Pages

Saturday, June 28, 2014

የደገሃቡር የጸጥታ አዛዥ ተገደሉ


ሰኔ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሶስት ቀናት በፊት የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት ታጣቂዎች በደጋሃቡር ላይ ድንገት በፈጸሙት ጥቃት ከሞቱት 7 የመንግስት ታጣቂዎች በተጨማሪ የደጋሃቡር የጸጥታ ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑት አቶ አሻር ፣ በታጣቂዎች ጥይት ቆስለው ወደ ደጋሃቡር ሆስፒታል ከተወሰዱ በሁዋላ ዛሬ ጠዋት ሰኔ 17 ቀን 2006 ዓም ማረፋቸውን የደረሰን ዜና አመልክቷል።
የአካባቢው የልዩ ሚሊሺያ አዛዥ የሆኑት ሙሃመድ ዳይክ ክፉኛ ቆስለው አሁንም በሆስፒታሉ በመታከም ላይ ሲሆኑ፣ አማጽያኑ ጥቃቱን ፈጽመው ከአካባቢው መሸሻቸው ታውቋል።
ኢህአዴግ በክልሉ እየተባባሰ የመጣው የጸጥታ ሁኔታ ስጋት ላይ መጣሉን ተከትሎ ከኦብነግ ጋር ሊያደርገው ያሰበው ድርድር ሁለት የኦብነግ አመራሮች ናይሮቢ ኬንያ ላይ ተይዘው ከተወሰዱ በሁዋላ ተደናቅፏል። መሪዎቹ እጃቸውን በፈቃዳቸው እንደሰጡ መንግስት ቢገልጽም፣ እስካሁን ድረስ የታፈኑት መሪዎች ቀርበው እጃቸውን በፈቃዳቸው መስጠታቸውንና አለመስጠታቸውን አልተናገሩም።
በአካባቢው እየታየ ያለው ሁኔታ ያሰጋው መንግስት የክልሉን ፕሬዚዳንት ለመተካት ውስጥ ውስጡን እንቅስቃሴ ቢጀምርም፣ በአካባቢው የተሰማራው የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች የፕሬዚዳንቱን መተካት በመቃወማቸው በመንግስት ሹሞችና በመከላከያ አዛዦች መካከል ልዩነት ተፈጥሮአል። በመንግስት በኩል ያለው አቋም ፕሬዚዳንቱ አቶ አብዲ ሞሃመድ ኡመር በሚከተሉት ፖሊሲ የክልሉ ህዝብ ይበልጥ እየተከፋ ተቃዋሚዎች ደጋፊ እየሆነ ነው የሚል ሲሆን፣ በመከላከያ አዛዦች በኩል ያለው አቋም ደግሞ አቶ አብዲ ለክልሉ ጸጥታ እና መረጋጋት እጅግ አስፈላጊ ናቸው የሚል ነው። ታዛቢዎች እንደሚሉት በክልሉ ውስጥ ከፍተኛ ኢንነቨስተር በመሆን እየሰሩ ያሉት የሌ/ጄኔራል ዮሃንስ ገ/መስቀል የፍቅር ጓደኛ አቶ አብዲን በስልጣን ላይ መቆየት በእጅጉ ይደግፋሉ። ከመከላከያ ባለስልጣናት ጋር የተፈጠረው ከፍተኛ የሙስና ግንኙነት አቶ አብዲ የአካባቢውን የመከላከያ አዘዦች ድጋፍ አስገኝቶላቸዋል።
ሰሞኑን አቶ አብዲ 1500 በክልሉ የሚገኙ የአገር ሽማግሌዎችን ሰብስበው የማእከላዊ መንግስት ባለስልጣናት በተለይም የደህንነት ሃላፊው አቶ ጌታቸው አሰፋ ሊያስገድላቸው እንደሚፈልግ በግልጽ ሲናገሩ ተሰምቷል።
አብዛኛውን አገር ሽማግሌዎች ባስደነገጠ መልኩ፣ መንግስት እኛን ሳይሆን መሬታችንን ነው የሚፈልገው ያሉት አቶ አብዲ፣ የክልሉ ሽማግሌዎች የመንግስትን የደህንነት ሃይሎች እንዳይፈሩ መክረዋል። የደህንነት ሃይሎች ከክልላችን ተጠራርገው ወጥተዋል በማለት የተናገሩት ሹሙ፣ የደህንነት ሹሙም በሙስና የተዘፈቁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ጅጅጋ የሚገኘው የነርሲንግ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ተዘግቶ ተሰብሳቢዎች ለ10 ቀናት ያክል እንዲያርፉበት የተደረገ ሲሆን፣ አቶ አብዲ አገር ሽማግሌዎች ከእርሳቸው ጎን እንዲቆሙ ከመማጸን ጀምሮ ፣ ክልሉን ሊቆጣጠሩ የሚፈልጉ ሃይሎች ካሉ አንቀጽ 39ን ተግባራዊ እስከማድረግ እንደሚደርሱ ሲዝቱ መሰማቱን ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉት የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
የአገር ሽማግሌዎችን ድጋፍ ለማግኘት በሚመስል መልኩ አቶ አብዲ ለእያንዳንዱ የአገር ሽማግሌ ከፍተኛ ገንዘብ እንዲሰጣቸው አድርገዋል።
የግቢያቸው የጸጥታ አጠባባቅ ከወትሮው በተለየ እንዲጨምር መደረጉንና የሚጠራጠሩዋቸውን ጠባቂዎች ማባረራቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ።
አቶ አብዲ ሙሃመድ አማራ እና ኦሮሞ ምንጊዜም ሊታረቅ የማይችል በመሆኑ የሶማሊ ክልል ህዝብ ከትግራይ ጎን እንዲቆም የተናገሩበት የቪዲዮ ማስረጃ በኢሳት መለቀቁ ይታወሳል።

ለጋሽ አገራት በኢትዮጵያ ስላለው የህዝብ መፈናቀል ምርመራ እንደሚያካሂዱ አስታወቁ


ሰኔ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉ አገራት በጋራ እንዳስታወቁት በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ እየታየ ያለውን የህዝብ መፈናቀል ለማጣራት አንድ መርማሪ ቡድን ወደ አካባቢው ይልካሉ።
ለስኳር ልማት በሚል ምክንያት መንግስት በአካባቢው የሚኖሩ የቦዲና ክዌጎ ጎሳ አባላትን ማፈናቀሉን ዜናውን ይፋ ያደረገው ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል አስታውቋል።
አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ጀርመን እንዲሁም የአለም ባንክን ያካተተው የለጋሾች ቡድን፣ የሚፈናቀሉና ወደ ሌሎች አካባቢዎች የሚሰፍሩ ሰዎች በቅድሚያ ፍላጎታቸው መጠየቅ አለበት የሚል መመሪያ አለው።
ለጋሽ አገራት እርምጃውን ለመውሰድ የተነሳሱት በእየ አገራቱ የሚገኙ በርካታ የፓርላማ አባላት ጥያቄ እያነሱ በመምጣታቸው ነው።

ዚምባቢዌ ኢትዮጵያውያንን ይዛ አሰረች


ሰኔ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-37 ኢትዮጵያውያን በህወገጥ መልኩ የዝንባብዌን ድንበር በማቋረጣቸው መያዛቸውን ዴይሊ ኔሽን ዘግቧል።
ኢትዮጵያውያኑ ባዞዎች በተሞላው የሊምፖፖ ወንዝ አቋርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ሙከራ ሲያደርጉ መያዛቸውን አገሪቱ ፖሊስ አስታውቋል።
ጉዳያቸው እየታየ መሆኑን የገለጸው ፖሊስ፣ ምርመራው ሲጠናቀቅ ወደ ፍርድ ቤት እንደሚወስዳቸውም ገልጿል።
በርካታ ኢትዮጵያውያን በእየአመቱ ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሚጎርፉ ይታወቃል። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ስራ አጥነት፣ የኑሮ ውድነት፣ የፍትህ እና የመልካም አስተዳደር እጦት ኢትዮጵያኑ አገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ ከሚያደርጉቸዋም ምክንያቶች መካከል በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳሉ።
ተያዙ ስለተባሉ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰጠው መግለጫ የለም።

Mullugeta, Shimless and HabteMariam arrested in Philadelphia prostitution bust


setegna-adari-750x400SOUTHWEST PHILADELPHIA (WPVI) 
Police have announced the arrested of seven men in connection to a prostitution bust in Southwest Philadelphia.
Authorities say on June 20th officers from the City Wide Vice Enforcement Unit conducted an operation targeting prostitution in the 12th District.
Undercover decoy officers arrested the following men and charged them with Patronizing Prostitution:
1) James Walker, 45, from the 1000 block of Bullock Avenue in Yeadon, Pa.
2) Mitchell Ballah, 22, from the 100 block of McDade Blvd in Folsom, Pa.
3) Mullugeta Goniche, 30, from the 2500 block of South 70th Street in Philadelphia
4) Shimless Badane, 39, from the 2500 block of South 67th Street in Philadelphia
5) Rudy Lagasca JR, 53, from the 500 block of Devon Road in Norwood, Pa.
6) Oldman Kabban, 37, from the 7100 block of Greenwood in Upper Darby, Pa.
7) HabteMariam Embaye, 32, from the 2500 block of South Claymont Street in Philadelphia

