይፋ የተነሳ ሲሆን በአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ከ750 በላይ የተማሪዎች ማደሪያ ክፍሎች ውስጥ የሚገኙ ከ2ሺ 700 በላይ አልጋዎች በድብቅ ሲከራዩ ቆይተዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በተመላላሽ ተማሪነታቸው የሚያውቃቸው ተማሪዎችና ማንነታቸው የማይታወቁ ግለሰቦች በወር ለአንድ አልጋ 400 ብር ሒሳብ እየከፈሉ እንደሚጠቀሙባቸው መረጋገጡን ጠቅሰዋል፡፡ በዚህ መሰረት በወር  ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ የሆነ ገንዘብ በሙስና ይበላል።
በውይይቱ ወቅት የዩኒቨርሲቲው አንዳንድ  አመራሮች ነገሩን ክደው የተከራከሩ ቢሆንም በመጨረሻ ግን  እውነታውን ለመግለጽ ተገደዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲው የተገኘው የማደሪያ ክፍሎች ቁጥር፤ ማደሪያ የለም ተብለው ከሚመላለሱ ተማሪዎች ቁጥር ጋር ተቀራራቢ ሆኖ መገኘቱም በዚሁ መድረክ ይፋ ሆኖአል፡፡
ይህ ዓይነቱ ሙስና  በሌሎችም የመንግስት ዩኒቨርሲዎች ከመለመዱ የተነሳ እንደሕጋዊ አሰራር እየታየ መምጣቱንም በውይቱ ወቅት ተነስቷል።

የአማራ ክልል ነዋሪዎችን ትጥቅ የማስፈታቱ ሂደት እንደቀጠለ ነው

የካቲት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ አሰተዳደር እና ፀጥታ ቢሮ መረጃ እንደሚያሳየው በክልሉ በሚካሄደው ትጥቅ የማስፈታት ሂደት በሰሜን ጎንደርና በምእራብ ጎጃም ዞኖች ብቻ 2 ሚሊዮን 13 ሺ 497 ልዩ ልዩ የጦር መሳሪያዎችና ጥይቶች ለክልሉ ሚሊሺያ ጽ/ቤት ገቢ ተደርጓል።
የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፀጥታ ጉዳዩች መምሪያ ኃላፊው አቶ ደጀኔ ሽባባው በጽ/ቤቱ የ2ዐዐ7 በጀት ዓመት ግማሺ አመት ሪፖርት ላይ እንዳመለከቱት ደግሞ ጽ/ቤቱ የጦር መሣሪያዎችን ዝውውር ለመቆጣጠር እና ለመግታት ባደረጋቸው እንቅስቃሴዎች 17ዐ የተለያዩ የጦር መሣሪያዎችን 3ሺ 635  ልዩ ልዩ ጥይቶችን እና 21 ቦንቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።
በቅርቡ በቀበሌ 16 በአንድ ግለስብ ቤት 21 ክላሺንኮቭ ጠመንጃ መገኘቱንም ተናግረዋል፡፡ በክልሉ የሚገኙ የካቢኔ አባላት ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ 8 ሺ 429 የወገብ ሺጉጥ ታጥቀው እንደሚገኙም የክልሉ ሚልሻ ጽ//ቤት መረጃ ያሣያል፡፡
በክልሉ ከ5 ሚሊዮን 5 መቶ ሺ ያላነሱ ጠመንጃዎች፣ ጥይቶችንና የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በግለሰቦች እጅ እንደሚገኝ ከጽ/ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።  በርካታ የክልሉ ነዋሪዎች የጦር መሳሪያችሁን አስረክቡ እየተባሉ እንደሚታሰሩ፣ እንደሚገረፉና ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣትም እንደሚጣልባቸው ይታወቃል።

የሰማዕእታት ቀን 78ኛ አመት ታስቦ ዋለ።

የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የወራሪው  የጣሊያን  ሰራዊት  በጦር  አዛዡ  ፊልድ  ማርሻል  ሮዶልፎ  ግራዚያኒ  አማካኝነት 30  ሺህ  ኢትዮጰያውያንን  በግፍ  የጨፈጨፈበት  78ኛ  ዓመት  ዛሬ  በመላው  ኢትዮጰያውያን  ዘንድ  በመተሳብ  ላይ  ነው።
በኢትዮጵያና  ከኢትዮጵያ  ውጭ  የሚኖሩ  ዜጎች ፣ የጣሊያን  ወራሪ  ሃይል  በንጹሃን  ኢትዮጵያውያን ላይ  የፈጸመውን  አስከፊ  ጭፍጨፋ የሚያስታውሱ  ጽሁፎችን  በመልቀቅ  እለቱን  ዘክረውታል።

