Pages

Tuesday, November 11, 2014

THE BRUSSELS ETHIOPIAN HISTORICAL MARCH!

November 10, 2014

Nightmare at the Woyyane Embassy

by Wondimu Mekonnen
Introduction
Nightmare at the Woyyane Embassy
The Woyyane (The TPLF) is a terrorist organisationi that is holding Ethiopia at ransom. Since the these criminals came to power, nothing changed in their wild behaviour. They were terrorists yesterday, they are terrorists today and unless they are stopped now, they wouldn’t change their behaviour in the future. The worsening brutality of the ethno-apartheid Woyyane (i.e. ethnic based black on black apartheid) regime has left Ethiopians with no option but to come together and resist tyranny of the worst kind in their history. As crackdown on the opposition members, journalists, religious leaders (both Christians and Muslims), and professional and human rights activists steps up, resistance is also rising to next level to defend the existence of oneself with more commitment and determination.
On 7th November 2014, this was the cause for the call of all Ethiopians to meet up in Brussels, the beautiful Belgian Capital City. The illegal and criminal abduction of Andargachew Tsege, General Secretary Ginbot 7 from Sana’a Airport was meant to scare-shock and silence the exiled community of Ethiopians to coil back into their shells but that was a wrong calculation on the part of the Woyyane. It proved otherwise.
The ethno-apartheid regime’s outrageous of series of abduction has ignited the fury of Ethiopians. They have been abducting the Oromo, the Ogadenese, the Gabellans from neighbouring counties. They have now upgraded that to the abducting an international air transport passenger. Will they get away with such blatant transgression of human rights? Their true colour is now exposed. Apart from the abduction, their murder squad has also been deployed in the cities of the World with diplomatic immunity. The recent brandishing of gun and shooting at demonstrators in Washington as we witnessed on 29 September 2014ii just a good example. That man has murdered single headedly during the 2005 election and before. Will we lie and day next day without resistance when they walk into our kitchen and murder us in exile tomorrow? No! Living under the yoke of fear is not life!
Protests and resistance are growing day by day, taking lessons from past mistakes and perfecting the means and methods of defending the Ethiopian interest, be it inside or outside the country. Woyyane (The TPLF – Tigray Peoples’ Looting Front) cannot continue governing by whining and dealing any more. The religious division be over. The ethnic politics is long rotten and should be abolished. When an Oromos is killed the Amara should protest. Ogadenese are our flesh and blood. We needed to wake up from our hypnotic stupors and rise up for resistance. Every ethnic group within the country are now aware the evil tactics of divide and rule. No more ruling Ethiopia by iron feast! Brussels! Thanks for hosting us!

Ethiopian Alliance in Europe

The November 7 Brussels demonstration in front of the EU Headquarters and the march to the Woyyane occupied Ethiopian Embassy was organised by “The Ethiopian United Task Force for Justice and Human Right in Europe” hereafter, “Task Force”, which is part and parcel of the global movement of Ethiopians for justice and democracy. Unity is power! Ethiopians are inching forward to create a formidable force to step up resistance to survive!
Earlier, on 5th September 2014, the same Task Force held a very huge and successful demonstration in Londoniii, Europe based Ethiopians in London, forcing the closure of Downing Street and creating traffic jam. The media that was ignoring the cry of passive Ethiopians now became alerted when their roads were jammed. We had to explain, peacefully and legally about how the British taxpayers’ money has been used to keep dictatorship breathing in Ethiopia. The Brussels demonstration is the 2nd in the series of planned actions and demonstrations to expose atrocities committed by the Woyyane regime in Ethiopia and even in neighbouring countries against Ethiopians living there. An evidence of that includes, the abduction of Mr Sulub Ahmed and Ali Hussein from Nairobi on 26 January 2014 (by the way theywere there to negotiate peace with Woyyane), Okelo Akuayi Ipola from Juba (South Sudan) in June 2014 and Andargachew Tsege from Sanaa Airport (Yemen) on 22 June 2014iv. These acts are nothing but pure terrorism. When on earth can a terrorist can be trusted to become an ally against terrorismof the democratic word?
Ethiopians everywhere have risen up to expose the irony across cities of the world. The Task Force’s objective is to transform those local actions into united global action to bring the Woyyane on its knees and stop the murders, killings, maiming, abductions and illegal imprisonment of citizens anywhere and harassing of refugees throughout the world. Where did the Woyyane got all that power. For sure, that power came from the money donated by West. To dry up the tears of mothers in Ethiopia, we need to dry the source of funding of tyranny.

The Brussels Schuman Square Demonstration

The objective of the demonstration at Schuman Square, the roundabout at the end of Rue de la Loi in Brussels, was to demand actions to be taken to tame the brutal dictatorial ethno-apartheid regime of Ethiopia, by the institutions of the European Union (EU), such as the European Parliament, the European Council, the Council of the European Union, the European Commission. Wining and dining with the aggressors is not the way to do business. Quiet diplomacy does not work on Woyyane. Money talks!
These terrorists come from the bush 23 years ago and still acting wild. They don’t understand at all the meaning of peace, democracy and justice. It doesn’t exist for them. They want to rule by gun and fear. The scare mongering and fear factor goes beyond their own citizens. We have witnessed recently how the Prime Disaster of Ethiopia threatened BBCv and CNN journalists with arrest if the journalists keep on putting their noses in what they do.
The European Union cannot claim ignorance about what is going on in Ethiopia with regards to the gross violation of human rights in that country. Their own investigation was reported back to them by the EU Human Rights Committee on 24 September 2014vi, regarding the gross violation of human rights and atrocities committed against citizens in Ethiopia, with particular reference to the case of Andargachew Tsege, Zone 9 bloggers, journalists, human rights activists, Muslim leaders, Oromos, Ogadenesevii and political opponents. After all that deliberation, as the Chairwoman and Rt Hon Anna Gomez said, the EU Governments are not really doing enough rather than expressing “CONCERNS”. Woyyane is too uncivilised to understand the message behind “CONCERNS”. Real and tangible action is what understands. Particularly when it comes to money to goes on its knees. We are not asking to march European army to protect the people from Ethiopia. Ethiopians can do that for themselves if need be. What is needed here is to stop bankrolling a regime that terrorises its people. However, EU and US Governments keep on sustaining the dictators in the name alliance against terrorism. Well, although we don’t expect the West learns lessons, Ethiopians just wanted to pay their attention to Burkina Faso. Comes the day, not money or guns of EU or USA would save dictators from the wrath of the people. The Woyyane came to power through blood shade; using money donated by kind hearted people to feed the starving but used it to buy deadly weapons. They will not be going anywhere as long as money keeps on pouring in from the West. Do the West know that these guys Albanian type communists?
We have learned that the human rights activists in the EU are so frustrated against their own governments for non-action. Of the record, all the government representatives admit that a quiet diplomacy is chosen with Ethiopia because if the EU take serious action to stop the brutality, the regime would go into the arms fold of the Chinese Government. Give me a break! The Chinese have already been in Ethiopia, working with the tyrant regime very closely in every area, including military, jamming of radios and televisions broadcastings, building roads for quick deployment of the army, banning of the internet and the social media, such as facebook, twitter and blogs. The TPLF (Woyyane) are unchanged communists. They are much closer the Chinese Communist part than any democratic parties in the world. However, the Chinese are not generous enough to bankroll Woyyane for ever. They are there to obtain resources. If the EU and USA borrow some guts from their historical ancestors, who were champions of democracy and justice in their countries, rather than unconditional provision of dollars, pounds and Euro in abundance to that regime, Woyyane would start respecting human rights for the sake of aide money. We are saying stop giving away taxpayers money to human rights abuser regimes. Is it too much to ask? Well, if that is too much, then just they have to sit back and wait until 90 million Ethiopians flee into exile and then knock at their doors seeking asylum, which many politicians are unashamedly using as their election manifesto. Let the West stop giving away the tax payers money to support a tyrants like that of Ethiopia and then no refugees risk pershing in the seas and deserts to reach here. Had there been no murderous regime in power, Ethiopia is not a country to run from, but to run to. That was the message Ethiopians wanted to deliver to the EU Governments.
As atrocities are stepped up, Ethiopians are rising up too, united, to use every means available to them to get rid of tyranny. In line with that, those of us, who were exiled to escape from persecution in our homeland reached Europe, have the moral obligation to the people left behind to become the voice for the voiceless millions of Ethiopians under the yoke of repression. Protests and demonstrations are the only legitimate means available to the Diaspora, and Ethiopians shall pursue vigorously their peaceful goal, while others in the country would defend themselves by any means necessary. No one condemns those who to took up arms in the country because they had no other option to combat tyranny. There is no political space for the opposition to struggle peacefully. Win election, you will be jailed for treason! Woyyane has got total monopoly on power!
On 07 November 2014, Ethiopians from Norway, Switzerland, Sweden, Netherland, France, Italy, Luxemburg, Germany and The United Kingdom traveled to Belgium to join their compatriots living there with one mission on their minds. All flocked to Brussels to pass the cry of their people, to hold EU Governments responsible for lengthening the suffering of that nation, by ignoring people’s cries and bankrolling their tormentors. Of course these voices are not in vain. Peaceful struggle may not produce a quick fix, but slow and agonising. However it is an indispensible part of overall struggle. These activities are bearing fruits in the United Kingdom. International Human Rights organisations residing in the UK, such as, Amnesty Internationalviii, Human Rights Watchix, the Frontline, Pen International, Reprieve, Redress, are holding the UK Government responsible for the suffering of the Ethiopian people by the supporting the human rights violators in Ethiopia. Giant newspapers, such as the Independentx, The Guardianxi, and The Daily Mailxii are questioning the government’s wisdom on the financing of the human rights violators in Ethiopia with the tax payers money. This has forced the UK Government, to withhold at least a token money of £2 million to fund masters degrees for 75 Woyyane officialsxiii. PM David Cameron has written Prime Disaster Hailemariam Dessalegn his “concern” about the arrest, disappearance of a British citizen Andargachew Tsege.xiv
The demonstration had media coverage. Belgian journalists were there from the start to the end, with their cameramen and reporters. We know about that because we talked to them. One of the wonderful things about them was that two journalists this writer met did not need any explanation about what is going on Ethiopia because they knew more than I knew regarding human rights violations in Ethiopia. The two European ESAT teams were there. The Amsterdam office came with journalists Fasil Yenelem, Afeworq Agidew and their cameraman. The London office was represented by Metasebia Qetsela and Wondimagegn Gashu. DW German Radio was reporting from the spot through Gebeyaw Negussie.
The demonstration at Schuman Square was well organised and coordinated. The organisers made sure everything was executed with precision. The messages were clearly heard and the posters were seen and read by thousands of local people. Leaflets were distributed and briefings given by activists to whoever wanted to know more. That noisy demonstration at the EU offices was the biggest and loudest. EU staffs were attracted and came out of their offices to find out what was going on. Pictures of Andargachew Tesege, Eskinder Nega, Reeyot Alemu, Woubshet Taye, Olbana Lelissa, Temesgen Dessalegn, Andualem Arage,Nathnael Mekonnen, Mitiku Damte, Yeshiwas Yehunalem, Kinfemichale Deebe, Andualem Ayalew, Yohannes Terefe, Zerihun Gebre-Egziabher, Abraha Desta, 5 Mulim leaders and many others prisoners were displayed.
The office of Signora FedericiaAround 3:00 p.m. two petition letters were submitted to the office of Signora Federicia Mogherini – High Representative of European Union for Foreign Affairs and Member of European Parliament, Rt Hon. Mrs Ana Maria Gomes. Earlier, Yemi (Andargachew’s wife) and Bizuwork (Andargachew’s sister) talked to official of EU, regarding gross violation of human rights in general and Andargachew in particular.
One of the amazing images at Shuman Schuman Square was a coffin carried by two Ethiopians. On it was written: “Justice is dead in Ethiopia! Freedom is Dead, Democracy is Dead!”. The following short clip shows how the demonstrator conveyed the message to EU.https://www.youtube.com/watch?v=Y8Ba5XUQ3II&feature=youtu.be. That coffin later was damped at the Woyyane occupied Ethiopian Embassy which will be describe later.
Another sight the attracted onlookers the actions of four Ethiopians youth in orange prisoners’ clothes. They kneeled down in the middle of the road surprising the Police and the onlookers with crossed hands above their heads symbolising the fact that that the whole nation was prison. That symbolic action of the demonstrators attracted a large crowd, to watch them and find out what was going on. Cars stopped, hooted their horns in support. Woyyane is exposed at the most important place source of its mony! Its brutality was exhibited both pictorially and symbolically like the youth did.
Woyyane is exposed at the most important place source of its mony!