Friday, June 27, 2014

ኢቲቪ እንደእነ ቢቢሲ በኮርፖሬሽን ደረጃ ሊዋቀር ነው


ሰኔ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ከእነቢቢሲ ያጠናውን  ልምድ መሰረት አድርጎ ስያሜው ወደ ኢትዮጽያ ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬሽን እንዲቀየርለት የሚጠይቅ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማው ቀረበ፡፡
ድርጅቱ ለ19 አመታት ሲጠቀምበ ትየቆየውን አዋጅ ማሻሻል ያስፈለገው አደረጃጀቱን በማስተካከል የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በብቃት እንዲወጣ እንዲያስችለው ነው ተብሎአል፡፡
ለትርፍያልተቋቋመናተጠሪነቱለፓርላማውየሆነየመንግሥትየልማትድርጅትበመሆንበኮርፖሬሽንደረጃየሚዋቀረውኢትዮጵያብሮድካስቲንግኮርፖሬሽንየዚህኣይነትአደረጃጀትበልምድነትየቀሰምኩትከቢቢሲ፣ከኤስ፣ኤ፣ቢ.ሲ፣ከኬንያውኬ.ቢ.ሲእናከህንዱከኦልኢንዲያንስነውብሏል፡፡
አዋጁለዝርዝርዕይታለኮምቴተመርቷል።

ለኢራቅ ችግር የፖለቲካ መፍትሄ እንደሚያሻው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ

ሰኔ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢራቅን እየጎበኙ የሚገኙት ጆን ኬሪ ይህን የተናገሩት አይ ኤስ ኤስ እየተባለ የሚጠራው በአብዛኛው በሱኒዎች የተሞላው ተዋጊ ሃይል የሰሜን ኢራቅን አካባቢዎች እየተቆጣጠረ መምጣቱን ተከትሎ ነው። ድርጅቱ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት አለው በሚል አሜሪካ እንደ አሸባሪ በመመልከቷ እውቅና አልሰጠችውም።

ጆን ኬሪ ኢራቃውያን የችግሩን አሳሳቢነት ተረድተው እየወሰዱት ያለው እርምጃ ሊደነቅ ይገባል አሉ ሲሆን፣ የኢራቅ ፖለቲከኞች በአስቸኳይ ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲፈልጉ ጠይቀዋል።
ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ጦርነቱ በሺአ እና በሱኒ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች መካከል የሚደረግ ሲሆን፣ ሱኒዎች በሺአዎች በሚመራው የኑሪ አልማላቂ መንግስት በመገፋታቸው ጠመንጃ ለማንሳት ተገደዋል።
በብርሃን ፍጥነት ከተሞችን እየተቆጣጠሩ የመጡት ኤኢ ኤስ ኤስ ተዋጊዎች ወደ ባግዳድ እንደሚያቀኑም እየዛቱ ነው። ታጣቂዎቹ ባግዳድ አካባቢ ጦርነት የሚከፍቱ ከሆነ ከፍተኛ እልቂት ሊፈጠር እንደሚችል ታዛቢዎች ይናገራሉ።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ኩርዶች ከኢራቅ ተገንጥለው የራሳቸውን መንግስት የመመስረት ፍላጎታቸው ከፍ እያለ ነው።
የኢራቅ መንግስት ሳውድ አረቢያ አመጽያኑን ትረዳለች በማለት እየከሰሰ ሲሆን፣ ሱኒዎች ደግሞ የኢራንን ጣልቃ ገብነት አጥበቀው እየተቃወሙ ነው።  ኢራቅ እንደ ኢራን ሁሉ አብዛኛው ህዝብ የሺአ እምነት ተከታይ ነው።

Tuesday, June 24, 2014

Sudan death row woman Meriam Ibrahim 'detained'


Meriam Yahia Ibrahim Ishag, a 27-year-old Sudanese woman sentenced to hang for apostasyMeriam Ibrahim gave birth to a baby daughter in prison

Related Stories

A Sudanese woman freed from death row on Monday has been detained with her family at Khartoum airport, sources have told the BBC.
Meriam Ibrahim was sentenced in May to hang for renouncing Islam, sparking widespread outrage at home and abroad.
About 40 security agents detained Mrs Ibrahim - along with her husband, Daniel Wani and two children - at the airport, the sources said.
A top Sudanese official has told the BBC she would be freed "soon".
Abdullahi Alzareg from the ministry of foreign affairs told the BBC's Newshour programme that Mrs Ibrahim had been arrested because she did not have the correct travel documents.
Although she is Sudanese, she was using emergency South Sudanese papers with a US visa, he said.
She would be asked to get a passport and exit visa on her release, he added.
Mrs Ibrahim's husband is a Christian from what is now South Sudan and has US nationality.
One of Mrs Ibrahim's lawyers, el-Shareef Ali, told the BBC that her legal team is being denied access to her.
She was released from prison on Monday after an appeal court annulled the death sentence imposed on her.
Meriam Ibrahim with her husband (L), children and legal team after her release in Khartoum on 23 June 2014 Meriam Ibrahim with her husband Daniel Wani (L), children and legal team after her release in Khartoum
She was arrested in February, and gave birth to a daughter in prison not long after being sentenced.
The family has been taken to the headquarters of one of Sudan's security agencies, the sources said.
Before she was detained on Tuesday, Western countries had welcomed the decision to rescind the death penalty.
line
Analysis: James Copnall, former BBC Sudan correspondent
The National Intelligence and Security Service (NISS) is an extremely powerful body, which frequently intervenes in Sudanese politics.
It is a key part of the informal coalition - also comprising the military, Islamists and pragmatists - which rules Sudan.
The different components are constantly jockeying for a better position.
In recent times, NISS has been flexing its muscles.
It is very possible that NISS did not like the decision to release Meriam Ibrahim, and re-arresting her and her family was a way of making this point to the rest of the Sudanese government.
However, security is not a homogenous entity either.
It is also conceivable that one part of NISS accepted Mrs Ibrahim's release, while another section was not happy with it.
Mrs Ibrahim's release and re-arrest simply underlines the fact that there are many decision-makers in Sudanese politics, and they do not always agree with each other.
line
Born to a Muslim father, Mrs Ibrahim, 27, married Mr Wani in 2011.
Sudan has a majority Muslim population, and Islamic law has been in force there since the 1980s.
Even though Mrs Ibrahim was brought up as an Orthodox Christian, the authorities considered her to be a Muslim because that is the religion of her father.

Woyane is a dead and deadly regime walking


June 17, 2014
Ethiopians must be very attentive to safeguard the safety of our people and the integrity of our country from a dead and deadly regime walking. We must warn the officials and the cadres of the regime to abandon Woyane like their colleagues or ultimately pay for all the crimes of the Woyane. There would be no excuses not to abandon the regime and expect a safe haven to hide or run.
by Teshome Debalke
Ethiopians must be very attentive to safeguard the safety of our people
The defection rate of Woyane’s officials and cadres are increasing faster than ever. In recent news several individuals including the Deputy Communication Minster Ermias Legesse, the Federal Prosecutor Tewodros Behar, the Ethiopian Commodity Exchange Executive Director Anteneh Assefa, and the General Manager of the Endowment Fund for Rehabilitation of Tigray (EFFORT) Getachew Belay Wendimu is the sign of a dead and deadly regime walking.
The testimony of the former Deputy Communication Minster Ermias Legesse 1 2 3 / alone is sufficient to the extent of the crimes of Woyane to abandon it. Others choose to remain silent as cowards from telling what they know. They will be sought out as conspirators of the regime’s crime for the rest of their lives.
Things are not going well for Woyanes. Desperation is setting in among the officials and the rank and file of the cadres of ruling regime Woyane. They are searching for a place to run for dear life.
There are no armed oppositions surrounding them to surrender yet. There is no popular uprising to overthrow the regime yet. They are afraid of the same regime they have been serving most of their adult life going to use them as fall guys for its extensive crimes to buy time.
The inner circles of TPLF are scared to their pants from each other and are in a no-way-in no-way-out position the regime put them in. It is like being in hard place and a rock. The grandfather of Woyane Sibhat Nega is seen shuttling back-and-forth to calm down the Gangs of Adwa to stick with each other or else.
The ethnic puppets Woyane assembled and use to justify its crimes are in more crises than ever. Used and abused as front men by TPLF’s ethnic agenda, they sensed they are disposable to get out of the jam the regime got itself in to save face. Stuck from getting out of their predicament of serving the criminal enterprise of TPLF they are looking for escape route out of the reach of the regime’s assassins.
The vocal Diaspora apologists are also looking for an easy way out of their association with Woyane. With very little options for their transgression against the people of Ethiopia for far too long, economic growth and peace and stability became the only safe things to say to feel better. The popular badmouths of Woyane are also toning down their insult of Ethiopians on behalf of TPLF– sounding more patriotic that unite Ethiopians than Woyane lovers. If it wasn’t for the perk, they would have bailed out sooner than later singing Tobia Hagre woy mot.
The top enchiladas of the regime are also scrambling to stop the bleeding of Woyane by throwing all kinds of bizarre propaganda as they go. Accordingly, terrorist are surrounding us is becoming the quick way of buying time until they find a better diversion.
Other developments are, the numbers of Woyane’s officials’ family abounding the country to settle around the world. ’According to the advocacy groups that follow up these case most of the families of high officials are seeking residency permits as investors while the low ranked cadres are applying for political asylum. Sources inside the regime reviled the operatives of the regime are issuing passport and legal papers for substantial fee to smuggle officials to preferred destination of Western countries.
Others that fear Diaspora oppositions in Western countries prefer to migrate in African countries, South Africa in Africa and Thailand and Malaysia in Asia being the preferred destination.
As much as many corrupt officials and their families are free to migrate anywhere around the world with stolen public money without much challenge, oppositions rarely challenge them with all legal means available in the countries of their destinations.
Ethiopians have a long way to go to setup legal groups to challenge the officials of the regime and their families that committed crimes of atrocities and corruptions. Medias can’t any longer seat ideal and watch when the regime officials and their family launder public money in front of our nose. Political parties can no afford to squabble over minor differences than saving their country and protecting their people they want to rule. Individual Ethiopians no longer can pretend the little benefit they may have gotten from Woyane in a form of land is sufficient to abandon their people and country for the criminal enterprise of TPLF.
It is time to standup and be counted