አቶ አባይ ወልዱ የህወሃት ክንፍ እንዲፈጠር ከሳሞራ ጋር አሲረዋል በሚል ተገመገሙ

የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቤተመንግስት ትንሹ አዳራሽ ውስጥ የተካሄደውን የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ግምገማ የሚቃኘው መረጃ እንደሚያሳየው የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አባይ ወልዱ የህወሃት ክንፍ እንዲፈጠር ከመከላከያ ኢታማጆር ሹም ሳሞራ የኑስ ጋር ማሴራቸው በሌሎች የኢህአዴግ አባላት ሂስ ቀርቦባቸዋል። አቶ አባይ ወልዱ የቀረበባቸውን ሂስ በደፈናው ተቀብያለሁ፣ አርማለሁ በማለት መመለሳቸውን ሰነዱ ያስረዳል።
አቶ አባይ ግለሂሳቸውን እንዲያወርዱ ሲጠየቁ የስራ ሰአት የማክበር ችግር እንዳለባቸው፣ ከአሉባልታ ወሬ ጋር በተያያዘ ችግር እንዳለባቸውና በ1 ለ5 አደረጃጃት እንደማይሳተፉ ተናግረዋል።
በምክር  ቤቱ  የተሰበሰቡት ባልደረቦቻቸው  በበኩላቸው ” አስተያየት የመቀበል ችግር አለብህ፣ በረባ ባልረባው ከስራ ገበታህ ትቀራለህ፣ ችግሮችን በውይይት የመፍታት እጥረት አለብህ፣ የሰራሃውን ስራ በጊዜ የማምጣት ችግር አለብህ፣ ህጎችን የማክበር ችግር ይታይብሃል” በማለት ገምግመዋቸዋል። አቶ አባይ በአጠቃላይ ግምገማየ ” ቢ” ውጤት ማግኘታቸውም በሰነዱ ተመልክቷል።
የጠ/ሚኒስትሩ የጸጥታ አማካሪ የሆኑት የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕ/ት ጸጋየ በርሄ ደግሞ ” የማሳቀድ ውስንነት አለብኝ፣ በንባብ ራስን የማብቃት እጥረት አለብኝ፣ በጥራት የማሰራት እጥረት አለብኝ” በማለት ግለ-ሂሳቸውን ሲያወርዱ ወይም ራሳቸውን ሲገመግሙ፣ ጓደኞቻቸው ደግሞ ” ሞጋች የሆኑ ነገሮችን ያለመንካት ችግር አለብህ፣ አስተባብሮ የመስራት እጥረት አለብህ፣ ሌሎችን አሳቅዶ የመስራት እጥረት አለብህ፣ ሰአት አታከብርም፣ ውሳኔ የመስጠት ችግር አለብህ፣ የክትትልና ቁጥጥር እጥረት ይታይብሃል” በሚል ሂስ ሰጥተዋቸዋል።
አቶ ጸጋየ ለቀረበባቸው አስተያየት ተቀብየዋለሁ ያሉ ሲሆን በስራቸውም “ቢ” ተሰጥቷቸዋል።
ዶ/ር ካሱ ኢላላ በበኩላቸው የማንበብ እጥረት አለብኝ በማለት ራሳቸውን የገመገሙ ሲሆን፣ ሎሎች ባልደረቦቻቸው ደግሞ ” የስልክ አጠቃቀም ችግር አለብህ፣ ወሬ የመስማት፣ የማኩረፍ ችግር አለብህ፣ የቢሮ ስነምግባር አለማክበር ይታይብሃል፣ ፈሪ ነህ፣ ግንባር ቀደም አይደለህም፣ ሰርቶ የማሰራት እና የመምራት ችግር አለብህ፣ ለተተኪዎች አይንህ ደስተኛ አይደለም” በሚል ተገምግመዋል፤፡ ዶ/ር ካሱ ኢላላ ሂሱን መቀበላቸውን ገልጸው ፣ ሲ ውጤት ተሰጥቷቸዋል።
አቶ አርከበ እቁባይ ደግሞ በቁጭትና በእልህ የመስራት እጥረት አለብኝ፣ ስራን አድምቶ የመስራት እጥረት አለብኝ፣ ሰአት ማክበር፣ በቡድን መስራት ላይ ውስንነቶች አሉብኝ በማለት ራሳቸውን የገመገሙ ሲሆን፣ ሌሎች ጓደኞቻቸው ደግሞ ስራን የማዘግየት ችግር አለብህ፣ ከስራ ባልደረቦች ጋር ተግባብቶ የመስራት ችግር አለበት፣ ነገሮችን አግዝፎ የማየት፣ ቂመኛነት አለበት፣ ለችግሮች መፍትሄ የመሻት እጥረት አለብህ፣ ግጭትን ያለማርገብ ችግር አለብህ” በሚል ተገምግሟል።
የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳ አቅዶ የመስራት ክፍተት አለብኝ፣ ራስን በማያቋርጥ የንባብ ባህል የማብቃት እጥረት አለብኝ በማለት ራሳቸውን የገመገሙ ሲሆን፣ ባልደረቦቻቸው ደግሞ ” በንባብ ራስን የማብቃት ችግር አለብህ፣ አሳምኖ የማሰራት እጥረት አለብህ፣ ለሌሎች ሀሳብ የመስጠት ቁጥብነት አለብህ፣ ያለህን እውቀት ለሌሎች የማጋራት እጥረት አለብህ፣ ሳሞራን ትፈራዋለህ፣ በሚኒስቴር መስሪያ ቤትህ ያለው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ደካማ ነው” በሚል ተተችተዋል።
አቶ ሲራጅ መከላከያ ውስጥ ያለው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ደካማ መሆኑን ፣ ችግሩ በመስሪያ ቤቱ ብቻ ሳይሆን በጦሩም እንደሚታይ ገልጸው፣ አደረጃጀት ለመፍጠር ቢሞክሩም የሚተባበራቸው አመራር ማጣታቸውን፣ ከሳሞራ ጀምሮ ሃይለማርያምም እንደሚያውቅ ” ተናግረው፣ ሌሎች የተነሱት ሃሳቦች ገንቢ ናቸው፣ ተቀብያቸዋለሁ ብለዋል።
የኦሮምያ ም/ል ፕ/ት የሆኑት ወ/ሮ አስቴር ማሞ በበኩላቸው “የስራ ሰአት እሸራርፋለሁ፣ ስሜታዊነት አለብኝ፣ በአንድ ለአምስት ላይ ክፍተት አለብኝ” በማለት ራሳቸውን የገመገሙ ሲሆን፣ ሌሎች የምክር ቤት አባላት ደግሞ ” ተግባብቶ የመስራት እጥረት አለብሽ፣ ከስራ ማርፈድ ፣ መቅረት አለብሽ፣ የቢሮ ሰአት አታከብሪም፣ ትሸራርፊያለሽ፣ ከባልደረቦችሽ ጋር ትጋጫለሽ፣ በቢሮው ውስጥ ሶስት የአካባቢሽን ልጆች አዲስ አበባ በአጠቃላይ ዘጠኝ የሚደርሱ በሚኒስትር ቢሮዎች በሹመት እንዲመጡ አድርገሻል ” የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።
ወ/ሮ አስቴር ሰዎቹ የመጡት በእርሳቸው ትእዛዝ መሆኑን፣ ነገር ግን ሰዎቹ ከአቅም በታች ናቸው ማለት እንደማይቻልና፣ ሁላችንም በተመሳሳይ መንገድ በችሎታቸው ያመጣናቸው አሉ ሲሉ ተከላክለዋል።
የገንዘብ ሚኒስትሩ ሶፍያን አህመድ ደግሞ ስራን በፍጥነት የመፈጸም እጥረት አለብኝ ብለው ራሳቸውን ሲገመግሙ፣ ሌሎች ባልደረቦቻቸው ደግሞ “ከደባል ሱስ የጸዳህ ብትሆን፣ ስራ ያዘገያል፣ ስራን ለነገ ባትል፣ ራስህን ከሌሎች ማራቅህ ብተተው” በሚል ገምግመዋቸዋል።
የሴቶችና የወጣቶች ሚኒስትር ወ/ሮ ዘነቡ ታደሰ በበኩላቸው የስራ ሰአት መሸራረፍ አለብኝ፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰፊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የታቀደውን ያህል አልሰራሁም በሚል ስለድክመታቸው ሲናገሩ፣ ሌሎች የምክር ቤት አባላት በበኩላቸው ” ለኢህአዴግ ተልእኮ አስፈላጊ ነገሮችን ጠይቆ ማሟላት ላይ እጥረት አለብሽ፣ ይሉንታ ያጠቃሻል፣ ሴቶች ተሳትፎ ስራው ላይ እንዲሻሻል የጎላ ድርሻ አልተወጣሽም ፣ ክፍት ሚኒስቴር ነው ማለት ይቻላል፣ የሃሰት አፈጻጸም እና ሪፖርት ታቀርቢያለሽ” በሚል ገምግመዋታል። ወ/ሮ ዘነቡ “የተሰጠኝ አስተያየት ገምቢ ነው ወደ ፊት አየዋለሁ፣ ሂሱን ወስጀዋለሁ” ብለዋል።
ሽፈራው ሽጉጤ ደግሞ “የስራ ሰአት አለማክበር ብቻ ሳይሆን ትቀራለህ፣ ስብሰባ ላይ አትገኝም፣ አማራን ባስወጣህበት የደቡብ ክልል መስተዳደር ጊዜህ ለክልሉ ነዋሪዎች ነፍጠኛ ከኛ ይወገዳል ብለህ ተናግረሃል” በሚል ከብአዴን ተወላጆች አስተያየት ቢሰጥም፣ አቶ ሽፈራው ” ከጠ/ሚኒስትሩ የተሰጠኝን ተልእኮ ነው በአግባቡ የተወጣሁት፣ ሌላ አልጨመርኩም አላስወጣሁም” ብለው መልሰዋል።
የአማራ ክልል ም/ል ፕሬዚዳንት እና የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አለምነው መኮንን ” የመለስን ቦታ የመተካት ህልም አለህ፣ የስልጣን ጥመኝነት አለብህ፣ የድርጅቱን ህልውና አደጋ ላይ በሚጥል መልኩ ተንቀሳቅሰሃል፣ ከመለስ ውጭ ሌላው የሞተ ነው ብለህ ተናግረሃል፣ ሆን ብለህ ለኢሳት መረጃ እንዲደርስ ታደርጋለህ፣ የብሄሮችን እኩልነት አትቀበልም፣ የስልጣን ሰንሰለት በጎጠኝነት መስርተሃል፣ አጉል ጀብደኝነት አለብህ” ተብለው ሲገመገሙ፣ እርሳቸው ግን ከተሰጠኝ ተልእኮ ውጭ አልተንቀሳቀስኩም፣ ነገሩን አጣመው የሚያቀርቡ ሰዎች አሉ በማለት በብሄር እኩልነት አታምንም በተባሉት ላይ ከረር ያለ መልስ ሰጥተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ደግሞ “በእቅድ ላይ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ላይ ስኬታማ አይደለሁም፣ የስራ ሰአት አከባበር ችግር አለብኝ” ብለው ራሳቸውን የገመገሙ ሲሆን፣ ሌሎች ደግሞ ” ስራን የማዘግየት ችግር አለበት፣ በማህበራዊ ሚዲያ የግለሰቦችን ታሪክ ለራሱ ገጽታ ግንባታ አውላል፣ ለአብነትም ከአረብ አገራት የተመለሱ ሰዎችን፣ ከተሰጠው ተልእኮ ውጭ ይንቀሳቀሳል” ብለዋቸዋል። ዶ/ር ቴዎድሮስ ሂሱን እንደማይቀበሉት የቃለ ጉባኤ ሰነዱ ያሳያል።
የአፋር ክልል ፕሬዚዳንት እስማኤል አሊ ሴሮ ” የንባብ ባህል እጥረት አለብኝ” ብለው ራሳቸውን ሲሄሱ፣ ሌሎች ደግሞ አርፍዶ የመግባት፣ ፈጥኖ የመውጣት ነገር ይታይበታል፣ እቅድ እና ቅድመ ዝግጅት ላይ እጥረት አለበት፣ ሰአት አለማክበር ይታይበታል” ብለዋቸዋል።
ደግሞ “ጥራት ያለው ስራ መስራት ላይ እጥረት አለብኝ፣ የንባብ ባህል ችግር አለብኝ፣  አንድ ለአምስት ላይ ብዙም ንቁ ተሳትፎ አላደረኩም ” ብለው ራሳቸውን የገመገሙ ሲሆን፣ ሌሎች ደግሞ በክልሉ ውስጥ ችግር ሲከሰት ለመፍታት አትሞክርም፣ አሉባልተኝነት ላይ ራስህን በደንብ ብታይ ” ተብለዋል።
የፌደራል ሚኒስትሩ ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም በበኩላቸው ” ጥራት ያለው  ስራ እሰራለሁ ብየ አላስብም፣ የንባብ ባህል ላይ ችግር አለብኝ፣ ሰአት እሸራርፋለሁ” ብለው ሰለራሳቸው ድክመት ከተናገሩ በሁዋላ፣ ሌሎች ደግሞ ” ስራ ሲታዘዝ እገሌ ሳይሰራ የማለት ባህሪ አለው ቢያስተካክል፣” ብለው ሲገመግሙዋቸው . ዶ/ር ሽፈራው አልቀበለውም ብለዋል። ጉዳዩ እንደገና ይታይ የሚል ከቤቱ አስተያየት በመቅረቡ ” ሌሎች እንደገና ” የባህሪ ቁጡነት ይታይብሃል፣ አንድ ለአምስት አዘውትረህ አትሳተፍም፣ ይሉንታ አለብህ፣ አሁንም በከፍተኛ ደረጃ ያለውን አክራሪነት መቆጣጠር አልቻልክም” የሚል ሂስ አቅርበዋል። ዶ/ር ሽፈራው ” ማህበረ ቅዱሳንን መንካት መሞት መሆኑን ሁላችንም እናውቃለን፣ ከሱ ውጭ ያለውን ግን እየሰራሁ ነው።” ብለው መልስ ሰጥተዋል። አንዳንድ ሂሶችን መቀበላቸውን ተናግራል።
ሩድዋን ሁሴን በኮሚኒኬሽን ስራ ተቃዋሚዎች እንዲበልጡን አስደርግሃል የሚሉና ሌሎች በርካታ ትችቶች ሲቀርቡባቸው፣ አባ ዱላ ገመዳ ደግሞ ከስራቸው እና በኦሮምያ ከሚታየው ችግር ጋር ተያይዞ ትችት ቀርቦባቸዋል።