The march to the Woyyane occupied Ethiopian Embassy

The Ethiopian embassy in Brussels is about 15 good minutes walk from Schuman Square. At about 3:30 p.m., the demonstrators started marching to the embassy. Although the demonstrators marched through Parc du Cinquantenaire the noise remained deafening. From the front, one can barely see the middle of the line, although the demonstrators were walking in four lines, singing and shouting slogans. Those in the park were stunned and were watching with wide opened eyes. Although the Police tried to keep traffic disruption at minimum, truly speaking it The march to the Woyyane occupied Ethiopian Embassy.did not help them much due to a huge number of the crowed and long lines of well ordered marchers. The roads leading to Avenue de l’Yser, Avenue des Gaulois, Avenue des Celtes and Avenue de Tervuren were blocked. Traffic was halted, trams stopped moving for almost froze, and the residents of the quiet area shocked for witnessing such a noisy protest along that line for the first time in their area.https://www.youtube.com/watch?v=iyM2nmQGApM&feature=youtu.be!
The former Ethiopian Embassy, now occupied by the Woyyane gangsters is located on Avenue de Tervuren 62. When the front line of demonstrators arrivedmarchers were confused confused because although there were flags of other Embassies hoisted high on the buildinga, no Woyyane Ambasha flag to be seen anywhere. The writing on the wall was small. Until the Belgium resident Ethiopians arrived to guide no one where to look. The demonstrators were shocked to find the Woyyane flag with Ambasha emblem in the middle was actually brought down from its mast, left on the 2nd floor, still some parts of it attached to the mast as could be witnessed from the following picture.
The demonstrators were shocked to find the Woyyane flag with Ambasha emblem in the middle
That was incredible! Somebody had taken it down but failed to remove it from the mast and left it as a trash! Well, so much for Woyyane, who had designated a “Flag Day!” (ድንቄም “የባንዲራ ቀን”). They dishonoured their flag with their own emblem on it. They reject it! We don’t know what had happened, really. If somebody from the inside did it in solidarity with us, we simply say “Good job!” Anyway, as diplomats keep defecting, we will soon know the whole story when one of them defects from Amsterdam. Just watch it.
After all the demonstrators gathered at the Embassy gate, all that was left was to storm the Embassy and try to hoist the true right flag on the mast. We did expect one of the Woyyane thugs to come out and start shoot at the demonstrators, but it did not happen this time. Leave alone coming out to confront the demonstrators, they were nowhere to be seen. They shut the doors and windows and remained out of sight. The demonstrators broke the Police barrier, and rushed to the front door. Everyone poured in. Some demonstrators managed to pass the Police to smash through the locked door. The Police wrestled with them. And yet, the demonstrators had managed dumped the Coffin at the door reading “Justice is dead in Ethiopia! Democracy is dead! Freedom is dead”, murdered by Woyyane thugs. That was the message to be delivered and it was done with precision. The Police did not remove the coffin. They left it there. More and more riot Police arrived and joined the skirmish. An Ethiopian girl fought her way with the Police, past the force and hoisted the true flag on the fence, which is only about a couple of meters from the entrance door. Police bundled her back, among the shouts and screams. Still be it for few minutes, Ethiopians still managed to hoist the true flag by the Embassy building as it can be seen here in the picture above.
Ethiopians managed to hoist the true flag by the Embassy building
Once points were successfully made, and Woyyane officials buried themselves like a scared mice behind closed door, windows and curtain, only one thing was left. To avoid arrests, the organisers begged the demonstrators to go back to their line. Interestingly, that large crowed decided to listen to the organisers at once. Where the Police failed to manage the large crowed with all that huge force, the organisers managed to achieved it with simple instructions to move back.
Close to 4:30 p.m., the demonstrators decided to call it a day. The nightmare at 62 Avenue de Tervuren, was over in an hour battle with the Police. No one was arrested or hurt.
The majority went straight to a meeting hall to discuss on the next move and strategy. There is a unanimous agreement among the demonstrators that European cities should not be safe to any Woyyane official coming from Addis. The rest of the demonstrators rushed to the train stations and Airport to travel back to the countries they came from.
The Brussels protest has been a success. Our Brussels Task Force branch headed by Gebeyehu Desta need to be commended for organising and catering for the needs of all those demonstrators from all European countries.

ፓርቲዎች ለሃይማኖት ተቋማት ጥሪ አቀረቡ

ጥቅምት (ሠላሳቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ››በሚል መርህ ትብብር  የመሰረቱት 9 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቀደም ብለው ባሳወቁት የአንድ ወር መርሃ ግብር መሰረት የጀመሪያውን ጥሪ ለሃይማኖት ተቋማት አድርገዋል።
ፓርቲዎቹ አገራችንና ህዝቧ በተፈጥሮ ሚዛን መዛባት በሚከሰትበትም ጊዜ ሆነ በአገዛዝ ሥርዓቶች ምክንያት በችግር ውስጥ በሚወድቁበት ጊዜ የኃይማኖት  ተቋማትና ምዕመናን ሚና ከፍተኛ እንደነበር አውስተው፣ ዛሬ ላይ እነዚህ የሞራልና ሥነ-ምግባር እሴቶች እየተናዱ በመሄዳቸው ዜጎች ለማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ
ምስቅልቅል ተጋልጠዋል፣ የአገር ፍቅር ስሜት በጥያቄ ውስጥ ወድቋል ብለዋል። በመቻቻል ፋንታ ግጭትና መፈናቀል በአራቱም አቅጣጫ ህዝብን ለሥቃይና ለሥጋት ዳርጓል የሚሉት ፓርቲዎቹ፣  የህግ ‹‹አምላክ›› ክብር እያጣ ፍትህ እየተዛባ ፣ ወህኒ ቤቶች በታሳሪዎች እየተጨነቁ፣ የምግብ ተረጂውና የጎዳና ላይ
ተዳዳሪው ዜጋ ቁጥር እየተበራከተ በአጠቃላይ የህዝባችን ኑሮና ህይወት፣ የአገራችን ሠላምና መረጋጋት ፈታኝና አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑም ገልጸዋል።
” ተቃዋሚዎች እና ገዢው ፓርቲ በአገራችን ጉዳይ ላይ ጨፍ እና ጫፍ መቆማቸውን  በመግለጫቸው የገለጹት ፓርቲዎች፣ በተለያየ ምክንያት በሁለት ጠርዝ ላይ የቆሙ ኃይሎች ወደ ብሄራዊ መግባባትና ዕርቅ እንዲመጡ፣ በህዝብ ውስጥ የሚታየው የሞራልና ሥነምግባር ጉድለት እንዲቃናና የመቻቻልና መተሳሰብ
ስሜት እንዲያንሰራራ   የዜጎች ሥቃይና ሥጋት ተወግዶ በተስፋ እንዲሞላ ፣ በአገራችን መረጋጋትና ዘላቂ ሠላም እንዲሰፍን ዜጐች ይጠልዩ ዘንድ ጠይቀዋል አንዲሁም ቀጣይና ዘላቂ ልማት እውን እንዲሆን፣ አብሮነታችንና አንድነታችን እንዲጠናከር፣ የአገር ፍቅር ስሜት እንዲለመልምና ለሉዓላዊነታችን ያለን ቀናዒነት
እንዲጠናከር በሰንበትና የጁምኣ ቀናት በጋራ እንዲሁም በየግል የዘወትር ጸሎት ፈጣሪ አምላክን በመለመን ለተያያዝነው አገራዊ ዓላማና የጋራ ጥረት ድጋፋችሁን እንድታደርጉ ” እንጠይቃለን ብለዋል።
9ኙ ፓርቲዎች ለአንድ ወር በሚካሄደው የትግል መርሃ ግብር፣ የቤት ውስጥ ስብሰባዎችን ከማዘጋጀት ጀምሮ ለአንድ ሙሉ ቀንና ሌሊት የሚቆይ የተቃውሞ ሰልፍ አዘጋጅተዋል።

በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ በተለይ በዚህ ሳምንት ተባብሶ መቀጠሉ የአዲስአበባ ነዋሪዎችን እያበሳጨ ነው፡፡

ጥቅምት (ሠላሳቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-‹በተለይ ባሳለፍነው አንድ ሳምንት ጊዜያት ውስጥ መቆራረጡ በወሳኝ ሰዓታት ጭምር ማለትም በምሽት እና በጠዋቱ ጊዜያት ተጠናክሮ መቀጠሉን የገለጹት ነዋሪዎች በዚህ ምክንያት ለከፍተኛ ኪሳራና ወጪ እየተዳረጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ባለስልጣናት «የኃይል እጥረት የለም፣ እንዲያውም ተርፎን ለጎረቤት ሀገራት ኤክስፖርት እያደረግን ነው» በሚሉበት በዚህ ወቅት በተለይ የአፍሪካ ርዕሰ መዲና መሆንዋ በሚነገርላት አዲስአበባ ከተማ በቀን በአማካይ እስከ ሶስት ጊዜ ያህል በተደጋጋሚ ኤሌክትሪክ የሚቆራረጥበት ምክንያት ጨርሶ
ሊገባቸው እንዳልቻለ አስረድተዋል፡፡ ነዋሪዎቹ በቤት ውስጥ እንጀራ ለመጋገር ሲዘጋጁ መብራት እንደሚጠፋ ቆይቶ ሲመጣ እህሉ ለብልሽት እንደሚዳረግባቸው እንዲሁም በወቅቱ በኤሌክትሪክ አብስለው ለመመገብ አለመቻላቸው ተናግረዋል፡፡ አንድ ስሙን መጥቀስ ያልፈለገ ወንደላጤ ወጪ ለመቆጠብ በብዛት
ቤት ውስጥ አብስሎ እንደሚመገብ ጠቅሶ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ግን መብራት በተደጋጋሚ ስለማይኖር በቋሚነት በሆቴል ለመመገብ መገደዱንና ይህ ደግሞ ከአቅም በላይ ወጪ እንዳስከተለበት በምሬት ተናግሮአል፡፡ አንድ የአራት ልጆች አባት እንደሆኑ የተናገሩ ነዋሪ በበኩላቸው  በቀን እስከአራት ጊዜ መብራት መጥፋቱን
መታዘባቸውን አውስተው መብራት በሚጠፋበት ወቅት ማታ ማታ ልጆች በጊዜ ስለሚተኙ የቤት ስራ እንኩዋን መስራት አለመቻላቸውን አስረድተዋል፡፡
የኤሌክትሪክ ሃይል በሚቆራረጥበት ጊዜ የሞባይልና የኢንተርኔት አገልግሎትም የሚታወክ ሲሆን አግልግሎት ሰጪ ተቁዋማት ማለትም ባንኮች፣ አየር መንገድ፣ ካፌና ሬስቶራንቶችን የመሳሰሉት ድርጅቶች ስራቸው እንደሚስተጉጎል ዘጋቢያችን ካሰባሰበው መረጃ ለመረዳት ተችሎአል፡፡
የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አቶ አለማየሁ ተገኑ በተደጋጋሚ የሚከሰተውን  የሃይል መቆራረጥ በዘላቂነት ለማስወገድ የሚያስችሉ የተለያዩ የመፍትሄ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑን ሰሞኑን ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል፡፡ ሚኒስትሩ አያይዘውም በሃይል ማስተላለፍ ስራ ላይ በተሰማሩ ባለሙያዎች ላይ
መንግስት የጀመረውን ጥብቅ ክትትል አጠናክሮ ይቀጥላል። ሚኒስትሩ አቶ አለማየሁ ተገኑ  እንዳሉት በአገሪቱ ምንም አይነት የሃይል እጥረት ሳይኖር በተደጋጋሚ የሚስተዋለውን የኤሌክትሪክ መቆራረጥ  እልባት ለመስጠት የአጭር ፣የመካከለኛና የረዥም ጊዜ እቅድ  በማውጣት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ተጀምሯል
ማለታቸው ይታወሳል። ሚኒስትሩ ይህን ይበሉ እንጂ መብራት ለምን እንደሚቆራረጥ እንኩዋን መ/ቤታቸው ካለማወቁም በተጨማሪ እየተወሰደ ነው የተባለው እርምጃም አስካሁን ምንም ኣይነት የመሻሻል መፍትሔ አለመምጣቱ በተለይ የአዲስአበባን ሕዝብ ተስፋ አስቆርጦአል፡፡
የከተማው ነዋሪ ህዝብ ተስፋ በመቁረጥ በመብራት ኃይል ሰራተኞች ላይ የሃይል ርምጀ አልፎ አልፎ ሲወስድ ይታያል።እንደ ዘጋቢያችን ሪፖርት ብዙዎቹ የመብራት ሃይል ሰራተኞች ለጥገና በሚሄዱበት ወቅት በተበሳጩ ወጣቶች ይደበደባሉ፣ የመብራት ሃይል መኪኖችም እየተሰበሩ ይመለሳሉ።

