Pages

Tuesday, February 25, 2014

የ 2014 የዓለም የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት፡- ኢትዮጵያ

2013_Ethiopia_Maekelawi  ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ በነሀሴ ወር 2012 ዓ.ም. መሞታቸውን ተከትሎ በኢትዮጵያ የተተካው አዲሱ አመራር ሰብዓዊ መብቶችን የሚመለከቱ ማሻሻያዎች እንደሚያደርግ ተጥሎ የነበረው ተስፋ ተዳፍኗል፤ በ2013 ዓ.ም ተጨባጭ የሆነ የፖሊሲ ለውጥ አልታየም፡፡ ይልቁንም የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ሃሳብን የመግለጽ፣ የመደራጀት እና በሰላም የመሰብሰብ ነጻነት ላይ የጣሉትን ጥብቅ ገደብ ማስፈጸማቸውን የቀጠሉበት ሲሆን የሲቪል ማህበራትን እና ነጻ መገናኛ ብዙሃንን እንቅስቃሴ ለማዳከም አፋኝ ሕጎችን ይጠቀማሉ፤ግለሰቦችንም ፖለቲካዊ መነሾ ያላቸውን ክሶች በመመስረት የጥቃት ዒላማ ያደርጋሉ።
መንግስት በሃይማኖታዊ ጉዳዮቻቸው ላይ ጣልቃ መግባቱን የተቃወሙ ሙስሊሞች ዓመቱን ሙሉ በጸጥታ ሃይሎች የዘፈቀደ እስር፣ እገታ፣ ድብደባ እና ሌሎች ተገቢ ያልሆኑ አያያዞች ተፈፅሞባቸዋል፡፡ በሐምሌ ወር 2012 ዓ.ም. የታሰሩት 29ኙ የተቃውሞው መሪዎች የፍርድ ሂደት ከጥር ወር 2013 ጀምሮ ለህዝብ፣ ለመገናኛ ብዙሃን፣ እና ለቤተሰብ አባላት ዝግ ተደርጓል፡፡ እጅግ አወዛጋቢና መሠረታዊ ግድፈት ያለባቸውን ድንጋጌዎች በያዘው የሃገሪቱ የጸረ ሽብርተኝነት ህግ መሰረት ጥፋተኛ የተባሉ የተቃዋሚ መሪዎች እንዲሁም አራት ጋዜጠኞች አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡
ከሃገር ውስጥ በሚገኝ ገቢ እና ከውጭ በሚመጣ እርዳታ በሚደገፉ ስፋት ያላቸው የልማት ፕሮግራሞች አፈጻጸም ምክንያት የአንዳንድ ማህበረሰብ ተወላጅ ነዋሪዎች ያለበቂ ምክክር ወይም ምንም አይነት ካሳ ሳይከፈላቸው ከመኖርያቸው እንዲፈናቀሉ ይደረጋል፡፡ የጸጥታ ሃይሎች ነዋሪዎችን ከመኖሪያ ቀያቸው አንስተው ወደ ሌላ ቦታ ለማስፈር ሃይል፣ ማስፈራሪያ እና ዛቻ ይፈጸማሉ፤ ለምሳሌ በታችኛው የኦሞ ሸለቆ የሚገኙ ተወላጅ ነዋሪዎች ለዘመናት የኖሩበት መሬት መንግስት ለሚያካሂደው የስኳር መስኖ ልማት ይፈለጋል በሚል መፈናቀላቸው እንደቀጠለ ነው።
በሰላም የመሰብሰብ ነጻነት
ከ2012 ዓ.ም. ጀምሮ ከሀገሪቱ አጠቃላይ ህዝብ ቢያንስ 30 በመቶ የሚሆነውን ቁጥር የሚይዙት የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ አባላት ተከታታይ ህዝባዊ ተቃውሞ አድርገዋል፡፡ የተቃውሞው መነሻ ምክንያት መንግስት በእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ውስጥ እና በአዲስ አበባ በሚገኘው የአወሊያ መስጊድ ላይ ይፈጽማል የተባለውን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ነው፡፡
የተቃውሞ እንቅስቃሴዎቹን ለመግታት መንግስት ሃይል ተጠቅሟል፤ የዘፈቀደ እስር እና ድብደባ በተቃዋሚዎቹ ላይ ፈጽሟል፤ እነዚህ ሕገ ወጥ ተግባራት በሀምሌ 2012 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ውለው በጥቅምት 2012 ዓ.ም በጸረ ሽብርተኝነት አዋጁ መሰረት ክስ በተመሰረተባቸው 29 ታዋቂ የተቃውሞ እንቅስቃሴው መሪዎች ላይም ተፈጽመዋል፡፡ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደቱን መገናኛ ብዙሃንን፣ ዲፕሎማቶችን እና የቤተሰብ አባላትን ጨምሮ ህዝብ እንዳይከታተለው ከጥር ወር ጀምሮ ዝግ አድርጎታል፡፡ አንዳንዶቹ ተከሳሾች በእስር ላይ እያሉ ተገቢ ያልሆነ አያያዝ እንደተፈጸመባቸው ተገልጿል። እንዲሁም እንዳንዶቹ ተከሳሾች ለሁለት ወራት ያህል የሕግ አማካሪ ወይም ጠበቃ ያላገኙበት ሁኔታና ከቤተዘመድ ጋር ለመገናኘት የነበረውን ችግር ጨምሮ የፍርድ ሂደቱ በሕግ በተቀመጡ ስርዓቶች አግባብ መካሄዱን ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ በርካታ ግድፈቶች ተፈጽመዋል።
በተከሳሾቹ ላይ በመንግስት ቴሌቪዥን ውንጀላ እና ክስ ያለበት መረጃ በማስተላለፍ መንግስት ተከሳሾቹ ከፍርድ ውሳኔ በፊት ነጻ ሆነው የመገመት መብታቸውን የሚጋፋ ድርጊት ፈጽሟል። መንግስታዊ በሆነው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ኢቲቪ) ጃሃዳዊ ሃረካት የሚል ርዕስ ያለው ፕሮግራም በጥር ውስጥ የተላለፈ ሲሆን ፊልሙ ከተከሳሾቹ ውስጥ አምስቱ የፍርድ ሂደቱ ከመጀመሩ በፊት በቁጥጥር ስር እያሉ የተቀረጸ ክፍል አካቷል። ፕሮግራሙ የተቃውሞው መሪዎችን እንደ አሸባሪዎች በመቁጠር የሙስሊሞቹን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ከአክራሪ የእስልምና ሃይሎች ጋር አነጻጽሯል፡፡
እስሩ እንዳለ ቢሆንም በ2013ም ተቃውሞው ቀጥሏል፡፡ በነሃሴ ወር መጀመሪያ ላይ በአዲስ አበባ እና በሌሎች ከተሞች የረመዳን ወር መጨረሻ የሆነው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሚከበርበት ዕለት የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል፡፡ የአይን እማኞች በአዲስ አበባ በርካታ ቁጥር ያላቸው ፖሊሶች ተሰማርተው እንደነበረ የገለጹ ሲሆን ታማኝ ምንጮች ደግሞ ሰልፈኞቹን ለመበተን ፖሊስ ከተገቢው በላይ ሃይል እንደተጠቀመ እና ለጊዜውም ቢሆንም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞችን በቁጥጥር ስር አውሎ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ተሳትፎ አዲስ መጭ የሆነው ሰማያዊ ፓርቲ በሰኔ ወር ሰላማዊ ሰልፍ አካሂዷል፤ ሰልፉ በስምንት ዓመት ጊዜ ውስጥ በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ የተዘጋጀ የመጀመሪያው ሰልፍ ነው፡፡ የጸጥታ ሃይሎች የሰማያዊ ፓርቲን ጽህፈት ቤት ጥሰው በመግባት በርካታ ሰዎችን በማሰራቸውና የፓርቲውን ንብረቶች በመውረሳቸው ምክንያት ፓርቲው በነሀሴ ወር ሊያካሂድ አቅዶ የነበረው ሰልፍ ተሰርዟል። ሰማያዊ ፓርቲ ቀደም ብሎ ሰላማዊ ሰልፉን ለማካሄድ ለመንግስት አቅርቦ የነበረው ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቶ ነበር።
የዘፈቀደ እስር እና ጎጂ አያያዝ
የዘፈቀደ እስር እና በእስር ቤቶች የሚደረግ ጎጂ አያያዝ ከፍተኛ ችግር መሆኑን ቀጥሏል፡፡ ተማሪዎች፣ የተቃዋሚ ጎራ አባላት፣ ጋዜጠኞች፣ የሰላማዊ ሰልፍ ተሳታፊዎች እና ሌሎችም የመሰብሰብ፣ ሃሳብን የመግለጽ እና የመደራጀት መብታቸውን መግለጽ የሚፈልጉ ሰዎች በየጊዜው በዘፈቀደ ይታሰራሉ፡፡
አብዛኛውን ጊዜ በፖለቲካ ምክንያት የሚያዙ ሰዎች ላይ በተለይም እነዚህ ሰዎች ከክስ ወይም ከፍርድ ሂደት በፊት በሚታሰሩበት እና ማዕከላዊ በመባል በሚታወቀው አዲስ አበባ በሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ማዕከል ጎጂ አያያዝ ይፈጸማል፡፡ በሃይል በማስገደድ ከእስረኞች መረጃ፣ የእምነት ቃል እና ሃሳብ ለማውጣጣት እስከ ማሰቃየት የሚደርስ ጥቃት እና ሌሎች ጎጂ አያያዞች የሚፈጸሙባቸው አጋጣሚዎች ብዙ ናቸው።
የተያዙ ሰዎች በተለይ ክስ ከመመስረቱ በፊት ብዙ ጊዜ የህግ አማካሪ እንዳያገኙ ይደረጋል፡፡ ያልተገባ አያያዝ የተፈጸመባቸው እስረኞች ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ከፍርድ ቤቶች የሚያገኙት መፍትሄ እጅጉን ውሱን ነው፤ አንዲሁም እስር ቤቶች እና ሌሎች የማቆያ ቦታዎች በገለልተኛ መርማሪዎች በመደበኛነት እንዲጎበኙ አይፈቀድም፡፡ ከመንግስት ጋር ቀረቤታ ያለው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የተወሰኑ እስረኞችን እና እስር ቤቶችን የጎበኘ ቢሆንም በማንኛውም ገለልተኛ የሰብዓዊ መብቶች ወይም ሌላ ድርጅት መደበኛነት ያለው የክትትልና የምርምራ ስራ አይሰራም።
በሃምሌ ወር ወደ ኢትዮጵያ ተጉዞ የነበረው የአውሮፓ ፓርላማ የልዑካን ቡድን አባላት አስቀድሞ ፈቃድ ተሰጥቶአቸው የነበረ ቢሆንም አዲስ አበባ የሚገኘውን የቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዳይጎበኙ በባለስልጣናት ተከልክለዋል።
ሃሳብን የመግለጽ እና የመደራጀት ነጻነት
በ2009 ዓ.ም የጸረ ሽብርተኝነት አዋጅ እና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት አዋጅ ከወጡ በኋላ በኢትዮጵያ ሃሳብን የመግለጽ እና የመደራጀት ነጻነት በከፍተኛ ደረጃ ተገድቧል፡፡ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት አዋጁ በዓለም ላይ ካሉ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ለመቆጣጠር ከወጡ በጣም አፋኝ ህጎች አንዱ ነው፡፡ በሰብዓዊ መብቶች፣ መልካም አስተዳደር፣ ግጭት አፈታት፣ እና የሴቶች፣ የህጻናት እና አካል ጉዳተኛ ሰዎች መብቶች ዙሪያ አድቮኬሲ የሚሰሩ ድርጅቶች ከጠቅላላ ገቢያቸው 10 በመቶ በላይ እርዳታ ከውጭ ምንጮች መቀበል እንደማይችሉ ይደነግጋል፡፡