የሶማሊው ክልል መሪ የመንግስት ደህንነቶች ሊገድሉዋቸው እንደሚችሉ በመጠቆም ጠባቂዎቻቸውን ቀየሩ


ሰኔ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሶማሊ ክልል መሪ አብዲ ሞሃመድ ኡመር የፌደራሉ መንግስት የደህንነት ሰዎች ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ በማለት ቀድሞ ሲጠብቁዋቸው የነበሩ ጠባቂዎቻቸውን በመቀየር አካባቢው በታማኞቻቸው በአይነ ቁራኛ እንዲጠበቅ እያደረጉ ነው።
ካለፉት ሳምንታት ጀምሮ ወደ የፕሬዚዳንቱ ቢሮ ወደሚገኝበት አካባቢ የሚዘዋወሩ ሰዎች ልዩ ፍተሻ እየተደረገባቸው ነው።
አቶ አብዲ ባለፈው ሳምንት ከ9 ዞኖችና ከ68 ወረዳዎች የተውጣጡ 1 ሺ 500 የሚሆኑ ከመላው ኦጋዴን የተውጣጡ የአገር ሽማግሌዎችን ሰብስበው ማእከላዊውን አስተዳደር የሚተቹ ንግግሮችን ተናግረዋል።
የደህንነት ሃላፊው ጌታቸው አሰፋ በሙስና የተበለሻ “ሌባ ነው” ሲሉ የፈረጁት አቶ አብዲ፣ ለፓስፖርት ማውጫ በሚል ከኦጋዴን ተወላጆች ገንዘብ እንደሚቀበሉ ለተሰብሳቢው ተናግረዋል።
“አትፍሩ የኢህአዴግ የደህንነት ሃይል በሙሉ ከክልላችን ተጠራርጎና ተሰባብሮ እንዲወጣ አድርጌዋለሁ፣ በክልሉ ያለሁት እኔ ነኝ” በማለት የተናገሩት አቶ አብዲ፣ ማንኛውም የአገር ሽማግሌ የኢህአዴግን የደህንነት ሃይሎች  እንዳይተባበር ጥሪ አቅርበዋል።
“ኢትዮጵያውያን አይወዱንም፣ መሬታችን እንጅ እኛን አይፈልጉንም፣ እንደሁለተኛ ዜጋም ያዩናል” ያሉት አቶ አብዲ፣ ህገመንግስቱ እስከመገንጠል የሚደርስ መብት ያጎናጸፋቸው መሆኑን ለሽማግሌዎቹ አስረድተዋል።
በከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ የሚገኙት ፕሬዚዳንቱ፣ የእጅ ስልካቸውን ከመቀየር ጀምሮ በግቢያቸው ውስጥ የሚካሄዱ ማንኛውንም አይነት እንቅስቃሴ  ክትትል እንዲደረግበት ትእዛዝ ሰጥተዋል። ለመንግስት ደህንነቶች ይሰራሉ ብለው የጠረጠሩዋቸውን ሰዎች ቢሮ ማዘጋታቸውም ታውቋል።
በጅጅጋ አንዳንድ አካባቢዎች በተለይ እርሳቸው ጫት በሚቅሙበት ቀበሌ 6 አካባቢ ከ11 ሰአት በሁዋላ የህዝቡ እንቅስቃሴ እንዲገታ የተደረገ ሲሆን፣ ወደ ከተማዋ የሚደረጉ ፍተሻዎችም ተጠናክረዋል።
በአቶ አብዲ እና በኢህአዴግ መካከል በተለይም በደህንነት ሹሙ ጌታቸው አሰፋ መካከል ልዩነት ተነስቶ እንደነበር ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል። በቅርቡ አልሸባብ በክልሉ በመንግስት ታጣቂዎች ላይ የፈጸመው ጥቃት በሀወሃት ባለስልጣናትና በአቶ አብዲ መካከል ያለውን ልዩነት ሳያሰፋው እንዳልቀረ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ገልጸዋል። አቶ አብዲ በከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንዲወድቁ ያደረጋቸውም የልዩነቱ መስፋት ሳይሆን አይቀርም።
በሌላ ዜና ደግሞ አቶ አብዲ የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት ተዳክሟል በማለት በተናገሩ ማግስት፣ ከደገሃቡር 1 ኪሜ ርቀት ላይ ኦብነግ በወሰደው ጥቃት 7 ሰዎች ተገድለው 9 ቆስለዋል።
ክፉኛ ከቆሰሉት መካከል የደገሃቡር የጸጥታ ሃላፊ አቶ  አሻርና የአካባቢው የልዩ  ሚሊሺአ አዛዥ ሙሀመድ ዳይክ ይገኙበታል። ሁለቱም ሰዎች ሲታከሙበት ከነበረው ደገሃቡር ሆስፒታል ወደ ካራማራ ሆስፒታል እንዲወሰዱ ተደርጓል።
ከትናንት በስቲያ ፕሬዚዳንቱ 100 የሚሆኑ የልዩ ሚሊሺያ አባላቱን ወደ አካባቢው መላካቸው ታውቋል።

የአንድነት የአዋሳ ሰልፍ “በእስር ተጀምሮ በእስር ተጠናቀቀ”


ሰኔ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት በሚል አንድነት ፓርቲ በአዋሳ ሊያካሂደው የነበረው ሰልፍ ፣ የሰልፉ አስተባባሪዎችና የፓርቲው የአመራር አባላት በመታሰራቸው ምክንያት ሳይካሄድ ቀረ።
ሰልፉ ከመካሄዱ አንድ ቀን ቀደም ብሎ በፓርቲው ቅስቀሳ የተደናገጡት የሚመስሉት የአዋሳ ባለስልጣኖችና ፖሊስ አባላት 37 የሚሆኑ በቅስቀሳ ላይ የተሰማሩ አመራሮችንና ደጋፊዎችን ይዘው በተለያዩ እስር ቤቶች አስረዋቸዋል።
በማግስቱ እስረኞችን ለመጠየቅና ስንቅ ለማቀበል ከሄዱት መካከልም አንዳንዶች መታሰራቸውን በስፍራው የሚገኘው የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ያሬድ አማረ ለኢሳት ገልጸዋል።
ከአዲስ አበባ የሄዱና የአዋሳ የፓርቲው አመራሮች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡና ክስ ሳይመሰረትባቸው በመታሰራቸው የረሀብ አድማ ያደረጉ ሲሆን፣ ዛሬ ሰኞ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ እየተጠበቀ መሆኑን አቶ ያሬድ አክለው ተናግረዋል።
መድረክ በአዋሳ በከፍተኛ ወከባ ውስጥ ሆኖ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጉ ይታወቃል። አንድነት ፓርቲ በተለያዩ ክልሎች እየዞረ በርካታ ህዝብ የሚሳተፍበት ሰላማዊ ሰልፎችን እያደረገ ነው። በአዋሳው ሰላማዊ ሰልፍ በኦሮሞ ወጣቶች ላይ የተወሰደው እርምጃ፣ የኑሮ ውድነት፣ ከማንነት ጋር በተያያዙ የሚታዩት የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እና የመሳሰሉት ጉዳዮች ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቅ ነበር።
አንድነት በአዋሳ ለሚያካሂደው የተቃውሞ ሰልፍ ለክልሉ መንግስት የእውቅና ደብዳቤ ያስገባው ከአንድ ወር በፊት ነበር። የከተማው ምክር ቤት እስካለፈው አርብ ድረስ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለመስጠት እየተነጋገርነበት ነው በማለት ሲያጓትተው ቆይቷል።
አንድነት ፓርቲ  በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ “በተለየ ሁኔታ በደቡብ ክልል እየታየ ያለው መንግስታዊ አፈናና ጸረ ህግ አቋም እንዲገታ ትግላችንን አጠናክረን እንቀጥላለን” ብሎአል።
“የስርዓቱ መንግስታዊ አፈናና ፀረ-ሕዝብ አቋም በመላ ኢትዮጵያ የተዘረጋ ቢሆንም ፓርቲያችን በእንቅስቃሴዎቹ ውስጥ እንደታዘበው በደቡብ ክልል በተለየ ሁኔታ ተጠናክሮ ቀጥሏል” ያለው አንድነት፣  “በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ ሹማምንቶች ባደረባቸው የገዥነት መንፈስ ሰላማዊ እንቅስቃሴዎችን በማፈንና ብሎም ያለምንም ማስረጃና ምክንያት ሰላማዊ ታጋዮችን ወደ እስር ቤት በመክተት ተግባራዊ እያደረጉት ” ነው ብሎአል።
በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ወደእስር ቤት መወሰዳቸውን፣ ቁጫ ላይ ተጠርቶ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍም እንዲሁ በጉልበት፣ በእስርና አፈና እንዳይካሄድ መደረጉን የገለጸው አንድነት፤ የክልሉ ዋና ከተማ በሆነችው አዋሳ የተጠራው ሰልፍ በህገወጥ እስር መጠናቀቁን ገልጿል፡፡
“በክልሉ ለመዝጋት እየተሞከረ ያለውን የህዝብ ጥያቄ ከህዝብ ጋር በመሆን መፍትሔ እንዲያገኝ እናደርጋለን” የሚለው አንድነት ጉዳዩን ወደ ህግ እንደሚወስደውም ገልጿል።
ያለምንም ወንጀል የታሰሩ አባሎቻችንና አመራሮቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳ እንዲፈቱ የጠየቀው ፓርቲው ፣ በደቡብ ክልል እየታየ ያለውን መንግስታዊ አፈናና ፀረ-ሕዝብ አቋም እንደሚታገለው አስታውቋል።ዘግይቶ በደረሰን ዜና ደግሞ በቅስቀሳ ላይ የነበሩት አመራሮች የዋስትና መብታቸውን ተከልክለው ወደ እስር ቤት እንዲመለሱ ተደርጓል።
መስተዳድሩ ከጻፈው ደብዳቤ ለመረዳት እንደሚቻለው ሰዎቹ የታሰሩት በህገወጥ መንገድ ሲቀሰቅሱ ተገኝተዋል በሚል ነው።      

የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኛውን የዘነጋው የኢትዮጽያ መንግሥት የሲቪል ሰርቪስ ቀንን እያከበረነው


ሰኔ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሠራተኛው በከፍተኛ የኑሮ ውድነት በደመወዝ መኖር የማይችልበት ስቃይ ውስጥ በሚገኝበትና ሲቪል ሰርቪሱ በገዥው ፓርቲ ቁጥጥር ሥር ሙሉ በሙሉ በወደቀበት በዚህ ወቅት ፣ ኢህአዴግመራሹ  መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናቱ በተገኙበት በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ የሲቪል ሰርቪስ ቀንን በድምቀት እያከበረውይገኛል፡፡
በየዓመቱሰኔ 16 ቀንየሚከበረውየሲቪልሰርቪስቀንዘንድሮለስምንተኛጊዜየሚከበረው “በተደራጀሲቪልሰርቪስለውጥሠራዊትፈጣንናቀጣይነትያለውልማትበተግባርእናረጋግጥ” በሚልመርህመሆኑታውቋል፡፡
የሲቪልሰርቪስዘርፉከፖለቲካጋርተቀይጦሠራተኛውየኢህአዴግአባልበመሆንናባለመሆንመካከልባለበትእንዲሁምበየተቋማቱሠራተኛውአንድለአምስትእንዲደራጅበማስገደድበከፍተኛቁጥጥርውስጥባለበትሁኔታሲቪልሰርቪሱበለውጥሂደትላይነውበሚልጉሮወሸባዩመያዙእንዳሳዘናቸውያነጋገርናቸውአንዳንድየመንግሥትሠራተኞችተናግረዋል፡፡”ሙስናናየመልካምአስተዳደርችግሮችንለመቅረፍየሚያስችልየለውጥሠራዊትለመገንባትበሚልአንድለአምስትእንድትደራጅትገደዳለህ፣እምቢካልክትገለላለህ፡፡በየቀኑተሰብስበህትወያያለህ፣ይህንንምሪፖርትታደርጋለህ፡፡በዚህሁኔታአንዱከአንዱእየተፈራራናእየተጠባበቀ፣ሰዎችበችሎታናበሜሪትሳይሆንበፖለቲካአቋማቸውብቻተጠቃሚየሚሆኑበትስርዓትእንዲሰፍንሆኗል፡፡በዚህምምክንያትየመንግሥትሥራናአገልግሎትአሰጣጥእያሽቆለቆለ፣ምርታማነትእንዲቀንስበማድረግየሠራተኛውንየስራዋስትናጭምርአሳሳቢደረጃላይአድርሶታል” ሲሉያነጋገርናቸውገልጸዋል፡፡
በመንግሥትሁለተኛደረጃት/ቤትየሚያሰተምሩአንድመምህርበሰጡትአስተያየትከሲቪልሰርቪሱሠራተኞችየመምህራንቁጥርከፍተኛመሆኑንአስታውሰውበአሁኑሰዓትመምህራንእጅግበአነስተኛደመወዝየሰቆቃህይወትእየመሩመሆኑንአስታውሰዋል፡፡ “እኔበማስተምርበትትቤትዲግሪያላቸውመምህራንኑሮአቸውንለመደጎምሲሉበሰፈርአካባቢየድለላስራላይጭምርመሰማራታቸውን፣አንዳንዶቹምበተለይየደመወዝመዳረሻሰሞንበጣምስለሚቸገሩከሥራገበታቸውበተደጋጋሚስለሚቀሩበመማርማስተማሩሒደትላይአሉታዊተጽዕኖእየደረመሆኑ እውነትነው” ብለዋል፡፡
ሌላበአንድየሚኒስትርመ/ቤትበሕዝብግንኙነትሙያላይየተሰማራባለሙያእንዳስረዳውበመ/ቤቱውስጥሲካሄድየነበረውየቢፒአርእናየቢኤሲሲየለውጥፕሮግራሞችሠራተኛውሊቀበለውባለመቻሉከፍተኛወጪወጥቶበትተግባራዊሊሆንእንዳልቻለአስረድተዋል፡፡
አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የዋጋ ንረት በማይፈጥር መልኩ የደሞዝ ጭማሪ ለማድረግ እንደታሰበ መናገራቸውን ዘግይቶ የደረሰን ዜና ያመለክታል። ስለደሞዝ ጭማሪው ዝርዝር የሰጡት ማብራሪያ የለም።

ከምዕራብ ወለጋ የተፈናቀሉ እና አሁንም በአካባቢው ያሉ ዜጎች ፍትህ ማጣታቸውን ተናገሩ


ሰኔ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ከምእራብ ወለጋ ዞን ጊምቢና ከቄለም ወለጋ ዞን የተፈናቀሉ አማርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ ያቀረበውን ዘገባ ተከትሎ ኢሳት ከጊምቢ በታች በሚገኘው አሹ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑትን እንዲሁም ተፈናቅለው ባህርዳር ከሚገኙት መካከል አንዳንዶቹን አነጋግሮ እንደተረዳው ፍትህ አጥተው የሚሰቃዩ ወገኖች በብዙ መቶዎች ይቆጠራል።
አሹ ቀበሌ ውስጥ የሚኖረው በንግድ ስራ የሚተዳደረው ወጣት እንደተናገረው ወንድሙ አካባቢውን ለቆ ባህርዳር ቢገባም፣ እርሱና ቤተሰቡ ግን ለመውጣት አልቻሉም። ” መውጣት መግባት አልቻንልም፣ ንብረት ተቃጥሎአል፣ ሰዎችም ተገድለዋል” የሚለው ወጣቱ፣ የአካባቢው ባለስልጣናት እጅ አለበት ብሎ እንደሚያምን ገልጿል። ድርጊቱን የሚፈጽሙትን ወጣቶች የሚያደራጁት ልዩ ሃይሎች፣ ፖሊሶችና ባለስልጣኖች መሆናቸውን ከድርጊታቸው መረዳት ይችላል ብሎአል
ተፈናቅለው ባህርዳር ከሚገኙት መካከል  ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገው ኢትዮጵያዊ ደግሞ ፖሊሶች ልበሳቸውን ቀይረው እየመጡ ድርጊቱን የሚፈጽሙትን እንደሚያበረታቱዋቸው ገልጿል
የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተፈናቃዮችን ቢያነጋገሩዋቸውም፣ ምንም አይነት መፍትሄ ሊሰጡዋቸው አለመቻላቸውን ተፈናቃዮች ተናግረዋል ጉዳዩን በማስመልከት ጥያቄ ያቀረብንላቸው የመኢአድ የሰሜን ቀጠና ሃለፊ ኢንጂነር ሽፈራው ዋሌ የክልሉ መንግስት ሰዎቹን በአድማ በታኝ ፖሊስ ከመስተዳድሩ አካባቢ እንዲርቁ ማድረጉን ገልጸዋል
ተፈናቅለው ወደ ባህርዳር ከመጡት መካከል አብዛኞቹ ሴቶችና ህጻናት መሆናቸውንም ኢ/ር ሽፈራው ገልጸዋል
በጉዳዩ ዙሪያ የአማራ ክልል እና የኦሮምያ ክልል ባለስልጣኖችን ለማነጋገር የተደረገው ሙከራ አልተሳካም። ይሁን እንጅ የኦሮምያ  የኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ራብያ ኢሳ ተፈናቃዮቹ መቶ የማይሞሉ መሆናቸውን ገልጸው ፣ አንድ የኦሮሞ ብሄር ተወላጅ እና 2 የሌሎች ብሄር ተወላጆች መሞታቸውን ገልጸው መንግስት ሌሎችም እንዳይፈናቀሉ፣ የተፈናቀሉትም እንደሚለሱ የአማራ ክልልና የኦሮምያ ክልሎች በጋራ እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል

አንድነት ፓርቲ በአዋሳ ለሚያደርገው የተቃውሞ ሰልፍ ችግር እንደገጠመው ታወቀ


ሰኔ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመጪው እሁድ በአዋሳ የሚካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ በቅስቀሳ ላይ የሚገኘው አንድነት፣ ሶሰትአባሎቹ እንደታሰሩበት አስታውቛል።
አዲስ አበባ መስተዳድር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ያሬድ አማረ በቅስቀሳ ላይ የነበሩ 3 ሰዎች መያዛቸውን ገልጸዋል።
መስተዳድሩ የሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ለመስጠት በሂደት ላይ በመሆኑ መቀስቀስ አትችሉም መባላቸውን የገለጹት አቶ ያሬድ፣ የእውቅና ጥያቄ ካስገቡ አንድ ወር ሞላቸው በመሆኑ በመስተዳድሩ የቀረበውን ምክንያት እንደማይቀበሉት ተናግረዋል።
የመስተዳድሩ ባለስልጣናት አዋሳ ከተማ ውስጥ የድምጽ ማጉያ  መጠቀም አይቻልም የሚል አቋም እንዳላቸው የገለጹት አቶ ያሬድ፣ ሰልፉን እሁድ እንደሚያካሂዱ በእርግጠኝነት ገልጸዋል።
አንድነት “የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት” በሚል አላማ ሰልፉን የሚካሂድ ሲሆን፣ በኦሮምያ መንግስት የወሰደውን እርምጃ፣ በክልሉ ከማንነት ጋር በተያያዘ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ፣ የሙስና መበራከትና ሌሎችም ጉዳዮች አንስቶ ያወግዛል።
መድረክ በቅርቡ በአዋሳ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጉ ይታወሳል።

አዲሱ የጉምሩክ ረቂቅ አዋጅ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በፍርቤቶች ሊወሰን የሚገባ ጉዳዮችን እንዲወስን የተለ የመብት መስጠቱ አነጋጋሪሆነ፡፡