በግብር እዳ የሚማረሩ ነጋዴዎች ቁጥር እየጨመረ ነው

ጥቅምት (ሠላሳቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-‹በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት ከገቢያቸው ጋር በማይመጣጠን የግብር  እዳ እየተሰቃዩ  ነው።
የገዢው ፓርቲ ባለስልጣኖች አድሎአዊ በሆነ መልኩ በሚጥሉት ግብር ነጋዴዎች ድርጅታቸውን እየዘጉ ነው። በእነብሴ ሳር ምድር   ወረዳ አሰፋ ሁነኛው፣ ኢሳየ ቸኮል፣ የንጉስ ዋለና  መሰሉ የሚባሉት ነጋዲዎች በጋራ ለቤት መስሪያ በባንክ ከስያዙት  ገንዘብ ላይ ያለፍላጎተቻው በቀላጤ ብቻ ለግብር በሚል
ገንዘባቸው ተወስዷል።
በባህርዳር ከተማ ቀበሌ አስራ ሶስት የሚገኙ ነዋሪዎች በአከራይ ተከራይ የግብር ጥያቄ ቤት ባልሰሩበት አመታት ሁሉ ግብር እንዲከፍሉ  መጠየቃቸው እንዳበሳጫቸው ለዘጋቢያችን ገልጸዋል። በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ነጋዴዎች ለመንግስት አቤቱታ እያቀረቡ ቢሆንም፣ ከመስተዳድሩ በኩል ይህ ነው
የሚባል መልስ አላገኙም። በሌላ ዜና ደግሞ በአማራ ክልል የሚገኙ መስሪያ ቤቶች በጀት አጠቃቀምና አያያዝ ካለፈው ዓመት መሻሻል ያልታየበትና ለልዩ ኦዲት ሪፖርቶች ምላሽ የመስጠት ዝግጁነት ዝቅተኛና አዝጋሚ ሆኖ መታየቱን የክልሉ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት አስታውቋል፡፡
የአማራ ክልል ምክር ቤት 4ኛ ዙር፣5ኛዓመት የስራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤውን በባህርዳር ከተማ ባካሄደበት የመጀመሪያ ቀን ውሎው በቀረበው የኦዲት ሪፖርት 31 መንግስታዊ መስሪያ ቤቶች  በኦዲት ምርመራ ጊዜ በታየባቸው ጉድለት ዙሪያ ምላሽ እንዲሰጡ ቢጠየቁም በዓመቱ ውስጥ ምንም ምላሽ
አለመስጠታቸውን የኦዲት ቢሮው ሃላፊ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡ ዋና ኦዲተር ደሴ ጥላሁን ባቀረቡት በዚህ ሪፖርት በ2005/2006 የበጀት ዓመት ኦዲት ከሆኑት 152 መስሪያ ቤቶች ውስጥ የገንዘብ አያያዝና አስተዳደሩም ሆነ የውስጥ ቁጥጥር ሥርአቱን መርምሮ ተዓማኒነቱንና በቂ የሂሳብ አያያዝ
አስተዳደር መኖሩን ለማረጋገጥ ስለ ሂሳቡ ትክክለኛ መሆን አለመሆን ሙያዊ አስተያየት ለመስጠት አለመቻሉ ጉልህና መሰረታዊ ችግር መሆኑን ገልጸዋል፡፡በኦዲት ህጉ መሰረት በአግባቡ ያልሰሩ ስድስት መስሪያ ቤቶች መካከል የወልዲያና ቦሩ ሜዳ ሆስፒታሎች እንዲሁም የአንዳስ ዶሮ ብዜት ማዕከልም
በችግር ውስጥ መሆናቸው በኦዲቱ ሪፖርት እንደታየ ገልጸዋል፡፡ እንደ ዋና ኦዲተሩ አባባል -በተጠቀሰው የበጀት ዓመት ሂሳባቸው ኦዲት ከተደረጉት መካከል የጥሬ ገንዘብ ሂሳብ ከወጪ ቀሪ ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ያልተቻለባቸው 59 መስሪያ ቤቶች ችግር አለባቸው፡፡
ኦዲት ከተደረጉ  ሶስት መስሪያ ቤቶች ከ 84 ሽህ ብር በላይ በገንዘብ ያዦች የባከነና በመስሪያ ቤቶች የገንዘብ ካዝና ሰኔ 30 መገኘት ከነበረበት ገንዘብ በ 9 መስሪያ ቤቶች 6 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር  በጉድለት መገኘቱ ሌላው በምዝበራው ዙሪያ የተጠቀሰው የሪፖርቱ አካል እንደ ሆነ ገልጸዋል፡፡
ሌላው የማጭበርበር ድርጊት ተፈጸመበት ጉዳይና ዘዴዎቹ ሲሆኑ ከህዝብና መንግስት የተሰበሰበው ገንዘብ ለታለመለት አላማ ሳይውል በፎገራ ፣ደሴ ዙሪያና ጓንጓ ወረዳዎች በሶስት መስሪያ ቤቶች ከ86 ሽህ ብር በላይ ለብክነት እንደተዳረገ  ተናግረዋል፡፡
በበጀት አመቱ መሰብሰብ ከነበረበት ገንዘብ ውስጥ ሳይሰበሰብ የቀረ በውዝፍ የሚገኝ በ48 መስሪያ ቤቶች 26.1 ሚሊዮን ብር በገቢ አሰባሰብ ስርዓት መሰረት ገቢ አለመደረጉም ተገልጿል፡፡
ያለ አግባብ በተፈጸመ ክፍያ ዙሪያም የክልሉ 106 መስሪያ ቤቶች  ወይም ኦዲት ከተደረጉት 70 በመቶ ያህሉ ክፍያዎችን በፋይናንስ ደንብና መመሪያ መሰረት ባለመፈጸም ከ 8.6 ሚሊዮን ብር በላይ መባከኑን በሪፖርታቸው ጠቁመዋል፡፡
በክልሉ በሚሰሩ ልዩልዩ የግንባታ ስራዎች የሚሰራውን ብክነትም ሲናገሩ በ27 መሰሪያ ቤቶች ከ19 ሚሊዮን ብር በላይ ከተያዘው የግንባታ ውል ጋር ባልተጣጣመ ሁኔታ ክፍያ በመፈጸም የህዝብ ንብረት ለብክነት ተዳርጓል፡፡
በክልሉ አዲት በተደረጉት መስሪያ ቤቶች አስራ ሁለቱ ላወጡት ወጪ ክፍያ የፈጸሙባቸውን ማስረጃ ተጠይቀው ባለማቅረባቸው 13.8 ሚሊዮን ብር በጉድለት ተገኝቶባቸዋል፡፡
በግዢ ስርአት ዙሪያም መመሪያውን የልተከተለ ግዢ የፈጸሙ 118 መስሪያ ቤቶች ከ107.3 ሚሊዮን ብር በላይ ለብክነት መዳረጋቸውን ገልጸው፤ካለፈው አመት ሪፖርት በመነሳት የግዢ መመሪያውን በመፈጸም ላይ አሁንም መሻሻል እንደሌለ ተናግረዋል፡፡
በአጠቃላይ በክልሉ ባሉ መስሪያ ቤቶች ከፍተኛ የሆነ ለምዝበራ የሚጋልጡ የአሰራር ግድፈቶች መኖራቸውን ለምክር ቤቱ አቅርበው፤ ገቢ ተሰብሰቦባቸው ለኦዲት ያልቀረቡ ከ2.8 ሚሊዮን ብር በላይ የያዙ ደረሰኞች በየወረዳዎቹ በተለያዩ ሃላፊነት የሚገኙ ተሿሚዎች የተመዘበሩ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ለሰራተኛ ከሚከፈል ደመወዝ በላይ በጀት እንዲጸድቅ በማድረግ ልዩነቱን ለግል ጠቅም ማዋል ፣በአንድ አመት የ567 ቀናት ውሎ አበል መወሰድ ፣ከዕቃ አቅራቢዎች ጋር በመመሳጠር የማጭበርበር እና ኢፍትሃዊ ውድድር እንዲኖር ማድረግ ፣ የግንባታ ጥራት ላልጠበቁ ስራዎች ክፍያ ከፍለው መገኘት ፣ መስክ
የወጡ በማስመሰል የመኪና ነዳጅ ቅባትና ጥገና ገንዘብ በማውጣት ለግል ጥቅማቸው ማዋል በሹማምንቱ ከተሰሩት ወንጀሎች ጥቂቶቹ መሆናቸውን  በሪፖርታቸው ማጠቃለያ አቅርበዋል፡፡
በአንድ በኩል መንግስት ህዝቡን እያጨናነቀ ግብር እንዲከፍል ሲያደርግ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ከድሃው የሚሰበሰበውን ገቢ ባለስልጣናቱ በየጊዜው መዝረፋቸው ነጋዴዎችን እያበሳጨ መሆኑን የክልሉ ዘጋቢያችን ገልጻለች።

የደቡብ ሱዳን መንግስት ለኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ የተላከውን መሳሪያ አገደ

ጥቅምት (ሠላሳቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-ለደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ታማኝ የሆኑ የደህንነቶች ሰራተኞች ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የጦር መሳሪያ እና ሌሎች እቃዎችን ጭነው ሲጓዙ የነበሩ 4 መኪኖችን አስቁመዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴቨን ዱጃሪክ እንደገለጹት የደህንነት ሰራተኞች መሳሪያዎቹ ለአንድ ተቃዋሚ ሃይል ሊሰጥ ነው በሚል እንደያዙትና በሹፌሮቹ ላይ ጉዳት እንዳደረሱባቸው ገልጸዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይ መኪኖቹ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጥሪ አቅርበዋል።

ኢህአዴግ በሚያካሂደው የፖለቲካ ስልጠና ላይ ህዝቡ ቅሬታዎችን እያሰማ ነው

ጥቅምት  (ሃያ ሰባቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-በየስብሰባዎቹ የተሳተፉ ምንጮች ለዘጋቢያችን እንደተናገሩት በየመድረኩ የጋዜጠኞች መታሰር፣ የሃይማኖት እኩልነትና ነጻነት አለመከበር፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መባባስ፣የሙስናና ብልሹ አሠራር መንሰራፋት፣ የህወሃት የበላይነት መኖር፣ የድህነት መንሰራፋትና የዋጋ ግሽበት አለመቀረፍ፣ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ ወከባና እስር መጠናከር በተደጋሚሚ የሚነሱና ኢህአዴግ በቂ ምላሽ ሊሰጥባቸው ያልቻለባቸው አበይት ጉዳዮች መሆናቸው ታውቆአል፡፡
ጥያቄዎቹ በተለይ በግንባሩ አባላትና በካድሬዎች ጭምር የሚነሱ መሆናቸው ግንባሩን ከፍተኛ ስጋት ላይ እንደጣለው የጠቀሱት ምንጮቻችን የበላይ አመራሩ በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን የወሰደው አቋም የለም፡፡
በተለይ ሰሞኑን በዋቢሸበሌ ሆቴል እና በፌዴራል ፖሊስ እየተካሄደ ባለው የመንግስት መገናኛ ብዙሃንና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ስብሰባ ላይ የመንግስት ጋዜጠኞች እያነሱት ያሉት ጥያቄዎች ትምህርት ለመስጠት ከተመደቡ የኢህአዴግ ሰዎች አቅም በላይ መሆኑ ትዝብት ላይ ከመጣሉም በላይ ጠንካራ ጥያቄዎቹ እንዳስደነገጣቸው ታውቋል፡፡
በተለይ የፕሬስ ነጻነትና የጋዜጠኞች የጅምላ  እስርና ስደት ጉዳይ የተነሱ ጥያቄዎች ተድበስብሰው መታለፋቸው በርካታ ጋዜጠኞችን አሳዝኖአል፡፡ አንዳንዶቹም መግባባትና መተማመን ለማይገኝበት ስብሰባ ለምን የህዝብ ሐብትና ገንዘብ እንደሚባክን በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጸሙና የሚፈጸሙ ወንጀሎችን መረጃ የሚይዝ መረጃ ፍትህ ማእከል የተባለ ድረገጽ ይፋ ሆነ