በዚህ ሕግ ሳቢያ እጅግ መልካም ስም የነበራቸው የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ይሰሩ የነበረውን ስራ በከፍተኛ ደረጃ የቀነሱ ሲሆን ሌሎቹም ሰብዓዊ መብቶችን የሚመለከቱ ስራዎችን መስራት ጭራሹኑ አቁመዋል። በርካታ ታዋቂ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች በተፈጠረባቸው ስጋት ምክንያት ሃገሪቱን ለቀው ተሰደዋል፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን በከፍተኛ የመንግስት ቁጥጥር ስር ይገኛሉ፤ እንዲሁም በርካታ ጋዜጠኞች ራሳቸው ላይ ቅድመ ምርመራ ያካሂዳሉ፡፡ መንግስትን በፅኑ የሚተቹ ድረ ገጾች እና ጦማሮች በመደበኛነት ይዘጋሉ እንዲሁም የውጭ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ስርጭቶች በተደጋጋሚ ይታፈናሉ። ለነጻ የሃገር ውስጥ ጋዜጦች የሚሰሩ ጋዜጠኞች የሚደርስባቸው ተከታታይ ጥቃት እና ማስፈራራያ እንደቀጠለ ነው።
የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጁ የፖለቲካ ተፎካካሪዎችን ለማጥቃት፣ ነጻ ሃሳብን ለማፈን፣ እንዲሁም ጋዜጠኞችን ዝም ለማሰኘት ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በሐምሌ ወር 2012 ዓ.ም የሽብር ጥቃት ለመፈጸም በማሴር እና አሸባሪ ድርጅት ውስጥ በመሳተፍ በሚል በተከሰሰው ጋዜጠኛ እና ብሎገር እስክንድር ነጋ ፈንታ ላይ የተሰጠውን የ 18 ዓመት የእስር ቅጣት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በግንቦት ወር 2013 እንዲጸና ወስኗል። እስክንድር ‘የፔን’ የመጻፍ ነጻነት ሽልማትን በ2012 ተሸልሟል፡፡
የፍትህ ጋዜጣ ጋዜጠኛ የሆነችው ርዕዮት ዓለሙ ገቤቦ በጻፈችው ጽሁፍ ምክንያት በጸረ ሽብር ህጉ በተጠቀሱ ሶስት ክሶች ተከሳ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቶባታል፡፡ በመጀመርያ ተፈርዶባት የነበረው 14 ዓመት በይግባኝ ወደ 5 ዓመት የተቀነሰላት ቢሆንም የቀረው የአምስት ዓመት ፍርድ ላይ ያቀረበችው ይግባኝ በጥር ወር ውድቅ ተደርጎባታል፡፡ ርዕዮት ከፍተኛ ዝና ያለውን የ2013 የዩኔስኮ ጉሌርሞ ካኖ የዓለም ፕሬስ ነጻነት ሽልማት ተሸልማለች፡፡
የሙስሊሙ ህብረተሰብ የሚያካሂዳቸውን የተቃውሞ ሰልፎችን ሲዘግቡ የነበሩ ጋዜጠኞች ማስፈራሪያ ደርሶባቸዋል እንዲሁም በዘፈቀደ ታስረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከህትመት ውጭ የሆነው የሙስሊሞች ጉዳይ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው ሰለሞን ከበደ በጥር ወር የታሰረ ሲሆን የጸረ-ሽብር ህጉን አዋጅ በመጣስ ክስ ተመስርቶበታል፡፡ የጋዜጣው የቀድሞ ዋና አዘጋጅ ዩሱፍ ጌታቸው በ2012 በተመሳሳይ ህግ ተከሷል፡፡ ሌሎች በርካታ ጋዜጠኞች በ2013 ከኢትዮጵያ ተሰደዋል፤ ይህም ሃገሪቱን በስደት ላይ ባሉ ጋዜጠኞች ብዛት ከዓለም ሶስተኛ ሃገር አድርጓታል፡፡
ከልማት ፕሮግራሞች ትግበራ ጋር በተያያዘ የሚፈጸም በሃይል ማፈናቀል
የኢትዮጵያ መንግስት ከሚያካሂደው የሰፈራ መርሃ ግብር ጋር በተያያዘ አንደሚፈፀሙ የሚገለጸውን በደሎች መንግስትም ሆነ የለጋሽ ማህበረሰብ አባላት በበቂ ሁኔታ መመርመር አልቻሉም፡፡ የመሰረታዊ አገልግሎቶችን አቅርቦት ለማሟላት በሚል ምክንያት በዚህ መርሃ-ግብር 1.5 ሚሊዮን የገጠር አካባቢ ነዋሪዎች ከመኖርያ አካባቢያቸው ተነስተው በሌሎች ቦታዎች እንዲሰፍሩ ተደርጓል፡፡ ይሁንና መርሃ ግብሩ ተግባራዊ በተደረገበት በመጀመሪያው ዓመት በጋምቤላ ክልል አንዳንድ ቦታዎች የተካሄደው ሰፈራ በሃይል የተደረገ ሲሆን ድብደባ እና የዘፈቀደ እስር የተፈጸሙባቸው አጋጣሚዎችም ነበሩ። ከዚህም ሌላ የማስፈሩ ስራ የተካሄደው ከተነሺዎቹ ጋር በቂ ምክክር ሳይደረግ እና በቂ የካሳ ክፍያ ሳይፈጸም ነው።
የዓለም ባንክን የአሰራር ተጠያቂነት የሚከታተለውና ከባንኩ ነፃ የሆነው የቁጥጥር ቡድን በስደት ላይ የሚገኙ የአኙዋክ ብሔረሰብ አባላት ባንኩ ጋምቤላ ውስጥ የራሱን የአሰራር ሁኔታዎች ጥሷል በማለት ያቀረቡት አቤቱታ ላይ ሙሉ ምርመራ እንዲደረግ በማለት ያቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ የዓለም ባንክ ስራ አስፈጻሚ ዳይሬክተሮች ቦርድ በሐምሌ 2013 ተቀብሎታል። ይህ ሪፖርት በሚዘጋጅበት ወቅት ምርመራው በመካሄድ ላይ ነበር፡፡
ኢትዮጵያ በታችኛው የኦሞ ሸለቆ የሚኖሩ 200 ሺህ ተወላጅ ነዋሪዎችን ከመሬታቸው ላይ በማስለቀቅ በ245 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የስኳር ልማት ስራ ማከናወኗን ቀጥላለች። እነዚህ በጥምር ግብርና እና ከብት እርባታ የሚተዳደሩ ተወላጅ ነዋሪዎች ለዘመናት ከኖሩበት መሬት ተፈናቅለው በሰፈራ መርሃ ግብር አማካኝነት በቋሚ መንደሮች እንዲሰፍሩ ተደርጓል።
ዋና ዋና ዓለምአቀፍ አካላት
ኢትዮጵያ ከውጭ ለጋሾች እና ከአብዛኞቹ የቀጠናው ጎረቤቶቿ ጋር መልካም ግንኙነት አላት፡፡ ይህ ጠንካራ ግንኙነት የተመሰረተው ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ በመሆኗ፣ ለተባበሩት መንግስታት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ በምታደርገው አስተዋጽኦ፣ ከምዕራብ ሃገራት ጋር በጸጥታ ጉዳይ ላይ ባላት ትብብር እና የተወሰኑ የሚሊኒየም የልማት ግቦችን በማሳከት ረገድ ባስመዘገበችው እድገት ምክንያት ነው፡፡ ሃገሪቷ ያላት ይህ ጠንካራ ግንኙነት የዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ላይ ያለችበትን አሳሳቢ ሁኔታ በዝምታ እንዲያልፍ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡
በ2013ም ኢትዮጵያ በሱዳን እና በደቡብ ሱዳን መካከል ያላትን የአደራረዳሪነት ሚና የቀጠለች ሲሆን ወታደሮቿም በአወዛጋቢው አቢዬ ግዛት የሰፈነውን አስተማማኝ ያልሆነ ጸጥታ በማስጠበቅ ተግባር ላይ ተሰማርተዋል። የኢትዮጵያ ወታደሮች ወደሶማልያ ዘልቀው መግባታቸውን የቀጠሉ ቢሆንም ወታደሮቹ በዚያ የተሰማራው የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሃይል አካል አይደሉም።
ኢትዮጵያ ከፍተኛ መጠን ያለው ድጋፍ ከለጋሾች ማግኘቷን የቀጠለች ሲሆን በ2013 ያገኘችው ድጋፍ 4 ቢሊዮን ዶላር ይጠጋል፡፡ የኢትዮጵያ የልማት አጋሮች አንደመሆናቸው መጠን ለጋሽ ሃገራት እጅግ አስከፊ ሆነውን የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ አስመልክቶ ግን ዝምታን መርጠዋል። ከልማት መርሃ ግብሮች አፈጻጸም ጋር በተያያዘ ተፈጽመዋል የተባሉ በደሎችን አስመልከቶ የሚቀርቡ ክሶችን ለመመርመር የሚወስዱት እርምጃም እጅግ ውሱን ነው።
ግብጻዊያን ኢትዮጵያ በምትገነባው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ምክንያት ከናይል ወንዝ ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ ወደ ግድቡ ይቀየሳል የሚል ስጋት ስለገባቸው በ2013 ዓ.ም. የኢትዮጵያ እና የግብጽ ግንኙነት የበለጠ ሻክሯል። 85 በመቶ የሚገመተው የናይል ወንዝ ውሃ ምንጭ ኢትዮጵያ ስትሆን ግብጽ ደግሞ ለሚያስፈልጋት ማንኛውም የውሃ ፍላጎት ሙሉ በሙሉ በናይል ወንዝ ላይ ጥገኛ ነች፡፡ ግድቡ 6 ሺህ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል በማመንጨት ከአፍሪካ ትልቁ የሃይድሮኤሌክትሪክ ፕሮጀክት ይሆናል፡፡ የግድቡ ግንባታ የተጀመረው በ2012 ሲሆን በ2018 ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ከምዕራባዊያን ለጋሽ ሀገራት በተጨማሪ ቻይና፣ ህንድ እና ብራዚል የተለያዩ ከፍተኛ መጠን ላላቸው የልማት ስራዎች የሚያደርጉት የገንዘብ ድጋፍ በየጊዜው እየጨመረ መጥቷል። ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው የውጭ የግል ኢንቨስትመንት እየጨመረ የሚገኝ ሲሆን በ2013 የግብርና ንግድ፣ ሃይድሮኤሌክትሪክ፣ ማዕድን ማውጣት እና ነዳጅ ፍለጋ ኢንቨስትመንት ስራዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመሩ ነው።የግብርና ንግድ ኢንቨስትመንት በዋናነት ከህንድ፣ ከመካካለኛው ምስራቅ እና በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚመጡ ሲሆን የመሬት ዋጋው ዝቅተኛ መሆን እና ለጉልበት የሚከፈለው ዋጋ አነስተኛነት ባለሃብቶቹን የሚስብ ሆኗል። እንደ ሌሎቹ በርካታ ትልልቅ የኢትዮጵያ የልማት ፕሮጀክቶች ሁሉ እነዚህ መርሃ ግብሮች ሲተገበሩ ሰዎችን ከመሬታቸው በሃይል የማፈናቀል ተግባር ሊፈጸም ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት አለ።