ከ200 በላይ ዕጩዎች የተሰረዙበት ሰማያዊ ፓርቲ የነጻነት ትግሉን እንደሚገፋት አስታወቀ

የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ  የአገሪቱ ክፍሎች ከ200 በላይ ዕጩዎቹ በምርጫ ቦርድ ትዕዛዝ የተሰረዙበት መሆኑን የገለጸው ፓርቲው፣ የካቲት 22  ከትብብሩ ፓርቲዎች ጋር በ15 ከተሞች የሚያደርገው የተቃውሞ ሰልፍ  የነጻነት ትግል አካል ነው ብሎአል።
የድርጅቱ ሊ/መንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ  እንደገለጹት ሰማያዊ ፓርቲ በመላ አገሪቱ በተለይም በደቡብ ወሎ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በወላይታ፣ በቤንች ማጅ፣ በምዕ/ጎጃም፣ በሲዳማ፣ በከምባታ፣ በጋሞጎፋ፣ አዲስ አበባ፣ በደቡብ ጎንደርና ጉጅን ጨምሮ በሌሎችም የአገሪቱ ክፍሎች ከ200 በላይ ዕጩዎቹ ‹‹ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደብዳቤ ታዘናል›› በማለት ከህዝብ ተወካዮች ምክርቤትና ከክልል ምክር ቤቶች ዕጩ ተወዳዳሪዎቹን መዝገብ ላይ እንዲሰረዙ ተደርጓል።
የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች የቦርዱን ሰብሳቢ ፕ/ር መርጋ በቃናን ለማግኘት ቢጥሩም ‹‹ከከተማ ውጭ ናቸው፡፡ አሁን አታገኟቸውም›› መባላቸውን፣ ፕ/ር መርጋ ግን የህወሓትን 40ኛ አመት ለማክበር መቀሌ መሆናቸውን ጋዜጣው ዘግቧል።
የምርጫ ቦርድ ውሳኔ ለነጻነት የሚያደርጉትን ትግል ትክክለኛ  እንደሆነ እንዳስረገጠላቸው፣ ይህን የነጻነት ትግልም አጠናክረው እንደሚቀጥሉና የካቲት 22 ፓርቲያቸው ከትብብሩ ጋር በ15 ከተሞች በተመሳሳይ ጊዜ የሚያደርገው ሰልፍ የዚሁ የነጻነት ትግል አካል እንደሆነ ኢ/ሩ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
የ9 ፓርቲዎች ትብብር የካቲት 22 የጠራው የተቃውሞ ሰልፍን በተመለከተ በመንግስት በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም። ፓርቲው ግን የተቃውሞ ሰልፉን በተያዘለት ቀን እንደሚያካሂድ ቀደም ብሎ  አስታውቋል።

በቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ላይ ዛቻና ማዋከቡ ተባብሶ ቀጥሏል።

የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በህገወጥ መንገድ በታገደው የአንድነት ለፍትሕና ለዲሞክራሲ  አመራሮች ላይ  ደህንነቶች ዛቻ፣ማስፈራሪያና ማዋከብ እየፈጸሙ ነው።
የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበሩት አቶ አስራት አብርሀ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ  ባለፈው እሁድ ማታ መናኛ አለባበስ የለበሱ ሁለት ወጣቶች የተከራዩበት ቤት ድረስ በመሄድ  “እንፈልገሃለን”  እንዳሏቸው በመጥቀስ፤ “በዚህ ሰዓት የምትፈልጉኝ እናንተ ደግሞ እነማናችሁ?” ብለው ሲጠይቋቸው  “ከደህንነት መስሪያቤት ነው የመጣነው ” እንዳሏቸውና መታወቂያ አውጥተው  እንዳሳዩዋቸው ገልጸዋል።
መሽቶ ስለነበር  በዚያ ሰዓት ሊያናግሩዋቸው ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ሲገልጹላቸውም መረጃ ፈልገው እንደመጡ መናገራቸውን የጠቀሱት አቶ አስራት፤  ምን ዓይነት መረጃ እንደፈለጉ ሲጠይቋቸውም  “አቶ በላይ ፍቃዱ ከሀገር ስለወጣበት ሁኔታ የምታውቀው ነገር ካለ እንድትነግረን ነው።” እንዳሏቸው ገልጸዋል።
ይህን ተከትሎ የአንድነት ሊቀ-መንበር አቶ በላይ ፈቃዱ በአሜሪካን ሀገር ጥገኝነት ጠየቁ የሚል ዜና በሶሻል ሚዲያ በስፋት የተሰራጨ ሲሆን፤ ስለ ጉዳዩ የተጠየቁት አቶ አስራት ግን በጉዳዩ ላይ መረጃ እንደሌላቸው፤ሆኖም ወሬው እውነት ነው ብለው እንደማይገምቱ ተናግረዋል።
አንድነት- በሀይል ለነ ትእግስቱ አወል ከተሰጠ በሁዋላ አቶ በላይን አግኝተዋቸው እንደማያውቁ የጠቀሱት አቶ አስራት ለደህንነቶቹም ይህንኑ እንደነገሯቸው ጠቅሰዋል።
<ጉዳዩ ግን በዚህ ብቻ አላበቃም>> የሚሉት አቶ አስራት፤ከቀናት በሁዋላ የቀበሌ ካድሬዎች የተከራየሁበት ቤት ድረስ ሄደው የቤቱን ባለቤት “የኪራይ ውል አለህ ወይ? መታወቂያውን ኮፒ አድርገሀዋል ወይ?” በማለት  እንዳዋከቧቸው የገለጹት የቀድሞው የ አንድነት የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ፤  ከዚያም ስማቸውን መዝግበው መመለሳቸውን ተናግረዋል።
በሁኔታው የተበሳጩት አቶ አስራት፦ <<ፓርቲ መስርተህ ስትታገል ሊያጠፉህ ይፈልጋሉ፤ ቤትህ አርፈህ ስትቀመጥ ቤትህ ድረስ መጥተው ሰላም ይነሱሃል፤ ይሄን መዓት አውርድ እንጂ ሌላ ስም ልሰጠው አልችልም፤ መዓቱን ያውርድላቸው>> ብለዋል።