ጥቅምት  (ሃያ ሰባቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-የድረገጹ አዘጋጆች ለኢሳት በላኩት መግለጫ እንደጠቀሱት ድረገጹ በኢትዮጵያ ውስጥ ወንጀሎችን ያቀዱ፣ ለወንጀሎቹ ውሳኔ የሰጡ፣ ወሳኔዎችን ያስፈጸሙ፣ የመሩና ያቀነባበሩትን በሰሜን አሜሪካ፣ በአውሮፓ እንዲሁም በየትኛውም የምእራብ ሀገሮች እንደ የሀገሮቹ
የህግ አግባብ መሰረት ክስ ለመመሥረት የሚያስችሉ ልዩ ልዩ መረጃዎችንና ምስክሮችን ማሰባሰብ እና ማጠናቀር አላማ አድርጓል።
ወንጀል በፈጸሙት ላይ በቂ መረጃዎች ከተሰበሰቡ በኋላ ህግ ፊት የማቅረብ በተለይም ወንጀል ፈጻሚዎቹ በምዕራብ አገሮች መሸሸጊያ እንዲሁም የመኖሪያ ፈቃድ እንዳያገኙ እና ያሸሹት ገንዘብም ሆነ የገዙትን ንብረት ለማሳገድ እንቅስቃሴ እንደላቸው አዘጋጆች በመግለጫቸው ጠቅሰዋል።
ድረገጹ የሚያሰባስባቸውና መዝግቦ የሚይዛቸው የወንጀል አይነቶች  የሰብዓዊ መብት ረገጣ ፣የዘር ማጥፋት ወንጀል፣ የጦር ወንጀል፣ የጅምላ ግድያዎች፤ አስገድዶ መድፈር፣ አሰቃቂ ድብደባና ሰቆቃ መሆናቸው በመግለጫው ተመልክቷል።
ህዝቡ የሕወሓትና የኢሕአዴግ የሲቪል ከፍተኛ ባለሥልጣኖችና ውሳኔ ሰጭዎች፣ የሕወሓት/ኢሕአዴግ የደህንነት፣ ወታደራዊና የፌዴራል ፓሊስ ከፍተኛ ኃላፊዎች፣አዛዦችና ውሳኔ ሰጭዎች፣ በየእርከኑ የሚገኙ የሕወሓት/ኢሕአዴግ የመከላከያ አዛዦች፣የደህንነት የፌዲራል ፓሊስ ውሳኔ አስፈጽሚዎች፣ ውሳኔ
ፈጻሚዎች፣ ሰቆቃ ፈጻሚና ገራፊ መርማሪዎች፣ በዜጎች ላይ በግፍ የፈረዱ፣ከወንጀለኞች የተባበሩና በየእርከኑ የሚገኙ የፌደራልና የከፍተኛ ፍርድቤት ዳኞችና አቃብያነ ህግ እንዲሁም በየክልሉ በየደረጃው የሚገኙ የፌደራልና የክልል ፖሊስ አዛዦች፣ የልዩ ሃይል አዛዦች፣የፖሊስ መሪማሪዎች፣ በየክልሉ የሚገኙ
የደህንነት ሃላፊዎች፣ ቁልፍ የደህንነት አባላት፣የየክልሉ ሚሊሽያ አዛዦችና በተዋረድ የሚገኙ ሹሞች፣  በየእርከኑ የሚገኙና በግፍ በዜጎች ላይ ፍርድ በመስጠት ንጹሃን ዜጎችን ያጠቁና ያስጠቁ ዳኞችና አቃብያነ ህግ፣ በተለያዩ የሃገሪቱ የአስተዳደር ክልሎች ከየማዘጋጃ ቤቱ ህጋዊ የቤት ባለቤትነት ይዞታና የካርታ
ማስረጃዎችን አሰርቀው በማውጣት የተጭበረበረ ሰነዶችን እያቀረቡ የህዝብን ንብረት የወሰዱና ለዚህም ተግባራቸው የተባበሯቸውን ግለስቦች ማንነት መዝግቦ መያዝና ማገለጥ እንደሚኖርበት በመግለጫው ላይ ሰፍሯል።
በተለያዩ የመንግስት መስሪያቤቶች ከህጋዊ ጨረታ ውጪ በአገር ውስጥና በውጪ አገር ከሚገኙ ኩባንያዎች ጋር በመመሳጠር በኰሚሽንና በሃሰት በተዘጋጀ የሰነድ ማስረጃ በርካታ ገንዘብ የዘረፉ ግለሰቦች ማንነትና ዝርዝር የወንጀል ድርጊቶች፣ ከአገር ወደ ውጪ፣ከውጪ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ሸቀጦች ከቀረጥ ነፃ
ሆነው እንዲገቡና እንዲወጡ በማድረግ በአየር ለአየር ንግድ የከበሩና ህጋዊ የንግድ ድርጅቶችን በማዘጋት የግል ሃብትና ንብረት እየዘረፉ የሚገኙ ሰዎችን ማንነትና አድራጐት በዝርዝር መያዝ አስፈላጊ መሆኑንም ጠቅሷል።
በኢትዮጵያ ውስጥ ቤተሰብ ዘመድ በአገዛዙ የተገደሉባችው፣ አሰቃቂ ድብደባ ፣ሰቆቃ የተፈጸመባችው፤በየጊዜው ስለ ተፈፀሙ ልዩ ልዩ መንግስታዊ ወንጀሎች፣ ግፍ፣ ግድያ፣ ሰቆቃ፣አድራጊዎችና ፈጻሚዎች ማንነት የሚያውቁ፣ ቤተሰብ፣ ዘመድ አዝማድ፣ ጓደኛ የደረሱበትን የማያውቁ፣ ወንጀሎች የት፣ በማን፣ መቼ
እንደተፈጸሙ የሚያውቁ፣ እማኝ የሆኑ፣ ወንጀሎችን በሚመለክት ያዩ፣የሰሙ ግለሰቦችን የሚያውቁ፤ ስለወንጀሎቹ ዝርዝርና ሰለ አድራጊዎቹ ማንነት የሚያውቁ መረጃዎችን ለማዕከሉ በመስጠት እንዲተባበሩ ጥሪ ቀርቧል።
የመረጃ ፍትህ ማእከል በሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና በህግ ባለሙያዎች የተቋቋመ ሲሆን እስካሁን የ73 ተፈላጊ የሲቪል፣ ወታደራዊና የደህነት ሰዎችን ስም ዝርዝር አዘጋጅቷል። ተጨማሪ ተፈላጊዎችን ስም ለማዘጋጀት ከህብረተሰቡ ጋር በመተባባር እንደሚሰራም ገልጿል። መረጃ ለመስጠት የሚፈልጉ
editor@masreja.com ወይም በስልክ ቁጥር 1 ( 800) 3851804 መጠቀም ይችላሉ።

ከአባይ ግድብ ስራ ጋር በተያያዘ በተወሰኑ የህወሃት ደጋፊዎች ከፍተኛ የደን ጭፍጨፋ እና ምዝበራ እየተካሄደ ነው

ጥቅምት  (ሃያ ስድስትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-የአባይ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት እቅድ እንደሚያሳየው ግድቡ ሲጠናቀቅ 1600 ኪሎሜትር ስኩየር  መሬት የሚሸፍን ውሃ የሚተኛበት ሲሆን፣ የዚህ መሬት አካል 90 በመቶው በደን የተሸፈነነ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ አንጻራዊ በሆነ መልኩ የተሻለ የደን
ሽፋን አለው የሚባለው ግድቡ የሚሰራበት የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቢሆንም፣ ከ200 ኪሎ ሜትር ያላነሰ ስፋት ያለው የክልሉ ደን በፍጥነት እየተጨፈጨፈ ነው።
እጅግ የሚያሳዝነው ይላሉ አካባቢውን ለመግብኘት የሄዱ ታዛቢዎች፣ ደኖችን እየመነጠሩ የሚሸጡት ከአንድ አካባቢ የተሰባሰቡ የህዝባዊ ወያን ሃርነት ትግራይ ደጋፊ ባለሀብቶች ናቸው። ደኑን መንጥሮ የመሸጥ ሃላፊነት የተሰጣቸው እነዚህ ታማኝ የህወሃት ነጋዴ አባላት፣ ከቤንሻንጉልና ከተለያዩ አካባቢዎች የሰበሰቡዋቸውን
የጉልበት ሰራተኞች አነስተኛ በሆነ ክፍያ እያሰሩ ለራሳቸው መሰብሰባቸው ነው። አሰሪዎቹ ታክስ አይከፍሉም፣ እጅግ አነስተኛ ክፍያ ከሚከፈላቸው ሰራተኞች ላይ ለአባይ ግድብ ማሰሪያ እያሉ የሚሰበስቡትን ገንዘብም ወደ ኪሳቸው ያደርጉታል ሲሉ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ሰዎች ይናገራሉ።
ነጋዴዎቹ ከሰል በማክሰል ወደ ሱዳንና አዲስ አበባ እያመጡ ከመሸጥ በተጨማሪ፣ በትላልቅ መኪኖች እንጨቶችን ወደ ከተሞች በመላክ እየሸጡ በወር ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እየዘረፉ ነው።
አካባቢውን በቅርብ ጎብኝቶ የመጣ ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቀ ሰው ሲናገር ደግሞ ፣ አሰሪዎቹ እንጨት ጭነው ወደ መሃል አገር በሚሄዱበት ወቅት ዛፎችን የሚቆርጡ ሰራተኞች በየጫካው እየተረሱ ችግር እየደረሰባቸው ነው።
ታዛቢዎች እንደሚሉት ከደን ምንጠራው በተጨማሪ በግድቡ ዙሪያ ከባድ እቃዎችን ከማቅረብ ጀምሮ ሻሂ እስከመሸጥ ያሉ ስራዎችን የህወሃት ታማኞች መቆጣጠራቸው እንዳስገረማቸው ገልጸዋል።

የደህንነት ሃይሎች ዜጎችን እያፈኑ መውሰዱን ቀጥለውበታል

ጥቅምት (ሠላሳቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-ለደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ታማኝ የሆኑ የደህንነቶች ሰራተኞች ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የጦር መሳሪያ እና ሌሎች እቃዎችን ጭነው ሲጓዙ የነበሩ 4 መኪኖችን አስቁመዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴቨን ዱጃሪክ እንደገለጹት የደህንነት ሰራተኞች መሳሪያዎቹ ለአንድ ተቃዋሚ ሃይል ሊሰጥ ነው በሚል እንደያዙትና በሹፌሮቹ ላይ ጉዳት እንዳደረሱባቸው ገልጸዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይ መኪኖቹ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጥሪ አቅርበዋል።

ኢህአዴግ በሚያካሂደው የፖለቲካ ስልጠና ላይ ህዝቡ ቅሬታዎችን እያሰማ ነው

ጥቅምት  (ሃያ ሰባቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-በየስብሰባዎቹ የተሳተፉ ምንጮች ለዘጋቢያችን እንደተናገሩት በየመድረኩ የጋዜጠኞች መታሰር፣ የሃይማኖት እኩልነትና ነጻነት አለመከበር፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መባባስ፣የሙስናና ብልሹ አሠራር መንሰራፋት፣ የህወሃት የበላይነት መኖር፣ የድህነት መንሰራፋትና የዋጋ ግሽበት አለመቀረፍ፣ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ ወከባና እስር መጠናከር በተደጋሚሚ የሚነሱና ኢህአዴግ በቂ ምላሽ ሊሰጥባቸው ያልቻለባቸው አበይት ጉዳዮች መሆናቸው ታውቆአል፡፡
ጥያቄዎቹ በተለይ በግንባሩ አባላትና በካድሬዎች ጭምር የሚነሱ መሆናቸው ግንባሩን ከፍተኛ ስጋት ላይ እንደጣለው የጠቀሱት ምንጮቻችን የበላይ አመራሩ በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን የወሰደው አቋም የለም፡፡
በተለይ ሰሞኑን በዋቢሸበሌ ሆቴል እና በፌዴራል ፖሊስ እየተካሄደ ባለው የመንግስት መገናኛ ብዙሃንና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ስብሰባ ላይ የመንግስት ጋዜጠኞች እያነሱት ያሉት ጥያቄዎች ትምህርት ለመስጠት ከተመደቡ የኢህአዴግ ሰዎች አቅም በላይ መሆኑ ትዝብት ላይ ከመጣሉም በላይ ጠንካራ ጥያቄዎቹ እንዳስደነገጣቸው ታውቋል፡፡
በተለይ የፕሬስ ነጻነትና የጋዜጠኞች የጅምላ  እስርና ስደት ጉዳይ የተነሱ ጥያቄዎች ተድበስብሰው መታለፋቸው በርካታ ጋዜጠኞችን አሳዝኖአል፡፡ አንዳንዶቹም መግባባትና መተማመን ለማይገኝበት ስብሰባ ለምን የህዝብ ሐብትና ገንዘብ እንደሚባክን በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጸሙና የሚፈጸሙ ወንጀሎችን መረጃ የሚይዝ መረጃ ፍትህ ማእከል የተባለ ድረገጽ ይፋ ሆነ