Open letter to the President of Switzerland: Re: Ethiopian Co-Pilot…

February 24, 2014
The Swiss Confederation
C/O Embassy of Switzerland 
2900 Cathedral Ave. NW 
Washington, DC 20008 
February 24, 2014
Dear President Didier Burkhalter,
Re: Ethiopian Co-Pilot Hailemedhin Aberra Tegegn
It is to be recalled that on Monday, February 17th 2014, a Boeing 767 Ethiopian Airlines commercial airliner, Flight ET702, which was en route to Rome, was diverted to Geneva, where it safely landed at 6:02 am (0502 GMT). As it has been widely reported, the airliner was diverted from its official route by the Ethiopian co-pilot, Hailemedhin Abera Tegegn, who made a request for political asylum in Switzerland while hovering over Geneva.
Those of us who have gathered here today at the Swiss Embassy in Washington D.C. as well us so many others who have been unable to come due to work and other commitments, are eager to humbly appeal on behalf of our compatriot Hailemedhin Aberra Tegegn, who appears to have great faith in the fairness, judiciousness and hospitality of the people and government of Switzerland. Having first-hand experience of facing persecution in Ethiopia, we have little doubt that Mr. Tegegn was desperate not only to seek political asylum but also feel that he was evidently eager to attract global attention to the predicament and suffering of his fellow citizens in Ethiopia who are routinely being killed, jailed and tortured by the TPLF-led regime.
We would, therefore, like the government of Switzerland to consider the following facts, inter alia, in dealing with Mr. Tegegn’s case, as he clearly wanted to attract global attention to the plight and suffering of Ethiopians under the tyrannical minority regime in Ethiopia, the Tigray People’s Liberation Front (TPLF/EPRDF).
  1. Ethiopia under the TPLF is one of the most repressive states in the world. Human Rights Watch, Amnesty International, Genocide Watch, UN Committee against Torture, the Committee to Protect Journalists, the U.S. State Department, the European Parliament, the United Nations Human Rights Council, among others, have repeatedly and consistently, though in vain, demanded the Ethiopian government to desist from committing crimes against humanity, gross human rights violations, extra judicial killings, mass displacement, torture and other forms of degrading mistreatment against innocent citizens.
  2. The government of Ethiopia abuses its own anti-terrorism proclamation to harshly and vengefully punish dissidents, journalists, religious leaders and activists. Hundreds of dissidents, Muslim rights defenders, civil rights leaders, activists and journalists have been charged with or convicted of terrorism offences in a bid to completely suppress dissident voices. So many of our compatriots are languishing in jails just for demanding freedom and respect for their basic rights.
  3. Among those convicted of terrorism offences under the Draconian law, are three internationally acclaimed award-winning journalists who are languishing in hellish jails. Eskinder Nega, Woubishet Taye and Reeyot Alemu, who is gravely ill but denied medical assistance, were convicted of trumped-up terrorism charges and are currently serving lengthy sentences. In Ethiopia, there is no freedom of expression, freedom of peaceful assembly, freedom of religion or freedom of movement under the current regime despite the fact that they were proclaimed in the ostensible Ethiopian constitution, which is violated willfully by its own authors.
  4. The Ethiopian Airlines, where Mr. Tegegn was in employment, is widely known to have been undermined and crippled by unbridled corruption, nepotism and ethnic discrimination. There are reports that indicate that Mr. Tegegn was a victim of discrimination due to his unwillingness to join the ruling party and ethnic background, a requirement that has been pervasively and forcefully implemented in the public sector.
  5. We are confident that the Swiss government has extensive information on the widespread human rights violations in Ethiopia, a reality which has forced so many Ethiopians to take extreme measures to leave the country including crossing perilous terrains, deserts and treacherous waters to in search of safe heavens. It should be remembered that so many of our compatriots have lost their lives in deserts, seas and oceans. This is the Ethiopia that Mr. Tegegn wanted to flee with a sense of urgency and desperation. By doing so, he has made a huge political statement and a call for attention to our suffering at a global scale.
While we acknowledge the unusual nature of Mr. Tegegn’s action and the inconvenience it created to the passengers, the airport as well as the country, it was clear that Mr. Tegegn had no intention of harming anyone. We are very grateful that he took utmost care so that nobody would be in harm’s way.
We appeal to the government of Switzerland to treat his asylum application expeditiously and the legal matters with sympathy, compassion, leniency and humanity because his fear of persecution is clear and present like so many Ethiopians face on a daily basis. We also call upon the government of Switzerland to reject any extradition bid on the part of the criminal TPLF government that tortures, kills and treats Ethiopian citizens in degrading and inhuman manners.
We call upon the people and government of Switzerland to grant political asylum and afford him a safe haven that he so desperately pleaded in your country, which is respected and known not only for its principle of neutrality but also for being an important seat for so many international organizations and UN agencies.
We look forward to a hearing positive outcome in Mr. Tegegn’s asylum case and legal matters.
With utmost regards,
Washington DC Ethiopian Joint Task Force.

የእንግሊዝ ኤምባሲ የፖለቲካ ክፍል ከአንድነት ፓርቲ የሲዳማ ዞን አመራሮች ጋር ተወያየ

የእንግሊዝ ኤምባሲ የፖለቲካ ክፍል ከአንድነት ፓርቲ የሲዳማ ዞን አባላት ጋር በወቅታዊና አካባቢያዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የሲዳማ ዞን የአንድነት ሰብሳቢ አቶ ሲዳ ኃይሌ ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል ፡፡

አቶ ሲዳ ኃይሌ ለፍኖተ ነፃነት እንደገለፁት የእንግሊዝ ኤምባሲ የፖለቲካ ክፍል ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ባለፈው ሳምንት በአዋሳ ሌዊ ሪዞርት ከአንድነት ፓርቲ የሲዳማ ዞን አመራሮች ጋር በአካባቢያዊና ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

በውይይቱ አንድነት ፓርቲ በሲዳማ ዞን እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴና የሚያጋጥሙ ችግሮች፣ የአካባቢው ገበሬዎች ላይ የመንግስት አካላት ስለሚያደርሷቸው ችግሮች እንዲሁም በኢህአዴግ የተዘረጋው የአንድ-ለ-አምስት የአፈና መዋቅር እያስከተለ ስላለው አፈና ከተነሱት አንኳር ነጥቦች መሃከል ይገኙባቸዋል፡፡

የአንድነት ፓርቲ የሲዳማ ዞን አደረጃጀቱን በማጠናከር የአዋሳ ጽ/ቤቱን ወደ መሀል ክፍለ ከተማ አዲስ አበባ ቀበሌ ገደብ ሆቴል አካባቢ ማዘዋወሩም ታውቋል፡፡

Sunday, February 23, 2014

ባሶንዳ በተባለችዉ የሱዳን ጠረፍ ከተማ 77 ኢትዮጵያዉያን ተገድለዋል ተባለ.

(ቢቢኤን) ከመተማ ቀጥላ በምትገኘዉ ባሶንዳ በምትባለዉ የሱዳን ጠረፍ ከተማና አካባቢ በኢዮጵያዉን ሽፍቶችና በሱዳን ሽፍቶች መካከል የተነሳዉን ግጭት ተከትሎ አራት ሱዳናዉያን በመሞታቸዉ ሳብያ ለብቀላ የተነሱት ሱዳናዉያን ታጣቂ ሐይላት ኢትዮጵያዉይንን በጅምላ እየገደሉ ነዉ አገር ወገን የድረስልን ሲሉ ወደ ሱዳን በመተማ በኩል የገቡ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች እየተጣሩ ነዉ።

አራት ሱዳናዉያን ስለሞቱ በመቶ ኢትዮጵያዊ ነዉ የምንበቀለዉ ያሉት ሱዳናዉያን እስከ አሁን 77 ኢትዮጵያዉይንን መገደላቸዉን በኩራት ይናገራሉ ያሉት ኢትዮጵያዉያን የአብዛኛዎቹ ሟቾች መቃብር የማታወቅ መሆኑንም ይናገራሉ። በየጫካዉ የተገደሉ ኢትዮጵያዉያን አስክሬናቸዉ ለዱር አራዊት መወርወሩን የሚገልጹት ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ሌላ 42 ኢትዮጵያዉያን የተቀበሩበት መቃበር መኖሩንም ይጠቁማሉ፤ ይህ መቃብር ግን ከሞቱት 77 ሰዎች ጋር የሚያገናኘዉ ነገር ይኑር አይኑር የሚያዉቁት ነገር እንደሌለም ያስረዳሉ ።

በህዳር 24/2006 የሱዳኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሊ አህመድ አልቀርዲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ሱዳንና ኢትዮጵያ ያላቸዉን የድንበር ልዩነት አስወግደዉ መስማማታቸዉን ይፋ አድርገዋል። ይህንንኑ ተከትሎ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማሪያም ደሳለኝ ወደ ሱዳን ለስራ ጉብኝት አቅንተዋል። የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኡመር ሐሰን አልበሽር ሁለቱ አገራት በጥበቃ፣በደህንንነት፣ ህገወጥ የሰዉና የ አደንዛዥ እጽ ዝዉዉርን ለመግታት መስማማታቸዉን ገልጸዋል። በሱዳኗ ባሶንዳ የኢትዮጵያዉያን በጅምላ መገደል ከዚሁ የደህንነት ስጋት ጋር ግንኙነት እንዳለዉ ባይታወቅም ሱዳናን ኢትዮጵያ ግድያዉን ለማስቆም ምንም አይነት ጥረት እንዳላደረጉ ከጥቃቱ የተረፉ ኢትዮጵያዉያን ያስረዳሉ ።

በየካቲት 11/2006 ህወሃት የተመሰረተበትን 39ኛ አመት ለማክበር የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ልዩ የክብር እንግዳ ሆነዉ መቐሌ ድረስ መምጣታቸዉ ታዉቋል። የሁለቱ አገራት መሪዎች ስለ ቀድሞ ስማእታት ቢናገሩም ወደ ሱዳን በኢኮኖሚ ሳቢያ ተሰደዉ ስለሚሞቱት ኢትዮጵያዉያን ምንም ያሉት ነገር አልነበረም። በባሶንዳ ሱዳን ኢትዮጵያዉያን ነጥሎ የማጥቃቱ ዘመቻ እንደቀጠለ ነዉ! ኢትዮጵያዉያን ወገን ይድረስልን ሲሉም ይጣራሉ።

Friday, February 21, 2014

አንድነት እና መኢአድ፤ በባዶ እግራቸው በመሆን በባህርዳር ቅስቀሳ እያደረጉ ነው።

አንድነት እና መኢአድ፤ በባዶ እግራቸው በመሆን በባህርዳር ቅስቀሳ እያደረጉ ነው።

andent ena mead
አንድነት እና መኢአድ፤ በባዶ እግራቸው በመሆን በባህርዳር ቅስቀሳ እያደረጉ ነው።
የአማራ ክልሉ ባለስልጣን፤ “አማራው በባዶ እግሩ ነው የሚሄደው…” ብለው እጅግ የከፋ ዘለፋ ካሰሙ ብኋላ ህዝቡ በያለበት ስለ ሰውዬው ያፈረላቸው ቢሆንም እርሳቸው ግን ሳያፈሩ ትላንት በቴሌቪዥን መስኮት ተከስተው ሲያስቁን ነበር።
ዛሬ እንደሰማነው እና እንዳየነው፤ የመኢአድ እና አንድነት አባላት እሁድ ለጠሩት ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ፤ በባዶ እግራቸው በመሆን ባደረጉት ቅስቀሳ “እኛም ጫማ የለንም፤ እኛም በባዶ እግራችን ነው የምንሄደው ቢሆንም ግን የሞራል ለዕልና አለን” የሚል ቅስቀሳ ሲያሰሙ ውለዋል።
በቅስቅሳው ወቅት ፖሊስ ጉልቤውን ሊያሳያቸው ቢሞክርም ህዝቡ ከበባ እያደረግ ሲከላከላቸው አንድነት ዛሬ ከለቀቀው ቪዲዮ አይተናል።
ድረ ገጻችን፤
…የምር ግን ህዘብ እየተዘለፈም እየተዘረፈም እንዴት ይችለዋል…. ???ብላ በትልቁ እየጠየቀች፤ አንድነት ያሰራጨውን ቪዲዮ ላላዩት እንድሚከተለው ታሳያለች።