ሰኔ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ረቂቅ አዋጁ ሰሞኑን ለፓርላማው የቀረበ ሲሆን በዚሁ አዋጅ በዋና ዳይሬክተሩ ውሳኔ ብቻ ክስ የማይመሰረትባቸው ድንጋጌዎች ማካተቱ በፓርላማ አባላቱ ዘንድ ጥያቄ አስነስቷል፡፡
ረቂቅአዋጁ “ለሕዝብጥቅምሲባል በዋና ዳይሬክተሩ ውሳኔ ክስ የማይመሰረትባቸው አዲስ ሁኔታዎች በሚል ከዘረዘራቸው ውስጥ ወንጀል ፈጽሞአል የተባለ ሰው በዕድሜ መጃጀት ወይም በበሽታ ምክንያት ጉዳዩን በፍርድ ቤት መከታተል የማይችል ሲሆን ፣ጉዳዩ በክስሒደትውስጥቢያልፍብሔራዊደህንነትንወይምዓለምአቀፍግንኙነትንይጎዳልተብሎሲታመን፣የክሱመመስረትተመጣጣኝናሚዛናዊያልሆነየጎንዮሽጉዳትየሚያስከትልመሆኑከታመነበት፣ወንጀሉስልጣንላለውፍርድቤትሳይቀርብበመቆየቱአስፈላጊነትያጣከሆነ ክስ እንዳይመሰረትዋና ዳይሬክተሩ ሊወስን እንደሚችል ደንግጎጓል፡፡
እነዚህ ድንጋጌዎች የፍርድ ቤቶች ሰልጣን እንጂ የአንድ መ/ቤት ሃላፊ ወይም ዋና ዳይሬክተር ስልጣን እንደማይሆን በመጥቀስ ድንጋጌዎቹ ለሙስናና ብልሹ አሰራር ቀዳዳ የሚከፍቱ ጭምር በመሆናቸው እንዲሻሻሉ አንዳንድ ፓርላማ አባላት ጠይቀዋል፡፡
በተለይየአንድሰውየዕድሜመጃጀትምሆነጉዳዩንበፍርድቤትቀርቦመከታተልአለመቻል የሕክምናማስረጃጭምርየሚፈልግጉዳይመሆኑንበመጥቀስይህጉዳይበዋናዳይሬክተሩውሳኔእንዲሰጥበትየተፈለገበትምክንያትግልጽአለመሆኑአስተያየትተሰጥቶበታል፡፡
ይህአዲስአዋጅጥፋቶችተፈጽመውበሚገኙበትጊዜአጥፊውንሁሉበቁጥጥርስርበማዋልጉዳዩለፍርድቤትቀርቦውሳኔእስኪያገኝሰዎችለእንግልትናእስርየሚዳረጉበትሁኔታንለማስቀረትአዋጁንበመተላለፍየሚፈጸሙጥፋቶችእንደክብደታቸውመጠንበአስተዳደራዊእናበእስርናበገንዘብቅጣትየሚታይበትሁኔታማካተቱእንደበጎጎንታይቶአል፡፡አዋጁለሚመለከተውቋሚኮምቴተመራሲሆንከሰኔ 30 በፊትይጸድቃልተብሎይገመታል፡፡

ሌ/ጄኔራል ዮሃንስ የጁባ የሰላም አስከባ ሃይል አዛዥ ሆኑ


ሰኔ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አስከባሪ ሃይል በአብየ አዛዥ የሆኑት ሌ/ጄ/ዮሃንስ ገብረመስቀል በደቡብ ሱዳን የሚመሰረተውን የሽግግር መንግስት ሂደት እንዲመሩ ተሹመዋል። ከ100 ያላነሱ ወታደሮች ደቡብ ሱዳን የገቡ ሲሆን፣ አዛዡም ጁባ መግባታቸው ታውቓል።
ጄ/ል ዮሃንስ በወር ከ20 ሺ የአሜሪካ ዶላር በላይ  እንደሚከፈላቸው የውስጥ ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። በአዲስ አበባ በተፈረመው የሰላም ስምምነት መሰረት በደቡብ ሱዳን አዲስ የሽግግር መንግስት ይመሰረታል።

በኢትዮጵያ 34 ድርጅቶች ጤፍ ወደ ውጭ በመላክ ላይ ናቸው


ሰኔ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመንግስት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የመንግስቱን የእርሻ ሰብል ድርጅት ጨምሮ 34 የንግድ ድርጅቶች ጤፍ ወደ ውጭ አገር በመላክ ላይ ናቸው።
መንግስት በአገሪቱ የጤፍ ምርት እጥረት ማጋጠሙን ተከትሎ ጤፍ ወደ ውጭ እንዳይወጣ አግዶ የነበረ ሲሆን እገዳውን ከ ግንቦት ወር 2005 ጀምሮ  አንስቷል።
አንድ ኩንታል ጤፍ በአዲስ አበባ ከ1800 እስከ 2000 ብር በመሸጥ ላይ ይገኛል።

በእነማይ ወረዳ የመኢአድ አባላት እየተዋከቡ ነው።


ሰኔ ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምስራቅጎጃም ዞን  በነማይወረዳደንጎሊማቀበሌ የሚኖሩት አቶሞሳአዳነቅዳሜሰኔ 7 ቀን በኢህአዴግ ታጣቂዎች ከተገደሉ በሁዋላ ሌሎችም አባሎች እየተዋከቡ መሆኑን የወረዳው የመኢአድ ተወካይ መቶ አለቃ ደመላሽ ጌትነት ተናግረዋል።
ግለሰቡ ገበያ ውሎ ሲመለስ አዲሱ ጫኔ እና ብርሃኑ ታምሩ የተባሉ ካድሬዎች መንገድ ላይ አስቁመው በዱላ ደብድበው እንደገደሉት የሟቹ ወገን የሆኑትና በህይወትና በሞት መካከል ባለ ጊዜ ደርሰው ቃሉን የተቀበሉት አቶ ይልቃል የሻነው ተናግረዋል።
አቶ ይልቃል እርሳቸውንም ለመግደል ሙከራ በመደረጉ አካባቢውን ለቀው መሰደዳቸውን ገልጸዋል። ፖሊስ ምንም የተጨበጠ መልስ እንዳለስጣቸውም አክለዋል
አቶይበልጣልወንድሜነህ የተባሉ በደብረጥሞና ቀበሌ የሚኖሩት ሌላው የመኢአድ አባል ደግሞ  መሣሪያ ደብቀሃል በሚል ቤታቸው ተከቦ እንደሚገኝ ግለሰቡ ግን ማምለጣቸውን መቶ አለቃ ደመላሽ ተናግረዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የወረዳውን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

ለመለስ ፋውንዴሽን ማሰሪያ እየተባለ በግዴታ የሚዋጣው ገንዘብ ፋውንዴሽኑን ለመስራት ከሚፈልገው በእጅጉ እንደሚልቅ ታወቀ


ሰኔ ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን በሚል በአገሪቱ ያሉ ወረዳዎች እያንዳንዳቸው በአማካኝ ከ17 እስከ 25 ሚሊዮን ብር ከህዝብ እንዲሰበስቡ ቢታዘዙም የሚዋጣው ገንዘብ ፋውንዴሽኑን ለመስራት ከሚፈለገው 300 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑን የሚናገሩት ምንጮች ትርፉ ገንዘብ የት እንደሚገባ እንደማይታወቅ ጠቁመዋል።
በአማራ ክልል  106 ወረዳዎች ያሉ ሲሆን ለፋውንዴሽኑ ማሰሪያ 2 ቢሊዮን 600 ሚሊዮን ብር ያላነሰ ገንዘብ ይሰበሰባል። በኦሮምያ ደግሞ ከ205 በላይ ወረዳዎች ሲኖሩ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ይሰበሰባል። በትግራይ ከ38 ወራዳዎች ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ ፣ በደቡብ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ ሲዋጣ፣ በአዲስ አበባ የሚወጣው ደግሞ እስከ 2 ቢሊዮን ብር ይደርሳል። በመላ አገሪቱ  በሚገኙ ወረዳዎች ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ የሚወጣ ሲሆን፣ ለፋውንዴሽኑ ከተበጀተው 300 ሚሊዮን ብር ውጭ ያለው ከ9 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ የት እንደሚገባ እንደማይታወቅና ቁጥጥር የሚያደርግ አካል አለመኖሩንም ምንጮች ገልጸዋል።
ደሃውበምግብውድነት: ነጋዴውበግብር አርሶአደሩ በማዳበሪያ እዳ እየተሰቃዩ ባለበት ጊዜ ይህን መክፈል አይቻልም በማለት ተቃውሞ ያስነሱ ሰዎች፣ ተቃውሞቸአውን የሚሰማቸው አካል አላገኙም። አንዳንድ  ዜጎች ገንዘብ የከፈሉበትን ደረሰኝ ለኢሳት በመላክ፣ ዝርፊያው እንዲቆም ህዝቡ ተቃውሞ እንዲያሰማ እየጠየቁ ነው።
የመለስ ፋውንዴሽን፣ የቀድሞውን ጠ/ሚ መለስ ዜናዊን የሚዘክሩ ስራዎችን የመስራት አላማ አለው። ፋውንዴሽኑ በህዝብ ፈቃድ እና ከመንግስት በሚሰጥ ገንዘብ ይሰራል ተብሎ ቢነገረም፣ ህዝቡ  ለማዋጣት ፈቃደኛ ባለመሆኑ በግዴታ እንዲያዋጣ እየተደረገ ነው። ከህዝብ ፈቃድ ውጭ የተሰራ ፋውንዴሽን ፣ ኢህአዴግ እስካለ ጊዜ ብቻ እንደሚቆይ የሚናገሩት አስተያየት ሰጪዎች፣ ፋወንዴሸኑ ከደሃው ኢትዮጵያዊ ገንዘብ መሰብሰቢያና ሃብት ማካበቻ መሆኑንም አክለዋል።