ጥቅምት  (ሃያ ሰባቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-የድረገጹ አዘጋጆች ለኢሳት በላኩት መግለጫ እንደጠቀሱት ድረገጹ በኢትዮጵያ ውስጥ ወንጀሎችን ያቀዱ፣ ለወንጀሎቹ ውሳኔ የሰጡ፣ ወሳኔዎችን ያስፈጸሙ፣ የመሩና ያቀነባበሩትን በሰሜን አሜሪካ፣ በአውሮፓ እንዲሁም በየትኛውም የምእራብ ሀገሮች እንደ የሀገሮቹ
የህግ አግባብ መሰረት ክስ ለመመሥረት የሚያስችሉ ልዩ ልዩ መረጃዎችንና ምስክሮችን ማሰባሰብ እና ማጠናቀር አላማ አድርጓል።
ወንጀል በፈጸሙት ላይ በቂ መረጃዎች ከተሰበሰቡ በኋላ ህግ ፊት የማቅረብ በተለይም ወንጀል ፈጻሚዎቹ በምዕራብ አገሮች መሸሸጊያ እንዲሁም የመኖሪያ ፈቃድ እንዳያገኙ እና ያሸሹት ገንዘብም ሆነ የገዙትን ንብረት ለማሳገድ እንቅስቃሴ እንደላቸው አዘጋጆች በመግለጫቸው ጠቅሰዋል።
ድረገጹ የሚያሰባስባቸውና መዝግቦ የሚይዛቸው የወንጀል አይነቶች  የሰብዓዊ መብት ረገጣ ፣የዘር ማጥፋት ወንጀል፣ የጦር ወንጀል፣ የጅምላ ግድያዎች፤ አስገድዶ መድፈር፣ አሰቃቂ ድብደባና ሰቆቃ መሆናቸው በመግለጫው ተመልክቷል።
ህዝቡ የሕወሓትና የኢሕአዴግ የሲቪል ከፍተኛ ባለሥልጣኖችና ውሳኔ ሰጭዎች፣ የሕወሓት/ኢሕአዴግ የደህንነት፣ ወታደራዊና የፌዴራል ፓሊስ ከፍተኛ ኃላፊዎች፣አዛዦችና ውሳኔ ሰጭዎች፣ በየእርከኑ የሚገኙ የሕወሓት/ኢሕአዴግ የመከላከያ አዛዦች፣የደህንነት የፌዲራል ፓሊስ ውሳኔ አስፈጽሚዎች፣ ውሳኔ
ፈጻሚዎች፣ ሰቆቃ ፈጻሚና ገራፊ መርማሪዎች፣ በዜጎች ላይ በግፍ የፈረዱ፣ከወንጀለኞች የተባበሩና በየእርከኑ የሚገኙ የፌደራልና የከፍተኛ ፍርድቤት ዳኞችና አቃብያነ ህግ እንዲሁም በየክልሉ በየደረጃው የሚገኙ የፌደራልና የክልል ፖሊስ አዛዦች፣ የልዩ ሃይል አዛዦች፣የፖሊስ መሪማሪዎች፣ በየክልሉ የሚገኙ
የደህንነት ሃላፊዎች፣ ቁልፍ የደህንነት አባላት፣የየክልሉ ሚሊሽያ አዛዦችና በተዋረድ የሚገኙ ሹሞች፣  በየእርከኑ የሚገኙና በግፍ በዜጎች ላይ ፍርድ በመስጠት ንጹሃን ዜጎችን ያጠቁና ያስጠቁ ዳኞችና አቃብያነ ህግ፣ በተለያዩ የሃገሪቱ የአስተዳደር ክልሎች ከየማዘጋጃ ቤቱ ህጋዊ የቤት ባለቤትነት ይዞታና የካርታ
ማስረጃዎችን አሰርቀው በማውጣት የተጭበረበረ ሰነዶችን እያቀረቡ የህዝብን ንብረት የወሰዱና ለዚህም ተግባራቸው የተባበሯቸውን ግለስቦች ማንነት መዝግቦ መያዝና ማገለጥ እንደሚኖርበት በመግለጫው ላይ ሰፍሯል።
በተለያዩ የመንግስት መስሪያቤቶች ከህጋዊ ጨረታ ውጪ በአገር ውስጥና በውጪ አገር ከሚገኙ ኩባንያዎች ጋር በመመሳጠር በኰሚሽንና በሃሰት በተዘጋጀ የሰነድ ማስረጃ በርካታ ገንዘብ የዘረፉ ግለሰቦች ማንነትና ዝርዝር የወንጀል ድርጊቶች፣ ከአገር ወደ ውጪ፣ከውጪ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ሸቀጦች ከቀረጥ ነፃ
ሆነው እንዲገቡና እንዲወጡ በማድረግ በአየር ለአየር ንግድ የከበሩና ህጋዊ የንግድ ድርጅቶችን በማዘጋት የግል ሃብትና ንብረት እየዘረፉ የሚገኙ ሰዎችን ማንነትና አድራጐት በዝርዝር መያዝ አስፈላጊ መሆኑንም ጠቅሷል።
በኢትዮጵያ ውስጥ ቤተሰብ ዘመድ በአገዛዙ የተገደሉባችው፣ አሰቃቂ ድብደባ ፣ሰቆቃ የተፈጸመባችው፤በየጊዜው ስለ ተፈፀሙ ልዩ ልዩ መንግስታዊ ወንጀሎች፣ ግፍ፣ ግድያ፣ ሰቆቃ፣አድራጊዎችና ፈጻሚዎች ማንነት የሚያውቁ፣ ቤተሰብ፣ ዘመድ አዝማድ፣ ጓደኛ የደረሱበትን የማያውቁ፣ ወንጀሎች የት፣ በማን፣ መቼ
እንደተፈጸሙ የሚያውቁ፣ እማኝ የሆኑ፣ ወንጀሎችን በሚመለክት ያዩ፣የሰሙ ግለሰቦችን የሚያውቁ፤ ስለወንጀሎቹ ዝርዝርና ሰለ አድራጊዎቹ ማንነት የሚያውቁ መረጃዎችን ለማዕከሉ በመስጠት እንዲተባበሩ ጥሪ ቀርቧል።
የመረጃ ፍትህ ማእከል በሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና በህግ ባለሙያዎች የተቋቋመ ሲሆን እስካሁን የ73 ተፈላጊ የሲቪል፣ ወታደራዊና የደህነት ሰዎችን ስም ዝርዝር አዘጋጅቷል። ተጨማሪ ተፈላጊዎችን ስም ለማዘጋጀት ከህብረተሰቡ ጋር በመተባባር እንደሚሰራም ገልጿል። መረጃ ለመስጠት የሚፈልጉ
editor@masreja.com ወይም በስልክ ቁጥር 1 ( 800) 3851804 መጠቀም ይችላሉ።

ከአባይ ግድብ ስራ ጋር በተያያዘ በተወሰኑ የህወሃት ደጋፊዎች ከፍተኛ የደን ጭፍጨፋ እና ምዝበራ እየተካሄደ ነው

ጥቅምት  (ሃያ ስድስትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-የአባይ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት እቅድ እንደሚያሳየው ግድቡ ሲጠናቀቅ 1600 ኪሎሜትር ስኩየር  መሬት የሚሸፍን ውሃ የሚተኛበት ሲሆን፣ የዚህ መሬት አካል 90 በመቶው በደን የተሸፈነነ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ አንጻራዊ በሆነ መልኩ የተሻለ የደን
ሽፋን አለው የሚባለው ግድቡ የሚሰራበት የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቢሆንም፣ ከ200 ኪሎ ሜትር ያላነሰ ስፋት ያለው የክልሉ ደን በፍጥነት እየተጨፈጨፈ ነው።
እጅግ የሚያሳዝነው ይላሉ አካባቢውን ለመግብኘት የሄዱ ታዛቢዎች፣ ደኖችን እየመነጠሩ የሚሸጡት ከአንድ አካባቢ የተሰባሰቡ የህዝባዊ ወያን ሃርነት ትግራይ ደጋፊ ባለሀብቶች ናቸው። ደኑን መንጥሮ የመሸጥ ሃላፊነት የተሰጣቸው እነዚህ ታማኝ የህወሃት ነጋዴ አባላት፣ ከቤንሻንጉልና ከተለያዩ አካባቢዎች የሰበሰቡዋቸውን
የጉልበት ሰራተኞች አነስተኛ በሆነ ክፍያ እያሰሩ ለራሳቸው መሰብሰባቸው ነው። አሰሪዎቹ ታክስ አይከፍሉም፣ እጅግ አነስተኛ ክፍያ ከሚከፈላቸው ሰራተኞች ላይ ለአባይ ግድብ ማሰሪያ እያሉ የሚሰበስቡትን ገንዘብም ወደ ኪሳቸው ያደርጉታል ሲሉ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ሰዎች ይናገራሉ።
ነጋዴዎቹ ከሰል በማክሰል ወደ ሱዳንና አዲስ አበባ እያመጡ ከመሸጥ በተጨማሪ፣ በትላልቅ መኪኖች እንጨቶችን ወደ ከተሞች በመላክ እየሸጡ በወር ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እየዘረፉ ነው።
አካባቢውን በቅርብ ጎብኝቶ የመጣ ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቀ ሰው ሲናገር ደግሞ ፣ አሰሪዎቹ እንጨት ጭነው ወደ መሃል አገር በሚሄዱበት ወቅት ዛፎችን የሚቆርጡ ሰራተኞች በየጫካው እየተረሱ ችግር እየደረሰባቸው ነው።
ታዛቢዎች እንደሚሉት ከደን ምንጠራው በተጨማሪ በግድቡ ዙሪያ ከባድ እቃዎችን ከማቅረብ ጀምሮ ሻሂ እስከመሸጥ ያሉ ስራዎችን የህወሃት ታማኞች መቆጣጠራቸው እንዳስገረማቸው ገልጸዋል።

የደህንነት ሃይሎች ዜጎችን እያፈኑ መውሰዱን ቀጥለውበታል

ጥቅምት  (ሃያ ስድስትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን ተጠናክሮ የቀጠለው የገዢው ፓርቲ አፈና መንግስት ራሱ ያስታጠቃቸውን ታጣቂዎች ትጥቅ እስከማስፈታት መድረሱን ምንጮች ገለጹ
በትግራይና በአማራ ክልሎች ባለፉት ሶስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው አፈና ቀጥሎ ጥቅምት 26 ቀን 2007 ኣም የሰላም ታጋይ እየጠባለ የሚታወቅ ወጣት ሽሻይ አዘናው በመቀሌ ከተማ በትግራይ ክልል የፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ገ/ህይወት ካህሳይ እና በደህንነት ሃይሎች ከሚሰራበት የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት የትግራይ
ክልል ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ታስሮ እና ቤቱ ተበርብሮ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስዷል። ሽሻይ አዘናዉ የዓረና ትግራይ መስራችና ማእከላዊ ኮሚቴ አባል የነበረ በቅርቡ ደግሞ ከዓረና  ወደ አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ የተቀላቀለ ወጣት ነው።
በተመሳሳይ ዜና ደግሞ ቋራ በደላ ቀበሌ አካባቢ መሳሪያ የታጠቁ አርሶአደሮች መሳሪያቸውን እየተነጠቁ ነው። ትክል ድንጋይ አካባቢም እንዲሁ በርካታ ታጣቂዎች መሳሪያቸውን እንዲያስረክቡ መደረጋቸውን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል።
ባለፉት ሶስት ቀናት በትግራይ ክልል በምዕራባዊያን ዞን ቃፍታ ሁመራ ወረዳ ዳንሻ ከተማ የአረና ፓርቲ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ዘነበ ሲሳይ ጥቅምት 25፣ 2007 ዓም ከቤታቸው ተወስደው ሲታሰሩ፣ እንዲሁም በተመሳሳይ ቀን በሁመራ አረና የቁጥጥር ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ አማረ ተወልደ  ታስረዋል። ከወራት
በፊት የታሰሩትን አብራሃ ደስታንና አያሌው በየነን  ጨምሮ 7 የፓርቲው አመራሮች በእስር ላይ ናቸው። በተመሳሳይ ቀን በአማራ ክልል ምዕ/ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ  የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ ጥላሁን አበበ እና ሶስት የድርጅቱ አባላት ተይዘው ወዳልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል።    ባለፉት ሶስት ቀናት ብቻ ከ10
ያላነሱ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል። የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የሆኑት አንዱአለም አራጌ፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ ናትናኤል መኮንንና ሃብታሙ አያሌው አሁንም በእስር ላይ ናቸው።
የሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል እና የሰሜን ጎንደር የዞን ሰብሰቢ አቶ አግባው ሰጠኝም እንዲሁ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ወዳልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል። ሶስት የሰማያዊ ፓርቲ  የአርባምንጭ አመራሮች አሁንም ድረስ በእስር ላይ ናቸው።
በምእራብ ጎጃም  በፍኖተሰላም ከተማ የመኢአድ የወረዳው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ) ሰብሳቢ የሆነው  ዘሪሁን ብሬ ረቡዕ ጥቅምት 26፣ 2007 ዓም ተይዞ ወዳልታወቀ ስፍራ ተወስዷል።