የብአዴን ድንጋጤና የእሁዱ የተቃውሞ ሰልፍ

የብአዴን ድንጋጤና የእሁዱ የተቃውሞ ሰልፍ

ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አለምነው መኮንን በአማራ ህዝብ ላይ የሰነዘሩትን ዘለፋ ተከትሎ የተነሳውን ተቃውሞ ለማብረድ የብአዴን የወጣቶች ሊግ ለአባለቱ የስልጠና እና የግምግማ ስራ በባህር ዳር ፤ ደሴ እና ጎንደር እያከናወነ ነው።
የካቲት 16 አንድነትና መኢአድ በጋራ የጠሩትን ሰልፍ ተከትሎ በባህር ዳር ከተማ ባሉ ዘጠኝ ክፍለ ከተሞች 12 የገጠር ቀበሌዎች ብአዴን አባላቱ እና አባል ያልሆኑ ወጣቶችን በግዳጅ በማስጠራት ባቀረበው የውይይት ሃሳብ እና መመሪያ በማህበራዊ ድረ ገፆች በሚተላለፉ ሃሰተኛ መረጃዎች ማንም ተወናብዶ ሰልፉን መቀላቀል እንደሌለበት አሳስቧል።
የጥፋት ሃይሎች የሚያስወሩት ሴራ ነው የሚለው ብአዴን፣ ሰልፉን ለማጨናገፍ ና ማህበረሰቡ በሰልፉ ላይ እንዳይገኝ ወጣቶች አስፈላጊውን ስራ መስራት እንዳለባቸው መክሯል።
የባህር ዳር ከተማ ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ሃላፊ ወጣት ጌታቸው ብርሃኑ ባቀረበው ጽሁፍ የተሳሳቱ መረጃዎችን በማምጣት ህዝብ እና መንግስትን የማለያየት ስራ እየሰሩ በማለት ለወጣቶች ተናግሯል፡፡
የብአዴን ጽ/ቤ ሃላፊ የሆኑት አቶ እሱባለው መሰለ በበኩላቸው “የማህበራዊ ድህረ ገጾችን አትመልከቱ ችግር አለባቸው የሚያስተምሩት ጥላቻ እና አመጽን ነው” በማለት ምክራቸውን ለግሰዋል።
“በማህበራዊ ድረ ገፆች በሚተላለፉ ሃሰተኛ መረጃዎች አንታለልም” የሚል መሪ ቃል ይዞ እየተከናወነ ያለው ይህ ስልጠና ፣ ኢሳትንና ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ማእከል አድርጎ የሚካሄድ ነው።
አንዳንድ ተሰብሳቢዎች ” በድምጽ የሰማነውን ጉዳይ አይን ባወጣ ውሸት እንዴት ይክዱናል” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የአቶ አለምነውን ንግግር ሳያስተባብሉ ” የብአዴን የወጣት ሊግ እና ታች ያሉ አመራሮች ወጣቱን ለማሳሳት መመኮራቸው ብዙ ተሰብሳቢዎችን አስደምሟል።”
አንዳንድ ወጣቶች ” መረጃውን ለምን ማህበራዊ ሚዲያ እና ኢሳት አቀረበው ብሎ ከመጥላት ለምን አቶ አለምነው ከ22 ሚልየን በላይ የሚሆነውን ህዝብ ተሳደበ ብሎ” ውይይት አይከፈትም ነበር ሲሉ ተደምጠዋል። ብአዴን ከህዝብ ይልቅ ግለሰብ ይበልጥብኛል በማለት ጉዳዩን እየሸፋፈነው ነው በማለት አንዳንድ አባሎቹ ለዘጋቢያችን ነግረዋታል። የጎንደር መሬት ለሱዳን ተቆርሶ መሰጠቱን በተመለከተም ኢህአዴግ ተቃዋሚዎችን በመሳደብ ስታራቴጅ ችግሩን ለማድበስበስ እየሞከረ መሆኑን ወታጦች መናገራቸውን ሪፖርተራችን ከባህርዳር ዘግባለች።
አቶ አለምነው የአማራው ህዝበ የትምክህት ለሃጩን ማራገፍ አለበት በማለት መናገራቸው ይታወቃል
አንድነትና መኢአድ እሁድ ለሚካሄደው ተቃውሞ በባህርዳር ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ሲሆኑ፣ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ ተቃውሞውን እንዲገልጽም ጠይቀዋል።

Tuesday, February 18, 2014

አቶ አለማየሁ አቶምሳ በገዛ ፍቃዳቸው ከሥልጣናቸው ለቀቁ (በጽዮን ግርማ)

አቶ አለማየሁ አቶምሳ በገዛ ፍቃዳቸው ከሥልጣናቸው ለቀቁ (በጽዮን ግርማ)

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አለማየሁ አቶምሳ በገዛ ፈቃዳቸው ከኦሕዴድ ሊቀመንበርነታቸው ለቀቁ፡፡በዛሬው ዕለት በተካሄደው የኦሮሞ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ መልቀቂያቸውን ያስገቡት አቶ አለማየሁ አቶምሳ ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቶ ከሥልጣን መነሳታቸው ታውቋል፡፡አቶ አለማየሁ ቀድሞውንም ሥልጣን ሲይዙ በከባድ ሕመም የሚሰቃዩ መኾናቸው እየታወቀ ሲኾን ምንጮች እንዳረጋገጡት አቶ አለማየሁ ወደ መንፈቅ ለሚጠጋ ጊዜ በውጭ አገር በሕክምና ላይ ነበሩ፡፡ በተደጋጋሚ ኮማ ውስጥ ይገቡም ነበር ተብሏል፡፡ በዚህ ጊዜ የፕሬዝዳንትነቱን ቦታ ተክተው ይሠሩ የነበሩት አቶ አብዱላዚዝ አህመድ ሲኾኑ የኦሕዴድ ሊቀመንበርነታቸውን ሥልጣን ደግሞ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩና የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙክታር ከድር እንደነበሩ ምንጮች ጨምረው አረጋግጠዋል፡፡
የረዳት ፓይለቱ ሀይለመድህን እህት መልዕክት Message from co-pilot Hailemedin's Sister

በመጀመሪያ ይህን ጽሁፍ የምታነቡ ሰዎች በሙሉ የተዝረከረከ ከሆነባችሁ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ከትናንት ከሰዐት በኋላ ጀምሮ እስካሁን ኢንተርኔትና ቴለቪዥን ላይ ያለማቋረጥ ተተክየ ስለቆየሁና በጥልቅ ሃዘን ስለተመታሁ አይምሮየ ትክክል ላይሆን ይችላል።

‘የኢትዮጵያ አየር መንገድን ወደ ሮም ይጓዝ የነበረ አውሮፕላን ጠልፎ ጄነቫ ላይ ያሳረፈው ረዳት አብራሪ እጁን ለስዊዝ ስጠ። ምክንያቱም ስዊዘርላንድ ውስጥ ጥገኝነት ለመጠየቅ ነው ብሏል።’ የሚለውን ዜና በርካታ የዜና ማሰራጫዎች ከየፊናቸው አስተያየት ጋር አቅርበውታል። የዜና ማሰራጫዎች ብቻ ሳይሆኑ የተለያዩ ወገኖች ያሻቸውን ብለዋል። የፖለቲካ ድርጅቶች የሰብዐዊ መብት ተሟጋቾችና እንደ አቤ ቶኪቻው ያሉ ቀልደኞች የየራሳቸውን ሃሳብ ለማስተላለፍ ተጠቅመውበታል። በጣም አሳዝኝ ነገር ነው። ሁሉም የየራሱን እምነት ለማስተላለፍ እንጂ እሱስ ምን ሆኖ ይሆን ብሎ አለማሰቡ ልብ ይሰብራል።

ወንድሜ ሃይለመድህን አበራ የሰዎችን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል አይደለም እንስሳትን ለመጉዳት የሚፈልግ ሰው አይደልም። ደግሞም ያንን የጨነቀውን ያክል ከፈራው ነገር ለመሸሽ ሞከረ እንጂ ማንንም ባለመጉዳቱና ሃሳብ እንኳ እንዳልነበረው ምንም አይነት ማጥቂያ መሳርያ ባለመታጠቁ አሳይቷል። በሁሉም ዘንድ የሚታወቀው ለተቸገሩ በመድረስና ባዛኝነቱ ነው። ካገር ውጪ ሄዶ ለመኖር የሚፈልግ ሰው ቢሆን ለሱ በጣም ቀላል ነገር ነው። ከጥቂት ወራት በፊትንኳ ዩኤስ ኤ ሄዶ ነበር። ከ አስር ቀናት በላይንኳ መቆየት አልፈለገም። ዝም ብሎ ካገር መውጣት ቢፈልግ ከዛ የተሻለ አጋጣሚ አልነበረም። ደግሞም በኑሮ ደረጃ ውጪ ቢኖር ያን ያክል የሚያሻሽለው ነገር አይደለም። ምክንያቱም የገንዘብ ችግር የለበትም። ከራሱም አልፎ ለብዙ ሰዎች የሚተርፍ ገቢ ነበረው።

ከልጅነቱ ጀምሮ ጎበዝ ሳይሆን እጅግ በጣም ጎበዝ ጭንቅላት ያለው ወጣት ነው። አብዛኛዎቹን ክፍሎች ሁለት ሁለት እያለፈ አስራ ሰባት አመት ሳይሞላው ሀይስኩል ሲያጠናቅቅ የ አስራሁለተኛ መልቀቂያ ውጤቱ ሁሉም ኤ ነበር። የጀመረውን የ አርክቴክቸር ትምህርት ትቶ ወደ ፓይለትነት የገባው ለሙያው ካለው ፍቅር የተነሳ ነው። ለኢትዮጵያ አየር መንገድም የተለየ ክብር አለው።

ሃይለመድህን ሁሉንም አስታዋሽ ቤተሰቡን የሚወድና ተጫዋች ሰው ነበር እስከ ቅርብ ጊዜ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ለኛ ያለውን ፍቅር ደህነታችንን በማረጋገጥና የሚያስፈልገንን ሁሉ በመታዘዝ ቢገልጽም ከዘመድ ወዳጆቹ ጋር መገናኘትና አቆመ። የወትሮው ጨዋታና ደስተኝነቱ ቀርቶ ብቸኝነትን የሚወድ ዝምተኛ ሆነ። ህይወቱ ደስታ የራቀው መሰለ። በሁኔታው ተደናግጠን ደጋግመን በመጠየቅ ያወቅነው ሊያጠቁት የሚከታተሉት ጠላቶች እንዳሉ እንደሚያምን ነው። ስልኩን እንደጠለፉት ያስባል፤ በላፕቶፑ ካሜራ ሳይቀር ያዩኛል ብሎ ስለሚሰጋ ካሜራውን ሳይሸፍን አይከፍተውም፤ ወጥቶ እስኪገባ ቤቱን ሲበረብሩ የቆዩ ስለሚመስለው ካሜራ ጠምዶ መሄድ ሁሉ ጀምሮ ነበር። ባጠቃላይ በታላቅ የመንፈስ ጭንቀት እየተሰቃየ ነው። የሚያሳዝነው ደግሞ ይህንን ጉዳቱን ለኛ ለቤተሰቡንኳ አብራርቶ አለመናገሩ ነው። ወንድሜ ለሰዎች እርዳታ ለመድረስና የሌሎች አዳኝ ለመሆን የማይታክት ሰውንጂ እንዲህ በሚያንገበግብ ስቃይ ውስጥንኳ ለራሱ አስቦ እርዳታን የሚጠይቅ ሰው አይደለም። ሁኔታውን በደበስባሳው በታወቀበት ጊዜንኳ የሚያስፈልገውን የህክምና በማቅረብ ስላልረዳነው ቤተሰቡ ሁሉ እንደግር ሳት ይከነክነዋል።እሱ ግን እንዲህ ባለ ጥልቅ የመንፈስ ጭንቀት ውስጥንኳ ለኛ አንድም ቀን ሳያስብ ቀርቶ አያውቅም።