የዋስትና መብት የተነፈጉ ነጋዴዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ


ሰኔ ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሃረር በቅርቡ ከተነሳው ቃጠሎ ጋር በተያያዘ በእስር ላይ ከሚገኙት ከ20 በላይ ነጋዴዎችና ሰራተኞች መካከል ፍርድ ቤት የቀረቡት 3ቱ ተከሳሾች እንደገና ሌላ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል።
የ25  አመቱ  ቢኒያም ጌታቸው፣ የ28 አመቱ ሲሳይ አሊ አህመድ እና የ16 አመቱ  ዙቤር  አህመድ  በ1996 ዓም የወጣውን የወንጀል ህግ በመተላለፍ ” በፌደራል ህገመንግስት የተቋቋመውን የሃረሪ ህዝብ ክልል መንግስት ፣ በዚህ ክልል መንግስት የተቋቋሙትን የአስፈጻሚ አካላትን የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞች መስሪያ ቤቱ የእለት ተእለት ስራውን በተለይም የትራንስፖርት  መገናኛ ጽ/ቤት ባለስልጣን እና ሰራተኞች እንዲሁም የክልሉ ፖሊስ ሃይል አባላት የሃረር ብሀረሰብ እና ሰራተኞች በፌደራልና በክልል ህገመንግስት የተሰጣቸውን የማስተዳደር ስልጣን ለማደናቀፍ ተከሳሾች መጋቢት 1/2006 ዓም ከጠዋቱ ከ3፡00 እስከ 7 ሰአት ባለው ጊዜ በቀበሌ 14 ውስጥ በሚገኘው የትራንስፖርትና መገናኛ ጽ/ቤት እና ፊት ለፊቱ ባለው መንገድ ከ300 እስከ 500 የሚሆኑ ህወገወጥ ስለፈኞችን በመምራት በዛቻ፣ መንገድ በመዝጋት፣ ድንጋይ በመወርወር የመንግስት ሰራተኞች እና የክልሉ ነዋሪዎች ወደ እለት ስራዎች እንዳይሄዱ በመከላከል በመንገድ ትራንስፖርት መገናኛ ጽ/ቤት ላይ ግምቱ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ እና እንዲደርስ በማድረግ፣ አንድን ብሄረሰብ ነጥሎና ፖሊስን በመሳደብ፣ የመንገድ ትራንስፖርት መገናኛ ጽ/ቤት በእሳት ለማጋየት በሞመከር የክልሉን ሰንደቃላማ ከተሰቀለበት በማውረድ የመንግስትና የህዝብ ንብረት በማውደም የክልሉን ህገመንግስታዊ ተግባርን በማደናቀፍ ወንጀል” መከሰሳቸውን የክስ ቻርጁ ያመለክታል።
በተለይ አንደኛው ተከሳሽ ቢኒያም ጌታቸው የሃረሪ ክልልን ሰንደቃላማ በንቀት ከተሰቀለበት በማውረድና በማቃጠሉ የመንግስት ምልክት በመድፈር ወንጀል መከሰሱን የክስ ጃርጁ ያመለክታል።
ሶስቱም ተከሳሾች ” የሃረሪ ክልል ባለስልጣኖችን፣ ያሃረሪ ፖሊስን፣ የሃረሪ ብሄረሰብን ሌባ በማለት የሃሰት ወሬዎችን በመንዛት የፖለቲካና የዘር ጥላቻን በመቀስቀስ በፈጸሙት የሃሰት ወሬዎችን በማውራት ህዝብን በማነሳሳት ወንጀል መከሰሳቸውንም የክስ ቻርጁ ይዘረዝራል። ተከሳሾች በበኩላቸው የሃረሪን መንግስት እንጅ ህዝቡን አልተሳደብንም በሚል እየተከራከሩ ነው።
ፍርድ ቤቱ የዳኛ እጥረት አለብን በሚል ለሃምሌ 24 ቀጠሮ ሰጥቷል። በ20 ሰራተኞችና ነጋዴዎች ላይ የተመሰረተው ክስ ደግሞ ሰኔ 20 ቀን እንደሚታይ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ቻርለስ ቴለር ወደ አፍሪካ ሄደው የእስር ጊዜያቸውን እንዲፈጽሙ ጠየቁ


ሰኔ ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የላይቤሪያ መሪ ቻርለስ ቴለር በሴራሊዮን እኤአ ከ1991-2002 በነበረው የእርስ በርስ ጦርነት እጃቸው አለበት በሚል በሄግ ኔዘርላንድስ በተቋቋመው ልዩ ፍርድ ቤት  የ50 አመት እስር ተፈርዶባቸዋል።
የእስር ጊዜያቸውን በእንግሊዝ የሚያሳልፉት ቴለር፣ 15 ልጆቻቸውን በየጊዜው ለማየት ባለመቻላቸው ወደ ሩዋንዳ ተወስደው እንዲታሰሩ ጥያቄ አቅርበዋል።
ከቤተሰቦቻቸው እርቀው እንዲታሰሩ መደረጉ አለማቀፍ ህግን የሚጥስ መሆኑን የቴለር ጠበቆች ተናግረዋል። ይሁን እንጅ የእንግሊዝ መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ የሰጠው አስተየያት የለም።
ቻልረስ ቴለር በሰሩት ወንጀል የተቀጡ የመጀመሪያው አፍሪካዊ መሪ ናቸው። በስልጣን ላይ ካሉት መሪዎች መካከል የሱዳኑ ጄኔራል አልበሽር በአለማቀፍ ፍርድ ቤት የሚፈለጉ ሲሆን፣ የኬንያው መሪ ኡሁሩ ኬንየታና ምክትላቸው ዊሊያም ሩቶም ጉዳያቸው ዘሄግ በሚገኘው ፍርድ ቤት እየታየ ነው።

በኦሮምያ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ከታሰሩት መካከል አንዳንዶች ሲፈቱ ሌሎች ደግሞ ፍርድ አጥተው እየተሰቃዩ ነው


ሰኔ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ በኦሮምያ ተነስቶ የነበረውን ተቃውሞ ተንተርሶ ከተያዙት በሺ ከሚቆጠሩ ወጣቶች መካከል የተወሰኑት ከእስር ሲለቀቁ፣ አብዛኞቹ አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ።
የክልሉ ወኪላችን እንደሚለው በወለጋ፣  በአንቦና አጎራባች ወረዳዎች የታሰሩ በርካታ ወጣቶች አሁንም ፍትህ አጥተው በእስር ላይ ሲሆኑ በቡራዩ ታስረው ከነበሩት መካከል 3ቱ ዛሬ በዋስ ተለቀዋል። ጋዲሳ ጉደታ፣ ቱፋ በክሩ እና ጉዲሳ ድሪባ የተባሉት ተከሳሾች ዛሬ ከእስር ሲለቀቁ፣ ዳውድ ሃሰን የተባለው ደግሞ ከሳሽ አጥቶ ወደ እስር ቤት እንደሚለስ ተደርጓል። የዞኑ ፍርድ ቤት የዳውድ ክስ አይመለከተኝም ያለ ሲሆን፣ የወረዳው ፍርድ ቤትም ክስ እንደማይመሰርትበት አስታውቋል። ዳውድ ፍትህ አጥቶ በእስር ቤት እንዲቆይ በመደረጉ በከፍተኛ ሁኔታ የስሜት መረበሽ አጋጥሞት እንደነበር ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ሰዎች ለወኪላችን ገልጸውለታል።
በደዴሳና በአምቦ እስር ቤቶች የታሰሩ ወጣቶች አሁንም በፍትህ እጦት እየተሰቃዩ መሆኑን ወኪላችን አክሎ ገልጿል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአዲስ አበባ መስተዳድር በከተማዋ አዲስ ማስተር ፕላን ዙሪያ ውሳኔ ሰጥቶ ወደ ተግባር ለመንቀሳቀስ አለመቻሉን የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል።
እንደምንጮች ገለጻ ከፍተኛ ተቃውሞ ያስነሳውን የከተማዋን ካርታ ከመጪው ምርጫ በፊት  ተግባራዊ ማድረግ የአካባቢውን ህዝብ ቁጣ የሚቀሰቅስ በመሆኑ እስከ ምርጫ 2007 ጉዳዩን ላለማንሳት ሊወስን ይችላል።

የሞያሌ ነዋሪዎች የደህንነት ክትትሉ እንዳስመረራቸው ገለጹው


ሰኔ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-2 የአልሸባብ አባላት ናቸው የተባሉ የሶማሊ ተወላጆች መያዛቸውን መንግስት ካስታወቀ በሁዋላ፣ በኢትዮጵያዋ የድንበር ከተማ ሞያሌ ከፍተኛ ጥበቃ እየተካሄ መሆኑንና በዚህም የተነሳ መንግስት በህዝቡ ላይ የሚያደርገው ክትትል እንዳስመረራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።
መውጫ መግቢያ ማጣታቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ የደህንነት ሃይሎችና ታጣቂዎች ማታ ማታ በግለሰቦች ቤት ሳይቀር እየገቡ ፍተሻ ያካሂዳሉ ብለዋል።
በምሽት ለመውጣት መቸገራቸውን የሚገልጹት ነዋሪዎች፣ የአካባቢውን ታጣቂዎች ከፊት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ደግሞ ከሁዋላ ሆነው ቁጥጥር እንደሚያደርጉ፣ በከተማው ሰአት እላፊ ሳይታወጅ፣ ህዝቡ እንደልቡ መንቀሳቀስ እንዳይችል እንደተደረገ አክለዋል።
የአልሸባብ ታጣቂዎች በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ሰርገው በመግባት 33 የኢትዮጵያ ታጣቂዎችን ከገደሉ በሁዋላ በሁለቱ ክልሎች ያለው ጥበቃ ተጠናክሮአል።
የኢትዮጵያ ጦር ካለፉት 2 አመታት ጀምሮ በሶማሊያ ውስጥ እንደሚገኝ ይታወቃል። መንግስት በተደጋጋሚ አልሸባብ እንደተደመሰሰ ቢያውጅም፣ ታጣቂ ሃይሉ ግን አሁንም በኬንያና በሞቃዲሾ ከፍተኛ ጥቃት እየፈጸመ ይገኛል።