የኢህአዴግ መንግስት ከአረብ ሃገራት ጋር በአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት ላይ ሊያደርገው ያሰበው ስምምነት በአረብ ሃገራት መሪዎች ተቀባይነት ማጣቱ ታወቀ

ጥቅምት  (ሃያ ስድስትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ በኢትዮጵያ እና በአረብ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት እንዲሁም መንግስት ወደ አረብ አገራት በሚላኩ ዜጎች ጉዳይ ሊፈጽመው ያሰበው ስምምነት ምን ደረጃ ላይ  እንደደረሰ ግምገማ ተካሂዶ ነበር።
መንግስት ተጓዝ ሰራተኞችን በሚመለከተ ያወጣው ህግ በአረብ መንግስታት እውቅና የተነፈገው ሲሆን፣ የአረብ አገራት ባለስልጣናት ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች የሙያ ክህሎት የላቸውም፣ በአገሪቱ ማሰልጠኛ ተቋማት በደንብ አይሰለጥኑም የሚል ምክንያት በማቅረብ ስምምነቱን ለመፈረም ፍላጎት አለማሳየታቸው በውይይቱ ላይ ተነስቷል።
ከኤርትራ ፤ፊልፒንስ ፤ ሱዳን እና  ግብፅ የሚመጡ ሰራተኞች ከኢትዮጵያውያን በተሻለ በአረቦች እንደሚመረጡ በውይይቱ ላይ ተነስቷል።
የውጭ ጉዳይ ሚ/ሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የኳታር እና የሳውዲአረቢያ ተቃውሞ መነሻው በሙስሊም አመፀኞች ላይ ከምንወሰደው እርምጃ እና ከአባይ ግድብ ግንባታ ጋር በተያያዘ የግብፅን ወዳጀነት ላለማስከፋት ካላቸው ፍላጎት አንጻር ነው ብለዋል።
የጠ/ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው የዶ/ር ቴዎድሮስን አቋም ውድቅ በማድረግ የአረብ አገራት የወሰዱት እርምጃ ከግብፅ ጋር የሚያያይዘው ነገር የለም ብለዋል። ግብፅ ራሱን ያልቻለ ደካማ መንግስት ነው ያሉት አቶ ጌታቸው፣ መንስኤው የኛ የራሳችን የዲፕሎማሲ ጥራት ችግር ነው ሲሉ አክለዋል፡፡ በሁለቱ ባለስልጣኖች መካከል የተሰጠው ምክንያት መለያየቱን ተከትሎ የውጭ ጉዳይ  መስሪያ ቤቱ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴው ከመለስ ሞት በኃላ ተዳክሟል ወይስ ተጠናክሯል በሚል ጥናት እንዲያቀርብ ስምምነት ላይ ተደርሶ ተበትኗል።

በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ውሃ መጥፋቱን ተማሪዎች ተናገሩ

ጥቅምት  (ሃያ ስድስትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-በዩኒቨርስቲው ውስጥ በሚታየው ተደጋጋሚ የሃይል መቆራረጥና የውሃ እጥረት ተማሪዎች ትምህርታቸውን በአግባቡ ለመከታተል አልቻሉም።
ከውሃ እጥረት ጋር በተያያዘ ከጽዳት ጋር ለተያያዙ በሽታዎች ሊደራጉ እንደሚችሉ ተማሪዎች ፍርሃታቸውን ገልጸዋል።

Wednesday, November 5, 2014

ለሁለት ወራት ደሞዝ ያልተከፈላቸው የኢትዮ-ድሪም ሰራተኞች የአንድ ወር ደመወዝ ተከፈላቸው

ጥቅምት ፳፫(ሃያ ሦስትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-በሆለታ ገነት የሚገኘው የሼከ አላሙዲ ንብረት የሆነው “ኢትዮ ድሪም” የአበባ እና የእንጆሪ ሰራተኞች ጥቅምት 21 እና  22 ከፍያ ተፈጽሞላቸዋል። ሰራተኞች ደሞዝ እንዳልተከፈላቸው ለኢሳት ባስተዋቁ በቀናት ውስጥ እንደተከፈላቸው ቢገልጹም፣ አሁንም ከሰራተኞች ማመላለሻ መኪናና ከጤና ጋር የተያያዙ ችግሮችን እያነሱ ነው።  ድርጀቱ ለሰራተኛ ማመላለሻ  /ሰርቪስ/ እና ለምርት ማጓጓዣ የተከራያቸው መኪኖች የአገልግሎት ክፍያ ሳያገኙ ከ7 ወራት በላይ ያለፋቸው ሲሆን፣ ካለፈው ወር ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ በማድረጋቸው ሰራተኛው ከሚከፈለው አነስተኛ ገንዘብ እየቆጠበ ለትራንስፖርት በቀን እስከ አስር  ብር ለማውጣት ተገዷል። ሰራተኞች እንደሚሉት አብዛኛው ሰራተኛ 600 ብር ወርሃዊ ክፍያ የሚያገኝ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 150 ብር ለቤት ኪራይ፣ 260 ብር ለትራንስፖርት ከፍሎ በወር ከ200 በታች በሆነ ብር ቤተሰቡን ያስተዳድራል።
በአበባ እርሻ ውስጥ የተከሰተው የአበባ በሽታ ለጤናቸው አስጊ መሆኑን የሚናጉት ሰራተኞችን በተለይም “ማይቲ” የተባለው በሽታ ሰውነትን የሚያሳክክ ከመሆኑም በተጨማሪ የጤና ባለሞያዎች ሁኔታውን እንዲያጠኑና እዲያሳውቁ ከሰራተኞች የተውጣጡ አባላት  ለጤና ቢሮ አቤቱታ ለማስገባት ለ ጥቅምት 24 2007 ቀጠሮ  መያዙን ሰራተኞች ለኢሳት ገልጸዋል።

እንባጮ ተብሎ የሚጠራው አደገኛ መጤ አረም በጣና ሃይቅ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን የአካባቢው አርሶ አደሮችና ባለሙዎች ተናገሩ፡፡

ጥቅምት ፳፫(ሃያ ሦስትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-መጤ አረሙ ከሸፈነው መሬት ሁለት ሺህ ሄክታር በሩዝ ማሳ ላይ ሲሆን ቀሪው በኃይቁና በዙሪያው በሚገኙ ውሃ አዘል መሬት ላይ መሆኑን ተገልጿል፡፡ አረሙ በደንቢያ፣ በጎንደር ዙሪያ፣ በሊቦ ከምከም፣ በፎገራና በደራ ወረዳ በሚገኙ 16 ቀበሌዎች በፍጥነት እየተዛመተ እንደሆነም ታውቋል።አረሙን ለማጥፋት ሲሞከርም በሦስት ሳምንታት ራሱን መልሶ የሚተካ መሆኑና በውሃው ላይ በመንሳፈፍ በንፋስ ሃይል እየተገፋ የሚራባ በመሆኑ የመከላከል ስራውን ፈታኝ እንዳደረገው  ባለሙያዎችና አርሶ አደሮች ገልፀዋል።
አረሙ በቀጣይም ከፍተኛ መዋለ ንዋይ እየፈሰሰባቸው ለሚገኙ በጣና ዙሪያ እየተገነቡ ላሉ የመስኖ ግድቦችና ኤሌክትሪክ ሃይል ግድብ ስጋት ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎች አስታውቀዋል።በሊቦ ከምከም ወረዳ  አረሙ  በሦስት ቀበሌ በአንድ ሺህ 556 ሄክታር የወል መሬትና የሩዝ ሰብል ማሳ ላይ መከሰቱ ተገልጿል። በካብ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ አርሶ አደሮች እንደተናገሩት አረሙ በሩዝ ማሳቸው ላይ ከተከሰተ ጀምሮ በየቀኑ በመሰብሰብ የማስወገድ ስራ ቢያከናውኑም የሩዝ ምርታቸው በመቀነስ ተጽኖ እያደረሰ ነው። የእንስሳቱን የግጦሽ ቦታን ሙሉ በሙሉ በመውረር መኖውን በማጥፋቱ እንስሳቶቻቸው ለረሃብ እየተጋለጡ መሆኑን ገልጸው እንስሳቱ አረሙን ቢመገቡም ለበሽታ እያጋለጣቸው መሆኑን አስታውቀዋል።
አረሙ የውሃውን ሽታና ጣዕም በመቀየር በጤናቸው ላይ ጉዳት እያደረሰ እንደሆነ የቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደሮች  ተናግረዋል። እንዲሁም በአካባቢው በስፋት ይገኝ የነበረው የአሳ ምርት እየቀነሰ ከመምጣቱም በላይ ተፈጥሯዊ ጣዕሙም የመለዋወጥ ባህሪ እያሳየ እንደሆነ አመልክተዋል።
መጤ አረሙ ከአንድ ዓመት በፊት 20 ሺህ ሄክታር በሀይቁና በገጸ ምድር ተከስቶ ህብረተሰቡን በማሳተፍ በተደረገ ርብርብ ከ95 በመቶ በላይ ማጽዳት ተችሏል በሚል ከአንድ ዓመት በፊት የገዢው መንግስት ሚዲያዎች ቢናገሩም ፣ በጣና ሃይቅ ላይ ብቻ ከ46 ሽህ ሄክታር በላይ ተስፋፍቶ  እንደሚገኝ ባለሙያዎች ለኢሳት ገልጸዋል፡፡
የተለያዩ የግል ሚዲያዎችና አለም አቀፍ ጸሃፊዎች ከአመታት በፊት  ሲያሳስቡት እንደነበር የሚናገሩት የአካባቢው ተቆርቋሪዎች በፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ በ2004 ዓ.ም በጸሃፊ መምህር ደረጀ መላኩ በተጻፈው  ʻ የጣና ሃይቅ ብክለት ከየት መጣ? ʼ በሚል ርእስ ያስነበበውን ያስታውሳሉ፡፡    ከአመታት በፊት ሄንረይ ኒኦንዶ የተባሉ ጸሃፊ ስለ አረሙ ወረራ አስከፊነት ልዩ ልዩ መረጃዎችንና ተመራማሪዎችን በማነጋገር Africa science ላይ  በዚሁ መጤ አረም የነዋሪዎች ህልውና አደጋ ላይ መውደቁን ጠቅሰዋል።  በአሁኑ ሰአት በስፋት በየአካባቢው በሚደረጉ የድርጅቱ ስብሰባዎች ፋታ ያጣው ገዢው መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት እንዳልሰጠው ታዛቢዎች ይናገራሉ፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ የጎንደር አስተባባሪ ታሰረ

• ‹‹ጎንደር ውስጥ ያለውን የህዝብ ጥያቄ ለማፈን የተደረገ ነው፡፡›› አቶ ዮናታን ተስፋዬ
• ‹‹የፀረ ሽብር ህጉ የገዥው ፓርቲን ስልጣን ለመጠበቅ እየዋለ ነው፡፡›› አቶ ይድነቃቸው ከበደ
የሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል እና የሰሜን ጎንደር የዞን ሰብሰቢ አቶ አግባው ሰጠኝ ጎንደር ከተማ ውስጥ ጥቅምት 25/2007 ዓ.ም በገዥው ፓርቲ ደህንነቶች መታሰሩን የሰማያዊ ፓርቲ የህግ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ይድነቃቸው ከበደ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡


ፖሊስና የደህንነት ኃይሎች አቶ አግባው ሰጠኝን ወደ መኖሪያ ቤታቸው በመውሰድ ከ1 ሰዓት ተኩል በላይ ፍተሻ እና ብርበራ በማካሄድ ስፍራው ወደልታወቅ ቦታ እንደወሰዷቸው ጎንደር ውስጥ የሚገኙ የፓርቲ አመራርና አባላት ገልጸዋል፡፡
አቶ አግባው ከተያዘ በኋላ ጎንደር ከተማ የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት እንዲሁም ዘመዶቹ ፖሊስ ጣቢያዎችን እየዞሩ ቢያጠያቁም ‹‹ነገ ጠዋት ጠይቁ!›› ከሚል ትዕዛዝ ውጭ የታሰረበትን ማወቅ እንዳልቻሉ ገልጸዋል፡፡
አቶ አግባው ሰጠኝ ከመታሰሩ በፊት የማያውቃቸው ሰዎች ለእሱ ተቆርቋሪ መምሰል ‹‹አርፈህ ስራህ ስራ፣ ከሰማያዊ ጋር የምታደርገውን እንቅስቃሴ አቁም፣ አዲስ አበባ ያሉት የፓርቲው አመራሮች ግንኙነታቸው ከሌላ ሰው ጋር ነው፡፡ ስለማታውቅ ነው፡፡›› ይሉት እንደነበር እንዲሁም ከመታሰሩ በሁለት ቀናት በፊት ከደህንነት የተላኩ ነኝ የሚል ግለሰብ ‹‹ከዚህ የማትወጣ ከሆነ በህይወት ላይ እርምጃ እንወስዳለን፣ መጀመሪያም መክረንሃል›› ብለው ይዝቱበት እንደነበር የሰማያዊ ፓርቲ የህግ ጉዳይ ኃላፊ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
ፖሊሶች የያዙት የፍርድ ቤት ማዘዣ ‹‹በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ በመሆናቸው አስፈላጊውን ፍተሻ ማካሄድ እንዲችሉ›› እንደሚል መረጃው የደረሳቸው የህግ ጉዳይ ኃላፊው ‹‹በመጀመሪያ የፀረ ሽብር አዋጁም ተቀባይነት የሌለውና የተለየ ሀሳብ ያላቸውን ሰዎች ለማሰቃየትና ገዥውን ፓርቲ ለመጠበቅ የወጣ ህግ ነው፡፡ አሁንም የምናየው በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ አባላት በመጠናከራቸው ለመገደብ እየተጠቀመበት ነው፡፡›› ሲል ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡
በተመሳሳይ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት አቶ ዮናታን ተስፋዬ ‹‹ጎንደር አካባቢ በማህበራዊና ሌሎች ችግሮች ምክንያት በገዥው ፓርቲ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ አለ፡፡ አቶ አግባውን ጨምሮ ሌሎችም አመራሮችና አባላት ህዝቡን ስለሚያስተባብሩ ነው የታሰሩት፡፡ ጎንደር ውስጥ ያለውን የህዝብ ጥያቄ ለማፈን የተደረገ ነው፡፡ ከአሁን ቀደም አርባ ምንጭ ላይ ህዝቡ ተቀባይነት ያላቸውና ጠንካራ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አመራሮችና አባላት ላይ ተመሳሳይ እስር ተፈጽሞባቸዋል፡፡ ሌሎች አባላትና አመራሮችም አሁንም ድረስ እያዋከቧቸው ነው፡፡›› ብሏል፡፡
ኃላፊው አክሎም ‹‹በተለይ በአሁኑ ወቅት ፓርቲዎች በጋራ እየሰሩ በመሆኑ ስጋት ውስጥ የወደቀው ገዥው ፓርቲ እንቅፋት ለመፍጠር ነው እስራቱን የሚፈጽመው፡፡›› ሲል ገዥው ፓርቲ ጠንካራ እንቅስቃሴ የሚያደርጉትን የፓርቲ አመራሮችና አባላት በማሰር ፓርቲውን ለማዳከም የሚያደርገው የተለመደ ስልት መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ በተመሳሳይ ሰሞኑን በመኢአድ፣ አንድነትና አረና አመራሮችና አባላት ላይም ተመሳሳይ እስር እንደተፈጸመ ተዘግቧል፡፡

በአንድ አካባቢ ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚካሄድ ጥቃት በሁሉም ኢትዮጵያዊ ላይ የሚካሄድ ጥቃት ነው!

ጥቅምት 25፣2007 (ኖቨምበር 4፣2014)
ህወሓት/ኢህአዴግ በተለያዩ ኢትዮጵያውያን ላይ ያነጣጠረ የግፍ ተግባር ማካሄድና የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲውን ተግባራዊ ማድረጉን በሰፊው ቀጥሏል::  በዚህ አኳያበሶማሌ፣ በአማራው፣ በኦሮሞ፣ በሲዳማ፣ በአፋር፣….ወዘተ ተወላጆች ላይ የሚያካሂደው እልቂት በቂ መረጃ ነው::
shengoየዚህ ቀጣይ ረገጣ ተከታታይ ዒላማ የሆነው አንዱ የአማራው፡ተወላጅ ነው:: ህወሓት/ኢህአዴግ ከመነሻው የአማራ፡ተወላጁን  በጠላትነት ፈርጆ በተለያየ ደረጃየጥቃት ዒላማ አድርጎታል። በዚህም መሠረት በራሱ ትዕዛዝም ሆነ በተለጣፊ ድርጅቶቹ አማካኝነት እጅግ ዘግናኝ ግፍ የተሞላበት ወንጀል ፈጽሟል። ለዘመናት  ከኖረበት ቦታ “ወደ መጣህበት ሂድ” ተብሎ ንብረቱ ተነጥቆ ባዶ እጁን በግዳጅ እንዲባረር ተደርጓል። ይህ አልበቃ ብሎ ህፃናት ልጆች ሳይቀሩ አሰቃቂ በሆነ ግፍ እንዲታረዱ ዜጎች ወደ ገደል እንዲወረወሩና፣ ቤታቸው ውስጥ እንዳሉ እንዲቃጠሉ ተደርጓል። በአርባ ጉጉ፣ በወተር ፣በአርሲ .ወዘተ የተካሄደው ይህንኑ ነው የሚያሳየው።
ለዚህ ጨካኝና ህገወጥ ተግባርም የህወሓት/ኢህአዴግ ባለሥልጣኖች በቀጥታም በተዛዋሪም ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። በጊዜው ጠቅላይ ሚኒስተር የነበረው ታምራት ላይኔ በአማራው ተወላጅ ላይ የኦጋዴን ህዝብ እርምጃ እንዲወስድ ያካሄደው ግልጽ የሆነ መገፋፋት፣ በአርሲ በተካሄደ እልቂት እነ ኩማ ደመቅሳ ዋና ተዋናን እንደነበሩ፣ መለሰ ዜናዊ ከጉራፈርዳ የተባረሩትንና ለአቤቱታ የመጡን ዜጎች እንኳን አባረሯችሁ የሚል አንድምታ  የሚሰጥ መግለጫ በይፋ መስጠቱ ጥቂቶቹ ማስረጃዎች ናቸው።
ይህ ህወሓት/ኢህአዴግ ሆን ብሎ የሚፈጽመውና የሚያበረታታው ህዝብን እርስ በርስ የማጫረስ ተግባር እጅግ እየሰፋ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከር በአደገኛፍጥነትመም በመቀጠል ላይ ነው።
ትላንት ከትላንት በስቲያ በተለያዩ ቦታዎች እንደተደረገው ሁሉ፣ ባለፉት ጥቂት ሳምንታትም ባለማቋረጥ በጋምቤላ አካባቢ በተመሳሳይ ሁኔታ በዋናነት በዚሁ በአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ የድብደባ፣ የግድያና የማፈናቀል እርምጃ በሰፊው ተካሂዶ በመዠንገር አካባቢ ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሲሞቱ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ቆስለዋል፣ በሽዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ተፈናቅለዋል።
ይህ ሁሉ ሲሆን፣ የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታ ያለበት መንግሥት መንበር ላይ የተቀመጠው ህወሓት/ኢህአዴግ ሁኔታው እንዳይከሰት ቀድሞ ለመከላከልም ሆነ በጊዜ ለማስቆም የወሰደው ምንም እርምጃ የለም። ችግሩ ከተፈጠረ በኋላም ቢሆን የተጎዱትን ለመንከባከብ፣ ህክምና የሚሹትን ለመርዳት፣ መልሶ ለማቋቋምና ወንጀለኞቹን ለህግ ለማቅረብ የሚያደርገው ይህ ነው የሚባል ሙከራ አይታይም።  ይሀ ሁሉ  የሚያመለክተው ያለው ስርዓት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የዚህ ወንጀል አካል እንደሆነ ነው።
ሸንጎው የኢትዮጵያን ህዝብ አንዱን ከአንዱ በማጋጨት ሥልጣኑን ለማራዘም ህወሓት/ኢህአዴግ የሚያካሂደውን ቀጣይ ሀላፊነት የጎደለው ኢ-ሰብአዊ ግፍ አጥብቆ ያወግዛል። በአማራውም ሆነ በሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ በተከታታይ እየተካሄደ ያለውን የማፈናቀል፣የግድያ፣ የጅምላ እሰራትና  ሌሎች  ወንጀሎች ባስቸኳይ እንዲቆም ያሳስባል። እስካሁን የተፈጸመው ግፍ ሁሉ ብቃት ባለው እና  ከሥርዓቱ ባለሟሎች ነፃ በሆነ አካል እንዲጣራ፤ ወንጀለኞቹም ለፍርድ እንዲቀርቡ ያስገነዝባል።
በኦጋዴን፣ በኦሮሚያ፣ በሲዳማ፣ በአፋር፣ በወልቃይት እንዲሁም በሌሎች የሀገራችን ቦታዎች ውስጥ ይህ  ሥርዓት የሚያካሂደውን ማለቂያ የሌለው ግፍ ሸንጎ አጥብቆ ያወግዛል።
ሰዎችን በትውልዳቸው የተነሳ በጅምላ የጥቃት ሰላባ ማድረግ በዓለምአቀፍ ህግም አስጠያቂ እንደሆነ የዚህ ጥፋት ፈጻሚም አስፈጻሚም የሆኑ ሁሉ እንዲገነዘቡት በድጋሚ ለማሳሰብ እንወዳለን።
የዚህን  የግፍ ሥርዓት መጨረሻ ለማፋጠን ሁሉም ኢትዮጵያዊ አንድነቱን አጠናክሮ እንዲነሳ እናሳስባለን፡  በአንድ አካባቢ ኢትዮጳያዊያን ላይ  የሚካሄድ ጥቃት በሁሉም ኢትዮጵያዊ ላይ የሚካሄድ ጥቃት ነው!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