ይህን የምታነቡ ወገኖች ሁሉ ዛሬ እኔ ይሄን ከምጽፍ እግዚአብሄር ምስክሬ ነው እሱ ወደነበረበት ጤናና ሁኔታ ተመልሶ እኔ ሞቼ ቢሆን እመርጣለሁ። ውሸት ከሆነ ይህንን በማድረግ የውሸቴን መልስ እንዲያሳየኝ አምላኬን እለምነዋለሁ። በኛ አገር መስሪያ ቤቶች የሰዎችን እውቀት ብቃትና ቁመና ሳይቀር ሲመዝኑ የዐይምሮ ጤንነት ሁኔታን አለመከታተላቸው እጅግ የሚያሳዝን ነገር ነው።

ወንድሜ ትናንት አውሮፕላኑ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ምን አጋጥሞት ይሆን እነዛ የሚላቸው ሰዎች ሲመለስ ጠብቀው እንደሚገሉት ዝተውበት ያንን ፈርቶ ይሆን ወይም ፓይለቱ ከጠላቶቹ ጋር በመተባበር ሊይጠቃው እንደሚችል ብማመን ሰግቶ ይሆን ሲወጣ ራሱን ለመከላከል በሩን የዘጋው ከሁለቱ አንዱ ወይም ሁለቱም እንደሆነ አምናለሁ። አስቡት በዛች ቅጽበት አለሙን በሙሉ ሊያናጋ የሚችል ምንም አይነት ራሱን ሊከላከልበት የሚችል መሳርያ ሳይዝ ይህንን ድርጊት የሚያስፈጽም ምን ነገር ሊኖር ይችላል ስዊዘርላንድ ገነት አይደለችም። የዐይምሮ ህመም ሰለባ የሆኑ ሰዎችን ለዚያውም በማንም ላይ ምንም ጉዳት ባልፈጸሙበትና ሊፈጽሙም ባላሰቡበት ሁኔታ ወደስር ቤት እንዲወረወሩ ህግ የሚፈቅድ አይመስለኝም። ሃይለመድህን ለህይወቱ ሰግቶ ነበር። የሰው ልጅ ሊቋቋመው በማይችል የመንፈስ ጭንቀት ገሃዱና ሃሳባዊው አለም በተዘበራረቀበት የስቃይ አለም ውስጥ ብቻውን ሲሰቃይ ነው የቆየው። በተስተካከለ የዐይምሮ ጤንነት ላይ የሚገኝ ሰው ላይገባው ይችላል። እኔ ግን የሱን ግማሽ ባያክልም የተወሰነ ይህንን መሰል ችግር ስላለብኝ ህመሙን አውቀዋለሁ። ሁሌም በሳት እየተጠበሱ መኖር ማለት ነው

ወገኖች መልዕክቴን አንብባችሁ በምትችሉት ሁሉ ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ፍትህ አግኝቶ ወደ ነበረበት እንዲመለስ በመጣር እንድትተባበሩን መላ ቤተሰቡ በምታምኑት ሁሉ እንለምናችኋለን! እኛም የሚያስፈልገውን የህክምና እርዳታ አግኝቶ ወደ ቀድሞው ጤናው ከተመለሰ በኋላ ለዚች አገር ባለው አቅም ሁሉ እንዲያገለግል በማድረግ እንክሳለን!

እባካችሁ ይህን መልእክት በማስተላለፍ ተባበሩን!

ኢህአዴግ ራሱ ባወጣው አፋኝ ሕግ ታፈነ

ኢህአዴግ ራሱ ባወጣው አፋኝ ሕግ ታፈነ


February 18/2014
ለተፈጥሮ ሃብት የጠየቀው ዓለምዓቀፋዊ እውቅና ውድቅ ሆነ
eiti
ኢህአዴግ የተፈጥሮ ሃብትን በትክክለኛ መንገድ ለሕዝብ ጥቅም መዋሉን በመከታተል ለአገራት እውቅና የሚሰጠው The Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) ለተሰኘ ዓለም ዓቀፋዊ ተቋም ያቀረበው የእውቅና ጥያቄ ማመልከቻ ከተገመገመ በኋላ መመዘኛዎቹን ማሟላት ባለመቻሉ መውደቁ ተሰማ። ኢህአዴግ የእውቅና ማመልከቻ በድጋሚ ማስገባቱን አስቀድሞ ያወቀው ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ድርጅት (Human Rights Watch) ጉዳዩን ከሚከታተሉ ጋር ባገኘው መረጃ ኢህአዴግ የEITI መስፈርት የማያሟላና በሰብአዊ መብት ጥሰት የተወነጀለ ድርጅት መሆኑንን ማስረጃ አስደግፎ በመጥቀስ መሟገቻ ደብዳቤ ለድርጅቱ አስገብቶ ነበር።
EITI የዛሬ 11ዓመት አካባቢ የተቋቋመ በተፈጥሮ ሃብት ዙሪያ ዕውቅና የሚሰጥ ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱ የተፈጥሮ ሃብት የህዝብ መሆኑን የሚያምን ሲሆን ማንኛውም የተፈጥሮ ሃብት – ማዕድን፣ ዘይት፣ ብረታብረትና ጋዝ – ከመሬት በሚወጣበት ጊዜ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የሚኖረውን ያህል ግልጽነትና ተጠያቂነት በሌለባቸው አገራት ድርጊቱ ለሙስና እና ግጭት በር እንደሚከፍት ይናገራል፡፡ በመሆኑንም ድርጅቱ አገራት ለሚያቀርቡት የዕውቅና ጥያቄ ማሟላት ያለባቸውን መስፈርት በዝርዝር አስቀምጧል፡፡ ልማትና እድገት በሚል ሰበብ የሕዝብ ሃብት የሆነውን የተፈጥሮ ሃብት በማውጣት የህዝባቸውን መብት ለሚረግጡ አገራት የሚያቀርቡትን የዕውቅና ማመልከቻ ውድቅ ያደርጋል፡፡
የጎልጉል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ምንጭ እንደጠቆሙት ኢህአዴግ ያቀረበው የእውቅና ጥያቄ ውድቅ መደረጉ እውነት ነው። ምንጩ እንዳሉት ኢህአዴግ በውሳኔው በመበሳጨት ይግባኝ ለመጠየቅ በዝግጅት ላይ ነው። ድርጅቱ (EITI) አንድ አገር ለሚያቀርበው የእውቅና ማመልከቻ በመስፈርቱ መሰረት ግምገማ ካካሄደ በኋላ እውቅና እንዲሰጥ ሲያምን በራሱ ድረገጽ ላይ የዚያን አገር ስም በመመዝገብ ተጠቃሹ አገር ከተፈጥሮ ሃብት ጋር በተያያዙ ኢንቨስትመንቶች የሚገኘው ትርፍ ለህዝብ ጥቅም እንዲውል ያደርጋል የሚል እውቅና በመስጠት ምስክርነቱን ያሰፍራል፡፡
ኢህአዴግ የመጀመሪያው የማመልከቻ ጥያቄ ያቀረበው በአውሮጳውያኑ አቆጣጠር በ2009 አካባቢ ነበር፡፡ ከEITI አምስት መስፈርቶች መካከል አንዱ፤ ማመልከቻ የሚያቀርቡ አገራት ከመያዶች (መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች) ጋር ለመስራት ያላቸው ፍላጎት ተጠቃሽ ነው፡፡ በወቅቱ ኢህአዴግ በመያዶች ላይ አፋኝ ሕግ አውጥቶ የነበረ በመሆኑ እውቅና ሰጪው ድርጅት – EITI – የኢህአዴግን ማመልከቻ ውድቅ አድርጎታል፡፡ የEITI ቦርድ ይህን ዓይነት ውሳኔ ሲያስተላልፍ ያሰፈረው ነገር ኢትዮጵያ በእጩ አባልነት ለመመዝገብ በመጀመሪያ በመያዶች ላይ ያወጣችውን ሕግ ማስወገድ አለባት የሚል እንደነበር የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ድርጅት በድረገጹ ላይ አስቀምጦታል፡፡ በወቅቱ የተሰጠው ይህ ብያኔ በEITI እውቅና አሰጣጥ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያ እንደሆነ ተጠቁሞም ነበር፡፡
የEITI ዕውቅናን ለማግኘት ቋምጦ የነበረው ኢህአዴግ በድርጅቱ ውሳኔ ባለመደሰት ጥቂት ዓመታትን ቆጥሮ ከአቶ መለስ ሞት በኋላ በአቶ ሃይለማርያም በመመራት በድጋሚ ዕውቅና የማግኘት ዘመቻውን ማጠናከር ጀመረ፤ በይፋም እንቅስቃሴውን ቀጠለ፡፡ የማዕድን ሚ/ር መ/ቤትም ዕውቅና ማግኘቱ በጣም የሚያስፈልግ እንደሆነ በይፋ በመናገር ዘመቻውን አጧጡፎ ነበር፡፡ ከዚህም አልፎ ለዓመታት ሲጠቀምበት የነበረውን አሠራር በዓለምአቀፉ ድርጅት ላይ ተግባራዊ በማድረግ ኢህአዴግ Ethiopia Revenue Transparency Initiative (ERTI) የሚባል “ተለጣፊ” ተቋም በመመሥረት እንቅስቃሴ ሲያደርግ እንደቆየ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ለEITI በጻፈው ደብዳቤ ላይ ገልጾዋል፡፡
ጉዳዩን በቅርብ ይከታተሉ የነበሩ የዲፕሎማቲክ ምንጮች ኢህአዴግ በአውሮጳውያኑ አቆጣጠር 2013ዓም በድጋሚ ማመልከቻ የማቅረብ ዓላማ እንዳለው ለዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት አሳወቁ፡፡ በወቅቱ ኢህአዴግ ማሻሻያ እያደረጉ ነኝ የሚል ማስመሰያ ለማቅረብ የሞከረ ቢሆንም የመያዶችና የጸረ አሻባሪነት አፋኝ ሕጎቹ በተጨማሪ በቴሌኮሙኒኬሽን በኩል በስልክና ኢንተርኔት የሚያደርውን ህዝብን የመሰለል ተግባር አጠናክሮ የቀጠለበት እንደሆነ በመጥቀስ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ክፍሎች EITI ዕውቅና እንዳይሰጥ መወትወታቸውን ተያያዙ፡፡
እነዚሁ ወገኖች በተደጋጋሚ ያደረጉት “የወረቀትና የፔቲሽን ትግል” እየተባለ የሚቃለለው ትግል ውጤት በማምጣት ኢህአዴግ በደጋሚ ያስገባው የአባልነት ማመልከቻ ሰሞኑን ውድቅ መደረጉ ተሰምቷል፡፡ እንደ መረጃው ከሆነ EITI ማመልከቻ በሚመዝንበት በሁሉም መስፈርቶች ኢህአዴግ ወድቋል፡፡
አነስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙና ኢህአዴግ “ልማታዊ” የሚላቸው ኢንቨስተሮች ሳይሆኑ በከፍተኛ ደረጃ የሚመደብ መዋዕለ ንዋይ የሚያፈሱ ባለሃብቶች ኢንቨስት የሚያደርጉበትን አገር ለመምረጥ የመጀመሪያው መለያቸው የEITI ድረገጽ የአባል አገራት ዝርዝር እንደሆነ ስለ አሰራሩ የሚያውቁ ይናገራሉ። ኢህአዴግም አስፈላጊውን የምዝገባና የማመልከቻ መስፈርት በማሟላት የተቋሙን እውቅና የጠየቀው በድርጅቱ ድረገጽ ላይ ለመመዝገብ ነበር። የሁለት ጊዜ ሙከራው መክሸፉ ኢህአዴግ ራሱ ባወጣው አፋኝ ህግ መታፈኑ የሚያመላክት እንደሆነ የሚጠቅሱ ክፍሎች፤ ከኢህአዴግ ከፍተኛ ፍላጎት አኳያና ሰሞኑን በተለያየ አቅጣጫ እየተወጠረ ከመምጣቱ አንጻር ሁኔታው አጣዳፊና ፋታ የማይሰጥ በሽታ ምልክት እንደሆነ በምጸት ይናገራሉ፡፡
ስለEITI ውሳኔ ባጭሩ እንዲያብራሩልን የጠየቅናቸው ባለሙያ እንዳሉት “አንድ ዩኒቨርሲቲ ህንጻ በማስገንባቱና አስተማሪዎችን በመቅጠሩ ብቻ ዩኒቨርስቲ ተብሎ ሊጠራ አይችልም። ዩኒቨርስቲው ዓለም ዓቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ስለመሆኑ በዓለም አቀፍ መስፈርት መሰረት ተገምግሞ እውቅና የሚሰጠው መስፈርቶቹን በሙሉ አሟልቶ ስለመገኘቱ ምርመራ ተደርጎበት ፈተናውን ሲያልፍ ብቻ ነው። በዚሁ መሰረት አልፎ እውቅና ያላገኘ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ገብቶ መማር የተሳትፎ ያህል ነው። መስፈርቱን አሟልተው እውቅና ካገኙት ጋር መወዳደር ስለማይችል ተመራጭ አይሆንም። በተመሳሳይ Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) የተባለው ድርጅትም ከየአገራቱ እውቅና እንዲሰጥ የሚቀርብለትን ጥያቄ /ማመልከቻ/ የሚመዝንበት መስፈርቶች አሉት። ኢህአዴግ የተፈተነው በዚሁ አቅልጦና አንጥሮ በሚያወጣው መመዘኛ ነው ብለዋል፡፡”
ስለጉዳዩ የተጠየቀው የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ የህዝብ ግንኙነት ግብረ ኃይል ጉዳዩን በጥልቀት የሚያውቀውና ገና ከጅምሩ ሲከታተል የቆየው መሆኑን በመግለጽ በበርካታ ፈርጆች ከሚያካሂደው ትግል አንጻር በዕቅድ ሲያከናውነው የቆየ መሆኑን አመልክቷል። የህዝብ ግንኙነት ክፍሉ ለጎልጉል እንዳለው ከሆነ “የEITI ውሳኔ ኢትዮጵያን እንደ አገር የሚጎዳ መሆኑ ግልጽ ነው፤ ሆኖም ውሳኔው ኢህአዴግ በራሱ ግትረኝነትና እብሪት ያመጣው ጣጣ በመሆኑ የራሱን ተግባር ተከትሎ የተወሰነው ውሳኔ በአገሪቱ ላይ በማንኛውም መልኩ ለሚያደርሰው ኪሳራ ተጠያቂው ኢህአዴግና ህወሃት ናቸው” ብሏል። በማያያዝም የጋራ ንቅናቄው ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ መግለጫ በማውጣት አስፈላጊ ናቸው ለሚላቸው ወገኖች እንደሚበትንና ተቋሙ በውሳኔው እንዲጸና የሚቻለውን ሁሉ በማድረግ ላይ ለተሰማሩ መልዕክት እንደሚያስተላልፍ አመልክቷል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Monday, February 17, 2014