የቤተክርስቲያን ነዋየ -ቅድሳት ለዓባይ ግድብ ተብሎ መሰጠቱ ተዘገበ

የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው በእንጦጦ ማርያም ሙዚየም የወርቅ መስቀሎች ጠፍተዋል መባሉ በምእመናን ዘንድ  ተቃውሞ አስነስቷል።
ለርዕሰ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን፣ ከተለያዩ ምዕመናን በስለትና በስጦታ የተሰጡና እስከ አራት ኪሎ ግራም ሊመዝኑ ይችላሉ የተባሉ ሁለት የወርቅ መስቀሎችና አንድ የወርቅ ሐብል፣ በቅርስነት ከተቀመጡበት ሙዚየም ውሰጥ መጥፋታቸውን የደብሩ ካህናትና የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡
የቤተ ክርስቲያኗ ካህናት፣ ሠራተኞችና የአካባቢው ነዋሪዎች-በጋራ በመሆን  የደብሩ አስተዳዳሪና ሌሎች ኃላፊዎች ተባብረው ወርቆቹን ማጥፋታቸውን በመግለጽ ተቃውሟቸውን በፊርማ አስደግፈው  ለመንበረ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት፣ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት፣ ለሀገረ ስብከቱ ቅርሳ ቅርስ ክፍል፣ ለአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮና ለጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምርያ በፊርማ  አስገብተዋል፡፡
የደብሩ ካህናት፣ የተለያዩ ሠራተኞችና የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት፣ በቤተ ክርስቲያኗ የቅርስ ማስቀመጫ ሙዚየም ውስጥ፤ የአፄ ምኒልክ የወርቅ ጫማ፣ የእቴጌ ጣይቱ ብጡል የተለያዩ አልባሳት፣ አልጋና  በተለያዩ ምክንያቶች ለቤተ ክርስቲያኗ የገቡ በርካታ  የወርቅ፣ የብር፣ የነሐስ፣ የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችና ቅርሶች ይገኛሉ፡፡
በማንና በምን ሁኔታ እንደተወሰዱ ባይታወቅም፣ በቱሪስቶች በመጎብኘትም ከፍተኛ ገቢ ሲያስገኙ ከቆዩት  ከእነኚህ ቅርሶች መካከል  ጥቂት የማይባሉ ቅርሶች መጥፋታቸውን ካህናቱ ተናግረዋል።
የቤተ ክርስቲያኗ አስተዳዳሪ መልዓከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ገብረኢየሱስ መኮንን ጥቅምት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. ለሙዚየሙ ቁልፍ ያዥ ለመምሬ አስፋው ገብረ ማርያም  በጻፉት ደብዳቤ ፦ በቅርሶች መመዝገቢያ (መረካከቢያ) ቁጥር 170 ላይ የሚገኙትን ሁለት የወርቅ መስቀሎችና አንድ የአንገት ወርቅ ሐብል  ወጪ አድርገው ለሊቀ ህሩያን ቃለጽድቅ ኃይሌ እንዲሰጡ  ትእዛዝ ማስተላለፋቸው ተመልክቷል፡፡
ከቅርስ ማስቀመጫ ሙዚየሙ ወጥተዋል የተባሉት ወርቆች የት እንደደረሱ ባለመታወቁ ካህናቱ፣ ሠራተኞቹና ምዕመናን ግራ ተጋብተው ባለበት ሁኔታ፣ አስተዳዳሪው  መልዓከ ጸሀይ ታኅሳስ 27 ቀን 2007 ዓ.ም. ሠራተኞችን ሰብስበው ለዓባይ ህዳሴ ግድብ ቦንድ ለመግዛት በሙዚየሙ ውስጥ ያሉ ወርቆች መሸጥ እንዳለባቸው ሐሳብ ማቅረባቸውን  ሰራተኞቹ ተናግረዋል፡፡
‹‹ታሪክ አጥፍተን ታሪክ አንሠራም፤›› በማለት  የአስተዳዳሪውን ሐሳብ  በአንድ ድምጽ መቃወማቸውን የገለጹት  ሰራተኞቹ ፣ ደመወዛቸውን በማዋጣት ለህዳሴ ግድብ ቦንድ እንደሚገዙ የተናገሩ ቢሆንም፣ አስተዳዳሪው ግን እንዳስፈራሩዋቸው አስረድተዋል፡፡
ስለጉዳዩ የተጠየቁት የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ መልዓከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ገብረ ኢየሱስ መኮንን፣ ‹‹የተባለው ሁሉ በተለይ ቦንድ የተባለው ጉዳይ ውሸትና ሐሰት ነው፤›› በማለት አስተባብለዋል፡፡ ሀገረ ስብከቱ ከወሰነበት ውጪ የተደረገ ነገር እንደሌለም  አስተዳዳሪው አክለዋል፡፡ ጸሐፊው መጋቤ ሐዲስ ዲበኩሉ ገብረዋህድ  ግን፣ “ተሰጠ የሚባለው ወርቅ የአንገት ሐብልና የጣት ቀለበት ከምዕመናኑ በስለት የሚገባና ሀገረ ስብከቱ የወሰነበት መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡ ጉዳዩን ያውቀዋል የተባለውን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን  <<ምእመናኑና ካህናቱ ወርቅ ጠፍቷል በሚል ያቀረቡት ተቃውሞ ዝም ተብሎ የሚታይ ሳይሆን መጀመርያ ማጣራት ተገቢ ነው” ብለዋል።
ሀገረ ስብከቱ የካቲት 10 ቀን 2007 ዓ.ም. ጉባዔ አድርጎ አጣሪ ኮሚቴ መሰየሙን የተናገሩት ስራ አስኪያጁ፤ ከቅርስ ጥበቃና ባላደራ ባለሥልጣን፣ ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ፍትሕ ጽሕፈት ቤት፣ ከሀገረ ስብከቱ ካህናት አስተዳዳሪ መምርያ፣ ከቅርሳ ቅርስና ከክፍለ ከተማው ሀገረ ስብከት አምስት አባላት ያሉት ኮሚቴ ተሰይሞ የካቲት 11 ቀን 2007 ዓ.ም. በደብሩ በመገኘትና ኃላፊዎቹ ባሉበት እንደሚያጣራም አስታውቀዋል፡፡

ሚኒስትሮችንና አፈ-ጉባኤዎችን ጨምሮ የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች በቤተ መንግስት የተገመገሙበት ሰነድ ኢሳት እጅ ገብቷል።

የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግምገማው የተካሄደው እንደተለመደው ባለስልጧናቱ በየተራ አስቀድመው ችግራቸውን እንዲናገሩ በማድረግና የራሱን ችግር በተናገረው አመራር ላይ ሌሎቹ ያላቸውን ተጨማሪ ትችት እንዲያቀርቡ
በማድረግ ነው።
በአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ መሪነት በተካሄደው በዚህ ግምገማ  ከ አዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ  የተገመገሙት አፈ-ጉባኤ አባዱላ ገመዳ፣”የሀሰት የስራ አፈጻጽመ ታቀርቢያለሽ” የተባሉት የሴቶችና የወጣቶች ሚኒስትር ዘነቡ ታደሰ፣”ሳሞራን ትፈራዋለህ”ተብለው የተገመገሙት የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳ፣”ኮምፒዩተርና ሞባይል ላይ ጥብቅ ትላለህ” የተባሉት አቶ ሬድዋን ሁሴን፣”ከባልደረቦችሽ ጋር ትጋጫለሽ”የተባሉት ወይዘሮ አስቴር ማሞ ፣”ፈሪ ነህ” የተባሉት ዶፐክተር ካሱ ይላላ፣ “ከደባል ሱስ የጸዳህ አይደለህም”የተባሉት  የገንዘብ ሚኒስትሩ ሶፊያን አህመድ  እና ሌሎች በርካታ ባለስልጣናት ” ሲ” አግኝተዋል።
የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አባይ ወልዱ፣ የትምህርት ሚኒስትር ሽፈራው ሽጉጤ፣የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ ጸጋይ በርሄ፣ የ አማራ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት ዓለምነው መኮንን፣አቶ ስዩም መስፍን፣አቶ አርከበ እቁባይ  እና ሌሎች በርካታ ሹመኞች “ቢ” ውጤት ተሰጥቷቸዋል።
እስካሁን ለ ኢሳት በደረሰው ሰነድ በግምገማው “ኤ”ውጤት የተሰጣቸው የ ኢህአዴግ አመራር የህወሀቱ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም ብቻ ናቸው። ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም “በሶሻል ሚዲያ የግለሰቦችን ታሪክ ለራስህ ገፅታ ግንባታ አውለሀል፣ ስራ ታዘገያለህ” የሚሉና ሌሎችም ደከማ ነጥቦች የተነሱባቸው ቢሆንም፤ ከሌሎቹ አመራሮች በተለየ ሁኔታ “የቀረበብኝን ድክመት”አልቀበልም በማለት ነው ውድቅ ያደረጉት። ሌሎቹ  አመራሮች በሙሉ፤ ከግምገማቸው በሁዋላ፦ “ድክመታችንን ተቀብለናል፤እናሻሽላለን”
ማለታቸውን ተከትሎ ነው “ቢ” እና “ሲ” የተሰጣቸው።  “ሲ”ከተሰጣቸው የኢህአዴግ አመራሮች መካከል ” ኢህአዴግ ገለልተኛ ነው” እያለ የሚናገርለትን ምርጫ ቦርድን በሰብሳቢነት የሚመሩት ፕሮፌሰር መርጋ  በቃና ይገኙበታል። በኢህአዴግ ውስጥ ቀደም ሲል አንድን ነገር “ድርጅቱ ነው ያለው” ሲባል፤ “መለስ ነው ያለው”ማለት እንደሆነ የቀድሞው የኮሙኒኬሽን ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ኤርሚያስ ገሠሰ “የመለስ ትሩፋቶች” በተሰኘው መጽሐፋቸው መግለጻቸው ይታወቃል። ኢሳት እጅ የገባው የግምገማ ሰነድ እንደሚያመለክተው፤  የመለስን ቦታ-አቶ በረከት ስምኦን መያዛቸውን ነው።
አቶ ሬድዋን፤”የሀገሪቱን ገጽታ ለውጪ ሚዲያ ዝግ አድርገኸዋል” ተብለው ሲገመገሙ <<ዝግ ያደረኩት  እኔ ሳልሆን ድርጅቱ ነው” ብለው መልስ የሰጡ ሲሆን ፤ <<ድርጅቱ ማን ነው?>>ተብለው  በአቶ ሀይለማርያም ሲጠየቅ፦<<በረከት>> በማለት መልሰዋል።

አፈ ጉባኤ አባ ዱላ ገመዳ- ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ጋር እንደማይግባቡ ተናገሩ

የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አባ ዱላ-ገመዳ ከኦሮሚያ ክልል  ፕሬዚዳንት- ከአቶ ሙክታር ከድር ጋር እንደማይግባቡ የተናገሩት፤ የኢህአዴግ ምክር ቤት ከፍተኛ አመራር አባላት በቃኘው ጥልቅ ግምገማ ላይ ነው
አፈ-ጉባኤው በግምገማው”የኦሮምያ አባላትን በተለየ ትህትና ታሰተናግዳለህ፣የአፈ ጉባኤነቱን ቦታ በደስታ አልተቀበልከውም፣ በአዲስ አበባ አዲስ ማሰተር ፕላን ጋር ተያይዞ ተል እኮ የማስፈጸም ችግር አለብህ፣ ከማስተር ፕላኑ ጋር ተያይዞ ለተነሳው አመጽ መባባስ መንስኤ ነህ፡፡>> ተብለው  ነው የተወቀሱት።
አባ ዱላ  ለቀረበባቸው   ሂስ ምላሽ ሲሰጡ ፦”አመፅ የተባለውን አልቀበለውም፡፡ ዘረኝነት የተባለው ከሙክታር ጋር ስለማንግባባ ነው፤ እንዳውም አሁን አሁን ስልክ እየደወልኩ  በክልሉ ዙሪያ አሰተያየት መስጠት አቁሚያለሁ፡፡>> ብለዋል።
<<በእርግጥ እንደተባለው በአፈ ጉባኤነቱ ሹመት ቀደም ሲል ደስ አላለኝም ብዬ ነበር>> ያሉት አፈ-ጉባኤው፤<< አሁን ግን ደስተኛ ነኝ፡፡ ተሰማምቶኛል፡፡>>በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።
ከአሁኑ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ጋር አንግባባም ያሉት አፈ-ጉባኤ አባዱላ ገመዳ ፤ቀደም ሲል የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት  ነበሩ።
አፈ-ጉባኤው በተመሳሳይ፤ከአቶ ሙክታር ከድር በፊት የክልሉ ፕሬዚዳንት ከነበሩትና በ ኦህዴድ ጓደኞቻቸው ተመርዘው ከተገደሉት  ከአቶ ዓለማየሁ አቶምሳም ጋርም ጠበኞች እንደነበሩ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል።

በሙስሊሞች ላይ በከፍተኛ የደህንነት ሃይሎች የሚመራ የእስር ዘመቻ መከፈቱ ተነገረ

የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፍትሕ ራዲዮ እንደዘገበው፤በአዲስ አበባ ብቻ ከ800 -1000 የሚደርሱ ሰዎችን ለማሰር ታቅዷል፡፡
የሙስሊሙን ማህበረሰብ አካላት  በምክንያት ለማሰር በከፍተኛ የኢትዬጲያ መንግስት የደህንነት ሃይሎች የሚመራ ዘመቻ  መከፈቱን ፍትህ ራዲዬ ዘግቧል።
ራዲዮው ምንጮቹን በመጥቀስ እንደዘገበው፤ዘመቻው ያነጣጠረው፤ ከመጪው  ሃገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ በህዝበ-ሙስሊሙ መካከል ትልቅ ንቅናቄ ይፈጥሩ ይሆናል የሚል ስጋት ባሳደሩ ሙስሊሞች ላይ ነው።
መንግስት ምርጫው ከመድረሱ አስቀድሞ በሃገሪቱ እየተንቀሳቀሱ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በተለያዩ ምክንያቶች ሲያዳክምና ሲያግድ ከመቆየቱም በላይ የግል ፕሬስ ጋዜጠኞችን ለእስርና ለስደት መዳረጉ ይታወቃል።
በአሁኑ ወቅት ሳይታገዱ  የቀሩት የፖለቲካ ፓርቲዎች ለኢህአዴግ ስጋት ሊሆኑ የሚችሉት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ ብቻ መንጠላጠል ከቻሉ ነው የሚል ግምገማ የወሰደው ኢህአዴግ፤ በዚህም መሰረት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ የመጨረሻ የማዳከም ዘመቻ መከፈት አለበት የሚል ድምዳሜ ላይ  መድረሱ ተመልክቷል።
በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የኦሮሚያ ክልሎች የአሰሳ እና ስምሪት ተግባር እየተካሄደ ሲሆን፤በተለይ በአዲስ አበባና በጅማ በርካታ ሙስሊሞችን በጅምላ  የማሰሩ ዘመቻ ተጀምሯል።
እንደ ምንጮቹ መረጃ፤በከፍተኛ የደህንነት ሀይሎች በሚመራው በዚህ ዘመቻ፤ ሃገር አቀፍ ምርጫው ከመካሄዱ በፊት  በአዲስ አበባ ብቻ ቁጥራቸው ከ 800 እስከ 1000 የሚደርሱ  ሰዎችን ለማሰር እቅድ ተይዟል።
በዛሬው ዕለትም የራዲዬ ቢላል ጋዜጠኛ የነበረው ካሊድ መሐመድን ጨምሮ ቁጥራቸው እስካሁን በውል ያልታወቀ በርካታ ሙስሊሞች ከያሉበት በደህንነት ሃይሎች እየታፈኑ ወደ እስር ቤት እየተወሰዱ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡
ሙስሊሞቹ በተያዙበት አካባቢዎች በወደሚገኙ የፖሊሰ ጣብያዎች እየታጎሩ ሲሆን፤ የመኖሪያ ቤታቸውም በፖሊሶች እና በደህንነቶች እየተፈተሸ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ቤታቸው የሚገኙ የተለያዩ ላፕቶፕ እና የግል ንብረቶቻቸውም  “ለምርመራ ያስፈልጋሉ” እየተባሉ በደህንነቶች   መወሰዳቸው ታውቋል፡፡

ጋዜጠኞቹና ጦማርያኑ ጥፋተኛ አይደለንም ሲሉ የዕምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ

የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሦስቱ ጋዜጠኞችና ስድስቱ ጦማሪያን ዛሬ በልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ምድብ ችሎት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን፤ ሁሉም በተከሰሱባቸው ክሶች <<ጥፋተኞች አይደለንም>> ብለዋል።
የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ያደመጠው ፍርድ ቤትም፤ ለፊታችን መጋቢት 21 ቀጠሮ በመስጠት የእለቱን ችሎት  አጠናቋል፡፡
ተከሳሾቹ እጃቸው ከተያዘበት ከሚያዚያ ወር 2006 ዓመተ ምህረት ጀምሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከቆዩ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ክስ የተመሰረተባቸው ጥር 28 ቀን 2007 ሲሆን፤  ለመጀመሪያ ጊዜ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመስጠት እድል ያገኙት ግን በዛሬው ዕለት ነው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ፤  የጦማርያኑን ችሎት በመሀል ዳኝነት ሲያስችሉ የነበሩት አቶ ሸለመ በቀለ ተከሳሾቹ <<ይቀየሩልን>> ባሉት መሰረት ሐሙስ ጥር 28 ቀን 2007 ዓ.ም ራሳቸውን በፈቃደኝነት እንዳገለሉ የተገለጸ ቢሆንም፤ በዛሬው ችሎት ላይ ግን ቀርበው እንደነበር -ፍርድ ቤት ተገኝተው ችሎቱን የተከታተሉት የተከሳሽ ጓደኞችና ቤተሰቦች ተናግረዋል፡፡