የአዳዲሶቹ የስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ መጓተቱትን መረጃዎች አመለከቱ

ሰኔ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዳዲስ የስኳር ፋብሪካዎች ፕሮጀክቶችና የነባር የማስፋፊያ ፕሮጀክቶች የግንባታ ስራዎች አፈጻጸም እጅግ ደካማ መሆኑን ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ጠቁሟል።
ለዚህደካማአፈጻጸምሚኒስቴሩበዋንኛነት ያስቀመጠውምክንያትከስራውስፋትናውስብስብነትአንጻርያጋጠመውትልቅየማስፈጸምአቅምማነስነውብሏል፡፡በቀጣይዓመትበሚጠናቀቀውየመንግስትየዕድገትናየትራንስፎርሜሽንዕቅድየመጀመሪያዎቹሶስትዓመታትማለትምከ2003-2005 ኣ.ምየአዳዲስስኳርልማትፕሮጀክቶችየሚካሄዱትከዚህበፊትምንምየመሰረተልማትባልተዘረጋባቸውናለግንባታስራየሰለጠነየሰውኃይልበማይገኝባቸውአካባቢዎችበመሆኑበዕቅድዘመኑውስጥየመጀመሪያዎቹሁለትዓመታትማለትም 2003 እና 2004 የመንገድናሌሎችየአዋጪነትየጥናትስራዎችመከናወናቸውንመረጃውይጠቅሳል፡፡
በመሆኑምበእነዚህኣመታትለቀጣይስራመደላድልከመፍጠርባለፈተጠናቅቆ ወደምርትየገባፕሮጀክትአልነበረም፡፡ የነባርስኳርፋብሪካዎችየማስፋፊያፕሮጀክቶችየግንባታስራዎችመካከልየወንጂናየፊንጫስኳርፋብሪካዎችተጠናቅቀውበ2005 ኣ.ምወደስራየገቡሲሆንየተንዳሆስኳርፋብሪካበዚህዓመትወደስራእንደሚገባመረጃውይጠቅሳል፡፡
አዳዲሶቹስኳርፋብሪካዎችማለትምኩራዝ፣የጣናበለስእናወልቃትየመስኖመሰረተልማትግንባታ፣የመሬትዝግጅትናየሸንኮራአገዳተከላ፣የፋብሪካናየመኖሪያቤትግንባታዎችእየተከናወኑቢሆንምአፈጻጸማቸውበዝቅተኛደረጃላይእንደሚገኝተመልክቷል፡፡
በዚህምምክንያትፕሮጀክቶቹየዕድገትናየትራንስፎርሜሽንእቅዱ በሚጠናቀቅበትበቀጣይአንድኣመትጊዜያትእንደማይደርሱከወዲሁተረጋግጦአል፡፡
በአንድወቅትየስኳርኮርፖሬሽንዳይሬክተርየነበሩትአቶአባይጸሐዬየስኳርፋብሪካዎቹበዘርፉልምድ ባለመኖሩምክንያትየማስፈጸምአቅምማጋጠሙንአምነው  “እየተማርንበመስራትላይነን” በማለትበፓርላማመድረክያደረጉትንግግርበሃገርሐብትመቀለድነውበሚልከፍተኛትችትአስከትሎባቸውእንደነበርየሚታወስነው፡፡
በሌላ ዜና ደግሞ በውጭሃገርካሉኢትዮጵያዊያንእናመንግስታዊያልሆኑድርጅቶችአማካይነትወደ ሃገርውስጥየሚገባውሃዋላየወጪንግዱንገቢእየተገዳደረውመሆኑንከብሔራዊባንክየተገኘመረጃጠቆመ፡፡
እየተገባደደባለውየኢትዮጵያዊያን 2006 በጀትዓመትዘጠኝወራትከሸቀጦችኤክስፖርት 2  ቢሊየንዶላርሲገኝከግልሃዋላምተቀራራቢበሆነመልኩ 2 ቢሊየንዶላርተገኝቷል፡፡
አምናበ2005 በጀትዓመትሃገሪቱከሸቀጦችንግድ 3 ቢሊየንየአሜሪካንዶላርስታገኝከግልሃዋላደግሞ 4ቢሊየንዶላርማግኘትዋንመረጃውንይጠቅሳል፡፡
የባንኩመረጃእንደሚያሳየውበውጪአገርየሚኖሩኢትዮጵያዊንለወገኖቻቸውንናለተለያዩስራዎችማስኬጃወደሃገርውስጥየሚያስገቡትዶላርበዓመትእስከ 20 በመቶእያደገየመጣሲሆንበአንጻሩበቡናኤክስፖርትላይብቻየታሰረውየወጪንግዱእያሽቆለቆለመምጣቱንመረጃውያሳያል፡፡
የዚህዓመትየዘጠኙወራትኤክስፖርትገቢካለፈውዓመትተመሳሳይናከተያዘውዕቅድጋርሲነጻጸርአፈጻጸሙዝቅተኛመሆኑንየጠቀሰውየብሔራዊባንኩመረጃይህምሊሆንየቻለውበዓለምገበያላይበዋንኛነትየቡናናወርቅእንዲሁምየስጋምርቶችዋጋበማሽቆልቆሉነው፡፡

በኬንያ የሽብር ጥቃት ፈጽመዋል የተባሉ በርካታ ሰዎች ታሰሩ


ሰኔ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ እንደዘገበው በላሙ የወደብ ዳርቻ ሰሞኑን የተፈጸመው ጥቃት የ60 ሰዎችን ህይወት አጥፍቷል። ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጥቃቱን የፈጸመው አልሸባብ አለመሆኑን ገልጸው ነበር። ጥቃቱ በአልሸባብ እንደተፈጸመ ተደርጎ መረጃውን ያሰራጨውን ሰው መያዙም ተገልጿል።
ግድያው ከጎሳ ፖለቲካ ጋር የተያያዘ እንደሆነ የአገሪቱ መንግስት ገልጿል። ሰሞኑን በተፈጸመው ጥቃት ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪ 12 ሴቶችም ታፍነው ተወስደዋል። ታፍነው የተወሰዱት ሴቶች የት እንደገቡ የታወቀ ነገር የለም።
ኬንያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ሃይሎች ተደጋጋሚ ጥቃት እየደረሰባት ነው።

የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉት ዜጎች ለክስ የሚያበቃ በደል አልደረሰባቸውም አለ።


ሰኔ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎች በተወካዮቻቸው አማካኝነት የመሰረቱት ክስ በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 8ኛ ፍትሃ ብሄር ምድብ በዋለው ችሎት የታየ ሲሆን ፣ በቀረበው ክስ ላይ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴርና የቤንሻንጉል ክልል መንግስት መልስ ሰጥተዋል።
ከሳሾች ለበርካታ አመታት ከኖሩበት ቀየ በህገወጥ መንገድ በመፈናቀላቸው ሃብትና ንብረታቸውን ማጣታቸውን በጠበቃቸው አማካኝነት ተናግረዋል።
የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በበኩሉ ከሳሾቹ ቤት ንብረት አለማፍራታቸውን ጠቅሶ፣ ምንም ለክስ የሚያበቃ ነገር ሳይኖራቸው ጉዳያቸው ለፖለቲካ ፍጆታነት እየዋለ ነው በማለት መልስ ሰጥቷል።
በጉዳዩ ዙሪያ ላይ ያነጋገርናቸው ጠበቃው ዶ/ር ያእቆብ ሃይለማርያም  የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ‘ጉዳዩ የሚመለከተው የክልሉን መንግስት እንጅ የፌደራሉን አይደለም’ በማለት የሰጠው መልስ ትክክል አለመሆኑን ተናግረዋል። የህገመንግስቱ አንቀጽ 52 ማንኛውም የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲፈጸም የፌደራል መንግስቱን እንደሚያገባው፣ በዚህም የተነሳ የፌደራል መንግስቱ አይመለከተኝም ማለት እንደማይችል ገልጸዋል።
ዶ/ር ያእቆብ   ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ ‘ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ሰዎች እንዲፈናቀሉ ያደረጉትን ለፍርድ እናቀርባለን’ በማለት ተናግረው  እንደነበር አስታውሰዋል። አሁን እየታየ ያለው ግን የዚህ ተቃራኒ ነው ነው ሲሉ አክለዋል።

ከቁጫ የአገር ሽማግሌዎች በድጋሜ ለአቤቱታ ሊሄዱ ነው።


ሰኔ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በቁጫ ወረዳ በቅርቡ ከተነሳው የመልካም አስተዳደር ፣ የማንነትና የፍትህ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ፍትህ አጥተው ያለፉትን ስምንት ወራት በእስር ቤት ካሳለፉ ትመካከል የ14 የቤተሰብ አባላት አስተዳዳሪ የሆኑት የ39 ዓመቱ አቶ ሻልሼሸዋ ከሞቱና የሌሎችም እስረኞች ህይወት አደጋ ላይ በመውደቁ እንዲሁም በአካባቢው ድጋሜ ግጭት ይነሳል የሚል ስጋት በመፍጠሩ 4 የአገር ሽማግሌዎች ጉዳዩን ለፌደራሉ መንግስት በድጋሜ ለማመልከት ወደ አዲስ አበባ መንቀሳቀሳቸው ታውቋል።
ሁለት ሴቶችና 2 ወንዶች የሚይዘው የአገር ሽማግሌዎች ቡድን በአካባቢው ስላለው ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰትና በእስር ቤት ውስጥ ስለሚፈጸመው ግፍ ለመንግስት ባለስልጣናት የማሰማት እቅድ አለው።
ከዚህ ቀደም በህዝብ ተወክለው ጉዳያቸውን ለጠ/ሚንስትሩ ቢሮ ሲያቀርቡ የነበሩ የአገር ሽማግሌዎች አብዛኞቹ መታሰራቸው ይታወቃል።
300 ዎቹእስረኞች በአርባምንጭ እስር ቤት በህክምና አድሎአዊ በሆነ አያያዝ ከፍተኛ የሆነ መጎሳቆል እየደረሰባቸው መሆኑን ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል።