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ተጠለፈ፤ ጠላፊው ምክትል አብራሪው ነው ተባለ



(ዘ-ሐበሻ) ከአዲስ አበባ ተነስቶ በካርቱም በኩል አቋርጦ ወደ ጣሊያን ይበር የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጠልፎ በጄኔቭ ስዊዘርላንድ እንዲያርፍ መደረጉ ታወቀ። ጠላፊው ምክትል አብራሪው እንደነበርም የስዊዘርላንድ ፖሊስ አስታወቀ።
193 ተሳፋሪዎችን ጭኖ ይጓዝ እንደነበር ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ድረገጽ ዘ-ሐበሻ የተረዳች ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 140 የሚሆኑት የጣሊያን ዜጎች እንደነበሩ መረጃው ያመለክታል። እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ድረ ገጽ ገለጻ አውሮፕላኑ ቢጠለፍም ምንም ዓይነት ጉዳት በሰዎች ላይ ባለመድረሱ በተለዋጭ በረራ ሰዎችን ለማጓጓዝ ጥረት እየተደረገ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህን ከገለጸ በኋላ መረጃውን ከድረገጹ ላይ አንስቶታል።
ቦይንግ 767-300 አውሮፕላንን ጠለፈ የተባለው ምክትል አብራሪው ምንም አይነት የጦር መሣሪያ አለመታጠቁን የዘገቡት የስዊዘርላንድ ሚድያዎች ዋናው አብራሪ (ፓይለት) ወደ መጸዳጃ ቤት ሲያመራ በሩን ቆልፎ ወደ ስዊዘርላንድ እንዲበር አድርጓል ሲሉ ዘግበዋል። ረዳት ፓይለቱ አውሮፕላኑን ጄኔቭ አውሮፕላን ማረፊያ ካሳረፈ በኋላ ከአውሮፕላኑ በመስኮት በገመድ ተንጠላጥሎ በመውጣት እጁን ለፖሊስ በመስጠት ጥገኝነት እንደጠየቀ ተገልጿል፡፡ ጠላፊውም ጥገኝነት ለመጠየቅ ሲል አውሮፕላኑን አቅጣጫ በማስቀየር ለመጠልፍ መገደዱን ከታሰረ በኋላ ለፖሊስ ተናግሯል ሲሉ ሚዲያዎቹ ዘግበዋል።



(የስዊዘርላንድ ፖሊሶች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተሳፋሪዎችን ከአውሮፕላኑ ሲያስወጡ)

የኢትዮጵያ አየር መንገዱ አብራሪ በሃገሩ ላይ የሚደርስበት ስቃይ ይህን ድርጊት ለመፈጸም እንዳነሳሳው መግለጹን የስዊዘርላንድ ኤርፖርት ቃል አቀባይ የገለጹ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በ እስር ላይ እንደሚገኝም አስታወቀዋል።

አውሮፕላኑ ወደ ስዊዘርላንድ እየበረረ ባለበት ወቅት ነዳጅ እየጨረሰ የነበረ መሆኑን የገለጹት ሚድያዎቹ ምናልባትም በቶሎ ጄነቭ ላይ ባያርፍ ኖሮ ከ10 ደቂቃ በላይ የሚያስኬድ ነዳጅ አልነበረውም።
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ሥራ ለመቀጠርም ሆነ ኃላፊነት ለማግኘት የግድ የአንድ ዘር አካል፤ አልያም ደግሞ የኢሕአዴግ አባል መሆን እንደሚያስፈልግ በተደጋጋሚ ከድርጅቱ የሚለቁ ወገኖች መግለጻቸውን የሚያስታውሱ የፖለቲካ ተንታኞች ምክትል አብራሪው ይደርስበታል ወይም ደርሶበታል ተብሎ ከሚገመተው በደል አኳያ እንዲህ ያለውን እርምጃ መውሰዱ ላያስገርም ይችላል በማለት አስተያየታቸውን ይሰጣሉ። እነዚሁ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት የኢሕአዴግ መንግስት በዘር ላይ የሚያደርገውን አድልዎ፣ በደል እንዲሁም “እኔን ካልደገፋችሁኝ ምንም አታገኙም” የሚለውን አካሄዱን እንዲያቆም ይህኛው ትምህርት ሊሆነው ይገባል ይላሉ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ በሚሰራው አድሏዊ ሥራ የተነሳ በርካታ ኢትዮጵያውያን ፓይለቶች ድርጅቱን በመልቀቅ ለሌሎች ሃገራት አየር መንገዶች እንደሚሰሩ በተደጋጋሚ ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም።

‹‹ከኢትዮጵያ ጋር ከመደራደር ይልቅ ሌሎች አማራጮችን መውሰድ እንፈልጋለን›› የግብፅ የውኃ ሚኒስትር

‹‹ከኢትዮጵያ ጋር ከመደራደር ይልቅ ሌሎች አማራጮችን መውሰድ እንፈልጋለን›› የግብፅ የውኃ ሚኒስትር

  • -ግብፅ  ከኢትዮጵያ ጀርባ ቱርክ አለች ማለት ጀመረች
ባለፈው ሰኞ በአዲስ አበባ ለውይይት መጥተው ስብሰባው ተቋርጦ ወደ አገራቸው የተመለሱት የግብፅ የውኃና መስኖ ሚኒስትር መሐመድ አብዱል ሙታሊብ ካይሮ ሲደርሱ በሰጡት መግለጫ፣ ከኢትዮጵያ ጋር መደራደር እንደበቃቸው ከገለጹ በኋላ ‹‹ሌሎች አማራጮችን መውሰድ እንፈልጋለን፤›› ብለዋል፡፡
ሚኒስትሩ በደፈናው ሌሎች አማራጮችን ከማለት ውጪ ማብራሪያ አልሰጡም፡፡ ይሁን እንጂ ንግግራቸውን በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ያነበቡ ኢትዮጵያውያን ንግግሩን ፀብ አጫሪነት ነው ብለው፣ ‹‹ኢትዮጵያውያን ግድቡን እንገነባለን፣ ግብፆች ያላቸው ሌላ አማራጭ ምን እንደሆነ እናያለን፤›› በማለት በቁጣ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
‹‹የኢትዮጵያ የመንግሥት ባለሥልጣናት ግብፅን የመጉዳት ፍላጎት የለንም እያሉ ነው፡፡ ይህንን ግን በወረቀት አስቀምጡልን ብለን ስንጠይቅ አይቀበሉም፤›› ያሉት ሚኒስትሩ፣ በህዳሴው ግድብ ምክንያት በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለማጥበብ በግብፅ በኩል የሚደረጉ ጥረቶችን ኢትዮጵያ እያደናቀፈች ነው በማለት በአገራቸው ቴሌቪዥን ወቀሳ አቅርበዋል፡፡
ከዚህ በኋላ ውጤት ለሌለው ድርድር ጊዜ ማጥፋት ተገቢ እንዳልሆነ የተናገሩት ሚኒስትሩ፣ ‹‹ሌሎች አማራጮች አሉ፣ እነርሱን ወደ መተግበር እንሸጋገራለን፤›› በማለት የአማራጮቹን ምንነት ሳያብራሩ በደፈናው አልፈዋል፡፡
በቅርቡ ኢትዮጵያን የጎበኙት የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን በተመለከተም፣ የግብፅ የውኃና መስኖ ሚኒስትር በዚሁ መግለጫቸው ላይ አስተያየት ሰጥተውበታል፡፡
ሚኒስትሩ አብዱል ሙታሊብ፣ ‹‹ግብፅን የማይወዱ ወገኖች ከኢትዮጵያ ግድብ ጀርባ ይገኛሉ፤›› በማለት የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአዲስ አበባ ጉብኝትን ተችተዋል፡፡ የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአዲስ አበባ በተገኙበት ወቅት ኢትዮጵያ ለምትገነባው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ባለሙያዎችን ለመላክ ፈቃደኛ ሆነዋል ሲሉም ወቀሳ አቅርበዋል፡፡
‹‹ቱርክ፣ አታቱርክ የተባለውን ግድቧን ስትነገባ ሶሪያና ኢራቅ ተቃውሞ ነበራቸው፡፡ ቱርክ የሶሪያና የኢራቅ ተቃውሞን ቸል በማለት ሁለቱን አገሮች ለውኃ ጥም ዳርጋና ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን ጥሳ ግንባታውን አከናውናለች፡፡ አፅንኦት ሰጥቼ ማለት የምፈልገው ኢትዮጵያ ቱርክ አይደለችም፡፡ ግብፅም እንደዚሁ ሶሪያ ወይም ኢራቅ አይደለችም፤›› በማለት ዛቻ መሰል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
እስካለፈው ዓርብ ምሽት ድረስ የቱርክ መንግሥት ለሚኒስትሩ አስተያየት ምላሽ አልሰጠም ነበር፡፡
የግብፅ ሚኒስትር በይፋ በአገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ የተናገሩትን ተርጉመው የዘገቡ የተለያዩ ድረ ገጾችን የተመለከቱ በርካታ ኢትዮጵያውያን፣ ‹‹ሚስተር ሙታሊብ ኢትዮጵያ አሁንም ግብፅን የመጉዳት ፍላጐት የላትም፡፡ የእርስዎ ንግግር ግን የተለመደው የግብፅ ባለሥልጣናት ድንፋታ ነው፡፡ ሌሎች አማራጮች ያሉትን እስኪ እንያቸው፡፡ ከንግግርና መግባባት የተሻለ በዚህ ጉዳይ ላይ አማራጭ የለም፤›› የሚሉ አስተያየቶችን አንፀባርቀዋል፡፡
እኚሁ የግብፅ ሚኒስትር ባለፈው ሰኞ በኢትዮጵያ ተገኝተው ከኢትዮጵያ አቻቸው አቶ አለማየሁ ተገኑ ጋር ተገናኝተው የነበረ መሆኑን፣ ሚኒስትሩ ግን የህዳሴው ግድብ ግንባታ ቆሞ እንወያይ በማለታቸው ስብሰባው መቋረጡን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
ከዚህ ስብሰባ ማግሥት ጋዜጠኞችን በመሰብሰብ በሁለቱ አገሮች መካከል ስላለው ወቅታዊ ጉዳይ በኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ማብራርያ ተሰጥቶ ነበር፡፡
በዚህ ስብሰባ ላይ ከጋዜጠኞች ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል፣ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ ጦርነት በዚህ ዘመን ሊሆን አይችልም በማለት ግብፅ በአማራጭነት እንደማትመርጠው እየተናገሩ ቢገኝም፣ ጦርነት ሊፈጠር ቢችልስ ሲሉ የኢትዮጵያን አቋም ጠይቀዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጡት የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን፣ ‹‹አለመግባባቱን በጦርነት ለመፍታት ኢትዮጵያን መውረርና መቆጣጠር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ይህ ግን መሆን አይችልም፤›› በማለት ምላሽ ሰጥተው፣ ‹‹ማንኛውም አገር ጐረቤቱን ነቅነቅ ለማድረግ የሚፈልገው የጐረቤቱ እግር ወልከፍከፍ ያለ እንደሆነ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ደረጃ ግን ይህንን ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ የለም፤›› ሲሉ አረጋግጠዋል፡፡
የኢትዮጵያን ደኅንነት የበለጠ ለማረጋገጥ ቀዳዳዎችን መድፈን እንደሚገባ ያከሉት ሚኒስትሩ፣ ‹‹የጐረቤት አገሮችን ሰላምና ደኅንነት ማረጋገጥ፣ ከጐረቤቶቻችን ጋር ጥብቅ ቁርኝት መፍጠር፣ ለውጭ ኃይሎች ያደሩ የራሳችንን ሰዎች ነቅሶ ማውጣት፤›› ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ በመቀጠልም፣ ‹‹ጦርነት መክፈት ይቻላል ኢትዮጵያን ማሸነፍ ግን የማይቻል ነው፤›› ብለዋል፡፡
ግብፆች ኢትዮጵያን ብድር የማስከልከል እንቅስቃሴያቸውን አሁንም አጠናክረው መቀጠላቸውን የተናገሩት አቶ አለማየሁ ተገኑ በበኩላቸው፣ የህዳሴው ግድብ ግን የውጭ ኃይሎችን ዕርዳታ አይፈልግም ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ሪፖርተር