በህወሃት ውስጥ ፖለቲካዊ ጠባብነትና ትምክህት መኖሩን አቶ ስብሃት ተናገሩ

የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሐት) ውስጥ ፖለቲካዊ ጠባብነትና ትምክህት የሚያራምዱ ወገኖች መኖራቸውንና ሕገመንግስቱም በተሟላ ሁኔታ እየተተገበረ አለመሆኑን አቶ ስብሃት ነጋ የቀድሞ የህወሃት ሊቀመንበር እማኝነታቸውን ሰጡ፡፡
አቶ ስብሃት ነጋ የካቲት 9 እና 10/2007 ዓ.ም ከወጣው አዲስዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ በህወሃት ውስጥ ፖለቲካዊ ጠባብነትና ትምክህት መኖሩን አምነዋል፡፡ «ፖለቲካዊ ጠባብነትና ትምክህት በመንደራችን አለ፡፡ ቢሮክራሲው የጸዳ አይደለም፡፡ እንግዲህ ፓርቲውን የሚመራው መንግስት ነው፡፡ ተወዳዳሪና ቀና የሆነ ቢሮክራሲ ገና አልተገነባም፡፡ ከላይ እስከታች ሕገመንግስቱ በትክክል እየተተገበረ ነው ወይ የሚለው ጎዶሎ አለበት» ብለዋል፡፡
«የትግራይ ሕዝብ ጥያቄዎች ተመልሰዋል ወይ» በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ የሰጡት አቶ ስብሃት የመልካም አስተዳደር ችግር መኖሩን አረጋግጠው ችግሩን የምንፈታው ሕዝቡን ይዘን ነው ብለዋል፡፡ አይይዘውም «በአስተማማኙ ጎዳና እየተደረገ ያለው ሩጫ ዘገምተኛና እንከን ያለበት ነው፡፡ እንከን ስል ቢሮክራሲው የተሳለጠ ባለመሆኑና የቀናነት ጉድለት ስላለ ሕዝቡ በሚገባ ደረጃ እየተጠቀመ አይደለም፡፡ የተዛባ አመለካከትና የተንዛዛ አሠራር ይስተዋላል፡፡ ይህ ክፍተት መቀረፍ አለበት፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግ ስህተቱን ይፋ የሚያደርግና የሚያርም ድርጅት ነው፡፡ ስለዚህ ከሕዝቡ ጋር በመተባበር ችግሮቹ ይፈታሉ የሚል እምነት አለኝ» ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በ1993 ዓ.ም በልዩነት ህወሓትን ጥለው የወጡ የድርጅቱ ነባር ታጋዮች ጉዳይንም በተመለከተ ሟቹ የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስን በመደገፍና የእነስዬ አብርሃን ቡድንን በመንቀፍ  በሰጡት አስተያየት መነሻቸው የኤርትራ ጉዳይ ይሁን እንጂ ዋና ዓላማቸው የሥልጣን ጥማት ነው ብለዋል፡፡ «የሥልጣን ጥማቱ ታምቆ የቆየ ነው፡፡ ሻዕቢያ ኢትዮጵያን የመውረሩን ጉዳይ ያለመከታተላችን የሁላችንም ድክመት ነው፡፡ ቀደም ብለን ማወቅ ነበረብን የሚል እምነት አለኝ፡፡ ችግሩን ሰላማዊ በሆነ መልኩ ለመፍታት የዲፕሎማሲ ጥረት ማድረግ ያስፈልግ ነበር፡፡ ለሰላም አሟጠን ዕድል እንስጥ፣ ዕድሉ ካላዋጣን መዋጋት ማን ይከለክለናል የሚሉ የአመራር አባላት ነበሩ፡፡ እኛ ከኢሳያስ ተሸለን መገኘት አለብን፤  የእኛ ሰዎች ግን እንደ ኢሳያስ ሆኑ፡፡ ነፋስ በኤርትራ መጣ ከተባለ እንዋጋ ነው የሚሉት፡፡ ከወላጆቻቸው በምንም አይለዩም፡፡ ስንወረር ዝም ብላችሁ አያችሁ የሚለውን እንደምክንያት ወስደው ቡድን ፈጠሩ»ብለዋል፡፡
ተወልደ የህወሃት ምክትል ሊቀመንበር እያለ፣ ስዬም የመከላከያ ሚኒስትር እያለ ኤርትራ ነጻነትዋን ስታገኝ የአሰብ ወደብ ጉዳይ አብሮ ያለቀለት ነበር ያሉት አቶ ስብሃት፣ አሁን የአሰብ ጉዳይ እንደልዩነት የሚነሳው ሰበብ እንጂ ጉዳዩ ወንበር ፍለጋ ነው ሲሉ የእነስዬን ቡድን በሥልጣን ጥመኝነት ፈርጀዋል፡፡
ጡረተኛው አቶ ስብሃት በአሁኑ ወቅት እምብዛም እንቅስቃሴ የሌለውና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስር የሚገኘው የሠላምና የልማት ዓለም አቀፍ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ናቸው፡፡

የ9ኝ ፓርቲዎች ትብብር በ15 ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ ጠራ

የካቲት ፲ (አስር) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-‹‹ነጻነትለፍትሃዊምርጫ›› በሚልመርህ የሚካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ የካቲት 22 ቀን 2007 ዓም በ15 ከተሞች እንደሚካሄድ ትብብሩ አስታውቋል።
የሙስሊም ማህበረሰቡ ታህሳስ 10፣ 2007 ዓም  በኑር መስጂድ ፣ የካቲት 6፣ 2007 ዓም ደግሞ በአንዋር መስኪድ ያደረገው ተቃውሞ  እንዲሁም የባህርዳር ከተማ ህዝብ ታህሳስ 10፣ 2007 ዓም ያሳየው ህዝባዊ እምቢተኝነት ትግል በሃይል ሊዳፈን ቢችልም እንደማይጠፋ ትምህርት ሰጥቷል የሚለው የትብብሩ መግለጫ፣ ገዢው ፓርቲ እያደረሰ ያለው የመብት ረገጣ፣ የሙስና መስፋፋትና የመልካም አስተዳደር እጦት የህዝቡን የለውጥ ፍላጎትና የትግል ተነሳሽነት እንዳሳደገው ገልጿል።
ትብብሩ ገዢው ፓርቲ ለመድብለ ፓርቲ ስርአት ግንባታ ከቃላት ያለፈ እምነትም ሆነ ቁርጠኝነት እንደሌለው በመግለጽ፣ ምርጫ ቦርድን በቁጥጥር ስር በማዋል ጠንካራ ፓርቲዎችን ከመጪው ምርጫ ለማግለል እየሰራ መሆኑን የአንድነትና መኢአድን ጉዳይ በመግለጽ አብራርታል።
ከሰሞኑ ኢቢሲ ያቀረበው የተቃዋሚ ፓርቲዎችን የመኖር ትርጉም ዋጋ የሚያሳጣው ‹‹መንግስትንና የመንግስት አስፈጻሚዎችን ከተቻችሁ፣ ካላከበራችሁ ወይም ጸጥ ለጥ ብላችሁ የምርጫ አጃቢ ካልሆናችሁ እስከ 15 ዓመት ትታሰራላችሁ›› የሚል አንድምታ ያለው በ ‹‹ባለሙያዎች ትንታኔ ›› ሥም የተላከው የማስፈራሪያ መልዕክትና የሌሉ የፈጠራ ክሶችን ለመፈብረክ በአባል ፓርቲዎቻችን ላይ ‹‹የሞተ ጉዳይን ከመቃብር በመቀስቀስ›› እና በአዲስ መልክ የተጀመረው የሚዲያ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ በግልጽ  ያስተላለፈው ገዢው ፓርቲ የመድብለ ፓርቲ ስርአት እንዳይኖር መፈለጉን ነው ሲል አክሏል።
የእኛ፣ የአገራችንና ዜጓቿ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ በሁለት አማራጮች ላይ የተንጠለጠለ ነው የሚለው ትብብሩ  አንድም ያለውን አምባገነናዊ ሥርዓት ተቀብለን፣የአገራችን ሉዓላዊነት በጥያቄ ውስጥ ባለበት፣ የጭቆና ቀንበር ተሸክመን በከፋ ውርደት ሥር ሰጥ- ለጥ ብሎ መገዛት፤ አሊያም– አምባገነንነትና ጭቆናን ‹‹በቃ›› በማለት በሕዝባዊ የተቀናጀ ሰላማዊ ትግል ለአገራችን ሉዓላዊነትና የዜግነት ክብራችንን ለማስመለስ በህገ መንግስታዊ መብታችን ተጠቅመን  ትግላችንን እስከማይቀረው ለውጥ/ ድል ደጃፍ ድረስ በቆራጥነት መቀጠል፣ ናቸው ብሎአል፡፡
ሁሉን አቀፍ የነጻነትና ክብርን የማስመለስ ሰላማዊ ትግል ለ9ኙ ፓርቲዎች ብቸኛ አማራጭ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ፓርቲዎቹ በመጨረሻም በሚደረገው አገራዊ፣ ሰላማዊና ሕዝባዊ ትግል በማይቀረው የሥርዓት ለውጥ ለሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር በአንድነትና በቆራጥነት ህዝቡ እንዲነሳና በየካቲት 22 የተቃውሞ ሰልፍ ላይ እንዲገኝ በመግለጫቸው ጥሪ አቅርበዋል።