የጋዝጊብላ ነዋሪዎች ኢህአዴግ ክዶናል ሲሉ ተናገሩ።


ሰኔ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ከትግራይ ህዝብ በመቀጠል ኢህአዴግ ወደ ስልጣን እንዲመጣ ከፍተኛ የህይወት መስዋትነት የከፈለው የሰቆጣና አካባቢዋ ነዋሪዎች ቢሆኑም፣ ኢህአዴግ አዲስ አበባ ከገባ ጀምሮ እንደረሳቸው ገልጸዋል።
ከሶቆጣ 48 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘዋ ጋዝጊብላ ወረዳ የሚኖሩ የቀድሞ ታጋዮች ለኢሳት እንደገለጹት፣ ለኢህአዴግ ልጁን ያልገበረ ሰው ባይኖርም፣ ባለስልጣናቱ ግን ውለታቸውን መርሳታቸውን ተናግረዋል።
ከሰቆጣ ላሊበላ የህዝብ ትራንስፖርት አለመኖሩን ፣ ከአዲስ አበባ ሰቆጣ ደግሞ አገር አቋራጭ አውቶቡሶች ያልተመደቡ መሆናቸውን የሚገልጹት ነዋሪዎች ከአዲስ አበባ ሰቆጣ ለመድረስ ደሴ ከተማ ላይ እስከ 4 ቀናት መጠበቅ ግድ እንደሚላቸው ተናግረዋል። ከ 17 አመታት በፊት የተጀመረው ከአለም ከተማ ወደ ላሊበላ የሚወስደው መንገድም በአየር ላይ መቅረቱን ገልጸዋል። ህዝቡ ተቃውሞ ሲያሰማ ” ዛሬ ነገ ይሰራል” በማለት እንደሚደልሉት የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ መንግስት ለጥያቄያቸው መልስ ከመስጠት ይልቅ ህዝቡን መከፈፋል መምረጡን ገልጸዋል።
አቶ በረከት ስምኦንና ሌሎች ባለስልጣኖች ሲመጡ የህዝቡን ችግር ሰምተው እንዳልሰሙ ሆነው እንደሚያልፉት ነዋሪዎች ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ህዝብ ከዋግ ህዝብ ትምህርት ይውሰድ የሚሉት ነዋሪዎች፣ በተለይ የድሮ ታጋዮች በረንዳ ላይ መውደቃቸውንና የሚሰማቸው ማጣታቸውን ገልጸዋል።

በኬንያ በርካታ ሴቶች ታፍነው ተወሰዱ።


ሰኔ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አልሸባብ እንደፈጸመው በተጠቀሰው ጥቃት 48 ሰዎች በተገደሉ ማግስት፣ ሌሎች ተጨማሪ 12 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፣ ከ12 ያላነሱ ሴቶችም በታጣቂዎች ታፍነው መወሰዳቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
ምፔኬቲኒ እየተባለ በሚጠራው የወደብ ከተማ ላይ የደረሰውን ተከታታይ ጥቃት አልሸባብ እንደፈጸመው እየተዘገበ ባለበት ወቅት፣ የአገሪቱ መሪ ኡሁሩ ኬንያታ ፣ ጥቃቱ በራሳቸው ባለስልጣናት የተቀነባበረና ከጎሳ ጋር የተያያዘ መሆኑን በመግለጽ፣ አልሸባብ ፈጸምኩ የሚለውን ጥቃት አስተባብለዋል።
በአካባቢው የሚገኙ የፖሊስ አዛዦች ከሃላፊነት እንዲነሱ ያደረጉት ፕሬዚዳንቱ ለፍርድ እንደሚቀርቡም ተናግረዋል።
አልሸባብ በበኩሉ ኬንያ ጦሩዋን ከሶማሊያ እስካላስወጣች ድረስ ጥቃቱ እንደሚቀጥል ተናግሯል።

Saturday, June 21, 2014

Building Free African Futures (Prof Mammo Muchie)

Feature-Pan01By Prof Mammo Muchie
Profile-Pan02
Prof Mammo Muchie
Projecting a future can provide agency to realise what is selected to be addressed or do the exact opposite. Instead of projecting a future, what may be more sensible is to create a future by making it change both the makers as well as the destination.
In this OAU/AU@50 Jubilee, the question of whether Africans know where they have been, where they are now and where they are able to go is critical to reflect upon and to chart a future that will close all varieties of coloniality for good and open a free, prosperous, spiritual, humane and free and independent future. Africa’s new relationship with the rest of the world will be born when Africans learn to neutralise the harm that the unholy trinity of loans, aid and debt has done to them. How can Africa construct a future by creating a Pan-African monetary union to forge an integrated relationship with each other in order to relate with the rest of the world on equitable, fair and just principles and values and not through dependence and subordination as it is broadly understood to be now? Africa’s new relationship with the rest of the world will be born when Africans learn to neutralise the harm that the unholy trinity of loans, aid and debt has done to them. One key initiative African leaders can take collectively is to establish a dual currency system that can largely self-finance an integrated African development. The currency for the domestic economy should be an inconvertible people’s money. The existing state currencies that are not exchanged directly with each other, and whose exchange rate is mediated with the dollar, the franc and the Euro, should give way to direct exchanges based on a fair settlement of the appropriate par value. Naturally, diversities, inequalities, different levels of development, differing attitudes and interests present problems in constructing a workable unified currency system. It is precisely to deal with these varied problems that Africa needs a currency system to create liquidity. The direct exchange of local currencies promotes the exchange of private labour across Africa. The exchange of the local to local currency via a global currency continues to fragment Africa and integrate discrete interests and regions with the world economy. The key is to find strategies for Africa to integrate with a world economy as a whole and not in parts. The domestication of the foreign orientation of the existing national currencies is necessary to make Africa re- link with the world economy on its own terms and not terms dictated by others. Monetary union is a key strategy to bring about a new relationship. Its proper construction requires bountiful political will that we cannot take for granted exist given the ties and propensity of the existing states not to pursue real collective action that matters. Differences in economic size and significance of the existing 54 states cannot be shunned aside. In principle, large and small economies can enter into a unified system without loss. As long as a situation of ‘being better off for some without being worse off for all’ exists for all those embarking on currency union, negotiations for a peaceful and evolutionary monetary system can proceed. At all costs states should not demand parity between large economies and small economies. The objective is in the end to evolve into a unified market, unified currency area and unified economic zone. However, the move must be sensible and realistic and various domestic constituencies and their external supporters within the existing states have to be brought along by initiating a programme of fair, gradual and transparent African-wide currency or monetary union. If the cost and benefits for the various sections of social groups can be fairly worked out, possibilities exist even to neutralise transnational, supranational actors, who will no doubt be worked up by the suggestion for an African monetary union.

WFP Ethiopia Warns of Funding Shortfall to Respond to Sharp Influx of South Sudanese Refugees



othieing croppedAddis Ababa — As South Sudanese continue to flee their conflict-torn homeland, the United Nations World Food Programme in Ethiopia marks World Refugee Day with an urgent appeal for US$50 million to meet the needs of nearly 150,000 who have sought shelter here since the conflict began in December 2013-and for our larger refugee response.
“Thanks to its generous open-door policy, Ethiopia currently hosts the largest number of South Sudanese refugees of any neighbouring country,” said WFP Ethiopia’s Country Director, Abdou Dieng. “If WFP is to meet their food and nutritional needs, we need a massive and rapid influx of funds. Otherwise, we risk running out of food for our refugee operation in Ethiopia by the end of August.”
In Rome, WFP Executive Director Ertharin Cousin highlighted the devastating fallout of the humanitarian crises in South Sudan and in several other nations where conflict has uprooted millions. Roughly 45.2 million people are forcibly displaced worldwide, including half-a-million people who have fled the renewed violence in Iraq, according to the UN refugee agency, UNHCR.
Working with the UNHCR and other partners, WFP assisted 4.2 million refugees and 8.9 million internally displaced people around the world in 2013.
“As the newly displaced join the ranks of those already forced from their homes by conflict or natural disaster, no one should feel alone and without help. No refugee should ever feel forgotten,” Cousin said. “Together with our colleagues at UNHCR, partner organizations and donor governments around the world, we are diligently responding to their urgent and life stabilizing needs.”
In Ethiopia, WFP assists roughly 550,000 refugees from neighbouring countries, including the latest influx of asylum-seekers from South Sudan. At the border points, we are distributing calorie-packed High Energy Biscuits to give an immediate boost to the many South Sudanese who arrive here exhausted and famished, after walking for days to reach safety.
WFP also distributes rations of grains, pulses, vegetable oil, sugar and salt at camps and border points. And we are providing special nutritional supplements to counter often alarmingly high malnutrition rates among the most vulnerable, notably young children, pregnant women and nursing mothers.
“The fighting has prevented people from planting their fields,” WFP Country Director Dieng says of South Sudan. “This will push more people to flee their country – this time not because of conflict, but because of hunger. All the more reason for the international community to give generously to those in need.”
WFP is the world’s largest humanitarian agency fighting hunger worldwide, delivering food in emergencies and working with communities to build resilience. In 2013, WFP assisted more than 80 million people in 75 countries.
Follow us on Twitter @wfp_media
For more information please contact (email address: firstname.lastname@wfp.org):
Elizabeth Bryant, WFP/Ethiopia, Tel. +251 011 551 5188 ext. 2130, Mob. +251 911 077 708
Melese Awoke, WFP/Addis Ababa, Tel. +251 011 551 5188 ext. 2130, Mob. +251 911 201 981
Amanda Lawrence-Brown, WFP/Nairobi, Tel. +254 297 622 336, Mob. +254 707 722 105
Emilia Casella, WFP/Rome, Tel. +39 06 6513 3854, Mob. +39 347 9450634