Ethiopian Airlines flight hijacked

An Ethiopian Airlines flight bound for Rome has reportedly been hijacked and has now landed in Geneva after circling the air above the Swiss city.
Ethiopian Airlines flight 702 departed from Addis Ababa at 12.30am, and was supposed to land in Rome at 4.40am (local time).
As the plane was flying over Sudan it reportedly began broadcasting a 7500 alert call — which is airline code for a hijacking according to airlinereporter.com.
Images from the FlightRadar website showed the plane circling around Geneva, Switzerland, where it was reportedly low on fuel.
The plane landed at Geneva airport at 6.10am local time.
The airport is reportedly closed to all incoming and outgoing flights.
A press release issued by Ethiopian Airlines online (and since deleted) said the plane had landed safely at Geneva. “Ethiopian Airlines flight 702 on scheduled service departing from Addis Ababa at 00:30 (local time) scheduled to arrive in Rome at 04:40 (local time) was forced to proceed to Geneva Airport,” the statement read.
“Accordingly, the flight has landed safely at Geneva Airport. All passengers and crew are safe at Geneva Airport. “Ethiopian Airlines is making immediate arrangements to fly its esteemed customers on-board the flight to their intended destinations.”

የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር ጄኔራል ፍርድ ቤት ቀረቡ

የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር ጄኔራል ፍርድ ቤት ቀረቡ

-ጥፋት ፈጽመዋል የተባሉትን ፖሊሶች መለየት እንዳልቻሉ ተናግረዋል
በቅርቡ የቀድሞውን የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር ጄነራል አቶ ወርቅነህ ገበየሁን የተኩት የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር ጄነራል አቶ አሰፋ በዩ፣ ችሎት በመድፈር ወንጀል በተጠረጠሩ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ምክንያት ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡
በጥር ወር መጀመሪያ ሳምንት አካባቢ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ቅጥር ግቢ ውስጥ በጥበቃ ሥራ ላይ ሆነው፣ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዘጠነኛ ፍትሐ ብሔርን ችሎት በመድፈርና ዳኛን በማመነጫጨቅ ወንጀል፣ የስድስት ወራት የእስራት ቅጣት ተወስኖባቸው ከነበሩት ኢንስፔክተር ሀብታሙ አሰፋ ሐጎስ ጋር የነበሩ፣ ነገር ግን በወቅቱ ሳይቀርቡ የቀሩ የፌዴራል ፖሊስ አባላትን፣ ተቋሙ እንዲያቀርብ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቶ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል፡፡
ፍርድ ቤቱ በሰጠው ቀጠሮ መሠረት የፌዴራል ፖሊስ ነገረ ፈጅ ኮማንደር ደረጄ ወንድሙ የቀረቡ ቢሆንም፣ ችሎት በመድፈር ወንጀል ከተጠረጠሩ የፖሊስ አባላት መካከል የትኛው ተጠርጣሪ ድርጊቱን እንደፈጸመ መለየት አለመቻሉን አስረድተዋል፡፡
ፖሊሶቹ 15 ሲሆኑ የችሎት መድፈር ተግባር ፈጽመዋል በተባለበት ዕለት የስፖርት ዜና እየተከታተሉ እንደነበር ኮማንደሩ ለችሎቱ አስረድተው፣ አንዱ በሕመም ምክንያት ያልቀረበ ቢሆንም 14 አባላትን ማቅረባቸውንም አክለዋል፡፡ ‹‹ነበሩ የተባሉትን ሁሉ ስላቀረብን ፍርድ ቤቱ አጣርቶ ዕርምጃ ይውሰድ ወይም ይቅርታ ያድርግልን፤›› በማለትም ኮማንደር ደረጄ ለፍርድ ቤቱ አመልክተዋል፡፡
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ሥልጣን ሕግ መተርጎምና ዳኝነት መስጠት መሆኑን ያስረዳው ፍርድ ቤቱ፣ ወንጀልን የመመርመር ሥልጣን በአዋጅ የተሰጠው ለፌዴራል ፖሊስ በመሆኑ፣ ሥልጣኑን በመጠቀም ተጠርጣሪውን መርምሮ ማወቅና ማቅረብ እንዳለበት አስረድቷል፡፡ አንድን ውስብስብ የወንጀል ድርጊት ሕጉን ተከትሎ በመመርመርና በማጣራት ወደ ሕግ ማቅረብ እንደሚችል የታመነበት የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ፍርድ ቤቱን እንዲጠብቁ ከተላኩ የፖሊስ አባላት መካከል የተጠረጠረን አባል መለየት እንዳልቻለና ፍርድ ቤቱ እንዲያጣራ መጠየቁ አግባብ አለመሆኑን ፍርድ ቤቱ ገልጿል፡፡
ለፍርድ ቤት የተሰጠው ሥልጣን ሕግ መተርጎምና የዳኝነት ሥራ መሥራት እንደሆነም ጠቁሟል፡፡ ችሎት በመድፈር ወንጀል ተጠርጥሮ በሚቀርብ ማንኛውም አካል ላይ ፍርድ ቤቱ ተገቢውን የሕግ ትርጉም በመስጠት ተገቢውን ቅጣት መጣል እንጂ፣ ይቅርታ የሚያደርግ ተቋም አለመሆኑንም አስረድቷል፡፡ በተጨማሪም አጥፊው ሳይለይ በጅምላ ይቅርታ መጠየቅም ሆነ ይቅርታ ማድረግ እንደማይቻልም አክሏል፡፡
የፌዴራል ፖሊስ ችሎት በመድፈር ወንጀል የተጠረጠረውን አባል መለየት አለመቻሉን በማሳወቁ፣ ፍርድ ቤቱ የመጨረሻ እልባት ለመስጠት የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር ጄነራል አቶ አሰፋ በዩ ችሎት ቀርበው እንዲያስረዱ ባዘዘው መሠረት ቀርበው አስረድተዋል፡፡
ዳይሬክተር ጄነራሉ አቶ አሰፋ ችሎት በመድፈር የተጠረጠሩ ፖሊሶችን መለየት ስላለመቻሉ ሲያስረዱ፣ ችሎቱ ትዕዛዝ ካስተላለፈበት ቀን ጀምሮ ለማጣራትና ለመለየት የሞከሩ ቢሆንም፣ ‹‹ከ15 የፖሊስ አባላት መካከል የትኛው አባል ድርጊቱን እንደፈጸመ ማወቅ አልተቻለም፤›› ብለዋል፡፡ በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ወደ ተቋሙ (ፌዴራል ፖሊስ) መልሶት አስፈላጊው ዕርምጃ እንዲወሰድ ወይም ፍርድ ቤቱ የራሱን ውሳኔ እንዲሰጥ አቶ አሰፋ ለችሎቱ አስረድተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የመጨረሻ እልባት ለመስጠት በመቅጠር ዋና ዳይሬክተር ጄነራሉን ከምሥጋና ጋር አሰናብቷል፡፡

Friday, February 14, 2014

የአዲስ አበባ እድሮች ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በድጋሜ መዋጮ እንዲያዋጡ ታዘዙ.

የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ መስተዳድር የካቲት 2፣ 2006 ዓም ከእድር ተጠሪዎች ጋር ባደረጉት ስብሰባ እያንዳንዱ እድር በነፍስ ወከፍ 8 ሺ ብር ለአባይ ግድብ ማሰሪያ እንዲከፍል ታዟል።
ትእዛዙ የተጣለው የካቲት 2 ቀም 2006 ሲሆን፣ 650 እድሮች በነፍስ ወከፍ 8 ሺ ብር ይከፋላሉ። በዚሁ ከላይ በወረደው መመሪያ መንግስት ከእድሮች በአንድ ጊዜ 5 ሚሊዮን 200 ሺ ብር ይሰበስባል።
ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሰው እድሮች በፈቃዳቸው መለገስ ሲችሉ፣ በግዴታ ገንዘብ እንዲያዋጡ መደረጉ በአንጻራዊ መልኩ ገለልተኛ በሚባሉት እድሮች ሳይቀር ጣልቃ እየገባና እየመራ ነው ብለዋል።

Wednesday, February 12, 2014

የአቶ አለምነው መኮንን መኖሪያ ቤት በድንጋይ ተደበደበ

February 12/2014

የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የብአዴን ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን መኖሪያ ቤት በድንጋይ መደብደቡን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጠቆሙ፡፡ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች እንጠቆሙት ባሳለፍነው ሳምንት የካቲት 1 እና የካቲት 2 ቀን 2006 ዓ.ም(ቅዳሜና እሁድ) ለሊት በተደጋጋሚ ማንነታቸው ባልታወቀ ግለሰቦች መኖሪያ ቤታቸው በድንጋይ መደብደቡን ተከትሎ ቤታቸው ቀንና ለሊት በፖሊስ እየተጠበቀ ይገኛል፡፡
አቶ አለምነው መኮንን የአማራን ህዝብ የሚያዋርድና የሚዘልፍ ንግግር ሲያደርጉ የተቀዳ ድምፅ ለህዝብ ይፋ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ በብአዴን ውስጥ የንትርክ ምክንያት መሆናቸው አይዘነጋም፡፡

የጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ መልዕክት ከዝዋይ ማረሚያ ቤት፡ ሰው ለሆኑ ሰዎች በሙሉ!