የህወሃት ታጋዮች ቅሬታቸውን ገለጹ ።

የካቲት ፲ (አስር) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ  (ህወሃት) የትጥቅ ትግል የጀመረበት 40ኛ ኣመት በዓል በስኬት ላይ ብቻ የተመሠረተና ከበሮ ድለቃ የበዛበት የህወሃትን ጉድፎች የተደበቁበት ሆኖ እየተከበረ መሆኑ አሳዛኝ ነው ሲሉ የቀድሞ የድርጅቱታጋይገለጹ፡፡
ስማቸውእንዲገለጽያልፈለጉትየድርጅሩ የቀድሞታጋዮች ለኢሳት በላኩት መልእክትህወሃትየደርግአገዛዝበትጥቅትግል ለማሸነፍከሌሎችየትግልሃይሎችጋርበጣምራናበተናጠልሲታገልመቆየቱናአስከፊውንስርኣትመገርሰሱመልካም ነገር መሆኑ ባይካድም፣  ድርጅቱበሺየሚቆጠሩታጋዮቹን ለሞት ዳርጎ መንግስታዊስልጣን ከተቆናጠጠበሃላየታገለለትዓላማበመርሳትጥቂትሹማምንትራሳቸውንናቤተሰቦቻቸውንየሚያበለጽጉበት፣ቡድናዊ ወገንተኝነትበመመስረትብዙሃኑንያገለለስርዓትእንዲፈጠርአስተዋጽኦአድርጎአልብለዋል፡፡
ህወሃትመንግስታዊስልጣንላይበቆየባቸውባለፉት 23 ኣመታትዴሞክራሲ፣የህግየበላይነትእናየሰብዓዊመብት ጥበቃለማክበርናለማስከበርመታገሉንበመርሳትደጋግሞከሚረግመውየደርግስርዓትባልተናነሰአፋኝስርዓት እየገነባመምጣቱየፓርቲውንመክሸፍቁልጭአድርጎያሳያልሲሉ እነዚሁ ታጋዮች በመልክታቸው አስፍረዋል።
በትግልወቅትስንትናስንትጉዋዶቻችንንከአጠገባችንአጥተናልያሉትእኚሁየቀድሞታጋዮች፣ይህሁሉመስዋዕትነት የተከፈለውግንጥቂትየህወሃትሹማምንትንለማበልጸግሳይሆንበመላሀገሪቱሠላም፣ዴሞክራሲናእኩልነት እንዲሰፍንነበርብለዋል፡፡
በአሁኑወቅትኢትዮጽያውስጥሃሳብንበነጻመግለጽ፣ተደራጅቶየተቃውሞጠንካራእንቅስቃሴማድረግ፣የተቃውሞ ሰልፍማካሄድ፣ነጻየሲቪክማህበርማቋቋምበሸብርተኝነትጭምርእያስከሰሰ፣ዜጎችንምለእስርናለሞትናለስደት እየዳረገያለውበህወሃትጥቂትከፍተኛካድሬዎችአመራርሰጪነትመሆኑማንምአይዘነጋውምሲሉ አትተዋል።
በአሁኑወቅትየትግራይሕዝብየታገለለትንኣላማበራሱልጆችመነጠቁንያስታወሱትእኚሁታጋይየትግራይሕዝብና አመራሩበመለያየቱከፍተኛባለስለጣናትበመቀሌከተማየሰሩዋቸውንመኖሪያቤቶችሳይቀር «ሙስናሰፈር» ብሎ እስከመሰየምመድረሱሕዝቡለህወሃትያለውንትክክለኛአቋምያንጸባርቃልሲሉአክለዋል፡፡
የህወሃት 40ኛዓመትበዓልየካቲት 11 ቀን 2007 ዓ.ምበትግራይለማክበርሽርጉድእየተባለሲሆን በተከታታይሰሞኑንየራያዩኒቨርሲቲየመሰረትድንጋይ፣የመቀሌታጁራወደብየባቡርግንባታየመሰረትድንጋይ መጣሉ፣የሞሃለስላሳመጠጥፋብሪካግንባታምረቃ፣የራያቢራፋብሪካግንባታምረቃናየመሳሰሉትበማከታተል የህዝብንድጋፍለመሳብህወሃትተግቶእየሰራሲሆንበዚህበምርጫወቅት፣በመንግስትመገናኛብዙሃንየሚደረገው የአንድፓርቲየተጋድሎፕሮፖጋንዳ፣በመንግስትወጪየሚደረገውጉሮወሸባዩሕገወጥመሆኑንእንኩዋንአልተረዱትም ሲሉአስተያየታቸውን አስፍረዋል፡፡
ህወሃት ለበአሉ ዝግጅት በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ የሚያወጣ ሲሆን፣ ባላሃብቶች በግዳጅና በማስፈራሪያ እስካሁን ከ50 ሚሊዮን ያላነሰ ገንዘብ አዋጥተዋል።

የተመላሽ ሰራዊት አባላት የቀረበላቸውን የድጋፍ ጥሪ ወድቅ አደረጉት

የካቲት ፲ (አስር) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-በኮምቦልቻ ከተማ በቡራሮ አዳራሽ ጥሪ የተደረገላቸው የተመላሽ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ለመንግስት ደግፋቸውንና ታማኝነታቸውን እንዲገለጹ በተጠየቁበት ወቅት እስካዘሬ የት እንደወደቅን ሳትጠይቁን፣ አሁን ምን ስለተገኘ ነው በማለት ውድቅ አድርገዋል።
ያለፈው አልፏል ለወደፊቱ እንደጋገፍ በሚል ካድሬዎች የማግባባት ስራ ቢሰሩም ፣ የተመላሽ ሰራዊት አባላት ሳይቀበሉት ቀርተዋል።
አቶ መለስ ጽፈውታል የተባለውን ማንዋል  ለማስተማር በሚዘጋጁበት ወቅት ፣ የ ቀድሞ የመከላከያ አባሎቹ በመቃወማቸው ሳይካሄድ ቀርቷል።
መንግስት በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ ተመላሽ የሰራዊት አባላትን እየጠራ በማነጋገር ላይ ነው።

Tuesday, February 17, 2015

Ethiopianism TV Producer has got it Wrong !!! -Tedla Asfaw

I watched the “Ethiopianism TV” posted here.https://www.youtube.com/watch?v=tFpc6UM5kQc
Professor Mussie the ” Ethiopianism TV ” producer was very angry and agitated of the ESAT interview of Isayas Afewrokiof Eritrea. The professor should have dissected the interview with facts. He should have rather compared and contrasted the “Eritrean Constitution” with “Woyane Constitution” the core of the interview.The “Eritrean Constitution” does not divide Eritreans into  “Kilil” like the Woyane Constitution. There is no Article 39 in the “Eritrean Constitution”. The professor failed to do that.
I found the professor in the same camp with the diaspora Oromo groups, OLF/OPDO, who  claimed being colonized by Ethiopia/Habeshas who lashed out also against Isayas following the clip of the interview few weeks ago. OLF/OPDOendorsed the “Woyane Constitution” and their problem with Woyane is on controlling/liberating their Kilil. The diaspora Oromo Media Network recent partying in Minnesota is a good indicator of  the relationship of the so calledOromo opposition with the OPDO/Woyane Boss Aba Dula.
ESAT Ignoring of the human rights violations in Eritrea which the whole world knows and the professor also raised  was wrong. However, the core of the interview was Article 39 and Kililization of Ethiopia. Isayas Afeworki publicly said for the Ethiopian people on the record that he never endorsed the Ethiopian Constitution of divide and rule. No wonder theOLF/OPDO are crying foul on social medias and Professor Mussie joined this camp by default.
The interview has not yet been concluded. ESAT might raise the issue of human rights violation both in Eritrea and Ethiopia in the next part of the interview. Ethiopians and Eritreans are reacting to the first part of the interview thanks to the Interview. For that ESAT journalists should be thanked for starting this conversation. That is the job of a journalist.

Advocates Petition UN to Intervene on Jailed Ethiopian Bloggers’ Behalf

February 16, 2015

Last April, nine writers were arrested and imprisoned in association with Ethiopia’s Zone 9 blogging collective. Eleven weeks later, they were charged under the nation’s Anti-Terrorism Proclamation. Since their arrest, Soleyana Gebremicheal and Endalk Chala, two members of the collective who now live in the United States, have advocated tirelessly for their colleagues’ release. Global Voices is honored to publish this original contribution by Soleyana and her colleague, Patrick Griffith, who are now petitioning the UN Working Group on Arbitrary Detention to intervene on the bloggers’ behalf.

Despite early, high-level condemnation of the arrests of independent journalists and bloggers in Ethiopia nine months ago, international attention has waned as the pre-trial proceedings have dragged-on. The government’s continued detention of three independent journalists and six members of the Zone 9 blogging collective is not only an outrageous attack on the press – it is also illegal and unconscionable.Jailed Ethiopian Bloggers
After its founding in May 2012, the Zone 9 blog received widespread attention from Ethiopian activists and academics who used the site to promote political rights enshrined under both international and Ethiopian law. For a time, they managed to operate in anincreasingly restrictive media environment. When access to the site was blocked inside the country, members circulated articles through social media. When authorities summoned the contributors for questioning and accused them of threatening national security in 2013, the group temporarily stopped writing about political issues. But when the activists announced that they would revive the site and focus on Ethiopia’s upcoming national elections scheduled for May 2015, the government response was swift – within days, six members of Zone 9 and three independent journalists who knew them socially were behind bars.
Eventually, the government charged all nine detainees with terrorism and treason.
The use of overly broad national security laws to silence peaceful activists may seem like a surprising overreaction to online activism, but in Ethiopia, politicized prosecutions have become commonplace. Since the government passed the widely-criticized 2009 Anti-Terrorism Proclamation, prosecutors have cast an ever-widening net in an attempt to silence any kind of dissent. The government has applied the Proclamation to detain critical journalists, opposition activists, and religious protesters – apparently unconcerned that misusing such laws threatens to seriously undermine its credibility with security allies in a region with very real terror threats.
The condemnation of such tactics has been nearly universal. The former UN High Commissioner for Human Rights, the African Commission on Human and Peoples’ Rights, and political leaders – including US Secretary of State John Kerry – have all called for an end to the imprisonment of peaceful writers and activists on terrorism charges. In the case of the imprisoned Ethiopian publisher Eskinder Nega, the UN Working Group on Arbitrary Detention specifically found that the government violated international law when it sentenced him to 18 years in prison under the 2009 Anti-Terror Proclamation. Despite such calls, however, the prosecutions have continued.
It has now been nine months since Ethiopian authorities arrested the Zone 9 bloggers and their journalist friends. During the first three months, they were held at the notorious Maekelawi police station in Addis Ababa, where reports indicate that torture is rampant. In fact, a complaint prepared by the group for the Ethiopian Human Rights Commission indicates that authorities severely mistreated some detainees while interrogating them about their criticism of the government and their contacts with international human rights organizations. Some were beaten, gagged, deprived of food and sleep, subjected to cold temperatures, and threatened not to report the mistreatment. The women were insulted during questioning and faced harassment and intimidation based on their gender. All of them were forced to sign false confessions.
Although the government has held 16 preliminary hearings, the trial has yet to begin. If past cases are any indication, however, the outcome has already been determined. That is why the Ethiopian Human Rights Project and Freedom Now have filed a petition with the United Nations Working Group on Arbitrary Detention, which shows that the continued imprisonment of these peaceful activists violates international law. The work of these activists and journalists advocating for basic rights is clearly protected under international law and the treaties that the Ethiopian government has ratified, including the International Covenant on Civil and Political Rights and the African Charter on Human and Peoples’ Rights. As such, the government’s imprisonment of these individuals on spurious terror charges is arbitrary and illegal.
Soleyana S. Gebremicheal heads the Ethiopian Human Rights Project and is a member of the Zone9 collective. Patrick Griffith is an attorney with the legal advocacy organization Freedom Now.