የግንቦት 7 ወቅታዊ ጽሁፍ: የወያኔ ግፍ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ



ዘረኛዉ ወያኔና ባለሟሎቹ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በጋምቤላና በሸኮ መዠንገር አካባቢ የሚያካሄዱትን የማንአለብኝነት የመሬት ዝርፍያና ዜጎችን እርስ በርስ በማጋጨት ተጠቃሚ ለመሆን የሚያደርጉት አራዊታዊ ሩጫ የተነሳ ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ ህዝብ ይህ ነዉ ተብሎ ሊነገር የማይችል እልቂት እየተፈጸመበት ነዉ። የመዠንገር ህዝብ የሞትና የህይወትን ያክል የማይወጣዉ ምርጫ ስለቀረበለት ተወልዶ ያደገበትን የአባቶቹንና የአያቶቹን አካባቢ ለቅቆ በመዉጣት እራሱን ለመከላከል ባደረገዉ እንቅስቃሴ የብዙ ንጹሃን ዜጎችና ቁጥራቸዉ ቀላል የማይባል ምስኪን ወታደሮችም ህይወት ማለፉ በይፋ እየተሰማ ነዉ። ይህንን ተከትሎ ግፈኞቹ የወያኔ መሪዎች በአካባቢዉ ብዙ ዘመን በቆዩ ብሄሰቦች መካክል ሆን ብለዉ ግጭት እንዲነሳ እያደረጉ በህዝብ መካክል ግጭትትና ዕልቂት የተነሳ በማስመሰል በአካባቢዉ ከፍተኛ ሰቆቃ በመፈፀም ላይ ይገኛሉ።
በዚህ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች እየደረሰ ላለዉ መጠነ ሰፊ ግጭትና ዕልቂት ተጠያቂዉ በአካባቢዉ ለዘመናት አብሮ በመደጋገፍ የኖረዉ ህዝብ ሳይሆን የዚህ አሰቃቂ ዕልቂት ባለቤትና ጠንሳሽ ህወሓትና ዘረኛ መሪዎቹ መሆናቸዉን ለአንድም ደቂቃ ሊዘነጋ አይገባም። ይህ ግጭት ሊነሳ የቻለዉ ህወሓት የአካባቢዉን ደሃ ገበሬ ከትዉልድ መሬቱ ላይ እያፈናቀለ መሬቱን ለከፍተኛ የጦር መኮንኖቹና የኔ ለሚላቸዉ ባለሟሎቹ በማከፋፈሉ መሆኑን ይህንን ግፍ የሚሰማ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ልብ ሊለዉ ይገባል። ህወሃት የአማራን ተወላጆች አካባቢዉ የእናንተ አይደለምና ዉጡ እያለና እያፈናቀለ በሌላ በኩል ግን በየክልሉ የአካባቢዉን ነዋሪ እያፈናቀለ የራሱን ሰዎች የመሬት ባለቤት ማድረጉ አዲስ የጀመረዉ ክስተት ሳይሆን ቆየት ያለና ስር የሰደደ የወያኔ አሰራር ነዉ።
ይህ ዛሬ በጋምቤላና በአካባቢዋ እየደረሰ ያለዉ ግፍና መከራ ለአካባቢዉ ህዝብ ብቻ የሚተዉ ነጠላ ችግር ሳይሆን በአጠቃላይ ወያኔ በአገራችን ላይ ሆን ብሎ በማድረስ ላይ ያለዉ ችግርና መከራ አካል ነዉ። በጋምቤላ ዉስጥ የፈሰሰዉና እየፈሰሰ ያለዉ የሴቶች፤ የወጣቶች፤ የአረጋዉያንና የህጸናት ደም ለሁላችንም የነጻነት ጥሪ እያቀረበልን ነዉ። ይህ የነጻነት ጥሪ ሰምተን የምናልፈዉ ወይም ነገ እንደርሳለን በለን በቀጠሮ የምናልፈዉ ጥሪ አይደለም። ጥያቄዉ የአገርና የዜጎች ህልዉና ጥያቄ ነዉና ነገ ዛሬ ሳንል አሁኑኑ ይህንን የነጸነት ጥሪ ሰምተን ምላሽ ልንሰጠዉ ይገባል።
ginbot 7
ይህ ወያኔ በደቡብ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ዉስጥ በንጹሃን ዜጎቻችን ህይወት ላይ እየፈጸመ ያለዉ ግፍ በአገራችን ህዝብ ላይ ሲደርስ የመጀመሪያዉ አይደለም፤ ካላቆምነዉ በቀር የመጨረሻዉ እንደማይሆንም አካሄዱ በግልጽ እያሳየን ነዉ። ወያኔ ጋምቤላ ዉስጥ ለምለም መሬት እየፈለገና ነዋሪዉን እያፈናቀለ መሬቱን ለባለሟሎቹ ማደሉን ሳይታቀብ በማንለብኝነት እንደቀጠለበት ነዉ። መሬቱን የተቀማዉ ደሃዉ የጋምቤላ ገበሬም ጫካ እየገባ ከወያኔ ጋር መተናነቁን ቀጥሏል። ትናንት በኦሮሚያ፤ በጉራፈርዳና በቤንሻንጉል አካባቢዎች በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰዉ ግፍና መከራ ዛሬ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ዉስጥ በተለያዩ ብሄረሰቦች ላይ እየደረሰ ነዉ።
ግንቦት 7 የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ እንቅስቃሴ ይህ ለከቱን የለቀቀ የህወሓት ዕብሪት እንዲተነፍስና በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰዉ ግፍና ሰቆቃ እንዲቆም እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ነግ በኔ እያለ የነጻነት ትግሉን እንደቀላቀል የትግል ጥሪ ያደርጋል። ወያኔ እያደረሰ ያለዉ እስራት፤ ድብደባ፤ ግድያና ስደት የሁላችንንም ቤት እያንኳኳ ነዉና ሁላችንም እንደ አንድ ሰዉ ቆመን ወያኔንና ወያኔ የፈጠረዉን ዘረኛ ስርዐት በትግላችን መደምሰስ አለብን። በጋምቤላና በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች የፈሰሰዉ የንጹሃን ወገኖቻችን ደም ደመከልብ ሆኖ የማይቀረዉ ለመብታችንና ለነጻነታችን ቆመን ወያኔን ካስወገድን ብቻ ነዉ።
                                                                                                               በህብረት እንነሳ!!!!

በስብሰባ ጋጋታ የተማረውን ሕብረተሰ የሸፈተ ልብ ምርኮኛ ማድረግ አይቻልም


በሰደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ ከተቋቋመበት ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ  በትምህርት ሥርዓቱ ላይ ያጋጠመውን ዙሪያ ገብ ችግር ፣ በመምህራን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍና በደል ከዚህ አንፃር መምህራን የትምህርቱን ጥራት ለማስጠበቅና መብቶቻቸውን ለማስከበር ማድረግ ያለባቸውን  እንቅስቃሴና መወሰድ የሚገባቸውን እርምጃ በተመለከተ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ መግለጫዎችን በማውጣት  በ መላው ዓለም ላሉ ኢትዮጵያውያን ባጠቃላይና በተለይ ለጉዳዩ ባለቤቶች ለኢትዮያጵያ መምህራን ፣  ለተማሪዎችና ለወላጆች እንዲደርስ አድርጓል።

Saturday, November 1, 2014

የተመስገን መታሠር እንዳሳሰባት ዩናይትድ ስቴትስ አስታወቀች

የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በነበረው በተመስገን ደሣለኝ ላይ የተላለፈው የእሥራት ፍርድ እንደሚያሳስበው የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት አስታወቀ፡፡

የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በነበረው በተመስገን ደሣለኝ ላይ የተላለፈው የእሥራት ፍርድ እንደሚያሳስበው የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት አስታወቀ፡፡
ሃሳብን የመግለፅ መብታቸውን በመጠቀማቸው ታሥረዋል ያላቸውን ጋዜጠኞችም የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲፈታ ዩናይትድ ስቴትስ በድጋሚ ጥሪ እንደምታስተላልፍ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቷ አስታውቋል፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ ወይም ሌላ ማንም መንግሥት ስላለ ሳይሆን ኢትዮጵያ መብቶችና ነፃነቶች የተከበሩባት ሃገር ነች፤ ሲሉ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ አመልክተዋል፡፡
ለተጨማሪና ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Breaking News: አብርሃ ደስታ; ሀብታሙ አያሌው; የሽዋስ አሰፋ ; ዳንኤል ሺበሺ በይፋ ክስ ተመሰረተባቸው

• አብርሃ ደስታ የሁለት ድርጅቶች አባል ነው የሚል ክስ ተመስርቶበታል
• ወደ አዲስ አበባ ማረሚያ ቤት እንዲዘዋወሩ ታዟል
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
በልደታ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ምድብ ወንጀል ችሎት ዛሬ ጥቅምት 21/2007 ዓ.ም ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ በተሰየመው ችሎት 10 ተከሳሾች በፌደራል አቃቢ ህግ በይፋ ክስ ተመሰረተባቸው፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ከ100 ገጽ በላይ የክስ ቻርጅ የተነበበላቸው ሲሆን ከክስ ቻርጁ ጋር ከ300 ገጽ በላይ የምርመራ ሰነድ ቀርቦባቸዋል፡፡
የክሱ መዝገብ የተከፈተው ዘላለም ወርቃገኘሁ በተባለውና ‹‹የግንቦት 7 አመራር ነው፡፡›› ተብሎ ክስ በተመሰረተበት ግለሰብ ሲሆን በዚህ የክስ መዝገብ የተካተቱትም፡-
1ኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ
2ኛ ተከሳሽ ሀብታሙ አያሌው
3ኛ ተከሳሽ ዳንኤል ሺበሺ
4ኛ ተከሳሽ አብርሃ ደስታ
5ኛ ተከሳሽ የሽዋስ አሰፋ
6ኛ ተከሳሽ ዮናታን ወልዴ
7ኛ ተከሳሽ አብርሃም ሰለሞን
8ኛ ተከሳሽ ሰለሞን ግርማ
9ኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ደጉ
10ኛ ተከሳሽ ተስፋዬ ተፈሪ ናቸው
ለሁሉም ተከሳሾች ከዛሬ በፊት ክስ እንዳልደረሳቸውና ዛሬ ፍርድ ቤት ውስጥ እንደተሰጣቸው ታውቋል፡፡ በችሎቱ 6ኛ ተከሳሽ ከሆነው ዮናታን ወልዴ በስተቀር ሁሉም ያለ ጠበቃ የቀረቡ ሲሆን ጠበቃዎቹ ያልቀረቡበት ምክንያትም ጠበቆቹ ደምበኞቻቸው የሚቀርቡበት ቦታና ጊዜ ስላልተነገራቸው እንዲሁም ቀደም ብለው እንዳይገናኙ በመደረጋቸው መሆኑን አቶ ኃብታሙ አያሌው ችሎቱ ላይ ተናግሯል፡፡
ከሳሹ የፌደራል አቃቢ ህግ በ1996 የወጣው የወንጀል ህግ እና የጸረ ሽብር ህግ ጠቅሶ ክስ ያቀረበ ሲሆን ክሶቹ በሁለት ዋና ዋና ጭብጦች ቀርበዋል፡፡ የመጀመሪያው ጭብጥ ‹‹ከሽብርተኛ ቡድኖች ጋር በጋራ በመስራት›› የሚል ሲሆን ‹‹ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ፣ የመንግስትን መሰረተ ልማት በማፈራረስ፣ ህዝብን ለአመጸ በማነሳሳት መንግስትን መለወጥ አላማው አድርጎ ከሚሰራውና ራሱን ግንቦት 7 ብሎ ከሚጠራው ቡድን ጋር አባል በመሆንና በወንጀል ድርጊቶች በመሳተፍ›› በሚል ቀርቧል፡፡
ሁለተኛው የክስ ጭብጥ ‹‹የሽብር ቡድን አመራር በመሆን›› የሚል ሲሆን በተለይም የአንደኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ ‹‹የሽብር ቡድኑ አመራር በመሆንና አባል በመመልመል›› በሚል የክስ ጭብጥ ቀርቦበታልል፡፡
ከ2-5ኛ የክስ መዝገብ የሚገኙት ማለትም ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሽ፣ አብርሃ ደስታና የሸዋስ አሰፋ ‹‹ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲን ከለላ በማድረግ ግንቦት 7 የተባለውን የሽብር ቡድን አላማ ለማሳካት ተንቀሳቅሰዋል፡፡ ፋሲል የኔ ዓለምና ሌሎች የሽብር ቡድኑ አባላት ጋር በስልክ በመነጋገርና በማህበራዊ ድህረ ገጸ የተለያዩ መልዕክቶችን ተለዋውጠዋል›› የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡ አብርሃ ደስታ ከግንቦት 7 በተጨማሪ ‹‹ደምኢት የተባለ ቡድን አባል ነው፡፡›› የሚል ክስ ቀርቦበታል፡፡
በስተመጨረሻም ፍርድ ቤቱ ሁለት ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ አንደኛው ረቡዕ ጥቅምት 26/2007 ዓ.ም 3 ሰዓት ተከሳሾቹ ዋስትና ይሰጣቸው አይሰጣቸው በሚለው ጉዳይ ላይ ፍርድ ቤቱ ከተከሳሾቹ ጠበቆች ጋር ተማክሮ ውሳኔ ይሰጣል ተብሏል፡፡ በሁለተኛነት ተጠርጣሪዎቹ ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ቀደም ሲል ለአራት ወራት ወደቆዩበት ማዕከላዊ እስር ቤት እንዳይመለሱ ፍርድ ቤቱን ስለጠየቁ ፍርድ ቤቱ በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት (3ኛ) እንዲቆዩ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
ተከሳሾቹ ትናንት ጥቅምት 20/2007 ዓ.ም አራዳ ምድብ ችሎት ይቀርባሉ ተብሎ የነበር ቢሆንም ሳይቀርቡ ቀርተዋል፡፡ በተመሳሳይ ዛሬ ጥቅምት 21/2007 ዓ.ም ጠዋት ወደ ልደታ ፍርድ ቤት ተወስደው የነበረ ቢሆንም እንደገና ወደማዕከላዊ ተመልሰው ከሰዓት እንዲቀርቡ ተደርገዋል፡፡