February 12/2014

በጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፤ ከዝዋይ ማረሚያ ቤት


‹‹ይህንን ስለመሳሰሉ ጉዳዮች መወያየት ክልክል ነው፡፡›› በማለት በተንጎላጀጀ ድምፅ ጠባቂው ተናገረ፡፡ ቀጠል አደረገናም ‹‹መነጋገር የምትችሉት ስለቤተሰብ ጉዳዮች ብቻ ነው›› በማለት ተናገረ፡፡ ይህን ከላይ ያለውን ሐሳብ የሚመለከት ማንኛውም አንባቢ፣ ጉዳይ የተፈፀመው እዚህችው እማማ ኢትዮጵያ ሰማይ ስር ባሉ አጃኢበኛ እስር ቤቶች፣ ቤተሰብ መጠየቂያው እንደሆነ መጣራቱ አይቀርም፡፡

ይሁንና በመግቢያው ላይ ያለው ጽሑፍ ተቀንጭቦ የተወሰደ ‹እናት› ከተሰኘውና እ.ኤ.አ. በ1906 ከታተመው የስመ ጥሩው ሩስያዊ ደራሲ ማክሲም ጎርኪይ ታሪካዊ ልቦለድ ገፅ 102 ላይ ነው፡፡ የዛሬ 108 ዓመት አካባቢ ማለት ነው፡፡ አቤት ርቀቱ!… ይህ ርቀት ግን ለእኛ ምንም ማለት ያልሆነ ይመስላል፤ ለምን? ቢሉ ዛሬም ይህንንና ይህን የመሳሰለውን አስፍተን እየሠራን እንገኛለን፡፡ እንዲያውም በአንዳንድ ሁኔታዎች እየተጓዝን ያለነው የቁልቁለት ሩጫ በእጅጉ አሳሳቢ ሆኖ ይገኛል፡፡

የነገሮች ሁሉ መድረሻ እስር ቤቶች እየሆኑ መጥተዋል፡፡ ‹ጠበቅ ያለ እርምጃ፣ የማያዳግም እርምጃ፣ የማስወገድ እርምጃ፣…› ወዘተ የሞሉ ከሕግ መርሕዎች ሳይሆን ከጥላቻ ፖለቲካ የሚመነጩ ፀያፍ አነጋገሮችን በሕዝብ የመገናኛ ዘዴዎች ሲተላለፉ እየሰማን እየታዘብን ነው፡፡ ቃል በቃል ‹ቀይ ሽብር ይፋፋም› ብሎ ማወጅ የቀራቸው የሕግም የግብረገብም ሚዛን ያልወጣላቸው ቀረርቶች በተለይ በእስር ቤት የምንገኝ ኢትዮጵያውያንን እየሰበሰቡን ይገኛሉ፡፡

በኢ.ቴ.ቪ. የአብዮታዊ እርምጃ ፕሮግራሞች በቀረቡ ማግስት አሁን በዝርዝር ብለው የብዙ ቤተሰቦችን ስሜት ሊያሸማቅቁ የሚችሉ ሰቆቃና እንግልቶች በአስደማሚ ስልት ተቀናብረው ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡ እስኪ የተወሰኑትን እንይ፡፡ ማንኛውም ታሳሪ ቤተሰብ በቅርብ ሊጎበኘው በሚችለው እስር ቤት ይታሰር የሚለው ሕግ የተሻረው በእኛ ላይ ነው፡፡ ዝዋይ የአገራችን ‹ሳይቤሪያ ግዞት› ማለት ናት፡፡ ቤተሰብ ያን ያህል የበርሃ ጉዞ አቋርጦ የእኛዋ ሳይቤሪያ ሲደርስ በአድካሚና ግብረ-ገብ በጎደለው ፍተሻ መከራውን ማየቱ አንሶ ጆሮ ግንዱ ላይ በቆሙ የቤተሰብ አገናኞች ቤተሰባዊ ገመናውን አሳልፎ ይሰጣል፡፡ ሕፃናት ልጆች ወላጆቻቸው አንድ ላይ ሆነው ናፍቆታቸውን መወጣት አይችሉም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፖሊሶቹ ሲዘናጉልን ልጆቻችንን አቅፈን እንስማለን፡፡ ይህ ከሆነ ቁጣና ዘለፋው ምንም አይደለም፡፡ ግን በሁኔታው ሕፃናቱ ክፉኛ ይበረግጋሉ፣ የእኛ ስጋት ይጋባባቸዋል፤ በዚህም መንፈሳቸው እርብሽብሽ ብሎ ወደቤታቸው ይመለሳሉ፡፡

ሁኔታው በዚህ አያበቃም፡፡ ምንም እንኳን የመጠየቂያ ሰዓቱ በግልፅ የተቀመጠ ቢሆን ከቤተሰቦቻችን ጋር ገና መነጋገር ስንጀምር ‹‹በቃ… ቶሎ ጨርሱ›› የሚባልባቸው ጊዜዎች ብዙ ናቸው፡፡ ቀጥሎ የሚመጣው የእስር ቤት ማኅበራዊ ጉዳዮችን ማለትም ለሳሙና፣ ለምግብ ማጣፈጫ፣ ለሻይ ለቡና፣ ለውስጥ አልባሳት፣ ለውኃ ማከሚያ/ውኃ አጋር/ ወዘተ፤ ገንዘብ የሚያስፈልገን ቢሆንም እና እንደሚያስፈልጉ ቢታወቅም ጉዳዩ ለይቶለት የማሰቃየት፣ ማንገላታት፣ መበቀል ሆኗልና ለአንድ ወር ከአንድ መቶ ብር በላይ መጠቀም እንዳንችል የተከለከልን የመሆኑ አሳፋሪ ሐቅ ነው፡፡ ይህ እየተፈፀመ ያለው ደግሞ ዝዋይ እስር ቤት ውስጥ ብቻ ነው፡፡ በዚህ የተነሳም ለመግለጽ በሚከብድ ሁኔታ ሰብኣዊ ክብራችንን የማዋረድ ሙከራዎች እየተፈፀሙ ነው፡፡

በአገራችን ላይ እኔ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን የጨረስኩት ዝዋይ በመሆኑ ብዙ ወዳጅ ዘመዶቼ በእዚህ ይገኛሉ፡፡ ሆኖም ለአካባቢው ነዋሪዎች በሳምንት እንዲጠይቁን የተፈቀደላቸው አንድ ቀን /ረቡዕ/ ብቻ ሲሆን ‹‹የት ነው የምታውቁት? እንዴት አወቃችሁት? ምንድን ነው የሚያመላልሳችሁ?›› በሚሉትና በሌሎችም ጥያቄዎች ተደናግጠው መምጣቱን እርግፍ አድርገው ትተውታል፡፡

ሀገሩ ሞቃታማ ነውና በዚያ ላይ በእያንዳንዱ ቤት እስከ 150 ሰው ይታሰርበታል፡፡ ይህ ሁሉ ተደማምሮ እስረኛው የቱንም ያህል ፅዳቱን ለመጠበቅ ቢሞክርም የተባዩ መርመስመስ የእነ ትኋን እንዲህ መራባት፤ ለማሰብ እንኳን ይዘገንናል፡፡ ሌሊቱን ሙሉ ገላን ሲቆፍሩ ማደር ነው፡፡ ሊናገሩት ይከብዳል፣ አንባቢንም ቅር ያሰኛል፤ ግን ይህ የፊልም ትረካ ሳይሆን በእማማ ኢትዮጵያ ልጆች ላይ ሆን ተብሎ እየተፈፀመ ያለ ደባ ነው፡፡ […] ግን የባሰ አታምጣ ማለት ነው!

ግን የባሰ ነገር አለ፡፡ አፈር ቅጠል የማይል ምግብ ይቀርብናል፡፡ ‹በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ› ከፍተኛ የውኃ እጥረት /ዝዋይ ሀይቅ አናት ላይ ተቀምጠን/ አለ፡፡ የእስር እስር እንዲሉ ጄኔራል መኮንኖቹን ጨምሮ አብዛኛዎቹ አባሪዎቻቸውና ሌሎች ሌሎች የተወሰንን እስረኞች የምንገኘው በልዩ ቅጣት ጭለማ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ይህንን ሁሉ እንደምንም ለመቋቋም ጥረት ማድረግ ይቻል ይሆናል፡፡ አዲሱ ስልት ግን መዘዙ በጣም አደገኛ በመሆኑ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ፣ እያንዳንዱ ሃይማኖት ያለው፣ ፈርሐ እግዚአብሔር ያለው፣ እያንዳንዱ የመሠረታዊ ሰብኣዊ መብቶችና ነጻነቶች መከበር የሚያሳስበው እያንዳንዱ ሰው የሆነ ሰው ሁሉ ሊያውቀው ይገባል ስንል ድምፃችንን እናሰማለን፤ በሕክምና ንፍገት ወደሞት እየተገፋን ነው፡፡

ከወር በፊት ገደማ ወጣቱ የአንድነት ፓርቲ አባል ናትናኤል መኮንን ለሕክምና በሪፈር ወደ ቃሊቲ ተልኮ የነበረ ቢሆንም፣ የዛኑ ዕለት ሕክምናውን ተነፍጎ ከሌሊቱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ እንዲመለስ ተደርጓል፡፡ እስካሁን በሕመሙ እየተሰቃየ ይገኛል፡፡ የኢብአፓ ሊቀመንበር የነበረው ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር እንደዚሁ ለተጨማሪ ሕክምና ሪፈር ተብሎ ሲጠባበቅ ከቆየ በኋላ ዘዴው ተፈፃሚ ሆነበት እጁን አጣጥፎ ተቀምጧል፡፡ ከሕመሙ ጋር በተያያዘ በአካሉ ላይ አሳሳቢ ሁኔታ እየታየበት ይገኛል፡፡ ከዚህ ቀደም ገልጬው የነበረው የእኔ የኩላሊት ሕመም አሁን ለመቀመጥም፣ ለመንቀሳቀስ እያወከኝ የሚገኝ ሲሆን፣ እኔን ከቃሊቲ ዝዋይ ለማምጣት የተደረገው የተቀናጀ መረብ ሩብ ያህሉን ለሰብኣዊነት አውለውት ቢሆን ኖሮ እኔም ፋታ፣ እነሱም እርካታ ባገኙ ነበር፡፡ ሕመም ካልታከመ መጨረሻው ሞት ነው፡፡ የሞቱም ሰዎች አሉ!

የጄኔራል መኮንኖቹ አባሪዎች የነበሩት ኮረኔል ተስፋዬ ኃይሉ እና ኢንጂነር ክፍሌ ስንሻው፣ በዶክተር መረራ በሚመራው ኦሕኮ ፓርቲ አባል የነበሩት አሕመድ ነጃሺ፣ በጭለማ ቤት የከረመው ተስፋሀን ጨመዳ፣ የቤንሻንጉሉ አዛውንት ወዘተ ተገቢውን ሕክምና በማጣት ሕይወታቸውን ያጡ የእማማ ኢትዮጵያ ልጆች ናቸው፡፡ እንዴት ሕክምና ይከለከላል!? ግፍና ጭቆና ተቃውመው ደማቸውን ያፈሰሱና አጥንታቸውን የከሰከሱ ታጋዮችን በሥልጣን ማግስት ከፍርድ በመለስ በየእስር ቤቱ ያሉ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻቸው በሕክምና እጦት ሲረግፉ በእርካታ ማርመምን ከየት ተማሩት!? የኢትዮጵያ ሕዝብስ ምን ይላል!? ሰው የሆኑ ሰዎች ሁሉ ከቶ ምን ይላሉ!?

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

(ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚታተመው ኢትዮ-ምኅዳር ጋዜጣ የተወሰደ)