Ethiopia: A land grab twice the size of France

February 16, 2015

Stealing the Omo Valley, destroying its ancient Peoples

Megan Perry / Sustainable Food Trust | ECOLOGIST
A land grab twice the size of France is under way in Ethiopia, as the government pursues the wholesale seizure if indigenous lands to turn them over to dams and plantations for sugar, palm oil, cotton and biofuels run by foreign corporations, destroying ancient cultures and turning Lake Turkana, the world’s largest desert lake, into a new Aral Sea.
Ethiopia's Omo River in 2008.
Ethiopia’s Omo River in 2008. Photo: Marc Veraart via Flickr.com.
There is growing international concern for the future of the lower Omo Valley in Ethiopia. A beautiful, biologically diverse land with volcanic outcrops and a pristine riverine forest; it is also a UNESCO world heritage site, yielding significant archaeological finds, including human remains dating back 2.4 million years.
The Valley is one of the most culturally diverse places in the world, with around200,000 indigenous people living there. Yet, in blind attempts to modernise and develop what the government sees as an area of ‘backward’ farmers in need of modernisation, some of Ethiopia’s most valuable landscapes, resources and communities are being destroyed.
A new dam, called Gibe III, on the Omo River is nearing completion and will begin operation in June, 2015, potentially devastating the lives of half a million people. Along with the dam, extensive land grabbing is forcing thousands from their ancestral homes and destroying ecosystems.
Ethiopia’s ‘villagisation’ programme is aiding the land-grab by pushing tribes into purpose built villages where they can no longer access their lands, becoming unable to sustain themselves, and making these previously self-sufficient tribes dependent on government food aid.
A total disregard for the rights of Ethiopia’s Indigenous Peoples
What is happening in the lower Omo Valley, and elsewhere, shows a complete disregard for human rights and a total failure to understand the value these tribes offer Ethiopia in terms of their cultural heritage and their contribution to food security.
There are eight tribes living in the Valley, including the Mursi, famous for wearing large plates in their lower lips. Their agricultural practices have been developed over generations to cope with Ethiopia’s famously dry climate.
Many are herders who keep cattle, sheep and goats and live nomadically. Others practice small-scale shifting cultivation, whilst many depend on the fertile crop and pasture land created by seasonal flooding.
The vital life source of the Omo River is being cut off by Gibe III. An Italian construction company began work in 2006, violating Ethiopian law as there was no competitive bidding for the contract and no meaningful consultation with indigenous people.
The dam has received investment from the Industrial and Commercial Bank of China and the World Bank, and the hydropower is primarily going for export rather than domestic use – despite the fact that 77% of Ethiopia’s population lacks access to electricity.
People in the Omo Valley are politically vulnerable and geographically remote. Many do not speak Amharic, the national language, and have no access to resources or information. Foreign journalists have been denied contact with the tribes, as BBC reporter Matthew Newsome recently discovered when he was prevented from speaking to the Mursi people.
There has been little consideration of potential impacts, including those which may affect other countries, particularly Kenya, as Lake Turkana relies heavily on the Omo River.
At risk: Lake Turkana, ‘Cradle of Mankind’
Lake Turkana, known as the ‘Cradle of Mankind’, is the world’s largest desert lake dating back more than 4 million years. 90% of its inflow comes from the Omo. Filling of the lake behind the dam will take three years and use up to a years’ worth of inflow that would otherwise go into Lake Turkana.
Irrigation projects linked with the dam will then reduce the inflow by 50% and lead to a drop of up to 20 metres in the lake’s depth. These projects may also pollute the water with chemicals and nitrogen run-off. Dr Sean Avery’s report explains how this could devastate the lake’s ancient ecosystems and affect the 300,000 people who depend on it for their livelihoods.
Tribal communities living around the lake rely on it for fish, as well as an emergency source of water. It also attracts other wildlife which some tribes hunt for food, such as the El Molo, who hunt hippo and crocodile. Turkana is home to at least 60 fish species, which have evolved to be perfectly adapted to the lake’s environment.
Breeding activity is highest when the Omo floods, and this seasonal flood also stimulates the migration of spawning fish. Flooding is vital for diluting the salinity of the lake, making it habitable. Livestock around the lake add nutrients to the soil encouraging shoreline vegetation, and this is important for protecting young fish during the floods.
Lake Turkana is a fragile ecosystem, highly dependent on regular seasonal activity, particularly from the Omo. To alter this ancient ebb and flow will throw the environment out of balance and impact all life which relies on the lake.
Severely restricted resources around the lake may also lead to violence amongst those competing for what’s left. Low water levels could see the lake split in two, similar to the Aral Sea. Having acted as a natural boundary between people, there is concern that conflict will be inevitable.
Fear is already spreading amongst the tribes who say they are afraid of those who live on the other side of the lake. One woman said, “They will come and kill us and that will bring about enmity among us as we turn on each other due to hunger.”
Conflict may also come from Ethiopians moving into Kenyan territory in attempts to find new land and resources.
A land grab twice the size of France
The dam is part of a wider attempt to develop the Omo Valley resulting in land grabs and plantations depending on large-scale irrigation. Since 2008 an area the size of France has been given to foreign companies, and there are plans to hand over twice this area of land over the next few years.
Investors can grow what they want and sell where they want. The main crops being brought into cultivation include, sugar, cotton, maize, palm oil and biofuels. These have no benefit to local economies, and rather than using Ethiopia’s fragile fertile lands to support its own people, the crops grown here are exported for foreign markets.
Despite claims that plantations will bring jobs, most of the workers are migrants. Where local people (including children) are employed, they are paid extremely poorly. 750km of internal roads are also being constructed to serve the plantations, and are carving up the landscape, causing further evictions.
In order to prepare the land for plantations, all trees and grassland are cleared, destroying valuable ecosystems and natural resources.
Reports claim the military have been regularly intimidating villages, stealing and killing cattle and destroying grain stores. There have also been reports of beatings, rape and even deaths, whilst those who oppose the developments are put in jail. The Bodi, Kwegi and Mursi people were evicted to make way for the Kuraz Sugar Project which covers 245,000 acres.
The Suri have also been forcibly removed to make way for the Koka palm oil plantation, run by a Malaysian company and covering 76,600 acres. This is also happening elsewhere in Ethiopia, particularly the Gambela region where 73% of the indigenous population are destined for resettlement.
Al-Moudi, a Saudi tycoon, has 10,000 acres in this region to grow rice, which is exported to the Middle East. A recent report from the World Bank’s internal watchdog has accused a UK and World Bank funded development programme of contributing to this violent resettlement.
For many tribes in the Omo Valley, the loss of their land means the loss of their culture. Cattle herding is not just a source of income, it defines people’s lives. There is great cultural value placed on the animals. The Bodi are known to sing poems to their favourite cattle; and there are many rituals involving the livestock, such as the Hamer tribe’s coming of age ceremony whereby young men must jump across a line of 10 to 30 bulls.
Losing their land also means losing the ability to sustain themselves. As Ulijarholi, a member of the Mursi tribe, said, “If our land is taken, it is like taking our lives.”
They will no longer be independent but must rely on government food aid or try to grow food from tiny areas of land with severely reduced resources.
Ethiopia’s food security
Ethiopia is currently experiencing economic growth, yet 30 million people still face chronic food shortages. Some 90% of Ethiopia’s national budget is foreign aid, but instead of taking a grass-roots approach to securing a self-sufficient food supply for its people, it is being pushed aggressively towards industrial development and intensive production for foreign markets.
There is a failure to recognise what these indigenous small-scale farmers and pastoralists offer to Ethiopia’s food security. Survival of the Fittest, a report by Oxfam, argued that pastoralism is one of the best ways to combat climate change because of its flexibility.
During droughts animals can be slaughtered and resources focused on a core breeding stock in order to survive. This provides insurance against crop failure as livestock can be exchanged for grain or sold, but when crops fail there can be nothing left. Tribal people can also live off the meat and milk of their animals.
Those who have long cultivated the land in the Omo Valley are essential to the region’s food security, producing sorghum, maize and beans on the flood plains. This requires long experience of the local climate and the river’s seasonal behaviour, as well as knowledge of which crops grow well under diverse and challenging conditions.
Support for smallholders and pastoralists could improve their efficiency and access to local markets. This would be a sustainable system which preserved soil fertility and the local ecosystem through small-scale mixed rotation cropping, appropriate use of scarce resources (by growing crops which don’t need lots of water, for example) and use of livestock for fertility-building, as well as for producing food on less productive lands.
Instead, over a billion dollars is being spent on hydro-electric power and irrigation projects. This will ultimately prove unsustainable, since large-scale crop irrigation in dry regions causes water depletion and salinisation of the soil, turning the land unproductive within a couple of generations.
Short of an international outcry however, the traditional agricultural practices of the indigenous people will be long gone by the time the disastrous consequences becomes apparent.